inputs
stringlengths
86
2.15k
targets
stringlengths
1
2.05k
language
stringclasses
1 value
split
stringclasses
3 values
template
stringclasses
9 values
dataset
stringclasses
1 value
config
stringclasses
1 value
length
int64
46
653
Content: በኅዳር 19 እና 20/2013 ዓ.ም የተፈጸመው የጅምላ ግድያ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን እንደሚችል ሪፖርቱ ገልጿል። አንድ የዓይን ምስክር ለቢቢሲ እንደገለጹት በከተማዋ በተፈጸመው ግድያ በየመንገዱ አስከሬኖች ለቀናት ሳይነሱ መቆየታቸውን ገልጸው በርካቶቹ በጅብ መበላታቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ትግራይ ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች መግባታቸውን በይፋ ያስተባበሉ ሲሆን በአምነስቲ ሪፖርት ላይ የሰጡት ምላሽ የለም። ትግራይ ውስጥ የሚገኘውን የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ነበር ጥቅም 24/2013 ዓ.ም ወታደራዊ ግጭቱ የተቀሰቀሰው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለአገሪቱ ፓርላማ በዚህ ዘመቻም አንድም ሰላማዊ ዜጋ እንዳልተገደለ ቢገልጹም፤ አብዛኞቹ ያልታጠቁ ልጆችና ወንዶችን በጉዳና ላይ ወይም ቤት ለቤት በተደረጉ አሰሳዎች በኤርትራ ወታደሮች የተገደሉ ሰዎችን ስለመቅበራቸው የዓይን እማኞች ገልጸዋል። የአምነስቲ ሪፖርት በጥንታዊቷና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ስፍራ በሆነችው አክሱም ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቤተክርስቲያናት ውስጥ የቀብር ቦታዎችን የያዙ የተቆፈሩ ስፍራዎችን የሚያመለክቱ ከፍተኛ የምስል ጥራት ያላቸው የሳተላይት ምስሎችን አካቷል። የኮምዩኒኬሽን መስመሮች መቋረጥና ወደ ትግራይ ለመግባት አለመቻል በግጭቱ ወቅት ስለተከሰቱ ጉዳዮች በወቅቱ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። በአክሱም የነበረው የኤሌክትሪክና የስልክ አገልግሎት ግጭቱ በጀመረ በመጀመሪያው ዕለት ተቋርጦ ነበር። ከሪፖርቱ ጋር በተያያዘ ይህንን የአምነስቲን ሪፖርት በተመለከተ መንግሥታዊው የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳለው ምንም እንኳን ያልተጠናቀቀ ቢሆንም በአክሱሙ ክስተት ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል። የኮሚሽኑ የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቱ ጥቂት ነዋሪዎችና የህወሓት ታጣቂዎች ለፈጸሙባቸው ጥቃት የኤርትራ ወታደሮች በወሰዱት የበቀል እርምጃ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰላማዊ ሰዎች በከተማዋ ውስጥ ተገድለዋል ሲል አመልክቷል። ኮሚሽኑ ጥቃቱ በኤርትራ ወታደሮች የተፈጸመው የህወሓት ወታደሮች አካባቢውን ለቀው ከወጡ በኋላ መሆኑንም ገልጿል። በተማሪም በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ተፈጽመዋል ስለተባሉ በርካታ የከባድ መሳሪያ ድብደባዎች ምርመራዎችን እያካሄድኩ ነው ብሏል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአክሱም ከተማ ተፈጽሟል ያለውን ይህንን የሰብአዊ መብት ጥሰት የምርመራ ውጤት የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርና የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይል ቃል አቀባይ ለሆኑት ለአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ማቅረቡንና በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዳላገኘ በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል። ቢቢሲም ይህንን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከተመለከተ በኋላ ከኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ በኢሜይል ጥያቄ ቢያቀርብም ለጊዜው ምላሽ አላገኘም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ረቡዕ ለተካሄደው በ46ኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አገራቸው አሉ በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ አስፈላጊውን ማጣራት እንደምታደርግ ገልጸዋል። አቶ ደመቀ በንግግራቸውም ወሲባዊ ጥቃትን ጨምሮ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የመንግሥታቸው ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች እንደሆኑ አመልክተው "በዚህ ዙሪያ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ የድርጊቶቹን ፈጻሚዎች ተጠያቂ እንዲሁኑ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን" ሲሉ ተናግረዋል። አክሱም ከተማ። አምነስቲ በሪፖርቱ ከግድያው ባሻገር ሰፊ ዝርፊያ በኤርትራ ወታደሮች ተፈጽሟል...\nThe previous content can be summarized as follows:
በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች በኅዳር ወር በሁለት ቀናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደላቸውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት አመለከተ።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
395
Doc to summarize: በአዲሱ መመሪያ መሰረት የኮሮናቫይረስ ተመርምረው ፖዘቲቭ መሆናቸው ከተረጋገጠ ወይንም በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት መኖራቸው የታወቀ ሰዎች ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ የሚያዝ መመሪያ ወጥቷል። በአገሪቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደገና ማገርሸቱን ተከትሎም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠበቅ ያለ መመሪያ እንዲወጣ ያዘዙት። በትናንትናው ዕለት፣ መስከረም 9፣ 2013 ዓ.ም 4 ሺህ 422 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 27 ግለሰቦችም ህይወታቸው አልፏል። ከዚህም በተጨማሪ በስኮትላንድ 350 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ከግንቦት ወር በኋላም ከፍተኛ ነው ተብሏል። በዌልስ 212 ና በሰሜን አየርላንድ 222 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል። መመሪያውን ለተላለፉ በመጀመሪያ 1 ሺህ 300 ዶላር የሚያስቀጣ ሲሆን በተደጋጋሚ መመሪያውን ለሚጥሱት እስከ 13 ሺህ ዶላር ያስቀጣል። ከዚህም በተጨማሪ ጥሰቱ ከፍተኛም መሆኑ ከተረጋገጠ በመጀመሪያም ቢሆን መመሪያውን ለሚጥሱ 13 ሺህ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል። በእንግሊዝ እስካሁን ድረስ ግለሰቦች ራሳቸውን እንዲያገሉ የምክር አገልግሎት ብቻ ነበር የሚሰጣቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱን መመሪያ ባወጁበት እለትም ቫይረሱን ለመታገል ሁሉም መመሪያውን ማክበር አለበት ብለዋል። "ሁሉም ቢሆን ይሄ አዲሱ መመሪያ ጠቃሚ እንደሆነ ሊረዳ ይገባል። መመሪያውን ሁሉም ሊያከብረው ይገባል። የብሄራዊ ጤና አገልግሎት በሚያዛችሁ መሰረት ቫይረሱ ተገኝቶባችሁም ከሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካላችሁ ራሳችሁን ለይታችሁ ልታቆዩ ይገባል። ካለበለዚያ ግን እነዚህን መመሪያዎች ተላልፋችሁ ከተገኛችሁ ጠበቅ ያለ ቅጣት ይጠብቃችኋል" በማለት ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት እንዲሁም ተጋላጭ ማህበረሰቦቹን ከቫይረሱ ለመታደግና ህይወት ማዳንም እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር ቢጤ አዘል መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል። እስካሁን ድረስ 19 ሺህ ሰዎች መመሪያውን የጣሱ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑትም የተጣለባቸውን ቅጣት እንዳልከፈሉም ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ሰዎች በአንድ ጊዜ የሚሰጥም 650 ዶላር ይኖራል ተብሏል። \nSummary in the same language as the doc:
ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ የተነገራቸው እንግሊዛውያን መመሪያውን ካላከበሩ 13 ሺህ ዶላር እንደሚቀጡ መንግሥታቸው ከሰሞኑ አስታውቋል።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
259
የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ\nሆስኒ ሙባረክ ህይወታቸው ያላፈው ግብጽ ካይሮ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው ሳለ ነው። ሆስኒ ሙባረክ እ.አ.አ. 2011 ላይ በግብጽ የአረብ አብዮት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአገሪቱ ጦር ከሰልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገዋል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ግብጽን ለሦስት አስርት ዓመታት መርተዋል። የአረብ አብዮት በተቀሰቀሰ ወቅት ለተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በተወሰደው እርምጃ በተባባሪነት ተጠያቂ ተደርገው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸው ነበር። ይሁን እንጂ ከሦስት ዓመት በፊት የተመሰረቱባቸው ክሶች ውድቅ ተደርገው ነጻ ወጥተው ነበር። የቀድሞ ፕሬዝደንት ህልፈተ ህይወትን ይፋ ያደረገው የግብጽ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። ሙባረክ ከአንድ ወር በፊት የቀዶ ህክምና ማድረጋቸውን እና በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ መቆየታቸውን የቤተብ አባሎቻቸው ለግብጽ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ሙባረክ ከልጅ ልጃቸው ጋር በሆስፒታል ሳሉ የተነሱት ፎቶግራፍ በርካቶች ተጋርተውት ነበር። ባሳለፍነው ቅዳሜ የሙባረክ የልጅ ልጅ የሆነው አላ፤ አያቱ በጽኑ ሕሙማን ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ አረጋግጦ ነበር። እአአ 1928 የተወለዱት ሙባረክ፤ በወጣትነት እድሜያቸው የግብጽ አየር ኃይልን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ የአረብ-አስራኤል ጦርነት ወቅት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል። ፕሬዝደንት አንዋር ሳዳት መገደላቸውን ተከትሎ ሙባረክ የግብጽ ፕሬዝደንት በመሆን መንበረ ስልጣኑን ይዘዋል። \n\ntl;dr:
የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ በ91 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
amh_Ethi
train
tldr
GEM/xlsum
amharic
169
የአማራ ክልል የመንገድና የትራንስፖርት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዳጆን ጨምሮ የሚመለከታቸው የዞን ባለስልጣናት መንገዱ አልተዘጋም ሲሉ፤ የትግራይ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ በበኩሉ በደህንነት ስጋት ምክንያት ህዝቡ አቅጣጫ ለመቀየር ተገዷል ይላል። •በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው •በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ የሰሜን ወሎ ዞን የመንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጸሃይነው ሲሳይ በአሁኑ ሰዓት ወደ መቀሌም ይሁን ወደ አዲስ አበባ ምንም አይነት የትራፊክ መስተጓጎል እንደሌለና ኃገር አቋራጭ አውቶብሶችም እንደተለመደው እያለፉ መሆኑንም አበክረው ይናገራሉ። መነሻቸውን ከወልዲያ አድርገው በኮረም በኩል ሰቆጣ የሚሄዱትም መደበኛ ስምሪታቸውን ይዘው እየሰሩ ነው የሚሉት አቶ ጸሃይነው፤ በሰሜን ወሎ ዞን በመንገድ መዘጋት ምክንያት የተቋረጠ የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖሩን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም በጥቅምት ወር ላይ በአላማጣ ከተማ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ በጠየቁ የቆቦ ከተማ ወጣቶች የአላማጣ ቆቦ መስመር ለቀናት መዘጋት፣ እንዲሁም በወልዲያ በኩል ወደ ትግራይ ለበዓል ሲጓጓዙ የነበሩ በጎች በወጣቶች መዘረፍ፣ እንዲሁም ወደ ትግራይ ክልል ይጓዝ የነበረ ተሳቢ አማራ ክልል ውስጥ በወጣቶች እንዲቆም ተደርጎ ጭነቱ የመዘረፍ ሁኔታ ተከስቶ ነበር። በዚህም ምክንያት የፀጥታ ስጋት በመፈጠሩ ወደ ትግራይ ክልል ለመጓዝ በአፋር በኩል ተለዋጭ መንገዶችን መጠቀም ጀምረዋል የሚሉ ጉዳዮች በማህበራዊ ሚዲያ እየተነገረ ቢሆንም አቶ ጸሃይነው ይህ ከእውነት የራቀ ነው ይላሉ። አሽከርካሪዎች በአፋር በኩል ያለውን ተለዋጭ አማራጭ መንገድ መጠቀማቸውን አምነው ይህ ግን እንደሚባለው ሳይሆን ደሴ እና ደብረ ብርሃንን አቆራርጦ ከወልዲያ-አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ላይ ብዛት ያለው የፍጥነት መቀነሻ ግንባታ በመኖሩ ይህን ሽሽት የአፋሩን ተለዋጭ መስመር እንደማራጭ እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል ይላሉ "ከፍጥነት መቀነሻዎቹ ብዛት የተነሳ 'በአሽከርካሪዎች፣ በተሽከርካሪዎች እና በተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው። በሰዓታችን እየደረስን አይደለም' በማለት የታችኛውን [አፋር] ተለዋጭ መንገድ ሲጠቀሙ ነበር። እኛም ከፌደራል መንገዶች ባከስልጣን ጋር በመነጋገር የፍጥነት መቀነሻዎቹ እንዲነሱ ተደርጎ መንገዱ ክፍት ተደርጓል።" ይላሉ አቶ ጸሃይነው። የደቡብ ወሎ ዞን የሰላም እና ደህንነት መምሪያ ተወካይ ኃላፊ አቶ እጅጉ መላኬም በአቶ ጸሃይነው ሐሳብ ይስማማሉ ከትግራይም ወደ አማራ ክልል እንዲሁም ከአማራ ወደ ትግራይ ያሉ የተሽካርካሪዎች እንቅስቃሴ በተለመደው ቀጥለዋል ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ የአማራ ክልልን በማቋረጥ ትግራይን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘውን መስመር ዝግ አለመሆኑንና ምንም አይነት የፀጥታ ስጋት እንደሌለም አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም በአንድ ወቅት ለጥቂት ሰዓታት መንገዶች የተዘጉበትን አጋጣሚ አንስተው እሱም ችግሩ ተቀርፎ ወዲያው ተከፍቷል ይላሉ። "በአንድ ወቅት ብቻ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን የፍጥነት መቆጣጠሪያ መቀነሻዎችን ሲያፈርስ የተቀየሙ ወጣቶች መንገዱ ለጥቂት ሰዓታት ዘግተውት ነበር። ከዚህ ውጪ እኛ የምናውቀው ችግር የለም" ብለዋል። •“በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር ከዚህ ቀደም ጤፍ እና በጎች ከመኪና ላይ ተወሰዱ የሚባለው ባለፈው ዓመት መጀመሪያ ላይ የተፈጠረና በጣም የቆየ መረጃና የአንድ ጊዜ ክስተት መሆኑንም ገልፀዋል። ባለፈው አመት ወጣቶች የፍጆታ እቃዎችን የጫኑ መኪኖችን አያልፉም ብለው መንገድ ዘግተው የነበረ ሲሆን በወቅቱም የፀጥታ ኃይሉን በማሰማራት... \n\nGive me a good title for the article above.
ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል?
