input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
ድዋሌ ያሉትን ከማለታቸዉ ከብዙ ዓመታት በፊት የሶማሌዎችን መገዳዳያ ትልቅ እስር ቤት ጥሩ ሐገር ለማድረግ ብዙ ተሞክሮ ነበር። |
የጨረሻዉ ጉባኤ ቃል ዛቻ ከቀድሞዋ የሶማሊያ ቅኝ ገዢና የበላይ ጠባቂ ርዕሠ ከተማ ተሰማ። |
እንደ ወታደር ሱዳን ዘመተዉ ለሱዳን ነፃነት የሚፋለሙ አማፂያንን ወግተዋል። |
እንደ ሚንስትር ሶማሊያ ሲገቡም ፓኪስታንም ሱዳኑም የሐገራቸዉን ጦር ሲወጉ ያዩቸዉ ሙስሊሞች ቅኝ ገዢ ጦራቸዉን ሲወጉ አዩ። |
የብሪታንያ የኋላ ተወዳጅ ጠቅላይ ሚንስትር ለየቅኝ ተገዢዎቹ ሐገራት መዉደም ተጠያቂዎቹ ቅኝ ገዢዎች ሳይሆኑ እስልምና ነዉ ብለዉ አረፉ። |
ይህንን እምነታቸዉን ዘ ሪቨር ዎር ባሉት መፅሐፋቸዉ በሰፊዉ አተተቱት። |
ባለፈዉ ሳምንት ሐሙስ ለንደን ላይ የመከረዉን ዓለም አቀፍ ጉባኤ የመሩት ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬሳ ሜይ የቸርችል ፓርቲ መሪ ናቸዉ። |
ምናልባት ፖለቲካዊ ሥብዕናቸዉንም አድናቂ ሊሆኑ ይችላሉም ለጉባኤተኞች የነገሩት ግን የሶማሊያ ቀዉስ በጣም እንዳሳሰባቸዉ ነዉ። |
ይሕን ያክል የዓለም ማሕበረሰብ ተወካዮች እዚሕ አዳራሽ መገኘታቸዉም ሶማሊያን ማረጋጋት አስፈላጊ እንደሆነ ሥላመኑበት ነዉ። |
ተገቢዉን እርምጃ እንደምንወስድ ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ የምንገነባዉም የረጅም ጊዜም ትንሳኤ ተስፋ እንደሚሆን ማረጋገጥ አለብን። |
ሰኔ ጁቡቲ ላይ እንዲሕ እንዳሁኑ በሶማሊያ ጉዳይ ላይ የተነጋገረ ጉባኤ ነበር። |
ዓላማዉ ለሶማሊያን ማዕከላዊ መንግሥ መመሥረት ሐገሪቱን ማረጋጋት ሕዝቧን መርዳት የሚል ነበር። |
የፕሬዝደንት ዓሊ መሕዲ መሐመድ የመልዕክተኞች ቡድን ሞቃዲሾ በገባ ማግሥት ጁቡቲ ላይ የተባለ የታቀደ ቃል የተገባዉ ሁሉ በነበር ቀረ። |
ከጅቡቲዉ እስከ ሐሙሱ ጉባኤ ድረስ ከጅቡቲ ሁለት እስከ ናይሮቢ ከካይሮ እስከ ብራስልስ ከአዲስ አበባ እስከ ለንደን ጉባኤዎች ተደርገዋል። |
ለንደን ዉስጥ ብቻ በ እና በ ሁለት ጉባኤዎች ተደርገዋል። |
ዉጤቱ አንዲቷን ሐገር የሶማሊያ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የሶማሊ ላንድ የፑንት ላንድ የጋልሙዱግ የአዛኒያ ወደሚባሉ ትናንሽ ሐገር ወይም መንግሥትነት መከፋፈል ነዉ። |
ከ ጀምሮ የተደረገዉ ጉባኤ ሥብሰባ የጦር ዘመቻ ርዳታ በጥፋት ዉጤት የተጣፋዉም ሶማሌዎች ሠላም ሥለማይፈልጉ አይደለም። |
ሶማሊ ላንድ ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ዋና ከተማ ለንደን ዉስጥ ቆስላ ከፍታለች። |
አንድ ሰሞን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የሶማሊላንድ ወደብን በግልፅ ይጠቀም ነበር። |
የአረብ ሐገራት ከሶማሊላንድ ጋር ከጦር ሰፈር እስከ ንግድ የሚደርስ ግንኙነት አላቸዉ። |
ዩናይትድ ስቴትስ አረቦችም ሆኑ ኢትዮጵያ ሶማሊ ላንድን እንደ መንግሥት አያዉቁትም። |
አብረዋት ለሚሰሯት ሐገር የመንግስትነት እዉቀና ያልሰጡበት ምክንያት በርግጥ ያነጋግራል። |
