input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
የመብት ተሟጋች ሜሮን እስጢፋኖስ በበኩሏ ኤርትራዉያን ለሐገር ነፃነት ታግለናል ትላለች። |
ይሁን እንጂ በእነኝህ ዓመታት አልፎ አልፎ በታጠቁ ቡድኖች ሲያጋጥማቸው ከነበረው የከብት ዘረፋ በስተቀር የግብርና ሥራቸውን በሰላም ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ያስታውሳሉ፡፡ |
ሆኖም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ባልተለመደ መልኩ በታጠቁ ቡድኖች የሚፈጸሙ የግድያና የዘረፋ ተግባራት እየተባባሱ በመምጣቸው አካባቢውን ጥለው መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ |
አሁን የሚታየውን መፈናቀል ለማስቆምና በቀጣይ መደረግ ያለበትን ሁኔታ ለመገምገም ከተለያዩ አካላት የተውጣጣ ቡድንም ወደ አካባቢው መንቀሳቀሱን አመልክተዋል፡፡ |
በደቡብ ክልል የሰፈራ ፕሮግራም በተካሄደባቸው የቤንች ማጂና የከፋ ዞኖች በሠፋሪ አርሶአደሮች ላይ የመፈናቀል አደጋ ሲያጋጥም የአሁኑ መጀመሪያው አይደለም፡፡ |
ባለፈው ዓመት በነበረው ዝቅተኛ ዝናብ የተነሳ ከዞኑ ነዋሪዎች ገሚሱ አስቸኳይ ርዳታ የሚያሻው ነው ተብሏል። |
የችግሩን መነሻ ባለፈው ዓመት በአካባቢው በቂ ዝናብ በለመኖሩ ድርቅ በመከሰቱ እንደሆነ አቶ መልካሙ አብራርተዋል፡፡ |
አንድ የዝቋላ ወረዳ አርሶአደር በበኩላቸው ችግሩ አሳሳቢና አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ ነው ነው ያሉት፡፡ |
የምግብ እርዳታው በፍጥነት ወደ አካባቢው ካልደረሰ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚፈጠር አቶ መልክሙ ስጋታቸውን አስቀምተዋል፡፡ |
የዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ዝናብ አጠር ከሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ |
ኢትዮጵያ ጠ ሚ ዐቢይ አህመድ የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የዘንድሮውን የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ። |
ጠ ሚ ዐቢይ ለዚህ የበቁት በዋናነት ሃያ ዓመታት በዘለቀው የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ሰላም እንዲወርድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ መኾኑ ተገልጿል። |
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የዘንድሮውን የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ። |
በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉን ከተቃዋሚዎች ጋር ማስማማታቸውም ሽልማቱን እንዲያሸንፉ ረድቷቸዋል ነው የተባለው። |
አብይ አህመድ ኛው የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሲሆኑ የአሜሪካን ዶላርም ይበረከትላቸዋል። |
አፍሪቃ ጀርመን በዘር ማጥፋት ተከሰሰች ሁለት የናሚቢያ ጎሳዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች የሚሏት ጀርመን ላይ በኒው ዮርክ ክስ መስርተዋል። |
ጀርመን በዘር ማጥፋት ተከሰሰች የታሪክ ታዛቢዎች የ ኛው ክ ዘ የመጀመሪያው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይሉታል። |
ወደ የሔሬሮ እና ናማ ጎሳ አባላት በዛሬዋ ናሚቢያ ከጎርጎሮሳዊው እስከ ዓ ም ባሉት ዓመታት በጀርመን ቅኝ ገዢዎች እጅ ማለቃቸው ይታመናል። |
በጊዜው የዛሬዋ ናሚቢያ የጀርመን ደቡብ ምዕራብ አፍሪቃ ተብላ የምትጠራ ቅኝ ግዛት ነበረች። |
በ ዓ ም በቅኝ ገዚዎቻቸው ላይ ለተቃውሞ የወጡት የሔሬሮ እና የናማ ጎሳዎች በጀርመን ወታደሮች ወደ በረሐ ተባረሩ። |
በቅኝ ገዢዎቹ እርምጃ በመቶ የሔሬሮ ጎሳ አባላት እንዲሁም ከናማ ጎሳ ግማሽ ያክሉ አለቁ። |
ይኸ ሁሉ ግን ለበርካታ አመታት ለአውሮጳም ሆነ ለአፍሪቃ ተዘንግቶ የቆየ የሰቆቃ ታሪክ ነው። |