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
403
ዚምባብዌ ለሙጋቤ ብሔራዊ ቀን ሰየመች\nየሃገሪቱ ጋዜጣ እንደዘገበው የቀድሞው ፕሬዝደንት ሙጋቤ የልደት ቀን ብሔራዊ የህዝብ በዓል እንዲሆን ታወጇል። ሙጋቤ የሃገሪቱ ሠራዊት ጣልቃ መግባቱን እና ለቀናት የዘለቀ ህዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ሥልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል። 'ዘ ሄራልድ' የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው የቀድሞው ፕሬዝዳንት የልደት ቀን ብሔራዊ በዓል እንዲሆን የፓርቲያቸው ዛኑ-ፒፍ የወጣት ሊግ ከፍ ያለ ግፊት ሲያደርግ ቆይቶ ተቀባይነት ያገኘው ባለፈው ነሐሴ ወር ነበር። ውሳኔው ግን በይፋ እንዲመዘገብ የተደረገው አርብ ዕለት እንደሆነ ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት አዲሱ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እንደተናገሩት፤ ሙጋቤ ከሃገሪቱ መስራቾች እና መሪዎች መካከል አንዱ እንደመሆናቸው ተገቢው ዕውቅናና ክብር ሊሰጣቸው ይገባል። "በግሌ ሙጋቤ አባት፣ መምህር፣ የትግል ጓድ እና መሪ እንደሆኑ ይቆያሉ" ሲሉ ምናንጋግዋ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀው ነበር። ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን እንዲለቁ ለማግባባት 10 ሚሊዮን ዶላር ተሰጥቷቸዋል የሚለውን ሪፖርት እስካሁን ማረጋገጥ አልተቻለም። ሙጋቤና ባለቤታቸው ግሬስ በአሁኑ ጊዜ በዋና ከተማዋ ሐራሬ ውስጥ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን ሃገራቸውን ለቀው የመውጣት ዕቅድ የላቸውምም ተብሏል። \n\ntl;dr:
ዚምባብዌ የካቲት 14ን የሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ ብሔራዊ የወጣቶች ቀን በማለት ሰየመች።
amh_Ethi
train
tldr
GEM/xlsum
amharic
158
ፕሬዝዳንቱ ምርጫው እንዲራዘም ፈልገው የነበረው በፖስታ የሚሰጥ ድምጽ ማጭበርበር አያጣውም ከሚል ስጋት ነው። በሪፐብሊካን የበላይነት የሚመራው ሴኔት አባል የሆኑት ሚች ማክኮኔል እና በህግ መምሪያ ምክር ቤት ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ሪፐብሊካን የሚወክሉት ኬቨን ማክ ካርቲ ናቸው የትራምፕን ሃሳብ የተቃወሙት። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምርጫውን የማራዘም ሥልጣኑ የላቸውም፤ የትኛውም የምርጫ ማራዘም እቅድ መጽደቅ ያለበት በኮንግረሱ ነው ተብሏል። ቀደም ብሎ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳር ወር የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፖስታ የሚሰጥ ድምጽ ወደ ማጭበርበርና የተሳሳተ ውጤት ያመራል በሚል ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ሃሳብ አቅርበው ነበር። ምርጫው የሚዘገየው እስከመቼ ድረስ እንደሆነ ሲናገሩም ሰዎች "በአግባቡ፣ ደህንነታቸውና ምስጢራቸው ተጠብቆ" መምረጥ ሲችሉ ብለው ነበር። • ዶናልድ ትራምፕ መጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲዘገይ ጠየቁ • ጭምብል የማይለብሱ የአሜሪካ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት አባላት ይባረራሉ ተባለ • አውሮፓ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያሰጋታል? የፕሬዝዳንቱን ስጋት የሚያረጋግጥ መረጃ ያለው በጣም አነስተኛ ቢሆንም እርሳቸው ግን በተደጋጋሚ በፖስታ የሚሰጥ ድምጽን በመቃወም ሲናገሩ ይደመጣሉ። የአሜሪካ ግዛቶች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በፖስታ የሚሰጥ ድምጽን ቀለል ማድረግ ይፈልጋሉ። ሴናተር ማ ኮኔል አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከዚህ በፊት አንዴም ዘግይቶ እንደማያውቅ ተናግረዋል። " በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም። በጦርነት፣ በኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ እያለን አንኳ በፌደራል ደረጃ የተያዘ ምርጫ በወቅቱ ተካሂዶ ነው የሚያውቀው። በዚህ ዓመት ህዳር ወር ላይም ያንን ነው የምናደርገው' ብለዋል። ማክ ካርቲም የእርሳቸውን ሃሳብ በመደገፍ " በፌደራል በሚደረግ የምርጫ ታሪክ ይህ ተከስቶ አይታወቅም፤ ስለዚህ ምርጫችንን በታቀደለት ጊዜ እናከናውናለን" ብለዋል። የትራምፕ ደጋፊ የሆኑት ሴናተር ሊንድሲ በበኩላቸው ምርጫውን ማራዘም "መልካም ሃሳብ አይደለም" ብለዋል። ነገር ግን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ በፕሬዝዳንቱ ሃሳብ ላለመጠለፍ ሲታገሉ ተስተውሏል። ጋዜጠኞች፣ ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ያራዝሙት እንደሆነ ሲጠይቋቸው " በእንዲህ ያለ የህግ ትርጓሜ ውስጥ " መግባት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። የትራምፕ ዳግም ምርጫ ቃል አቀባይ ሆጋን ጊድሊ ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ጥያቄ ነው ያነሱት" ሲሉ ተከላክለዋል። በአሜሪካ ህግ መሰረት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምርጫውን የማራዘም መብት የላቸውም። የምርጫውን ቀን መቀየር የሚያስፈልግ ከሆነ መጽደቅ ያለበት በኮንግረሱ እና በህግ መወሰኛ ምክር ቤት ይሆናል። የህግ መወሰኛ ምክር ቤትን ደግሞ የሚቆጣጠሩት ዲሞክራቶች ሲሆኑ ከአሁኑ አስቀድመው አንዳንድ ምክር ቤት አባላት የምርጫው መራዘምን ሃሳብ ተቃውመውታል። የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወደ 2021 ለመግፋት የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ህገ መንግሥት ማሻሻያ ማድረግን እንደሚጠይቅ የሕገ መንግሥት ባለሙያ የሆኑ ግለሰቦችን ጠቅሰው አሜሪካ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ስድስት የአሜሪካ ግዛቶች በህዳር ወር የሚካሄደውን ምርጫ በአጠቃላይ "በፖስታ በሚሰጥ ድምጽ" ለማድረግ አቅደው ነበር። እነዚህ ግዛቶች ዋሺንግተን፣ ኦሪገን፣ ኮሎራዶ፣ ሃዋይ፣ ዩታህ እና ካሊፎርኒያ ናቸው። እነዚህ ስድስት ግዛቶች ለተመዘገቡ መራጮች ወዲያውኑ በፖስታ ድምጽ መስጫ የሚልኩ ሲሆን፤ ፖስታዎቹም በምርጫ ቀን ተመልሰው የሚላኩ አልያም በምርጫ ጣቢያ የሚመለሱ ይሆናል። ይህ የፕሬዝዳንቱ ሃሳብ የተሰማው የአሜሪካ ምጣኔ ሃብት በ1930 ከገባበት ድቀት በባሰ... \n\nGive me a good title for the article above.
ሪፐብሊካን ለትራምፕ፡ ምርጫውን ማዘግየት አይችሉም
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
400
Doc to summarize: ምን እኛ ብቻ ነን እንዴ፤ አገርም ችግር አጋጥሟታል እኮ! እንዴት? ኢንደስትሪያል ፓርኩም ኢንቨስተር ካልተገኘ ቆርቆሮ ነው አይደለም እንዴ? የአገር ኢኮኖሚው ቀዝቅዟል። የአገር ኢኮኖሚ ከቀዘቀዘ የአንዳንድ ሴክተሮችም ኢኮኖሚ ይቀዘቅዛል። ሁለተኛው በየትኛውም የቢዝነስ [ሽክርክሪት] ውስጥ እኛ አገር ብርቅ ሆኖ ነው እንጂ መነሳት፣ መውደቅ፣ መሞት፣ እንደ አዲስ መፈጠር ያለ ነው። ስለዚህ ችግር አጋጥሞናል እያሉኝ ነው፣ አቶ ዘሪሁን? ቆየኝ...ቆየኝ! እነዚህ የተባሉት ነገሮች ሁሉ እውነት ናቸው ቢባሉ ሊገርም አያስችልም፤ ግን እንደዜና ሊቀርብ ይችላል። የሚገርም ነገር እና ዜና የሚሆን ነገር ይለያያል። ስለዚህ ቢቢሲም የሚገርም ዜና ብሎ ሳይሆን ምናልባት የአገሪቱ ኢኮኖሚ የተለያዩ ሴክተሮችን 'አፌክት' እያረገ ነው በሚል ሊቀርብ ይችላል። ስለዛሚ ሬዲዮ ትኩረት አድርገን እናውራ፣ አቶ ዘሪሁን? ልመጣልህ ነው! ስለዛሚ እናውራ ከተባለ ዛሚ በሠራተኛ ደረጃ የዘገየ ደመውዝ የለም። የዘገየ ደሞዝ ቢኖር የዚህኛው ወር፣ እሱም የዘገየው ሁለት ቀን ነው። ስለዚህም ሁልጊዜ ወር በገባ በ30 እንከፍላለን። የአሁኑ ወር ላይ ወር በገባ በ30 ሳይሆን በ2 እና በ3 ተከፈለ። ምክንያቱም ደመወዝ የምንከፍለው ከምናገኘው የማስታወቂያ ገቢ ነው። ከምናገኘው የማስታወቂያ ገቢ የምንሰበስበው ደግሞ ማስታወቂያ [አምጪዎች] ሲከፍሉን ነው። እሱን በጊዜው ሊከፍሉን አልቻሉም። ደንበኞቻችን ናቸው። ስለሆነም እነሱን መጠበቅ ነበረብን። ያም ሆኖ ግን ተወጥተናል። በአጋርነት በጣቢያችሁ የሚሠሩትም እየሸሹ ነው የሄደው ኢትዯፒካሊንክ ነው። 6 ዓመት እኛ ጋር ቆይቷል። የራሱ ሬዲዮ ለመጀመር አሳብ አለው። እስከዛ ድረስ ለመሟሟቅ ወደ ፋና ሄጃለሁ ብሏል። ይሄ ምርጫቸውን እኛ ልናቆመው አንችልም። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወታደሮቹ ድርጊት ተበሳጭተው እንደነበር ተናገሩ • "ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው" ማስታወቂያ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ የገቢ ማነስ ሊሆን ይችላል፤ ቁጭ ብላችሁ ተነጋግራችኋል? አውርተናል። በቃ ልንሄድ ነው ምናምን ብለው ነግረውኛል። ከፋና ጋር በፊት ባለመግባባት ነው የተለያዩት። አሁን የይቅርታና የመደመር ዘመን ስለሆነ ይቅርታና መደመር አግኝተው ሄደው ሊሆን ይችላል። (ሳቅ) እሱም የኔ ችግር አይደለም። ምርጫቸውን ግን አከብራለሁ፡፡ ወዳጆቼ ናቸው። የ"ዛሚ ክብ ጠረጴዛ"…"ቆይታ ከሚሚ ስብሐቱ ጋ" ተቋርጧል እየተባለ ነው። የ"ዛሚ ክብ ጠሬጴዛ" መቼ ነው የተቋረጠው የሚለውን እናንተ ፈትሹ። አልተቋረጠም ነው የሚሉኝ፣ አቶ ዘሪሁን? አልተቋረጠም ሳይሆን ላስረዳህ። የ "ቆይታ ከሚሚ ስብሐቱ" ፕሮግራም ሚሚ አገር ውስጥ የለችም፤ ወደ ውጭ ሄዳለች። ለምን ሄደች? ለግል ጉዳይ ሄደች። የግል ጉዳይዋ ምንን ይመለከታል? ራሷን ማስደሰት ሊሆን ይችላል፤ መታከም ሊሆን ይችላል መብቷ ነው። አንደኛው ይሄ ነው። ይሄም ከሆነ በኋላ እሱን ለመተካት ሞክረናል። የሞከርነው ቤት ውስጥ ባሉ ጋዜጠኞች ነው። ስለሆነም አንድ ሳምንት ይቀርባል፤ አንድ ሳምንት አይቀርብም። እንደዚህ እያለ ሄዷል። በአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ ሁሉ ነገር ቢቀጥል በጣም አሪፍ ነው ቢቻል። እረፍት ሲወጡ የሚተካቸውና የእነሱን ካሊበር [ቁመና] የሚመጥን ሰው ቢኖር ሳይቋረጥ ቢሄድ አሪፍ ነው። • "የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተለው ዲፕሎማሲ ቀለም አልባ ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ ይሄ [ክስተት] የተገጣጠመበት ሁኔታ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መጥቶ ነበር። አቧራ በአቧራ ነው። ማጨብጨብ ነው። ወዴት ነው የምንሄደው? እንዴት ነው የምንሄደው? ከጥቅል ነገሮች ውጭ ምንም ነገር...\nSummary in the same language as the doc:
በሃገር ውስጥ ቀዳሚ ከሆኑት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነው ዛሚ 90.7 በችግር ውስጥ እንደሆነና ሊዘጋ እንደሚችል በስፋት እየተወራ ነው። በዚህና ጣቢያውን በሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን አቶ ዘሪሁን ተሾመን አነጋግረናል። የፋይናንስ ችግር አጋጥሟችኋል እየተባለ ነው
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
455
Title: ስቶርምዚ በካምብሪጅ የጥቁር ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ አድርጓል ተባለ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ስቶምዚ በየዓመቱ ወደ ካምብሪጅ ለሚገቡ ጥቁር ተማሪዎች ወጪያቸውን ይሸፍናል ዩኒቨርስቲው ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአጠቃላይ ተማሪዎቹ 3 በመቶ የሚሆኑ ጥቁር ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብሏል። ስቶርምዚ በየዓመቱ ወደ ዩኒቨርስቲው ለሚገቡ ሁለት ጥቁር ተማሪዎች ወጪያቸውን ለመሸፈን ቃል ገብቶ ነበር። ዩኒቨርስቲው ይህ ቁጥር የአጠቃላዩን የዩኬ ማህበረሰብ የሚያሳይ ነው ብሏል። • "የሞራል ባቢሎን ውስጥ ነን፤ በጎና እኩይ መለየት አቅቶናል" ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ • የከተማው ትምህርት ቢሮ 300ሺህ ተማሪዎችን ለመመገብ እየተዘጋጀ ነው ዘንድሮ ወደ ዩኒቨርስቲው 91 ጥቁር ተማሪዎች የገቡ ሲሆን በ 2018 በመስከረም ወር ትምህርት ከጀመሩት ከግምሽ በላይ የሚሆኑት ጥቁሮች ናቸው ተብሏል። ዩኒቨርስቲው አክሎም ስቶርምዚ የሁለት ተማሪዎችን ወጪ እችላለሁ ማለቱ ከተሰማ በኋላ ከዩኒቨርስቲው ውጪ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚፈልጉና ስለተለያዩ ኮርሶች የሚጠይቁ ጥቁር ተማሪዎች ቁጥር ጨምሯል። በዩኒቨርስቲው ለሚማሩ ጥቁር ተማሪዎች ቁጥር መጨመር ሌላው ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው በርካታ ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ዩኒቨርስቲውን ለማስተዋወቅ የወሰዱት ርምጃ ነው። ዩኒቨርስቲው በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘንድሮ ከ200 በላይ ጥቁር ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል። በዩኒቨርስቲው ውስጥ የትምህርት ጉዳዮች ምክትል ቻንስለር የሆኑት ፕሮፌሰር ግርሃም ቪርጎ " ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥቁር ተማሪዎች የተመዘገቡበት ዓመት ሲሆን በራሳቸው በተማሪዎችና በዩኒቨርስቲው ጥረት የተሳካ ነው ። እኛ የመግቢያ ነጥባችንን አልቀነስነም" ብለዋል። በዩኒቨርስቲው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዋኒፓ ንድሎቩ እንደሚገልፁት የተማሪዎቹ ቁጥር መጨመሩ " ጥቁሮችና ካሪቢያኖች የዩኒቨርስቲው የቀደመ ባህልን ለመስበር ጠንክረው በመስራታቸው ነው" ብለዋል። "ለሌሎች ጥቁር ተማሪዎች በካምብሪጅ ቦታ እንዳላቸውና ስኬታማ እንደሚሆኑ ጥሩ ማሳያ ይሆናል" ሲሉም አክለዋል።
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