ሶማሌን ሠላም ለማድረግ ከሶማሌዎች መሐል የመሐመድ አብዱላሒ መሐመድ መንግሥትን መርጦ ወዳጅን ማስታጠቅ አሸባብን ነጥሎ በሞቃዲሾ መንግሥት ማስመታት ነዉ። |
ከዚሕ በፊት ከ ጀምሮ ተሞክሮ መክሸፉ እንደገና ተደግሞ እንደገና መጨናገፉ እንጂ ድቀቱ። |
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተረሽ እንደሚሉት ዘንድሮም ረሐብ እያንዣበበ ነዉ። |
ከ ሺሕ የሚበልጡ ሕፃናት ደግሞ ለሕይወታቸዉ በሚያሰጋ ረሐብ እየተሰቃዩ ነዉ። |
የበለፀገዉ ዓለም ዘግይቶም ቢሆን ረሐብተኛዉን ሕዝብ እንደሚረዳ በለንደኑ ጉባኤ ላይ ቃል ገብቷል። |
ከሶማሌዎች መሐል ታማኝ ሶማሌዎች የተጋበዙበት ጉባኤ ያሳለፈዉ ዉሳኔ የጦርነት ረሐብ ዑደቱን ማስቀረት መቻሉ ግን ሲበዛ አጠራጣሪ ነዉ። |
የቀድሞዉ የሶማሊላንድ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አብዱላሂ መሐመድ ዱዋሌ እኛ ጨቅላ ዴሞክራሲን እየተንከባከብን ነበር ይላሉ ዓለም ግን ጀርባችንን ይዠልጠናል። |
የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኤማኑዌል ማክሮ አዲስ የጀርመን እና ፈረንሳይ ወዳጅነት ውል ተፈራረሙ። |
ሜርክል እና ማክሮ አገሮቻቸውን በሚያዋስነው ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው ድንበራቸው የሚካሄደውን የጋራ ትብብር ማሳደግ ፍላጎት አላቸው። |
ይህ በመሆኑም አንደኛ በአውሮጳ ህብረት ውስጥ ጀርመን እና ፈረንሳይ የያዙትን ኃላፊነት እንደአዲስ መመልከት አለብን። |
ሶስተኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጋራ ርምጃ መውሰድ በሚያስችለን የጋራ ሚና ላይ መግባባት ላይ መድረስ ይኖርብናል። |
የቤልጂየም ፖሊስ በጂሃዲስትነት የጠረጠራቸዉን ሁለት ከሶሪያ የተመለሱ መሆናቸዉ የተገለጸ ጥቃት አድራሾች ሲገድል አንዱን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተነግሯል። |
ፖሊስ የሽብር እቅዱን ያከሸፈዉ ከብራስልስ መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከጀርመን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘዉ የቨርቬርስ ከተማ ባካሄደዉ አሰሳ ነዉ። |
የቤልጂየም ጠቅላይ ሚኒስትር ፖሊስ የወሰደዉ ርምጃ መንግሥታቸዉ ሽብርን ማስፋፋት የሚሹትን ለመዋጋት መቁረጧን ያሳያል ብለዋል። |
ባለፈዉ ሳምንት ፓሪስ ላይ ከደረሰዉ የሽብር ጥቃት በኋላ ጀርመንን ጨምሮ አብዛኞቹ የአዉሮጳ ሃገራት ከፍተኛ ጥንቃቄና ቁጥጥራቸዉን አጠናክረዋል። |
በኬሚሴ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሒዷል ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |
የወታደሮቹ ተልዕኮ በመንግሥቱ ጦር እና በዓማፅያን መካከል የሚካሄደው ውጊያ ዒላማ ያደረገው የአካባቢው ሲቭል ሕዝብ ጉዳት እንዳይደርስበት መከላከል እንደሆነ አንሚስ አመልክቷል። |