ወንጀሉ የተፈፀመባቸዉ የሁለቱ የናሚቢያ ጎሳዎች ተወካዮች ካሳ ሊከፈለን ይገባል በማለት ሲሟገቱ አመታት አስቆጥረዋል። |
አሁን ክስ የመሰረቱት የፖለቲካዉ ሙግት ዉጤት አላመጣ ስላለ ይመስላል። |
የድርድሩን ሒደት አጥብቀው ከሚተቹት መካከል አንዷ የሆኑት የሔሬሮ ጎሳ ተወካይ ኤስተር ሙይንጃንጉዌ ለእኛ ሒደቱ በሕፀጽ የተሞላ ነው። |
በጉዳዩ ላይ የሚደራደሩት ወገኖች ሁለቱ ልዩ ልዑኮች እንዲሆኑ የወሰነው ማን ነው |
ከጎርጎሮሳዊው ዓ ም የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ጀርመን ዘር ማጥፋት ተብሎ መጠራቱን ባትክድም ካሳ ለመክፈል ግን ስታንገራግር ቆይታለች። |
ፍርድ ቤቱ ለበርካታ ዓመታት ሲንከባለል የቆየውን ጉዳይ ለመዳኘት ሥልጣኑ እንዳለው ገና አልታወቀም። |
ማንኛውም ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክስ የመዳኘት ሥልጣን እንዳለው ይመረምራል። |
መመርመር ብቻም ሳይሆን ጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሕጋዊ መሰረት መኖሩንም ያጤናል። |
አንድ የጀርመን ፖለቲከኞች በበኩላቸው አገራቸው ጉዳዩን የያዘችበት መንገድ ተገቢ አይደለም ሲሉ ይተቻሉ። |
ይፋዊ በሆነ መልኩ ዘር ማጥፋት ነው ብሎ መቀበሉ በርግጥም አንዳች እርምጃ ነው። |
ሆኖም ግን ሁልጊዜም ከሔሬሮ እና ከናማዎች ጋር የቀጥታ ድርድር ማድረግ እንደሚገባቸው ሲናገሩ አይደመጥም። |
ዛሬ ሥልጠናው ይፋ በተደረገበት መርሐ ግብር እንደተገለጸው በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ስልጠናዎች በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ይሰጣሉ። |
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እና ጆን ሖፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በምርጫ ላይ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት ጀመሩ። |
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገሪቱ ፖለቲከኞች ዘንድ ዛሬም ድረስ የክርክር መነሾ የሆነው አገራዊ ምርጫ ነሐሴ ቀን ዓ ም እንዲካሔድ ወስኗል። |
ቦርዱ ይፋ ባደረገው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከሚያዝያ እስከ ግንቦት ቀን ዓ ም ድረስ የመራጮች ምዝገባ ይከናወናል። |
ከግንቦት እስከ ግንቦት ባሉት ቀናት ደግሞ የእጩዎች ምዝገባ ይካሔዳል። |
ነሐሴ ቀን የሚካሔደው ምርጫ ውጤት ከነሐሴ እስከ ጳጉሜ ባሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል። |
የዶይቼ ቬለው ጌታቸው ተድላ ሥልጠናው ምን ይፈይዳል ሲል መርሐ ግብሩ ይፋ ሲደረግ የተገኙ አንድ ተሳታፊ ጠይቋል። |
አባቶቻችን ጥለዉልን ያለፉትን የታሪክ አሻራ እኛ ልጆቻቸዉ ታሪኩን በሞያችን እናስተላፍ ብለን ነዉ። |
የሟቾች ቁጥር በኢጣልያ ከ ሺህ በላይ በስፓኝ አስር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አምስት በአሜሪካን ሺህ በፈረንሳይ ደግሞ ሺህ ደርሶአል። |
በዓለማችን በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዛሬ እኩለ ቀን ላይ በወጣ ዘገባ መሠረት አንድ ሚሊዮን ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ስድስት ደርሷል። |
አንድ አራተኛው በአሜሪካን ሌሎቹ ደግሞ በተቀረው ዓለም ነው ያሉት። |
በኮሮና ምክንያት ከዓለም ህዝብ ግማሹ ማለትም ከ ቢሊዮን በላይ የሚሆነው በ ሃገራት ከቤቱ እንዲሰራ ተገዷል። |
ሜርክል ሐኪማቸው ተህዋሲው እንዳለባቸው ከታወቀ በኋላ ሦስት ጊዜ ምርመራ ተደርጎላቸው በሦስቱም ምርመራ ከተህዋሲው ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል። |
ስደተኞቹና ለስደተኞቹ መብት እንከራከራለን የሚሉ ወገኖች እንደሚሉት ለስደተኞቹ ይሰጥ የነበረዉ የምግብ ርዳታዉ ከተቋረጠ ሁለት ወር አለፈዉ። |