230
ግን ይህ ታሪኩን የምናጋራችሁ አባት ከአቅሜ በላይ ሆኖ የቁም ቅዠት ሆኖብኛል ይላል። ስቲቭ ይባላል፤ የሚወደው ልጁ ከተራ ጌም ተጫዋችነት አልፎ አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ላይ የደረሰ ሱሰኛ ሆኗል። ከዚህም ባለፈ መቆጣጠር የማይችለው የቁማር ሱስ ውስጥ ተዘፍቋል። "ልጄ በጌሞች እንዲህ ይሆናል ወይም መጨረሻው የቁማር ሱስ ይሆናል ብዬ በፍጹም ገምቼ አላውቅም።'' • የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? የስቲቭ ልጅ በሃያዎቹ መጀመሪያው ውስጥ የሚገኝ ወጣት ነው። በልጃቸው ምክንያት ስቲቭና ባለቤቱ ለሦስት ዓመታት ተሰቃይተዋል። ''እኛ ያየነውን መከራ ማንም ቤተሰብ ማየት የለበትም። ልጃችን የቁማር ሱሰኛ መሆኑን ስናውቅ ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ገብቶን ነበር።'' የስቲቭ ልጅ ለትምህርቱ የሚሰጠውን ሳምንታዊ ወጪውን በደቂቃዎች ውስጥ የሚያጠፋ ሲሆን ከአቅሙ በላይ ሲሆንበትም ቤተሰቦቹን አማክሯቸው ነበር። እነሱም በዚሁ የሚገላገሉ መስሏቸው ማንኛውም ቤተሰብ እንደሚያደርገው ሙሉ እዳውን ከፈሉለት። ነገር ግን ብዙ ነገሮች ተከትለው መጥተዋል። ከአንድ ከዓመት በኋላ ስቲቭ ልጃቸው ከእራሱ አልፎ የሰዎችን ገንዘብ እያስያዘ መቆመር መቀጠሉን ሲሰማ በጣም ነበር ያዘነው። የሚያስይዘው ገንዘብ ደግሞ እጅጉን የተጋነነና ትልቅ እዳ ውስጥ የዘፈቀው ነበር። ''በበይነ መረብ ካርታ ነበር የሚጫወተው። እጅግ አስፈሪ ሁኔታ ነበር።'' • እንወራረድ፡- የጦፈው የውርርድ ንግድ በአዲስ አበባ ስቲቭና ባለቤቱ ልጃቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳለ የተረዱት በዚህ ወቅት ነው። ምን ማድረግ እንዳለባቸውም ሆነ ማንን ማማከር እንዳለባቸው ምንም ዓይነት እውቀቱ አልነበራቸውም። ''የቁማርተኛው ቤተሰቦች መባልን በመፍራትና ልጃችን ገንዘብ የተበደራቸውን ጎረቤቶች ዓይ... Continue the article for another 4000 characters max:
ን ላለማየት እራሳችንን ከማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እስከ ማገድ ሁሉ ደርሰን ነበር።'' ''ተስፋ ቆርጠን ፊታችንን ወዴት ማዞር እንደምንችል ግራ ገብቶን ነበር። ለራሳችን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ለብዙ ወራት ምርምሮችን ስንሰራም ነበር'' ይላል ስቲቭ። በሠሩት ጥናት መሠረትም የልጃቸው ሱስ የጀመረው ገና የ12 ወይም የ13 ዓመት ታዳጊ እያለ እንደሆነ ደርሰውበታል። መጀመሪያ አካባቢ የሚያዘወትራቸው ጨዋታዎችም እግር ኳስና የመኪና ውድድር የመሳሰሉትን ነበር። በወቅቱ መኝታ ቤቱ ውስጥ ሆኖ ለሰዓታት ጌሞቹን የሚጫወት ሲሆን ጓደኞቹም ተመሳሳይ ነገር ያደርጉ ስለነበር፤ ብዙም አሳስቦን አያውቅም ይላል ስቲቭ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ሲያስታውስ። "ጨዋታዎቹ ምን ዓይነት እንደሆኑና ምን ዓይነት ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀሙ ምንም የማውቀው ነገር አልበረም" የሚለው ስቲቭ ከመጀመሪያው ጀምሮ ተከታትዬው ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ ላይፈጠር ይችል ነበር ብሎ ያስባል። ''ለረጅም ሰዓታት እግር ኳስ በመጫወት የተጀመረው ሱስ ቀስ በቀስ ወደ ቁማር ሱስ ተቀይሯል።'' በቅርቡ የተሠራ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው 55 ሺህ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ11 እስከ 16 የሚደርሱ የእንግሊዝ ታዳጊዎች አሳሳቢ የሚባል የቁማር ሱሰኞች ሲሆኑ ቤተሰቦቻቸው ስለሱሳቸው ብዙም አያውቁም። • በዩቲዩብ 22 ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው የሰባት ዓመቱ ህፃን ከሦስት ዓመታት ትግል በኋላ ስቲቭ የአስተማሪነት ሥራውን ትቶ ልጆች የቁማር ሱስ ውስጥ እንዳይገቡ የሚያስተምርና ቤተሰቦችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት አቋቁሟል። ''ነገር ግን በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው። ቤተሰቦች ልጆቻቸው ለረጅም ሰዓታት ኢንተርኔት ላይ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ምን እየሠሩ ነው ብለው ሊጠይቁ ይገባል'' ይላል። ልጆች ምን ዓይነት ጌሞችን እንደሚጫወቱ መጠየቅ፤ ቢቻል ደግሞ አብሮ ለመጫወት መሞከር ነገሮችን ለመቆጣጠርና በአጭሩ ለመቅጨት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ስቲቭ ይመክራል። ምንም እንኳን በኢንተርኔት የሚደረጉ ጨዋታዎችን በትምህርት ቤቶች አካባቢ ወይም ከ25 ዓመት በታች ለሆኑ ዜጎች እንዳይተዋወቁ በእንግሊዝ ሕግ የተከለከለ ቢሆንም ብዙም ውጤታማ የሆነ አይመስልም። ታዳጊዎቹ በትምህርት ቤታቸው አልያም በሚያዘወትሯቸው አካባቢዎቹ ጌሞቹ ባይተዋወቁም በተለያዩ አጋጣሚዎች ማስታወቂያዎቹን በኢንተርኔትም ሆነ በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች ያገኟቸዋል። ከዚህ ባለፈም ድርጅቶቹ ማስታወቂያዎቻቸውን በታዋቂ ሰዎችና በትልልቅ ስፖርተኞች ስለሚያሠሩ ታዳጊዎቹ ላይ ተጽእኖ የማሳደር አቅማቸው ከፍተኛ ነው። ስቲቭ እንደሚለው እሱና ቤተሰቡ አሁን በጥሩ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚገኙት። በተፈጠረው ነገር ከማዘንና ከመሸማቀቅ ይልቅ በጊዜ ወደ መፍትሄ ማፈላለግ መሄዳችን ጠቅሞናል ይላል።
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
491
Doc to summarize: ቀነኒሳ በቀለ ከማራቶን ክብረ ወሰን ቀጥሎ ሁለተኛው ምርጥ ሰዓት ነው በተባለ 2 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከአርባ አንድ ሰከንድ በማስመዝገብ ነው የበርሊን ማራቶንን ማሸነፍ የቻለው። ቀነኒሳ ከውድድሩ በኋላ ለቢቢሲ እንደተናገረው የዚህን ውድድር ውጤት "ከሞት እንደመነሳት ነው የምመለከተው" ሲል ጠቅሶ ምክንያቱንም ሲያስረዳ ለረጅም ጊዜ በህመም ምክንያት ከሩጫ ውድድር እርቆ መቆየቱን ይገልጻል። • በወለደች በ30 ደቂቃ ውስጥ የተፈተነችው ተማሪ ስንት አስመዘገበች? • በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ በቀጣይ በጤናው ላይ ምንም ችግር ካላጋጠመው የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰንን ለመስበር እንደሚሰራ ተናግሯል። "ህመም ላይ ስለነበርኩ ክብረወሰኑን ለመስበር የሚያስችል በቂ ልምምድ አላደረግኩም" የሚለው ቀነኒሳ ለዚህ ውጤት ያልተቋረጠ የወራት ልምምድ እንደሚያስፈልግ ጠቅሶ "በቅርቡ የማራቶን ክብረ ወሰን ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳል" ሲል ተናግሯል። በሴቶቹ የማራቶን ውድድር አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት ኢትዮጵያዊያን ያሸነፉ ሲሆን አንደኛ አሸቴ በከሬ ሁለተኛ ማሬ ዲባባ በመሆን ተከታትለው አሸናፊነቱን ተቆጣጥረውታል። • በወለደች በ30 ደቂቃ ውስጥ የተፈተነችው ተማሪ ስንት አስመዘገበች? በወንዶቹ ውድድር በአንደኛነት ካሸነፈው ቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያኑ ብርሐኑ ለገሰ ሁለተኛ እንዲሁም ሲሳይ ለማ ሦስተኛ በመውጣት በሁለቱም ጾታዎች የበርሊን ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያዊያን የበላይነት ተጠናቋል። የ37 ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለ ከዚህ በፊት በተካሄዱ የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮና ውድድሮች ላይ በተከታታይ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሲሆን ክብረ ወሰኖችንም ያሻሻለ ኮከብ አትሌት ነው። በኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ የተያዘው የማራቶን ክብረወሰን ላይ ለመድረስ ሁለት ሰከንዶችን ዘግይቶ ውድድሩን የጨረሰው ቀነኒሳ "አዝናለሁ፤ እድለኛ አልነበርኩም። ነገር ግን ተስፋ አልቆርጥም፤ ክብረ ወሰኑንም ለመስበር እችላለሁ" ሲል ከበርሊኑ ድሉ በኋላ ተናግሯል። \nSummary in the same language as the doc:
ከሩጫው መድረክ ጠፍቶ የከረመው የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ ዛሬ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ላይ ለውድድሩ ክብረወሰን ሁለት ሰከንዶች የቀሩት ውጤት በማስመዝገብ አሸነፈ።
amh_Ethi
test
docsummary
GEM/xlsum
amharic
245
Title: የኦጋዴን ጦርነት፡ የሲያድ ባሬ ወረራ ሲታወስ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ከቀኝ ወደግራ - መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ ፊደል ካስትሮ እና ራውል ካስትሮ የዓለም መገናኛ ብዙሃን በተሰበሰቡበት የኢትዮጵያንና ኩባን ወታደራዊ ምስጢር እንዲያወጣ ተደረገ። የኦጋዴን ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የተደረገው ጦርነት የዛሬ 42 ዓመት የካቲት 26/1970 ዓ.ም. ነበር የተጠናቀቀው። በ1966 ዓ.ም ሶማሊያ የአረብ ሊግን ተቀላቀለች። በወቅቱ የሶማሊያ መሪ የነበረው ሜጀር ጄኔራል ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ። ጦርነቱ የተጀመረ ሰሞን የሲያድ ባሬ [ዚያድ ባሬ] ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከዩናይትስ ስቴትስ ጋር ወዳጅነት አለው። በወቅቱ በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ የነበሩት ሶቪዬት ኅብረትና አሜሪካ ምሥራቅ አፍሪካ ገቡ። ፕሬዝደንት አብዲራሺድ አሊ ሸርማርኬን በመንፈቅለ-መንግሥት ፈንግሎ ሥልጣን የጨበጠው የዚያድ ባሬ መንግሥት ድንበር ማስፋፋት ዋነኛ ዓላማው አደረገ። ወሳኟ ቦታ ደግሞ - ኦጋዴን። ኦጋዴን ሠፍሮ የሽምቅ ውጊያ ያካሂድ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ግንባር የኢትዮጵያ ጦር ላይ ጥቃት ሠነዘረ። የጦርነቱ መባቻ ተደርጎ የሚቆጠረውም ይህ ጥቃት ነበር። በመቀጠል የዚያድ ባሬ ጦር በሶቪዬት ኅብረት የጦር መሣሪያ ታግዞ ወደ አጋዴን ገሰገሰ። በወቅቱ ከንጉሡ አገዛዝ ወደ ወታደራዊው ደርግ የተሻጋገረችው ኢትዮጵያ በይፋ ራሷን ማርክሲስት ስትል አወጀች፤ ወዳጅነቷም ከሶቪዬት ኅብረት ጋር ሆነ። አሜሪካ ደግሞ ድጋፏን ለሶማሊያ አደረገች። ሁለቱ አገራት ወደ ቀለጠ ጦርነት ገቡ። በወቅቱ የሲያድ ባሬ መንግሥት ኩባውያን የኢትዮጵያውን ጦር ደግፈው እየተዋጉ ነው ሲል ወቀሰ። ይህንንም ለማሳመን ሲሉ የኩባ ወታደሮች መያዝ ጀመሩ። የዚያኔ ነው ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ ተይዞ ለጋዜጠኞች መግለጫ እንዲሰጥ የተገደደው። ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ [በስተቀኝ] የዚያድ ባሬ መንግሥት ወራራውን አጠናክሮ በጅግጅጋ በኩል ደንበር አልፎ ገብቶ ብዙ ጥፋት አደረሰ። የንፁሃን ዜጎች ሕይወት ተቀጠፈ። አልፎም ወደ ሐረር ገሰገሰ። ይሄኔ ነው የኢትዮጵያ ክተት የታወጀው። ሐረር ላይ 40 ሺህ ገደማ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ጠበቀው። ተጨማሪ 10 ሺህ የኩባ ጦረኞች ከኢትዮጵያ ጎን ነበሩ። የኢትዮጵያ ጦር የዚያድ ባሬን ጦር አሳዶ ከመሬቱ አስወጣ። የመጨረሻው ውጊያ የነበረው ካራማራ ላይ ነበር። በወቅቱ በዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታገዘው የኢትጵያ ጦር በሰማይ በምድር ጥቃቱን በማጠናከር የሶማሊያ ጦርን ድባቅ መታ። ጦርነቱ ሲጀመር ኢትዮጵያ 10 በመቶ ብቻ የኦጋዴን መሬት በእጇ ነበር። ጦርነቱ ካራማራ ተራራ ላይ ሲያበቃ ኦጋዴን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ተያዘች። በካራማራ ጦርነት በርካቶች ተሰውተዋል። በቀጣናው ያለውን ድርሻ ለማስፋት ኢትዮጵያን የወረረው ሜጀር ጄነራል ሲያድ ባሬ ከሽንፈቱ በኋላ ተቀባይነቱ እየሟሸሸ መጣ። ታላቋ የሚል ቅጥያ የነበራት ሶማሊያም ከኦጋዴን ጦርነት በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት መታመስ ጀመረች። ሲያድ ባሬ 1983 ዓ.ም ከሥልጣን ተወግዶ ወደ ናይጄሪያ ሸሸ። ሕልፈተ ሕይወቱም ለአራት ዓመታት በስደት በቆየባት ናይጄሪያ ሆነ። በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል። ከ16ሺህ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። የኢትዮ-ሶማሊያ የኦጋዴን ጦርነት የብዙሃን ሰላማዊ ዜጎችን ቢቀጥፍም፤ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ጅግንነታቸውን ያሳዩበት እንደሆነ በታሪክ ይወሳል።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
397