ስለአሳሳቢው ሁኔታም ከተቃዋሚ ቡድኖች መሪዎች እና ከመንግሥት ተወካዮች እንዲሁም በወዝግቡ አብዝተው ከተጎዱት ተፈናቃዮች ጋር ተወያይተዋል። |
ሎውኮክ በማዕከላይ ኢኳቶርያ ግዛት ያነጋገሯቸው የተቃዋሚው ኤስፒኤልኤ አይ ኦ ተጠባባቂ መሪ ፒተር ሊዦ ጆሴፍ ለሕዝብ መቆሙን አረጋግጠውላቸዋል። |
ሕዝቡ የድርድሩ ማዕከል በሚሆንበትም ጊዜ በሀገሪቱ ሰላም እንደሚወርድ እርግጠኞች ነን። |
የነፍስ ግድያ እና ክብረ ንፅህና መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ የጠቀሙባቸዋል። |
እነዚህ ሁሉ ዓለም አቀፍ ሕጎችን የጣሱ ግዙፍ ወንጀሎች ናቸው። |
በአሁኑ ጊዜ ሰባት ሚልዮን ሕዝብ የሰብዓዊ ርዳታ ያስፈልገዋል ሁኔታዎችም እየከፉ በመሄድ ላይ ናቸው። |
በመሆኑም ውዝግቡ የሚመለከታቸው ሁሉ ሰላም ለማውረድ እንዲጥሩ ዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ባለስልጣን ማርክ ሎዎኮክ ተማፅነዋል። |
በሀገሪቱ የሚታየውን ሰብዓዊ ስቃይ ለመቀነስ የኃይሉን ተግባር ማብቃት የመጀመሪያው እና ብቸኛው ዋነኛ ጉዳይ ይሆናል። |
ስለዚህ የሚያስፈልገን ወደ ርዳታ ፈላጊው ሕዝብ መድረስ የምንችልበት ፈጣን አስተማማኝ እና ገደብ ያላረፈበት መንገድ ነው። |
የአፍሪቃ ህብረት በየቀኑ ሲብሎችን የሚገድሉትን ወይም ሲብሎች ለሚገደሉበት ድርጊት ድርሻ የሚያበረክቱትን ለመቅጣት በሚወስደውን ርምጃ አንጻር መቆም ለማንም ቢሆን ትክክለኛ አይደለም። |
የአፍሪቃ ህብረት ከኢጋድእና ከሌሎች አጋሮች ጋር ባንድነት በመሆን ሰላም ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉትን ለመቅጣት ሳያመነታ እና ሳያሰልስ መስራቱን ይቀጥላል። |
ድርድሩን በሸምጋይነት እየመራ ያለው ኢጋድ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች የፈረሟቸውን የሰላም ስምምነቶች እንዲያከብሩ ጥረት ቢያደርግም እስካሁን አልተሳካለትም። |
እንዲሁም ሌላው ደግሞ የስልጣን ክፍፍሉ ተመጣጣኝነት ብሎም የካቢኔው አደላደል ሶስተኛው በሀገሪቱ የሚኖሩት ግዛቶች ቁጥር ይጠቀሳሉ። |
ምን ያህል ግዛቶች ሊኖሩ ይገባል የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ አንዳንዶች ሲሉ መንግሥት ብሏል ይህ ጉዳይ መፍትሔ ሊገኝለት ይገባል። |
ሌላው የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞችን እያወዛገበ የሚገኘው ጉዳይ የፀጥታውን ጥያቄ ይመለከታል። |
የሀገሪቱ መንግሥት ዓማፅያን ቡድኖች በብሔራዊው ጦር ውስጥ እንዲዋኃዱ ሲጠይቅ ተቃዋሚዎች የመንግሥቱ የኤስፒኤል ጦር ተበትኖ አዲስ ጦር እንዲቋቋም ነው የሚፈልጉት። |
በድርድሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ሱዳን አንግሊካን ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ጃስቲን ባዲአራማ ተቀናቃኞቹ ወገኖች ልዩነታቸውን በማስወገድ ውዝግቡን ባፋጣን እንዲያበቁ አሳስበዋል። |
እና ሕዝባቸውን የሚወዱ ከሆነ ሕዝቡ ከመጥፋቱ በፊት የሕዝቡን ፍላጎት በማድመጥ ሰላምን መቀበል አለባቸው። |