ረዥም ጊዜ የፈጀው የሁለቱ ሲኖዶሶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በመጨረሻ ለፍፃሜ በቃ። |
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእንግዲህ አንድ ሲኖድስ ብቻ እንዳላትም ተገለጸ። |
በእርቀ ሰላሙ መግለጫ ላይ የተገኙት ዶ ር ዐብይ አህመድ ዛሬ በኢትዮጵያውያን ላይ ተገንብቶ የቆየው የጥላቻ ግንብ ተናደ ብለዋል። |
የውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር መሥሪያ ቤት በቃል አቀባዩ ነቢያት ጌታቸው አሰግድ አማካኝነት ዛሬ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ። |
አውሮጳ ጀርመን የአውሮጳ ህብረት እና የስደተኞች ጉዳይ የእሁዱ ጉባኤ ለጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እጅግ አስፈላጊ ነበር። |
የአውሮጳ ህብረት የስደተኞች መርህ የአውሮጳ ህብረት በስደተኞች ጉዳይ ላይ በአባል ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ እየጣረ ነው። |
በዚህ ሳምንት ሐሙስ ብራሰልስ ቤልጅየም የሚካሄደው የአባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ከሚነጋገርባቸው ጉዳዮች አንዱ እና ዋነኛው ይኽው የስደተኞች ጉዳይ ነው። |
ከዚህ ጉባኤ አስቀድሞ አባል ሀገራት ባለፈው እሁድ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂደዋል። |
የኮታ ስርዓቱን የተቃወሙት በተለይ ሀንጋሪ ፖላንድ ቼክ ሪፐብሊክ ስሎቫክያን የመሳሰሉ ሀገራት እስካሁንም በዚሁ አቋማቸው እንደጸኑ ነው። |
አሁን ደግሞ ኢጣልያ እና ማልታን የመሳሰሉ ሀገራት በፈንታቸው የጀልባ ስደተኞች አናስገባም ማለት ጀምረዋል። |
የአውሮጳ ህብረት በወቅቱ ሁለቱም ሀገራት የሰዎችን ህይወት ለመታደግ ቅድሚያ እንዲሰጡ ቢጠይቅም ጥሪው ሰሚ አላገኘም ነበር። |
ችግሩ ግን በስተመጨረሻ ስፓኝ ስደተኞቹን ለማስገባት ፈቃደኛ በመሆንዋ ተፈቷል። |
እነዚህ እና ሌሎችንም የህብረቱን አባል ሀገራት የማያስማሟቸው ጉዳዮች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት እያሰፋ ሄዷል። |
ይህ መነሻ ሆኖም የፊታችን ሐሙስ እና አርብ ከሚካሄደው የአባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ አስቀድሞ ባለፈው እሁድ አነስተኛ ጉባኤ ተካሂዷል። |
ሁላችንም ህገ ወጥ ስደትን ለመቀነስ ድንበሮቻችንን ለመጠበቅ እንደምንፈልግ ተስማምተናል። |
አንዳንዱ የመጀመሪያው የስደት ጉዳይ ተጋላጭ ሌሎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ የችግሩ ተጋሪ መሆን የለባቸውም። |
በማይቻልበት ጊዜ ደግሞ ፈቃደኛ የሆኑትን በአንድ ላይ አሰባስበን የጋራ የድጋፍ ማዕቀፍ እንፈልጋለን። |
የእሁዱ ጉባኤ ለጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እጅግ አስፈላጊ ነበር። |
ሜርክል ችግሩ በአጠቃላይ በአውሮጳ አቀፍ ደረጃ መፈታት አለበት የሚል አቋም ነው ያላቸው። |
እንደ ሜርክል አውሮጳ አቀፍ የስደተኞች ፖሊሲ ሲነደፍ ነው የጀርመንም ችግር የሚወገደው። |
እናም አባል ሀገራት በሙሉ የሚስማሙበትን የጋራ የስደተኞች መርህ ማምጣት እንዳልተቻለ በእሁዱ ጉባኤ ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል። |
ከእሁዱ ጉባኤ አስቀድሞ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሜርክልና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮም በርሊን ውስጥ በጉዳዩ ላይ መክረው ነበር። |
ማክሮ ሥልጣን እንደያዙ ያቀረቡትን የጋራ የስደተኞች ማዕከል የማቋቋም ሀሳብ በዚሁ ወቅት አንስተው ነበር። |
ሃይማኖት እንደምትለው የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት መንግሥታት ከሀገር ውስጥ የሚደርሱባቸው የተለያዩ ተጽእኖዎች አቋማቸውን እንዲቀያይሩ ምክንያት እየሆኑም ነው። |