Title: የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው 'ሞባይል' እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን?\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የሲሊከን ቫሊ ሥራ ፈጣሪዎች ተብለው ከሚታወቁቱ አብዛኛዎቹ አሁን ትዳር መሥርተው ወላጆች ሆነዋል። አሁን በሕይወት የሌለው የአፕል ፈጣሪ ስቲቭ ጆብስ 2011 ላይ ልጆቹ ቤት ውስጥ ስልኮቻቸውንም ይሁን ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ለተወሰነ ሰዓት ብቻ እንደሚጠቀሙ ተናግሮ ነበር። •ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? •የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ? የማይክሮሶፍት ባለቤት እና ፈጣሪ የሆነው ቢል ጌትስም ቢሆን ልጆቹ ለዉሱን ሰዓት ብቻ ወደ 'ሞባይል ስክሪን' ብቅ እንደሚሉ ጠቁመው ነበር። የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ፤ አቻምና ለተወለደች ልጁ በፃፈው ደብዳቤ ላይ «ወደ ውጪ ወጥተሽ ተጫወች» የሚል ቀጭን ትዕዛዝ አስፍሮ ነበር። ለመሆኑ ለምን ይሆን የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው ከሞባይል ስክሪን እንዲርቁ የሚፈልጉት? •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት ቴክ-ነፃ ልጅነት የሦስት ልጆች አባት ነው፤ ቴክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሠራው ፒዬር ሎረንት። በርካታ የሥራ ባልደረቦቹም ሆነ እርሱ ልጆቻቸው ከቴክኖሎጂ እንዲርቁ አብዝተው ይመክራሉ። ልጆቻቸውን የሚሰዱበት አስኳላም ቢሆን 'ልጆቻችሁን ከቴክኖሎጂ አርቁ' ሲል ሁሌም ያስታውሳቸዋል። «በልጅነትህ ከምታየው ስክሪን ላይ አይደለም ትምህርት መቅሰም ያለብህ። የሰው ልጅ የስሜት ህዋሳቱን ተጠቅሞ ነው ነገሮችን መከወን ያለበት። አእምሮ ነገሮች እንዴት እንደሚሠሩ በሂደት ሊረዳ ይገባል።» በራስ መተማመን፣ ዲስፕሊን፣ ነፃ አስተሳሰብ፣ የቡድን ሥራ፣ ጥበባዊ አገላለፅ፤ እኒህ ከሞባይል ስክሪን ላይ የማይገኙ ጥበቦች ናቸው ሲል ይከራከራል ሎረንት። ሁለት አባቶች፤ የተለያየ ምክር ምንም እንኳ የሲሊከን ቫሊ ወላጆች ልጆቻችን ከቴክኖሎጂ መራቅ አለባቸው ብለው ቢከራከሩም፤ ቴክኖሎጂ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን አስፈላጊ ነው ሲሉ የሚሞግቱ ወላጆች አልጠፉም። መርቬ ላፐስ በዘርፉ 'ጥርስ የነቀሉ' ባለሙያ ናቸው። «እርግጥ ነው፤ ቴክኖሎጂ በዝባዥ ነው። ግን እንዴት አድርገን ነው ልንጠቀመው የምንችለው? ምክንያቱም ሕፃናት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ሊበለልፅጉ ይችላሉና። ከቴክኖሎጂ ውጪ ያለውን ዓለም ደግሞ እንዲሁ ማጣጣም አለባቸው።» •ኤርትራውያን ኢሳያስን ለመጣል'#ይበቃል' የተሰኘ እንቅስቃሴ ጀመሩ የዓለም ጤና ድርጅትም በቅርቡ ሕፃናት ምን ያህል ጊዜ ስክሪን መጠቀም እንዳለባቸው የሚጠቁም መመሪያ አዘጋጅቷል። እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ያሉ ሕፃናት ብቻቸውን ቴሌቪዥንም ሆነ ሌሎች ስክሪኖችን ማየት የለባቸውም ይላል መመሪያው። አክሎም በቀን ከአንድ ሰዓት በላይ ስክሪን ላይ አፍጥጠው እንዳይቆዩ ይመከራል። ላፐስ «እኔ ምግብ በማበስልበት ጊዜ ልጆቼ 'ሰሲሚ ስትሪት' የተሰኘውን የልጆች ሾው ይመለከታሉ። ይህ ለአንድ ወላጅ ግልግል ነው። ግን ምን ተማራችሁ ብዬ እጠይቃቸዋለሁ።» የሕፃናት እና ስክሪን ግንኙነት ጉዳይ አከራካሪነቱ ቢቀጥልም ባለሙያዎች ስክሪን እንጂ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን መከልከል አስፈላጊ ነው ብለን አናስብም ይላሉ።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
333
ሂስባህ የሚል ስያሜ ያላቸው እነዚህ የሸሪያ ፖሊሶች በግዛቲቱ በተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ቀናት ቁጥጥር ሲያደርጉ ነው ግለሰቦቹን የያዙት። በፈረንጆቹ 2000 የሸሪያ ህግ እንደገና ተግባራዊ ከተደረገባቸው በርካታ የናይጄሪያ ግዛቶች መካከል አንዷ በሆነችው ካኖ ግዛት የሚኖሩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጸሃይ ወጥታ እስትክጠልቅ ድረስ ምግብ በአፋቸው እንዳይዞር ህጉ ያዛል። • በፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል? • የቢላል አዛን የናፈቃቸው ሀበሾች የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች በቤታቸው እንደፈለጉት መመገብ የሚችሉ ሲሆን የእስልምና ተከታዮች ግን በጾም ወቅት በአደባባይ መመገብ አይችሉም። በግዛቲቱ የሸሪያ ህጉም ከመንግሥታዊ ህጉ ጋር ጎን ለጎን በመሆን ይሰራል። በካኖ ግዛት የሂስባህ ቃል አቀባይ የሆኑት አዳሙ ያህያ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአደባባይ በመመገባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁሉም ሙስሊሞች ሲሆኑ የሸሪያ ህጉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ያልሆኑት ላይ ተግባራዊ አይሆንም። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አንዳንዶቹ ምግብ የበሉት የረመዳን ጨረቃን እራሳቸው ባለማየታቸው እንደሆነ ሲገልጹ፤ ሌሎቹ ደግሞ የጤና እክልን እንደ ምክንያትነት ቢያቀርቡም ባለስልጣናቱ ግን ተቀባይነት የሌለውና ምክንያት ነው ብለዋል። • ቴምር በረመዳን ለምን ይዘወተራል? በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰማንያዎቹ ግለሰቦች ተግባሩን ሲፈጽሙ የመጀመሪያቸው በመሆኑ በከባድ ማስጠንቀቂያ መለቀቃቸውን ቃል አቀባዩ አክለዋል። ከዚህ በኋላ በረመዳን ወቅት ከማፍጠሪያ ሰዓት ውጪ ምግብ ሲበሉ ቢገኙም ወደ ፍርቤት ተወስደው ለመዳኘት ቃል ገብተዋል። የሂስባህ አባላቱም በረመዳን የጾም ቀናት ከተማዋን በማሰስ ተመሳሳይ ተግባር የሚፈጽሙ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸ... Continue the article for another 4000 characters max:
ውን እንደሚቀጥሉበትም ተገልጿል።
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
200
Content: እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ 'መላዕክቶቼ' ብላ የምትጠራቸውና በአሰቃቂ ሁኔታ ላጣቻቸው ለሦስት ልጆችዋ፣ ለእህቷና ለእህቷ ልጅ ያላት ፍቅር ዘላለማዊ እንሆነ ትናገራለች። "ለብቻ ልጆች ማሳደግ ቀላል አይደለም፤ ቢከብድም ግን የልጆቼን ትምህርት በአግባቡ እከታተልና ሥራዬን እሰራ ነበር። ሦስቱም ልጆቼ የተለያየ ትምህርት ቤት ይማሩ ስለነበር እነሱን ማመላለስና መልሶ ወደ ሥራ መሄድ አስቸጋሪ ነበር" ትላለች። ነገር ግን ግን ሁል ጊዜ በፍቅር የምትወጣው ኃላፊነት ስለነበረ እንደለመደችው እና "ስሰራበት የነበረው የሥራ መስሪያ ቤቴ ሁኔታዬን በመረዳት ያግዘኝ ስለነበር ከብዶኝ አያውቅም።" የ13 ዓመቱ ዮሴፍ፣ የ5 ዓመቱ ያሴን ሻማምና የ6 ዓመቷ ኒስረን ሻማም፤ ሄለን በተለያዩ ጊዜያት የወለደቻቸው የህይወቷ ጌጦች ነበሩ። ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን፤ የዚህ ቤተሰብ ህይወት ባልተጠበቀ ሁኔታ የሚቀይር ክፉ አጋጣሚ ተከሰተ። ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በአውሮፓዊያኑ ሐምሌ 2010 ዕለተ ቅዳሜ ረፋድ ላይ፤ ሰማይና ምድር የሚያናውጥ ኡኡታ የወይዘሮ ሄለን ቤት ካለበት አካባቢ ተሰማ። ሃዘናቸውን የሚገልጹ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሲያትል ውስጥ ተሰብስበዋል። የልጆቹ እናትም "ልጆቼን ነው የምፈልገው" እያለች ደረትዋን እየደቃች ወደ መሃል መንገድ ትሮጥ ስለነበር፤ "ሊያቅፏትና ሊያጽናኗት የሚከተሉዋት ሴቶችም ነበሩ" ሲል ሲያትል ታይምስ የወቅቱን ክስትት ጽፎ ነበር። ሄለን በዚያች መጥፎ ዕለት በተመሳሳይ ሰዓትና በተመሳሳይ አደጋ ሦስቱንም ልጆችዋን፣ የ22 ዓመት እህቷንና የእህቷን ልጅ በድንገት አጣቻቸው። በእያንዳንዷ ቀን ገደብ አልባ ፍቅርና እንክብካቤ በመስጠት ሳቅና ደስታ እየፈጠረች በስስት ለብቻዋን ስታሳድጋቸው የነበሩትን ልጆችዋን በእሳት አደጋ የማጣት መዓት ወደቀባት። በወቅቱ የእሳት አደጋው በሲያትል በአስርት ዓመታት ውስጥ ያጋጠመ ከባዱ የእሳት አደጋ እንደነበርም ተነግሯል። ሄለን ከቤተሰቦቿ ጋር በመጨረሻ ያሳለፈችውን ዕለት ፈጽማ አትረሳውም። አርብ ማታ ነበር፤ ሄለንና ሦስት ልጆችዋ፣ እህቷና የእህቷ ልጅ አንድ ላይ ፊልም በፍቅርና በደስታ ቅዳሜ መልሰው እንደሚገናኙ በማሰብ ወደ መኝታቸው አመሩ። በእሳቱ አደጋ የሞቱት የሄለን ልጆች ነገር ግን ቅዳሜ ይህ ቤተሰብ እንደወትሮው አንድ ላይ የሚያሳልፋት ቀን አልሆነችም፤ እልቁንም ሄለንን ብቻዋን ያስቀረች ዕለት ሆነች። ከቤቱ ውስጥ የተነሳው ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ እጅግ ከባድ ነበር፤ አደጋውን ለመቆጣጠር ይጥሩ ለነበሩት የእሳት አደጋ ሠራተኞችም አዳጋች ሆነ። ከባድ ጭስና የእሳት ነበልባል ሌሊቱን በፍቅር አቅፋቸው ካደረችው ቤት መውጣቱን ቀጠለ። እሳቱን ሊቆጣጠር የመጣው የእሳት አደጋ መኪና የውሃ ሞተር ውሃ መግፋት አልቻለም። ሌላ እርዳታ የሚሰጥ መኪና እስኪ መጣ ደግሞ ደቂቃዎች አለፉ፤ በዚህም በእሳት በሚጋየው ቤት ውስጥ ያሉትን የአምስት ሰዎችን ነፍስ ማዳን ሳይቻል ቀርቶ በእሳቱ ተበሉ። በዚህ ክስተትም ሲያትል ላይ ከባድ ሃዘን ሆነ፤ ክስተቱን የሰሙ ሁሉ በእሳቱ ከተቀጠፉት ልጆች በተጨማሪ ከባዱ ሃዘን ለወደቀባት ሄለንም አነቡ፤ የበርካቶች ልብም በሃዘን ተሰበረ። "ለእኔ ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ውጪ ነበር፤ የውዶቼን ህይወት ማዳን የምችልበት አቅም አልነበረኝም። ስለዚህ ጉዳይ በጭራሽ ማውራት ይከብደኛል። እንዴት ብዬ ልንገርሽ? እህህህ . . . በቃ ከባድ ነው" ትላለች ሄለን ያለፈውን አስታውሶ ለማውራት አቅም እንደሌላት በመግለጽ። ወይዘሮ ሄለን የአሜሪካ ህልም በመቋደስ የእራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ላይና ታች ከሚሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ነች። "በዚች አገር ብዙ እድሎች አሉ፤...\nThe previous content can be summarized as follows:
ወይዘሮ ሄለን ወረደ፤ ሦስት ልጆችዋን ብቻዋ ያሳደገች ነገር ግን በድንገት ከእቅፍዋ የተነጠቀችው እናት ናት።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
422
Title: "ቦይንግ እኔ በሌለሁበት አባቴን ቀበረው" በአደጋው አባቷን ያጣችው ዚፓራ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ዚፖራ ኩሪያ ባለፈው ሐሙስ በአደጋው የሞቱና አስክሬናቸውን ለመለየት ያልተቻለ ተሳፋሪዎች በተመሳሳይ ሬሳ ሳጥን፣ በመደዳ ተቀብረዋል። ዚፓራ ይህ ሲከናወን በሥፍራው አልተገኘችም ነበር። በዕለቱ የቦይንግና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦታው እንደተገኙ ቢነገርም፤ ዚፓራና ቤተሰቦቿ ስለ ክንውኑ የሰሙት ዘግይተው ስለነበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ አልተኙም። በአደጋው ከሞቱ ተሳፋሪዎች የሦስቱ ቤተሰቦች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ስለ ሥነ ሥርዓቱ የተነገራቸው ከቀናት በፊት ነበር። ስለዚህም በዕለቱ መገኘት የቻሉት ከ157 የሟቾች ቤተሰቦች ሁለቱ ብቻ ናቸው። • በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው • ኬንያውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድንና ቦይንግን ሊከሱ ነው "ቦይንግና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአባቴ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን ሳስበው ያንዘፈዝፈኛል" ስትል ዚፓራ ሀዘኗን ትገልጻለች። እስካለፈው ሳምንት ድረስ አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ሥፍራ የሰዎች አስክሬን እንዲሁም የአውሮፕላኑ ስብርባሪም ይገኝ ነበር። በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ባለፈው ወር አካባቢውን ሲጎበኙ፤ የሰዎች ቅሪተ አካል እና ቁሳቁሶችም ማየታቸው እንዳስደነገጣቸው ተናገረው ነበር። በአደጋው የሞቱና አስክሬናቸውን ለመለየት ያልተቻለ ተሳፋሪዎች በተመሳሳይ ሬሳ ሳጥን፣ በመደዳ ተቀብረዋል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ 302 ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ መዲና ናይሮቢ በረራ በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መከስከሱ ይታወሳል። የሰዎች አስክሬን እና የአውሮፕላኑ የመረጃ ቋትም ተሰብስቦ ነበር። አደጋው የደረሰው በአውሮፕላኑ የበረራ መቆጣጠሪያ እክል ምክንያት ሲሆን፤ ከዓመት በፊት ኢንዶኔዥያ ውስጥም በተመሳሳይ ሁኔታ 737 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሷል። ማክስ 737 ላለፉት ዘጠኝ ወራት ከበረራ ታግዷል። • "ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም • ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ የቢቢሲ ባልደረቦች አደጋው የደረሰበትን ሥፍራ በጎበኙበት ወቅት የአውሮፕላኑ የተለያዩ ክፍሎች ወዳድቀው አግኝተዋል። አካባቢው እየተጠበቀ ስላልነበረ እንስሳት በተከለለው ሥፍራ ገብተው ነበር። በአካባቢው ዝናብ ሲበረታ ችግሩ መባባሱን ያስተዋሉ በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሰዎች አንዳች እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀው ነበር። ሳምያ ሮዝ ልጇ ሳምያ ሮዝን በአደጋው ያጣችው ናዲያ ሚሊሮን፤ "በአካባቢው በግልጽ የሚታየውን የሰዎች አጥንት ነዋሪዎች ይሸፍኑት ነበር፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎችን ቅሪተ አካል እንዲሸፍን እንፈልጋለን" ብላለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ችግሩ መኖሩን አምኖ፤ በኢንሹራንስ ምክንያት እርምጃ መውሰድ አለመቻሉን ለሟቾች ቤተሰቦች አስታውቆ ነበር። ሆኖም ከቤተሰቦች ጫና ሲበረታበት እና የቢቢሲን ምርመራ ተከትሎ ችግሩ ተቀርፏል። ከዚህ ቀደም ለፎረንሲክ ምርመራ የተነሱ የአጽም ቅሪቶች ተሰባስበው በሬሳ ሳጥን ተከተዋል። አካባቢው የቀብር ሥፍራም ተደርጓል። • የቦይንግ ኃላፊ የሟቾችን ቤተሰቦች በይፋ ይቅርታ ጠየቁ • «ሙሉ ቤተሰቤን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ» የሟቾች ቤተሰቦች፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከመካሄዱ አስቀድሞ ሊያሳውቃቸው ይገባ እንደነበር ገልጸዋል። ቦይንግ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ሆኖም "በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በላየን ኤር አደጋ ሳቢያ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሰዎች መጽናናቱን እንመኛለን፤ ድጋፍ በማድረግም እንቀጥላለን" የሚል መግለጫ አውጥቷል። ዚፓራ ኩሪያ ባለፈው ወር ወደ ኢትዮጵያ ተጉዛ የአባቷን አስክሬን ለመውሰድ...