ይዘት ሼክ አንታ ዲዮፕ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት ነጻነታቸውን በመቀዳጃቸው ዋዜማ በአህጉሪቱ በሚገኙ አብዛኞቹ ምሁራን ዘንድ አንድ መጽሐፍ ተወዳጅ ነበር። |
መጽሐፉ የኔግሮ ሃገራት እና ባህል በሚል ርዕስ በሴኔጋሊያዊው ሼክ አንታ ዲዮፕ የተከተበ ነው። |
በርካታ መጽሐፍትን ላሳተሙት ፕሮፌሰር አንታ ዲዮፕ ይህ የመጀመሪያ መጽሐፋቸው ነው። |
ፕሮፌሰሩ ከዘረኝነት ጭፍን ጥላቻ የተላቀቀ አጠቃላይ የአፍሪቃ ታሪክን የመጻፍን መንገድ የከፈቱ ናቸው ይባልላቸዋል። |
አዲስ አበባን ያስጨነቀው እስርና መግለጫ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |
የምርጫ ቅስቀሳ በደቡብ ክልል የምርጫ ምልክቶችን የያዘዉ የናሙና ፖስተር በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች አለመለጠፉንም መድረክ አክሎ ገልጿል። |
የኤርትራ ኛ ዓመት የነፃነት ዕለት ኤርትራ ተቺዎች እንደሚሉት አሁን የአፍሪቃ ሰሜን ኮሪያ ናት። |
ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች በቅርቡ ባወጣዉ የፕረስ ነፃነት ዝርዝር ከኤርትራ የባሰች ሐገር ብትኖር አንድ ናት። |
ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ የራስዋን መንግሥት በይፋ ከመሠረተች ዛሬ ዓመት ደፈነች። |
የቀድሞዎቹ አማፂያን የመሠረቱት መንግሥት ትንሺቱን ምሥራቅ አፍሪቃዊት ሐገር የመላዉ አፍሪቃ የልማት ዕድገት አብነት እንደሚያደርጓት ተስፋ ሰጥተዉ ነበር። |
ተስፋዉ ግን የዶቸ ቬለ ዳንኤል ፔልስ እንደዘገበዉ ብዙ አልቆየም። |
ኤርትራ ዛሬ ብዙ ተንታኞች እንደሚተቹት የአፍሪቃ ሰሜን ኮሪያ ናት። |
ስዊድን የምትኖረዉ ኤርትራዊት ሜሮን እስጢፋኖስ ዛሬ ለዋለዉ የኤርትራ የነፃነት ቀን ደንታ የላትም። |
በትግሪኛ የሐገር ነፃነት ማለት የሰዎች ነፃነት ማለትም ነዉ ትላለች የ ዓመቷ የመብት ተሟጋች። |
በዚሕም ምክንያት ቀጠለች ሜሮን ዳንኤል ፔልስ እንደጠቀሰዉ ብዙ ሰዎች ማንም ሰዉ ነፃ ሳይወጣ የነፃነት ቀን የምናከብረዉ ለምድነዉ |
የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት የዛሬን ቀን የኤርትራ ነፃነት ሲታወጅ ርዕሠ ከተማ አስመራ በደስታ ፌስታ ፈንጠዝያ ተደበላልቃ ነበር። |
ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በደስታ ባሕር ይዋኝ ለነበረዉ ሕዝባቸዉ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የኤርትራ ዳግማዊ ልደት ነዉ። |
አዲሲቱ ሐገር የመላዉ አፍሪቃ የልማት ዕድገት ተስፋ እንደምትሆንም የፕሬዝደንት ኢሳያስ መንግሥት ቃል ገብቶ ነበር። |
ብሪታንያዊቱ የኤርትራ ጉዳይ አጥኚና ደራሲ ሚሼኤላ ሮንግ እንሚሉት ደግሞ በ አስመራን የጎበኙበት ወቅት ልዩ ጊዜ ነበር ። |
ኤርትራ ከሙስና የፀዳች መንግሥቷ ለሁሉም ክፍት የፈለገዉ ሰዉ በፈለገ ጊዜ ሚንስትሩን ማናገር የሚችልባት ሐገር ነበረች። |
በ ዎቹ ተሰደዉ የነበሩ ኤርትራዉያን በብዛት ወደ ሐገራቸዉ እየተመለሱ መዋዕለ ንዋያቸዉን ሥራ ላይ እያዋሉ ነበር። |
ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያዋስነዉ ድንበር በቅጡ ባለመካለሉ በ ሌላ ጦርነት ፈነዳ። |
ኢሳያስ የቀድሞ ሚንስትሮች እና ታጋዮችን ሳይቀር የሚተቿቸዉን ሁሉ ባንድ ጊዜ እስር ቤት ወረወሯቸዉ ደራሲ ሮንጎ እንዳሉት። |
ዲፕሎማቶች ሳይቀሩ ከአስመራ ዉጪ መንቀሳቀስ የሚችሉት መንግሥትን አስፈቅደዉ ነዉ። |
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኤርትራ ጉዳይ ልዩ አጥኚ ሺይላ ኬታሩት የሰብአዊ መብት ጥሰቱ አሳሳቢ ነዉ። |
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የዛሬ ሁለት ዓመት የኤርትራ መንግሥትን ሰዎችን በባርነት በማሰቃየት በመድፈር እና ማንገላታት ተጠያቂ አድርጎታል። |
ሰብአዊ መብት ከሚጣስባቸዉ እና ወጣቶችን ለስደት ከሚዳርጉ ምክንያቶች አንዱ ብሔራዊ አገልግሎት ነዉ። |
በትወራ ደረጃ ዓመት የሞላዉ ኤርትራዊ ለተወሰነ ጊዜ ወታደራዊ እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጥበት ግዳጅ ነዉ። |
ብዙዎች ግን ለመንግሥት ገደብ የለሽ አገልግሎት የሚሰጥበት ነዉ ባዮች ናቸዉ። |
ኤርትራ ዉስጥ ምርጫ ላለመደረጉም ከኢትዮጵያ ጋር ያለዉ ግጭት መፍትሔ አለማግኘቱን ተጠያቂ ያደርጋሉ። |
የኤርትራ ስደተኞች ቁጥር እየተበራከተ ከመጣ ወዲሕ ጀርመንን ጨምሮ ጥቂት ምዕራባዉያን መንግሥታት ከአስመራ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ለማሻሻል አንዳድ እንቅስቃሴዎችን ጀምረዋል። |
በ የቀድሞዉ የጀርመን የልማት ሚንስትር ጌርድ ሙለር አስመራን ሲገበኙ ባመቱ አንድ የኤርትራ ከፍተኛ የባለሥልጣናት ቡድን በርሊንን ጎብኝቷል። |
ይላሉ አንዳድ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ተዋኞች ከኤርትራ መንግሥት ጋር ለመገናኘት ጥሪት እያፈሰሱ ነዉ። |
ከኤርትራ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ወደነበረበት ለመመለስ ባለፉት ሰወስት ዓመታት እየጣሩ ነዉ። |
ከዚሕ ቀደም ያነሳሁት መሠረታዊዉ የሰብአዊ መብት ይዞታ በተጨባጭ ምን መሻሻል ተገኝቷል |
ከቅርብ ዓመታት ወዲሕ ሥለ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጤና ማጣት የሚናፈሰዉ አሉባልታ እየተደጋገመ ነዉ። |
ሰዉዬዉ አንድ ቀን አንድ ነገር ቢሆኑ ምናልባት ለዉጥ ሊመጣ ይቻላል ባዮች አሉ። |
ደራሲ ሮንግ ግን ሥልጣኑ ከብዙዎቹ የኢሳያስ ጄኔራሎች ካንዱ እጅ አያመልጥም ባይ ናቸዉ ደራሲዋ። |
ብሔራዊ ሸንጎዉ እና የፍትሕ ሥርዓቱን የመሳሰሉ ተቋማት ትክክለኛ ሥልጣን የላቸዉም። |
ሥለዚሕ ኢሳያስ አፈወርቂ ጡረታ ቢወጡ ወይም ቢሞቱ ብዙ ጄኔራሎች አሉ። |
ከነሱ በታች ደግሞ የወጣቱን ስሜት የሚጋሩ ወጣት የጦር መኮንኖች አሉ። |
ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለመመስረት የሚደረግ እንቅስቃሴ ይኖራል ብዩ ግን አላምንም። |
እንደ ሚመስለኝ አንዱ ጄኔራል ሥልጣኑን ከኢሳያስ የመዉረስ እድሉ ሰፊ ነዉ። |