የአውሮጳ ህብረትን ለሁለት የከፈለ የሚመስለው የህብረቱ የስደተኞች መርህ በወደፊቱ ጉዞው ላይ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑ በግልጽ እየታየ ነው። |
ያም ሆኖ በገበያው እምነት የህብረቱን አንድነት ያፈርሳል የሚል ስጋት የለም ። |
ቁጥራቸው እና ዜግነታቸው በውል ያልታወቁት ቀሪ ስደተኞችም አስክሬን እንዲሁ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የ ያህሉ መሰብሰቡ ተዘግቦ ነበር። |
የሞሮኮ ባህር ኃይልም እንዲሁ ወደ ስፔን በጀልባ በጉዞ ላይ የነበሩ ስደተኞችን መታደጉን ገልጿል። |
እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሆነ ባለፉት ሰባት ወራት የሚጠጉ ስደተኞችን በሜዲትራንያን ባህር በኩል አድርገው ወደ አውሮፓ ገብተዋል። |
ምናልባትም ስደተኞቹ ሌሎች የገጠማቸውን እጣ ፈንታ አገናዝበው ከጉዞ ተቆጥበው ይሆናል። |
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኗ ሰዓት በአሁኗ ደቂቃ እጃቸው በህገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ስር ያሉ ስደተኞች አሉ። |
ታጋቾቹ እንደሚሉት ናስማህ በተባለው ቦታ ከአመት በላይ የታገቱ ሰዎች አሉ። |
ቢሳካላቸው ሁሉም ወደ አውሮፓ በባህር ለመሰደድ ነበር አላማቸው ። |
በአንድ ሊቢያዊ ታግተናል ከሚሉት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያዊት ያለችበትን ሁኔታ እንዲህ ገልጻልናለች። |
ከዚህም ሌላ በዚህ ዓመት ብቻ ከ በላይ ሰዎችን ወደ አውሮፓ እና ሌሎች ደህንነት የሚያገኙበት ቦታ ከተለያዩ የስደተኞች ማቆያ ለማስወጣት ችለናል። |
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በህጋዊ መንገድ ስደተኞቹ ሊቢያን የሚለቁበትን መንገድ እንዲተባበረን እየጠየቅንም እንገኛለን። |
ያም ሆኖ ታሪክ አርጋዝ እንደሚሉት በአሁኑ ሰዓት የሚጠጉ ስደተኞች በሊቢያ የተለያዩ የስደተኛ ማቆያዎች ይገኛሉ። |
ይህ ቀደም ሲል ያነጋገርናቸውን በህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በየቤቱ ታግተው የሚገኙትን ሰዎች ሳይጨምር ነው። |
ታሪክ አርጋዝ እነዚህን ታግተው የሚገኙ ስደተኞች ለመርዳት ስልጣን የለውም ይላሉ። |
ይህ የሊቢያ ባለስልጣናት ኃላፊነት ነው ምክንያቱም ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ነው። |
የአንድ ሀገር ፀጥታ እና የህብረተሰቡ ደህንነት ማስጠበቅ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሀላፊነት ነው። |
የዶናልድ ያማማቶ ሹመት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |
የአፍሪቃውያንን ችግር በአፍሪቃውያን መፍታት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |
የድርቁ መዘዝ በተለይ በአርብቶ አደሮች ኑሮ ላይ ጫና አሳርፏል። |
እንቦጭ የተሰኘው አረም በጣና ሐይቅ ላይ የደቀነው ስጋትም ሌላኛው ርእሳችን ነው። |
ጣና ሐይቅ እምቦጭ በተሰኘ መጤ አረም የመወረሩ ዜና በርካቶችን አሳስቧል። |
ከኢትዮጵያ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች መካከል አንዱ የኾነው ዘመን ድራማ ባልደረቦች በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ለቀረጻ ወጥተው እንግልት እንደደረሰባቸው በዚሁ መድረክ ገልጸዋል። |
የድራማው ሠሪዎች የአካባቢው ፖሊስ በስህተት ላደረሰባቸው እንግልት ይቅርታ እንደጠየቃቸው በፌስቡክ ገጻቸዉ ተናግረዋል። |
የለም ሌላ ተልዕኮ ነበራቸው ሲል በዛው በፌስቡክ ላይ የጻፈም አለ። |
የድራማ ቀረጻው አባላት ስለ ስደተኞች ለመቅረጽ በሄዱበት ሥፍራ አጋጠመን ስላሉት እንግልት ሲገልጹ፥ |
አባላቱ ለተለየ ተልዕኮ በሥፍራው መከሰታቸውን በመግለጥ የሚከስ ጽሑፍም በዛው በማኅበራዊ መገናኛ አውታር ተነቧል። |
የ ዘመን ድራማ ቀረጻ ወብርሃን መሪ ታሪኩ ደሳለኝ በወቅቱ ስለገጠማቸው በፌስቡክ ገጹ በዝርዝር ጽፏል። |
የታሪኩ ጽሑፍ ዘለግ ያለ ቢሆንም በአካባቢው ደረሰብን ያሉትን በዝርዝር በዐይነ ኅሊና የሚያሳይ ነው። |