amh_Ethi
train
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
397
Content: ጥቃቱ የደረሰው ከአትላንታ በስተሰሜን በምትገኘው አክዎርዝ ማሳጅ ቤት እና በከተማዋ ውስጥ ባሉ ሁለት ስፓዎች መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ደቡብ ኮሪያ ከተጎጂዎች መካከል አራቱ የኮሪያ ዝርያ ያላቸው መሆናቸውን አረጋግጣለች፡፡ ባለስልጣናት የ 21 አመት ወጣት በቁጥጥር ስር መዋሉን እና ከሁሉም ጥቃቶች ጀርባ እንዳለበት ይታመናል ብለዋል፡፡ የግድያው መነሻ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም፡፡ በእስያ-አሜሪካውያን ላይ የጥላቻ ወንጀሎች ከቅርብ ወራት ወዲህ እየጨመሩ ናቸው። ለኮቪድ -19 መስፋፋት ተጠያቂ መደረጋቸው ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ንግግር በእስያ-አሜሪካውያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት፣ እንግልት፣ ክስ እና ውንጀላ ኮንነዋል፡፡ ስለ ተኩስ ምን እናውቃለን? የመጀመሪያው የተኩስ ልውውጥ የተከናወነው በቼሮኪ አውራጃ በአክዎርዝ በሚገኘው በያንግ ኤሲያን ማሳጅ ፓርለር ነበር፡፡ የፖሊስ ቃል አቀባዩ ካፕቴይን ጄይ ቤከር ሁለት ሰዎች በቦታው መሞታቸውንና ሶስት ሰዎች ደግሞ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልፀዋል። ሆስፒታል ውስጥ ሌሎች ሁለት ሰዎች እንደሞቱ ተናግረዋል፡፡ ከተጎጂዎቹ ሁለቱ የእስያ ዝርያ ያለባቸው ወንድ እና ሴት መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ሌላ የሂስፓኒክ ዝርያ ያለበት ግለሰብ መቁሰሉን ተናግረዋል። ከአንድ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በሰሜን ምስራቅ አትላንታ በሚገኘው ጎልድ ስፓ "ዝርፊያ እየተካሄደ ነው" በሚል ፖሊስ መጠራቱን ገልጿል። ፖሊስ በሪፖርቱ እንደገለጸው "ፖሊሶች በቦታው በደረሱበት ወቅት የሞቱ ሶስት ሴቶች ተገኝተዋል፡፡ ከመንገዱ ባሸገር በሚገኘው የአሮማቴራፒ ስፓ የተጠሩት ፖሊሶች የተገደለች ሌላ ሴት አግኝተዋል፡፡ የአትላንታ ጆርናል-ኮንስቲትዩሽን፣ ፖሊስን ጠቅሶ እንዳስታወቀው አራቱ የአትላንታ ተጠቂዎች የእስያ ዝርያ ያላቸው ሴቶች ናቸው፡፡ መርማሪዎች በአንዱ ስፓ አቅራቢያ የተቀረጸን የተጠርጣሪ ምስል ለቅቀዋል፡፡ በጆርጂያ ጆርጅ ዉድስቶክ ነዋሪ የሆነው ሮበርት አሮን ሎንግ ከአትላንታ በስተደቡብ 240 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ክሪስፕ ካውንቲ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ካፕቴን ቤከር እንዳሉት በሦስቱም ግድያዎች ተጠርጣሪው ተመሳሳይ ግለሰብ እንደሆነ መርማሪዎች በጣም እርግጠኞች ናቸው፡፡ ምላሹ ምን ነበር? ተጎጂዎቹ በዘር ወይም በጎሳ ምክንያት የተለዩ ስለመሆናቸው ለማወቅ ምርመራው ገና መሆኑን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል፡፡ ኤሺያን አሜሪካንስ ኤንድ ፓስፊክ አይስላንደርስ የተባለው ተሟጋች ቡድን በበኩሉ "ሊገለጽ የማይችል አሳዛኝ አደጋ" ብሎታል፡፡ "በአሁኑ ወቅት በእስያ አሜሪካዊያን ማህበረሰብ ውስጥ መፍትሄ ሊበጅለት የሚገባው ከፍተኛ ፍርሃትና ህመም አለ" ሲል በትዊተር ገፁ አስፍሯል፡፡ የአትላንታ ፖሊስ ጥቃት ከተሰነዘረባቸው ጋር ተመሳሳይ በሆኑ የንግድ ተቋማት ዙሪያ የጥበቃ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የጆርጂያው ገዥ ብራያን ኬምፕ ለጉዳዩ ምላሽ የሰጡትን የህግ አስከባሪዎች አመስግነው "ለዚህ ዘግናኝ ድርጊት ሰለባዎች እየጸለይን ነው" ብለዋል፡፡ የኒው ዮርክ ፖሊስ መምሪያ የፀረ-ሽብርተኝነት ክፍል በበኩሉ "በከተማው ባሉ ታላላቅ የእስያ ማህበረሰቦቻችን ዙሪያ ለጥንቃቄ ሲባል ኃይል ያሰማራል" ብሏል፡፡ \nThe previous content can be summarized as follows:
በአሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ባሉ ስፓዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገደሉ። አብዛኛዎቹ ሟቾች የእስያ ተወላጅ ሴቶች ናቸው ተብሏል።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
360
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት በአዲሰ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ውስጥ ትናንት ተከናውኗል። በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተሸፍነው ወደ መቃብር ሥፍራው ያመሩት የአስከሬን ሳጥኖች ሙሉ በሙሉ ባዶ የሚባሉ ነበሩ። የሟቾችን ሙሉ አሰከሬን ማግኘት ባለመቻሉ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በባዶ ሳጥን ሊከናውን ግድ ብሏል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሟች ቤተሰቦች ራሳቸውን ከሬሳ ሳጥኑ ላይ እስከመጣልና መሬት ላይ እስከመጋጨት የደረሰ ጥልቅ ሐዘናቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል። • "የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ በተመሳሳይ የጸሎትና ሟቾችን የማሰብ ሥነ ሥርዓት በኬኒያዋ መዲና ናይሮቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥም ተከናውኗል። ዲፕሎማቶችና ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ከ30 በላይ ሀገራት ዜጎች በተገኙበት በቤተክርስቲያኑ ጸሎተ ፍትሐትና የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። በአደጋው ሥፍራ የተገኙ የሟቾች የሰውነት ክፍል ላይ ምርመራ አድርጎ ማንነታቸውን ለማወቅ ቢያንስ ስድስት ወር እንደሚያስፈልግ ለቤተሰቦቻቸው ተገልጿል። በመሆኑም ተጎጂዎችን ለማስታወስ የተወሰነ አፈር አውሮፕላኑ ከወደቀበት ስፍራ ኢንዲወስዱ የኢትዮጵያ መንግሥት ፍቃድ ሰጥቷል። ይሁንና የተጎጅ ቤተሰቦች ለቢቢሲው ሪፖርተር ፈርዲናንድ ኦሞንዲ እንደተናገሩት "አፈር ዘግኖ መውሰድ ሳይሆን የሐዘናችንን ክብደት ለመቀነስ ቢያንስ አንድ የሰውነት ክፍል አግኝተን አልቅሰን ብንቀብር ትልቅ እፎይታ ይሰማናል" ብለዋል። የኬንያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ጄምስ ማቻሪያ "ሁሉንም ነገር ለማድረግ ይሠራል፤ ለጊዜው ግን የሚቻለውን ማድረግ ይቀድማል" ብለዋል። • "አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞችም በአደጋው ያጧቸውን 8 ባልደረቦቻቸውን ለማሰብ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሐዘን መገለጫ የሆነውን ነጭ አበባ አስቀምጠዋል። በዚሁ ዝግጅትም የሃይማኖት አባቶች ተገኝተው የሟቾችን ወዳጅ ቤተሰቦችን የማጽናናትና ሃይማኖታዊ አስተምህሮ አከናውነዋል። \n\nGive me a good title for the article above.
የቀብር ሥነ ሥርዓት በባዶ ሳጥኖች ተከናወነ
amh_Ethi
validation
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
242
Title: ሳኡዲ አረቢያ በተወሰኑ ጥፋተኞች ላይ የሞት ቅጣትን ልታስቀር ነው\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
ንጉሥ ሰልማን ያረቀቁት ነው የተባለው ይህ ሕግ አገሪቱ ግርፋትን እንደ ወንጀል መቀጣጫ ማድረግ አቆማለሁ ካለች ጥቂት ቀናት በኋላ ነው የታወጀው። ሳኡዲ ፊርማዋን ያኖረችበት የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መብቶች ጉባዔ ሕፃናት ለሚፈፅሙት ቅጣት የሞት ፍርድ ሊፈርድባቸው አይገባም ይላል። የመብት ተማጋቾች ሳኡዲ አረቢያ የሰው ልጅ መብትን ክፉኛ እየረገጠች ነው ሲሉ ይኮንናሉ። ሐሳብን በነፃነት መግለፅ የታፈነው ነው የሚሉት ተሟጋቾቹ መንግሥትን መቃወም ያለ ሕግ አግባብ ሊያሳስር ይችላል ሲሉ የሳኡዲን አገዛዝ ይተቻሉ። ባለፈው ዓመት በሳኡዲ 184 ሰዎችን በሞት ቀጥታለች። ይህም እስከዛሬ ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው፤ ይላል አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ዓለም አቀፍ ቡድን። ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ ከ18 ዓመት በታች እያለ በፈፀመው ጥፋት ነው በሞት የተቀጣው ሲል ድርጅቱ በመግለጫው አመልክቷል። እሁድ የወጣው የሳዑዲ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽኝ መግለጫ እንደሚያመለክተው ንጉሡ ዕድሜያቸው ለጋ የሆኑ ሰዎች ለፈፀሙት ቅጣት የሚሰጠው ሞት ፍርድ ተሽሮ እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እሥር እንዲቀጡ ይሁን ብለዋል። የኮሚሽኑ ፕሬዝደንት አዋድ አላዋድ እንዳሉት አጥፊዎች ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች የሚታረሙበት እሥር ቤት ይገባሉ። ''ትዕዛዙ ወደ ዘመናዊ የወንጀል ቅጣት ዘዴ እንድመጣ ያግዘናል'' ሲሉ የኮሚሽኑ ፕሬዝደንት አዋድ የንጉሡን እርምጃ አድንቀዋል። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ጆሮ የነሱት ውሳኔ ከመቼ ጀምሮ እንደሚተገበር የተነገረ ነገር የለም። ምንም እንኳ ሳኡዲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ ክልከላዎችን ብታነሳም አሁንም ንጉሣዊው አስተዳደር ከወቀሳ አልዳነም። በተለይ ደግሞ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ከሁለት ዓመት በፊት ቱርክ በሚገኘው የሳኡዲ ቆንስላ የተፈጸመበት አሰቃቂ ግድያና በርካታ የሰብዓዊ መብትና የሴቶች መብት ተሟጋቾች እሥር ቤት መሆን የሳኡዲን ስም ያጠለሹ ናቸው። ባለፈው ሳምንት ለሰብዓዊ መብት በመሟገት የሚታወቅ አንድ የሳኡዲ ዜጋ እሥር ቤት ውስጥ እያለ መሞቱ ደግሞ ነገሮችን ከድጡ ወደ ማጡ አድርጓቸዋል።
amh_Ethi
validation
imaginearticle
GEM/xlsum
amharic
253
Content: በዛሬው ዕለት፣ ጥቅምት 5፣ 2013 ዓ.ም ጥዋት በእስር ላይ የነበረበት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተመስገንን ለመጠየቅም ሲያመራ መግባት አይቻልም ተብሎ እንደነበረና ፍርድ ቤት ሊያቀርቡት ይችላሉ በሚል እሳቤም እዛው እየጠበቁ የነበረ ቢሆንም ተፈትቶ ማየቱን አስረድቷል። ከሱ በተጨማሪ የፍትህ መፅሄት አዘጋጁ ምስጋናው ዝናቤም መፈታቱን ታሪኩ አክሎ ገልጿል። ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋለም ይሁን የተፈታተበትንም ምክንያት በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ እስካሁን እንዳላገኙም ታሪኩ ያስረዳል። በትናንትናው ዕለትም ታሪኩ ለጥቂት ደቂቃዎች እንዳገኘውና ለምን እንደታሰረ በጠየቀው ወቅት "የሐሰት ወሬ በማሰራጨት ትፈለጋለህ ከሚል ውጪ የነገሩኝ ነገር የለም።" "እኔም ጠበቃዬ ሳይመጣ ቃል አልሰጥም ብዬ ቁጭ ብያለሁ። ይልቅ ብርድ ልብስ እንዲገባልኝ ሞክር" ማለቱንም ታሪኩ በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል። ረቡዕ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ አዲስ አበባ ስምንት የሚሆኑ ፖሊሶች አቧሬ የሚገኘው የፍትህ ቢሮ መጥተው እንደነበርና በወቅቱም ቢሮ ያልነበረው ተመስገን የመፅሄቱ አዘጋጆች ደውለው ሁኔታውን እንዳስረዱት ከታሪኩ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ተመስገን በስልክ ከፖሊሶቹ ጋር የተነጋገረ ሲሆን መጥሪያ ወይም የክስ ወረቀት ይዘው ከሆነ ቢሮው እንዲተዉለት ነግሯቸው እንደነበርም ተገልጿል። ፖሊሶቹ በበኩላቸው እሱን ማናገር እንደሚፈልጉና ያለበትን እንዲነግራቸው በጠየቁት መሰረት እራሱ ፖሊሶቹን በአካል ለማግኘት ወደ ቢሮው መመለሱን ታሪኩ ጠቅሷል። ፖሊሶችም መኪናቸው ውስጥ አስገብተው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለምዶ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱንም አክሎ ገልጿል። የፍትህ መፅሄት አዘጋጅ ምስጋናው ዝናቤም ከተመስገን ጋር እንደተወሰደ ታሪኩ ለቢቢሲ ተናግሯል። ከሰሞኑ ተመስገን እታሰራለሁ የሚል ፍራቻ ነበረው ወይ ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ ምንም አይነት ስጋት እንዳልነበረው ወንድሙ አስረድቷል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ስለጋዜጠኛው መታሰር ተጠይቆ ጉዳዩ የፌደራል ፖሊስን እንደሚመለከተው በመግለጽ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። ቢቢሲ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ፌደራል ፖሊስ ቢደውልም በተመሳሳይ መልኩ ምላሽ ማግኘት አልቻለም። በሳምንታዊው ፍትህ መጽሔት ላይ በቅርቡ የተሾሙትን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳናች አቤቤን በሚመለከት ከወጣው ጽሁፍ ጋር በተያያዘ መጽሔቱን በተመለከተ፤ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተጻፈ ደብዳቤ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር በመቆቱ እስሩ ከዚሁ ጉዳይ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ተገምቷል። ከዚህ ቀደም ለሦስት ዓመታት በማረሚያ ቤት የቆየው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የእስር ጊዜውን አጠናቅቆ መውጣቱ ይታወሳል። ጋዜጠኛ ተመስገን በወቅቱ ለእስር የተዳረገው የፍትህ ጋዜጣ ላይ በጻፋቸውና ባሳተማቸው ጽሁፎች ምክንያት ነበር። በጋዜጠኛው ላይ የቀረቡት ክሶችም በሐሰት የመወንጀል፣ ስም የማጥፋት፣ የሐሰት ወሬዎች የመዘገብ እና ማሰራጨት፣ የሕዝብን አስተሳሰብ ማናወጥ እንደዚሁም ሕዝብ እንዲያምጽ መገፋፋት የሚሉ ነበሩ። ተመስገን ጉዳዩን በፍርድ ቤት ሲከታተል ቆይቶ በአንደኛው ክስ ብቻ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ለሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት እንደነበር ይታወሳል \nThe previous content can be summarized as follows:
በትናንትናው ዕለት (ረቡዕ )በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የፍትህ መፅሄት ዋና አዘጋጅና ባለቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው እለት መፈታቱን ቢቢሲ ከወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ መረዳት ችሏል።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
368
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: "በመንግሥት መዋቅር ሥር ውስጥ ሆነውም ግጭቶችን የሚያባብሱ ኃይሎች እንዳሉ እናውቃለን" ኢዜማ\nSummary: የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከሰሞኑ የተፈጠሩ ግጭቶችን በተመለከተ ትናንት ጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ. ም. መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው በተለይ ጥቅምት 13 እና 14 ለደረሰው ጥፋት መነሻ ነው ካለው እና ለመንግስት አካል ማሳወቅ ሲገባው "ተከብቤያለሁ" ብሎ ለሕዝብ መረጃ ካሳራጨው ጀምሮ ጥፋት ያደረሱ ሰዎች በሕግ እንዲጠየቁ ይጠይቃል። ስለ መግለጫውና ተያያዥ ጉዳዮች የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀን አነጋግረናል። ት ና ንት ኢዜማ ያወጣው መግለጫ ይዘት ምንድን ነው?\nArticle (Max 500 characters):
አቶ ናትናኤል፦ ስምንት ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ ነው ያወጣነው። ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በተፈጠሩ ሁከቶች የሰው ሕይወት መጥፋቱና ንብረት መውደሙ እንዲሁም የተለያየ አካል ጉዳት መድረሱን መነሻ በማድረግ የተሰጠ መግለጫ ነው። አገራችን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚደረግ ሽግግር ውስጥ እንደሆነች ይታወቃል። ያ ሽግግር እና የአገር አንድነትን ለማረጋገጥ ዜጎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ፍርሀት የፈጠረባቸው ኃይሎች የመጨረሻ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ የገቡበት እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተረድተናል። • "ምርጫው እንዲራዘም እንፈልጋለን" አቶ አንዷለም አራጌ • "ትግላችን ከጨቋኝ ገዥዎች ጋር እንጂ ከሕዝቡ ጋር አልነበረም" ኦዴፓ ለጠፋ ሕይወትና ለተጎዱ ሰዎች ሀዘናችንን ገልፀን፤ ይህንን ድርጊት በመፈፀም ከመነሻው ጀምሮ ምክንያት የሆኑና በተለያየ ደረጃ ወንጀሉን ሲፈፅሙ የነበሩ ለፍር
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
203
የሁለት ዓመቱ ታዳጊ አንበሳ ይኖርበት የነበረው ቤት ከአንድ ትምህርት ቤት በተቃራኒ ያለ ነው። አንበሳው በማደንዘዣ ጥይት ከተመታ በኋላ ቦጊጁ ኦሙ ወደተሰኘ የእንስሳት ማቆያ እንዲሄድ መደረጉን አንድ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሰኞ ዕለት የተያዘው አንበሳ ባለቤት ማንነት ያልታወቀ ሲሆን፤ ባለቤቱ ራሱን አሳልፎ ለፖሊስ እንዲሰጥ አሊያ የእሥር ትዕዛዝ እንደሚወጣበት የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል። የሌጎስ ስቴት ኢንቫይሮሜንታል ሳኒቴሽን አባል የሆኑ ባለሙያዎችና የመንደሪቱ ነዋሪዎች ለመንግሥት አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ ነው አንበሳው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው። የነዋሪዎችና ባለሙያዎች ቅሬታ በተሰበሰበ ፊርማ የደረሰው የናይጄሪያ የተፈጥሮ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የዱር እንስሳት ተንከባካቢ ባለሙያዎች ልኮ አንበሳው ራሱን እንዲስት ተደርጎ እንዲያዝ አስደርጓል። አንበሳው ይኖርበት ከነበረው ቤት ተቃራኒ አንድ የሕፃናት ማቆያ እንዲሁም ትምህርት ቤት እንዳለ የቢቢሲ የናይጄሪያ ወኪል ዳሚሎላ ኦዱሎዋ ዘግባለች። የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪዎች ለተማሪዎች ደህንነት ሲባል አንበሳው ከሥፍራው በመነሳቱ እፎይ ብለዋል። አንበሳው ከሁለት ወራት በፊት ነው መኖሪያው ከተያዘበት ቤት ያደረገው ተብሏል። \n\nGive me a good title for the article above.
ናይጄሪያ ውስጥ ቤት ሲጠብቅ የነበረው አንበሳ በፖሊስ ተያዘ
amh_Ethi
validation
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
146
Doc to summarize: ይህ የተፈፀመው በእስያ በምትገኘው ካይሪጊስታን በምትባለው አገር ነው። የ27 አመት እድሜ ያላት አይዛዳ ካናትቤኮቫ የተጠለፈችው ሰኞ እለት ሲሆን ሶስት ወንዶችም ገፍተው መኪና ውስጥ ከተቷት። ከነዚህ ውስጥ አንደኛው በግድ ሊያገባት የፈለገው ሰው ነው ተብሏል። የጠለፋው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በከፍተኛ ሁኔታ ቢጋራም ፖሊስ መኪናውን ለማግኘት አዳጋች ሆኖበት ነበር። አይዛዳ ከተጠለፈች ከሁለት ቀናት በኋላ አስከሬኗ አንድ ከጥቅም ውጭ በሆነ መኪና ውስጥ ሊገኝ ችሏል። አስከሬኗ የተገኘው በአንድ እረኛ አማካኝነት ከመዲናዋ ቢሽከክ ወጣ ብሎ በሚገኝ ሜዳ ነው። ጠልፎ ገድሏታል ተብሎ የሚታመነው ግለሰብ አስከሬንም በዚያው ስፍራ ተገኝቷል። ፖሊስ የግለሰቡን አሟሟት አስመልክቶ እንደሚለው የሞተው በቢላ እንደሆነና ራሱንም እንደገደለ ፍንጮች ማግኘቱን ነው። የሟቿ ቤተሰቦች እንደተናገሩት ልጃቸው ግለሰቡን እንደምታውቀውና ከዚህ በፊትም ትንኮሳዎች ሲያደርስባት እንደነበርና ከዚህ ተግባሩም እንዲታቀብ መጠየቃቸውን ነው። ግለሰቧን በመጥለፍ የተባበሩት ሌሎች ሶስት ወንዶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ የአገሬው ሚዲያ ዘግቧል። የግለሰቧን ግድያ ተከትሎም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በያዝነው ሳምንት ሃሙስ "አሳፋሪ" ነው በማለት በቁጣ ሲጮሁ ተሰምተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ የውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል። በአገሪቷ ውስጥ የጠለፋ ጋብቻ በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍቷል። ምንም እንኳን አንዳንዶች የጠለፋ ጋብቻ የካይርጊዝ የቀደመ ባህል ነው ብለው ቢከራከሩም ተመራማሪዎች በበኩላቸው በመካከለኛ እስያዊቷ አገር መስፋፋትን ያሳየው ከጥቂት አስርት አመታት በፊት ነው ይላሉ። በአውሮፓውያኑ 2013 የጠለፋ ጋብቻ ህገወጥ ሆኖ በህግ ቢደነገግም ሪፖርት የሚያደርጉ ሴቶች ቁጥር በጣም አናሳ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሰው ሊደርስባቸው የሚችለውን አፀፋዊ ምላሽ በመፍራት እንደሆነ ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በአገሪቷ ከሚፈፀሙ አምስት ጋብቻዎች መካከል አንዱ አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ሴቷ ተጠልፋ እንደሆነ ነው። \nSummary in the same language as the doc:
በጠለፋ ጋብቻ ለመፈፀም በሚል አንዲት ሴት ተጠልፋ መገደሏ ከፍተኛ ቁጣን አስነስቷል።
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
247
Doc to summarize: ውሾቻቸውን ይዘው ደን ውስጥ ሲንሸራሸሩ ይታያል "በወታደራዊ ማዕከሉ የሚቀጠሩ ከ20 እስከ 40 እድሜ ክልል ያሉ ጤናማ ሴት ሠራተኞች እንፈልጋለን። ጥሩ ደመወዝ እንከፍላለን። በነጻ ማረፊያና ልብስ እናቀርባለን።" ማስታወቂያው በግልጽ ያላስቀመጣቸው ሁለት ነጥቦች አሉ። አንደኛው ሠራተኞቹ የሚለብሱት የአዶልፍ ሒትለር የናዚ ፓርቲ የደንብ ልብስ መሆኑን ነው። ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ 'ወታደራዊ ማዕከል' የተባለው ሴቶች የታገቱበት የግዳጅ ማቆያ እንደሆነ ነው። እነዚህ በሰሜን በርሊን የሚገኙ እስር ቤቶች ከተዘጉ ዓመታት ተቆጥረዋል። በአቅራቢያቸው የሚገኙ ስምንት ቅንጡ ቤቶች ግን አሁንም ድረስ አሉ። እነዚህ ቤቶች የሴት ጥበቃዎች መኖሪያ ነበሩ። አንዳንዶቹ ጥበቃዎች ከልጆቻቸው ጋር ይኖሩ ነበር። በዛ ዘመን ጥበቃ ከነበሩት አንዷ ከቤቱ ማዶ ያለውን ደን በማስታወስ "በሕይወቴ ጥሩ ጊዜ ያሳለፍኩበት ወቅት ነበር" ይላሉ። በእርግጥ ከመኝታ ቤታቸው አሻግረው ሲመለከቱ እስረኞችን እና በጭስ ታፍነው የሚገደሉበትን የሰቆቃ ክፍል ይመለከታሉ። ራቨንስበርክ የሚባለው ይህ ቦታ አሁን መታሰቢያ ሙዝየም ሆኗል። የሙዝየሙ ዳይሬክተር ዶ/ር አንድራ ገንሰት እንደሚሉትም፤ አብዛኞቹ ጎብኚዎች የሚጠይቁት ከወንዶች ይልቅ ስለ ሴት ሠራተኞች ነው። "በርካታ ሰዎች ሴቶች ጨካኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ አያስቡም" ይላሉ ዳይሬክተሯ። አብዛኞቹ የተቀጠሩት ሴቶች ከድሀ ቤተሰብ የተገኙ፣ በልጅነታቸው ትምህርት ያቋረጡና ሌላ ሥራ መያዝ የማይችሉ ናቸው። በግዳጅ ማቆያው ጥሩ ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ማረፊያም ያገኛሉ። ዶ/ር አንድራ እንደሚያስረዱት በዘመኑ በዚህ እስር ቤት መቀጠር የፋብሪካ ሠራተኛ ከመሆን የተሻለ ነበር። አብዛኞቹ ሴቶች በናዚ የወጣት ሊግ የተመለመሉና በሒትለር ሐሳብ የሚያምኑ ናቸው። "ማኅበረሰቡን ከጠላቶቹ በመከላከል በጎ ተግባር እንደፈጸሙ ያምኑ ነበር" ይላሉ ዳይሬክተሯ። "እርጉም ሰዎች ናቸው" አሁን ሙዝየም በሆነው ክፍል የሚታዩ ፎቶዎች የያኔ ወጣት ሴቶች በዘመነኛ ልብስና የጸጉር አሠራር ተውበው ያሳያሉ። ብዙዎቹ በ20ዎቹ እድሜ ክልል ሲሆኑ፤ ቤታቸው ውስጥ እየሳቁና ተቃቅፈው ቡና ሲጠጡ፣ ኬክ ሲበሉ እንዲሁም ውሾቻቸውን ይዘው ደን ውስጥ ሲንሸራሸሩ ይታያል። እነዚህ ሴቶች የናዚ ፓርቲ መለያ ልብስ ማድረጋቸውን ሲያስተውሉ የያዟቸው ውሾች ሰዎችን ለማሰቃየት ይውሉ እንደነበር ያስታውሳሉ። በናዚ እስር ቤቶች ወደ 3,500 የሚጠጉ ሴት ጥበቃዎች ነበሩ። ሥራቸውን በራቨንስበርክ ጀምረው ኋላ ላይ ግድያ ይፈጸምባቸው ወደነበሩት ካምፖች የተዘዋወሩ አሉ። ጀርመናዊት የአይሁድ እምነት ተከታይ ሰልማ ቫን ደ ፔሬ 98 ዓመታቸው ነው። በናዚ እስር ቤት ታስረው ከነበሩ አንዷ ናቸው። አሁን ለንደን የሚኖሩት አዛውንት ያንን ዘመንና የናዚ ሰዎችን ሲገልጹ "እርጉም ሰዎች ናቸው" ይላሉ። "ሥራቸውን ይወዱት የነበረው ምናልባትም ኃያል እንደሆኑ ስለተሰማቸው ይሆናል። እስረኞቹ ላይ ጉልበታቸውን ያሳዩ ነበር። የተንገላቱ፣ የተደበደቡ እስረኞች ነበሩ" ሲሉ ሰቆቃውን ያስታውሳሉ። ሰልማ ያኔ በናዚ ተይዞ በነበረው ኔዘርላንድስ ስውር እንቅስቃሴ በማድረግ አይሁዳውያን ቤተሰቦችን ነጻ ለማውጣት ይለፉ ነበር። በያዝነው ዓመት መባቻ ላይ ስለ ሕይወት ተሞክሯቸው የሚያትት "ማይ ኔም ኢዝ ሰልማ" የተባለ መጽሐፍ አሳትመዋል። የሰልማ ወላጆችና እህታቸው የተገደሉት የናዚ ካምፕ ውስጥ ነው። በየዓመቱ ወደ ካምፑ እየሄዱ ቤተሰቦቻቸውን ይዘክራሉ። የተፈጸመው ግፍ እንደማይዘነጋም ያስባሉ። ራቨንስበርክ የሴቶች ብቻ ከሆኑ የናዚ ካምፓች ትልቁ ነው። ከመላው አውሮፓ ወደ 120,000 ሴቶች ታስረውበታል። አብዛኞቹ ናዚን የሚቃወሙ የንቅናቄ...\nSummary in the same language as the doc:
እአአ በ1944 በጀርመን ጋዜጣ የወጣ ማስታወቂያ እንዲህ ይነበባል. . .
amh_Ethi
train
docsummary
GEM/xlsum
amharic
411
Title: የኤርትራ ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ደርሰዋል\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልሕ እና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ የሆኑት የማነ ገብረ አብ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ሲደረግላቸው ለልኡካን ቡድኑ በቦሌ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል ያደረጉላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፣ የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ አህመድ ሽዴና አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) ናቸው። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ባለፈው ሳምንት በኤርትራ ቴሌቪዥን የሰማዕታት ቀንን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ስለአገራቱ የወደፊት ጉዞ የሚመክር አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልኩ መግለፃቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ መለስ አለም አርብ ዕለት በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሚኖር ሰላም ከሁለቱ አገራት ባለፈ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በጣም ጠቃሚ እንደሆነ "ፋይዳው ከክልሉ በላይ ነው" በማለት ነበር የተናገሩት። ጨምረውም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ለኤርትራ ልዑካን አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እንደሚኖር ተናግረው ነበር። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሰማዕታት ቀንን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ላይ እንደገለፁት የልዑካን ቡድኖቹ ወደ አዲስ አበባ የሚያቀኑት ጉዳዩን በቀጥታና በጥልቀት ለማወቅና ቀጣይ የስራ እቅድ ለማውጣት እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል። የኤርትራን የልዑካን ቡድን ለመቀበል በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የነበረው ድባብ ይህን ይመስላል። የግል እና የመንግሥት ሚዲያ ተቋማት ባለሙያዎች በቦሌ አየር ማረፊያ የሃይማኖት አባቶች የኤርትራ ልዑካን ቡድንን ለመቀበል በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይገኛሉ
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
209
Title: በአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ ምልክት ከታየባቸው አራቱ ነፃ ሆነው መገኘታቸው ተነገረ\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
በክልሉ የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸው ከነበሩት መካከል የሁለቱ ውጤት እንደታወቀ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል። ይህ የተገለጸው በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ዛሬ በባሀርዳር በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለሶስተ መቶ የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መልካሙ አብቴ አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም አምስት የለይቶ ማቆያዎች ብቻ እንደነበሩ የገለጹት ኃፊው በሁሉም ዞኖች አንድ አንድ የለይቶ ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ መደረጉንም ገልጸዋል። በክልሉ በሚገኙ አራት አውሮፕላን ማረፊያዎች እና በመተማ ድንበር እስካሁን 1900 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሙቀት ምርመራ ማድረጉን ቢሮው አስታውቋል። በክልሉ በበሽታው የተያዘ ሰው አለመኖሩን እንደ መልካም ዕድል መጠቀም ዝግጅቶችን አጠናክሮ ማካሄድ እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማህተመ ኃይሌ ናቸው። ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በመከታተል እና የግል ንጽህናውን አዘውትሮ በመጠበቅ የመከላከል ሥራውን ከእራስ መጀመር እንደሚገበባ አስረድተዋል። ከአውሮፕላን ማረፊያዎች እና ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር በተጨማሪ የክልሉ መግቢያ በሆኑት በደጀን፣ ደብረ ብርሃን እና ባቲ የሙቀት መለካት ሥራ ከሰኞ ጀምሮ ተግበራዊ ይደረጋል ብለዋል። የቫይረሱን ምርመራ በክልሉ ለመጀመር የሚመለከታቸውን አካላት እየጠየቁ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ የሚሆን ግብዓት ከተገኘ ዝግጁ የሆነ ቤተ-ሙከራ መኖሩን ጠቁመዋል። ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ በክልሉ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን በምክትል ርዕሰ መስተዳደድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ጠቁመው፤ ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል። የክልሉን ከፍተኛ ሥራ ኃፊዎች ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የሚመለከታቸው አካላት የተዋቀሩበት ግብረ-ኃይል ወደ ሥራ ገብቷል። የክልሉ መንግሥትም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለሚሠሩ ሥራዎች የሚውል 150 ሚሊዮን ብር መመደቡን ታውቋል።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
236
Title: ለአንድ የውሻ ዘር ብሔራዊ በዓል ያወጀችው አገር\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
አላባይ በተርከመኒስታን ለብዙ ዓመታት ብርቅዬ ዝርያ ተደርጎ የሚወደድ ነው በዲሞክራሲ መብቶች አፈናና በሙስና ስሟ ተደጋግሞ ይነሳል። ቱክሜኒስታን አሁን አዲስ የብሔራዊ በዓል አውጃለችው። በዓሉ ለአንድ ውሻ ዝርያ ክብር የታወጀ ነው። የውሻ ዝርያው ስም አላባይ ይባላል። የሼፔርድ ውሻ ዓይነት ሲሆን በዚያች አገር ለብዙ ዓመታት ብርቅዬ ዝርያ ተደርጎ የሚወደድ ነው። ትናንት እሁድ ልዩ የእውቅና በዓል ተደርጎለታል። ሽልማትም ተበርክቶለታል። ፕሬዝዳንት ጉባንጉሊ በርዲሙካሜዶቭ የዚህን አላባይ ውሻ በብሔራዊ ደረጃ መወደስ አስፈላጊነትን ያንቆለጳጰሱ ሲሆን ውሻው ብሔራዊ ኩራታችን ነው ብለዋል። በቱክሜኒስታን ይህ አላባይ ውሻ ብቻ ሳይሆን አሃል ቴክ ፈረስ ዝርያም የብሔራዊ ኩራት መገለጫ ነው። ትናንት እሁድ ለአላባይ ውሻ ዝርያ ልዩ ክብረ በዓል ተሰናድቶ ነበር። የአላባይ ውሾች የቁንጅና ውድድርም ተደርጓል። የአላባይ ውሾች ቁንጅና ውድድርን ተከትሎ ደግሞ ብልህና ቀልጣፋ ውሾች ውድድርና የእውቅና የመስጠት ሥነ ሥርዓት ተካሄዷል። የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር በርዴሙካመዶቭ በድንበር አካባቢ በጥበቃ ታማኝና ጀብዱ ለፈጸመ ውሻ የአገሪቱን ትልቅ ሜዳሊያ ሸልመውታል። ይህን ሜዳሊያ ለርዕሰ ብሔሩ ያቀበሉት ደግሞ የፕሬዝዳንቱ ወንድ ልጅና የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሰርዳር በርዲሞካመዶቭ ናቸው። በውቧ የቱክሜኒስታን ዋና ከተማ አሽጋባት የተገነባው የዚህ ውሻ ዝርያ ማራቢያ ማዕከልም በፕሬዝዳንቱ ተመርቋል። አላባይ ውሾች በቱርከሜኒስታን እጅግ ተወዳጅና በእረኞች ዘንድ የሚዘወተሩ ሲሆኑ በዓለም ውሾች ዝርያም ግዙፎቹ ናቸው። አንድ የአላባይ ውሻ በአማካይ እስከ 80 ኪሎ ይመዝናል። ባለፈው ዓመት የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር በርዲሙካመዶቭ 6 ሜትር ቁመት ያለው ከወርቅ የተሠራ የውሻ ሐውልት በዋና ከተማዋ አደባባይ መርቀዋል። ዋና ከተማዋ አሽጋባት በርካታ የውሻና የፈረስ ሐውልቶች አሏት። አምባገነን ናቸው፣ ተቀናቃኝ የላቸውም የሚባሉት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚስተር በርዴ ሙካመዶቭ የየትኛውንም አገር መሪ ሲጎበኙ የውሻ ወይም የፈረስ ስጦታን ይዘው ነው የሚሄዱት። በጎርጎሳዊያኑ 2017 ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን አላባይ ውሻን በስጦታ ባበረከቱበት ወቅት ድንክየውን ውሻ በማጅራቱ በኩል አንጠልጥለው በእንዝላልነትና ርህራሄ በጎደለው አኳኋን ለፑቲን ማስረከባቸው እጅግ ሲያስተቻቸው ነበር። ቅጽበቱም በቪዲዮ በመላው ዓለም ተዛምቶ ሚሊዮኖች ከፍ ዝቅ አድርገዋቸው የዓለም መሳቂያ ሆነው ነበር። ስጦታውን የተቀበሉት ቪላድሚር ፑቲን ግን አላባይ ድንክ ውሻውን በፍቅር አቅፈው መቀበላቸው በአንጻሩ ውዳሴን አስገኝቶላቸው ነበር።
amh_Ethi
train
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
301
ካለሁበት 27፡ 'እንጀራ ከበላሁ ዓመት አልፎኛል'\nወደዚህ የመጣሁት በአጋጣሚ ነው። መጀመሪያ የመጣሁት ታይላንድ ሲሆን ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ነበር ቪየትናም ቅርብ በመሆኗ ለጉብኝት ወደዚህ ያቀናሁት። እንደደረስኩ ያረፍኩባት በቪየትናም መዲና ሐኖይ ነበር። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሆ ቺ ሚን የምትባለው ሌላኛዋ የቪየትናም ከተማ መጣሁ። በመቀጠልም ሙይኔይን ስጎበኝ በጣም ወደድኳት እናም እዚሁ ለመቆየት አሰብኩ። እንደ አጋጣሚም ሆኖ የነበርኩበት ማረፊያ ውስጥ ደግሞ የበጎ ፈቃድ ሠራተኛ ያስፈልጋቸው ስለነበር፤ እዚያው እያገለገልኩኝ ለመቅረት ወሰንኩኝ። ይሄው መኖሪያየን ሙይኔይ ካደረግኩ ስድስት ወራት ተቆጥረዋል። ሙይኔይን ከአዲስ አበባ ጋር ሳነፃጽራት ከምግቡ አንስቶ፣ የኑሮው ዘዬ ሰዎቹ የተለያዩ ናቸው። ቪየትናም በጣም የተለየች ሃገር ናት። ሆኖም ግን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ለእኔ ትናንሽ ሱቆቹና ሱቅ በደረቴዎቹ ናቸው። በተለይ ይህ ጉዳይ ከናዝሬት ጋር ይመሳሰልብኛል። ከምግባቸው ደግሞ በጣም የምወደው አትክልትና ሥጋ ወይም አትክልትና የዓሣ ዓይነቶችን አቀላቅለው የሚሰሩትን ሾርባ 'ፈ' ተብሎ የሚጠራውን ነው። በተለይ የሚያቃጥል አዋዜ ነገር ቢጨምሩበት ደግሞ ጣዕሙ የተለየ ይሆናል። ኢትዮጵያ በጣም ትናፍቀኛለች። እንጀራ በዓይኔ ውል ውል ይላል። ይሄው እንጀራ ከበላሁ ዓመት አልፎኛል። ሬስቶራንት ሄጄ እንዳልበላ በቅርብ ያለው የኢትዮጵያ ምግብ ቤት የሚገኘው ካምቦዲያ ነው። እናም እንዳማረኝ እንጀራ በዓይኖቼ እንደዞረ ነው። ዲላይት የምትሠራበት ካምፕ የምሠራበት ቦታ ትንንሽ ድንኳኖችን ለቱሪስቶች የሚያከራይ የእንግዳ መቀበያ ቦታ (ካምፒንግ) ሲሆን ጥዋት ከእንቅልፌ ነቅቼ ካለሁበት ድንኳን ስመለከት የሚታየኝ አረንጓዴ መሬትና ዛፎች ናቸው። እኔ በሕይወቴ እንደዚህ በድንኳን ውስጥ ኖሬ አላውቅም ነበር ቢሆንም ለየት ያለ አኗኗር ዘይቤ ነውና ደስ ይላል። ይህ ብቻ አይደለም ለየት የሚለው እኔ ራሱ በዚህ ሀገር እንደ ልዩ ፍጥረት ነው የምታየው። ኢትዮጵያ እያለሁ ዘወር ብሎ የሚያየኝ ሰው የለም። ምናልባት ብዙ ከአፍሪካ የሚመጡ ሰዎችን አይተው ስለማያውቁና በክፋት ላይሆን ይችላል ብየ ባስብም የሚያፈጡበት ሁኔታ ያስደንቀኛል። ታይላንድ በነበርኩበት ወቅት ከተለያየ ዓለም ክፍል የሚመጡ ቱሪስቶች መናሀሪያ በመሆኗ ልዩነትን ማስተናገድ ችለዋል። ዲላይት የእንግዶችን ውሻ በባሕር ዳርቻ ስታንሸራሽር መጓዝ ስለምወድ እቃየን በሙሉ በአንድ በጀርባ በሚታዘል ትልቅ ቦርሳ በመያዝ ለባለፉት ሶስት ዓመታት የተለያዩ ሀገሮች ሄጃለሁ። ከሁለት ወይም ሶስት በስተቀር ኢትዮጵያውያን አላጋጠሙኝም ከዚህ ተነስቼ የተረዳሁት ብዘ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን እንሌሉ ነው። ለክሪሰቲን ዮሐንስ እንደነገረቻት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 28፡ "ያደግኩበት አካባቢና የሰፈሬ ልጆች በጣም ይናፍቁኛል" ካለሁበት 29 ፡ ''እዚህ ሰው በሰውነቱ ብቻ ትልቅ ክብር አለው'' \n\ntl;dr:
ዲላይት ጌታቸው እባላለሁ። ነዋሪነቴንም በጊዜያዊነት በቪዬትናም ባለችው ሙይኔይ ከተማ አድርጌያለሁ።
amh_Ethi
test
tldr
GEM/xlsum
amharic
326
ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አል-ሲሲን በመቃወም ሰልፍ ወጥተዋል በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በታህሪር አደባባይ ሰልፍ ወጥተው፤ ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2011ዱ ተቃውሞ ማዕከል ከነበረው ታህሪር አደባባይ በተጨማሪ በሌሎች አካባቢዎችም ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል። • መንግሥትን ተሳድቧል የተባለው ደራሲ ተከሰሰ • ግብፅ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሞት ውርጅብኝ እያስተናገደች ነው • በጥቅም ላይ የዋሉ የጥንታዊ ግብፅ የህክምና ጥበባት በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደው አል-ሲሲ በሙስና መወንጀላቸውን ተከትሎ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በታህሪር አደባባይ ሰልፍ ወጥተዋል ግብፃዊው ተዋናይና የቢዝነስ ሰው ሞሀመድ አሊ፤ አል-ሲሲ በቅንጡ ቤቶችና ሆቴሎች ላይ በርካታ ገንዘብ እያባከኑ እንደሚገኙ በመግለጽ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቪድዮዎች አሰራጭቷል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በድህነት እየማቀቁ ሳለ ፕሬዝዳንቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እያባከኑ መሆኑንም ተናግሯል። አል-ሲሲ የተባለው ነገር "ውሸት እና የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው" ሲሉ ውንጀላውን አጣጥለዋል። ትላንት በትዊተር ላይ በስፋት ሲሰራጩ የነበሩ መልዕክቶች ሕዝቡ አል-ሲሲ ከሥልጣን እንዲነሱ እንደሚፈልግ የሚጠቁሙ ነበሩ። አል ጀዚራ እንደዘገበው፤ በአሌክሳንድርያ እና ስዊዝ ከተሞችም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ስፔን ውስጥ በስደት የሚኖረው ግብፃዊው ተዋናይና የቢዝነስ ሰው ሞሀመድ አሊ፤ የመጀመሪያ ቪድዮውን የለቀቀው መስከረም ሁለት ነበር። ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን የሚወርዱበት ቀነ ገደብ አስቀምጦ፤ አል-ሲሲ በተባለው እለት ከሥልጣን ካልወረዱ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ገልጾም ነበር። ሞሀመድ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት፤ አል-ሲሲ ከሥ... Continue the article for another 4000 characters max:
ልጣናቸው አለመነሳታቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን ሰልፍ ወጥተዋል። ግብፅ ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የሆኑት ሞሀመድ ሙርሲን በማስወገድ አል-ሲሲ ስልጣን የጨበጡት 2013 ላይ ነበር። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መታሰራቸውን በማጣቀስ፤ የአል-ሲሲን አስተዳደር በጽኑ ይተቻሉ። 2018 ላይ በተካሄደው ምርጫ አል-ሲሲ ጠንካራ ተቀናቃኝ ሳይኖር 97 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል። አል-ሲሲ እስከ 2030 ስልጣን ላይ እንዲቆዩ ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ የማድረግ ሀሳብ አብላጫ ድምፅ ማግኘቱም ይታወሳል።
amh_Ethi
train
xp3longcontinue
GEM/xlsum
amharic
254
ቱርክ እና ግሪክ በምስራቅ ሜደትራኒያን በባህር ድንበር እና የኃይል ምንጭ ጋር በተያያዘ አለመግባባት ውስጥ ከገቡ ሰነባብተዋል። የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደነት ኡራሱላ ቮን ደር ላየን ቱርክ በምስራቅ ሜደትራኒያን እየወሰደች ካለችው የአንድ ወገን እርምጃ መቆጠብ አለባት ሲሉ አሳስበዋል። ቱርክ በፈረንጆቹ 2020 መጀመሪያ ላይ የነዳጅ ክምችት ለማሰስ የይገባኛል ጭቅጭቅ ወደሚያስተናግደው ምስራቅ ሜደትራኒያን መርከብ መላኳን ተከትሎ በቱርክ እና በግሪክ መካከል ውጥረት ኃይሏል። ግሪክ እና ቱርክ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን- ኔቶ አባላት ቢሆኑም በድንበር እና የውሃ ክፍል ይገባኛል በሚሉ ምክንያቶች በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ይገባሉ። የአውሮፓ ሕብረት የአባል አገር ለሆነችው ግሪክ ድጋፉን ሲግልጽ ቆይቷል። የአውሮፓ ሕብረት ፕሬዝደንቷ በብራሰልስ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ የአውሮፓ ሕብረት ከቱርክ ጋር መልካም እና ገንቢ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረው ይሻል፤ በዚህ ደግሞ ትልቁ ተጠቃሚ የቱርክ መንግሥት ነው ብለዋል። ቱርክ በቀጠናው እየፈጠረች ያለችውን ጫና እና ከጠብ አጫሪ እንቅስቃሴዋ የማትቆጠብ ከሆነ፤ የአውሮፓ ሕብረት ያሉትን ሌሎች አማራጮች ይመለከታልም ብለዋል። የሕብረቱ አባል አገራት መሪዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ቱርክ ከዚህ እንቅስቃሴዋ የማትቆጠብ ከሆነ ማዕቀብ እንዲጣልባት መስማማታቸው ተጠቁሟል። የኦስትሪያው ቻንስለር ሴባስቲያን ኩርዝ በትዊተር ገጻቸው ቱርክ ዓለም አቀፍ ሕጎችን መተላለፍ የምትቀጥል ከሆነ ሕብረቱ ማዕቀብ ይጥላል ብለዋል። ቱርክ እና የአውሮፓ ሕብረት ከዚህ ቀደምም መልካም የሚባል ግነኙነት የላቸውም። ቱርክ የሕብረቱ አባል ለመሆን ለዓመታት ጥረት ስታደርግ የቆየች ቢሆንም ጥረቷ ግን ፍሬ ሳያፈራ ዓመታት አልፈዋል። ሕብረቱ ቱርክ የሰብዓዊ መብት ጥስት ተፈጽማለች ይላል። በተለይ እአአ 2016 የረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን መንግሥትን ለመፈንቀል ሞክረዋል ተብለው በተወነጀሉ ሰዎች ላይ ቱርክ የወሰደችው እርምጃ ከሕብረቱ ጋር ቅራኔ ውስጥ ከትቷታል። ቱርክ ምንም እንኳ ከሕብረቱ ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት ባይኖራትም ለአውሮፓ ሕብረት አገራት ወሳኝ አገር ሆና ቆይታለች። ቱርክ መዳረሻቸውን አውሮፓ ማድረግ የሚሹ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች ይዛ ትገኛለች። ሰደተኞች ወደ ግሪክ እንዳይሻገሩ ይዛ ለመቆየትም ቱርክ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ከስምምነት ደርሳለች። \n\nGive me a good title for the article above.
የአውሮፓ ሕብረት ቱርክ ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ሲል አስጠነቀቀ
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
273
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ኢትዮጵያ ከዓለም ጥቂት አጫሾች ያሉባት አገር ናት\nSummary: ትምባሆ ማጤስ በማቆም ፈረንሳዊያንን የሚያህል አልተገኘም። በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ አንድ ሚሊዮን ዜጎች የትምባሆን ነገር በቃን ብለዋል። ይህም ከ2016 እስከ 2017 ብቻ የሆነ ነው።\nArticle (Max 500 characters):
አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ፈረንሳዊያን የትምባሆ ነገር በቃን ብለዋል በርካታ አገራት የትምባሆ ስርጭትን ለመግታት ፖሊሲያቸውን ከልሰዋል። ያም ሆኖ በዓለም ላይ የአጫሾች ቁጥር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም። ዛሬ የዓለም ትምባሆ ያለማጤስ ቀን ከመሆኑ ጋር አስታከን የአጫሽ አገራትን ዝርዝር አቅርበናል። 1. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የምትባል የማዕከላዊ ፓሲፊክ ደሴት በአጫሾች ቁጥር በዓለም ቀዳሚዋ ናት። ከሕዝቧ ሁለት ሦስተኛ ወንዶች ትምባሆ የሚያጤስ ነው። ከሴቶች ደግሞ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ደግሞ አጫሾች ናቸው። ኪሪባቲ ደሴት በትምባሆ ላይ የምትጥለው ግብር ትንሽ ነው በዚህች አገር 103,000 ሕዝብ ይኖራል። በትምባሆ ላይ የተጣለው ግብር አነስተኛ ሲሆን ሕዝቡ በቀላሉ በየትም ቦታ ትምባሆን ማግኘት ይችላል። 2. ሞንቴኔግሮ ምሥራቅ አውሮፓዊቷ አገር ሞንቴኔግሮ ከአውሮፓ በአጫሽ ቁጥ
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
159
Title: በመላው ኢትዮጵያ ያጋጠመው የኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያቱ ምንድን ነው?\nGiven the above title of an imaginary article, imagine the article.\n
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር እቶ ሞገስ መኮንንም የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ትናንት ምሽት ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ነገር ግን ላጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አለመታወቁን ገልጸው፣ ነገር ግን ከግልገል ጊቤ ሦስት ከሚቀርበው የኃይል አቅርቦት መስመር ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችልና ተቋማቸው የችግሩን ምንጭ ለማወቅና መፍትሄ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አቶ ሞገስ ተናግረው ነበር። • የግድቡ ውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት መፈረም አለበት፡ አሜሪካ • በሶማሌ ክልል የነዳጅ ማውጫ አካባቢ ያልተለመደ የጤና ችግር እያጋጠመ ነው ተባለ ከሰዓታት በኋላም በግልገል ጊቤ ማመንጫዎች ቦታ የጣና በለስና የፊንጫ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ከኃይል አቅርቦት ሥርዓቱ ጋር በማገናኘት የዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ መደረጉም ታውቋል። ግን ምንድን ነው ያጋጠመው? አቶ ሞገስ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ለቢቢሲ እንደገለጹት ላጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ምክንያት የሆነው በግልገል ጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ አካባቢ በጣለ ከባድ ዝናብ ሳቢያ መሆኑን አመልክተዋል። የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ጨምረውም ከባዱ ዝናብ በግልገል ጊቤ ሁለት ላይ ባስከተለው ችግር ምክንያት የኃይል ማመንጫው ተግባሩን በአግባቡ ማከናወን ባለመቻሉ የመቆጣጠሪያ ሥርዓቱ በእራሱ አሰራር ኃይል የማግኛ መስመሩን ወደ ግልገል ጊቤ ሦስት በማሸጋገር አገልግሎቱን ለመቀጠል ተሞክሯል። • እያንፀባረቁ ያሉት ኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች ይህ ደግሞ በግልገል ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ላይ ያልተጠበቀ ክፍተኛ ጫና በማስከተሉ ግልገል ጊቤ ሦስትም ሥራውን በአግባቡ እንዳያከናውን ምክንያት ሆኖ አገልግሎት በማቆሙ በአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ለሰዓታት እንዲቋረጥ ምክንያት መሆኑን አቶ ሞገስ እብራርተዋል። አክለውም የድርጅታቸው ባለሙያዎች ችግሩን ለመቅረፍ የኃይል መቋረጡ ካጋጠመበት ጊዜ ጀምሮ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አመልክተው ሙከራ እየተደረገባቸው ካሉ አንዳንድ እካባቢዎች በስተቀር በሁሉም ቦታዎች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መመለሱን ተናግረዋል።
amh_Ethi
test
xp3longimaginearticle
GEM/xlsum
amharic
246
Content: የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ወይዘሮ ስንታየሁ ለጤና ባለሙያዎቹ በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን በተመለከተም አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል በድንገተኛ እና በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚሰሩ ነርሶችና ዶክተሮች እንደሚገኙበት በመጥቀስ፤ በዚህ ክፍል የሚሰሩት ባለሙያዎች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ተጋላጭ መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ እስካሁን ድረስ ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረገላቸው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ከ500 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውንና 17 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማገገማቸውን የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ስንታየሁ ደበሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 66 ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ተካ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጊኒር ከተማ እና በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ በተደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ እነዚህ ታራሚዎች ኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታራሚዎች ለህክምና ወደ ሮቤ ሆስፒታል መላካቸውንም ቢቢሲ ከኃላፊው መረዳት ችሏል። ኃላፊው በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ታራሚዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ በማያስችላቸው እና ያለ ምንም ጥንቃቄ መልኩ መታሰራቸው በሽታው እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች የፀረ ተህዋሲ ርጭት ተደርጓል። በቀላል ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑንም ተናግረዋል። ታራሚዎቹን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦችም በሽታውን ወደ ኅብረተሰቡ ይዘው በመሄድ ስርጭቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ከተጠረጠሩት ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 470 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ 21 ሺህ 452 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህም መካከል በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 380 ደርሷል። \nThe previous content can be summarized as follows:
በድሬዳዋ 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋገጠ።
amh_Ethi
train
prevcontent
GEM/xlsum
amharic
383
የኦሮምኛ ዘፋኙ ዳዲ ገላ በምስራቅ ሸዋ በቢሾፍቱ አቅራቢያ በምትገኘው የሊበን ዝቋላ ወረዳዋ ትንሿ የገጠር ከተማ አሹፌ ካለፈው ቅዳሜ እስከ ሰኞ ምሽት ደስታና ጭፈራ ነበር። ይጨፈር የነበረው ለአንድ ሆቴል ምርቃት ነበር። ደስታና ጭፈራው ግን አልዘለቀም። •ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ? •ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን የምርቃቱ ታዳሚዎች በደስታ ጥይት ወደላይ ይተኩሱ ነበር። የመድረኩ ፈርጥ የነበረው ታዋቂው ኦሮምኛ ዘፋኝ ዳዲ ገላን ድንገት በጥይት ተመትቶ እንደወደቀ የሆቴል ምርቃቱ የሙዚቃ ድግስ መድረክ አስተባባሪ የነበረው ጓደኛው አቶ ቱፋ ወዳጆ ይናገራል። "ለቅሶም ላይም ይተኮሳል። ልጅም፣ አባትም ክላሽ መታጠቅ ባህል ነው። በወቅቱ እየተተኮሰ እያለ ማን እንደሆነ አይታወቅም ከመሀል ልቡን መትቶት ወደቀ" በማለት ይገልፃል። በህግ የተከለከለ ቢሆንም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለሰርግ፣ለሃዘን ፣ለልደትና ለሌሎችም መሰል አጋጣሚዎች ጥይት መተኮስ የተለመደ ነው ማለት ይቻላል። በሃይማኖት አባቶችና በገዳዎች ምክር ጭምር ጥይት መተኮስ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ አዲስ እንደተጀመረ ዘፋኙ ህይወቱን ያጣበት የሊበን ጩቃላ ወረዳ ፖሊስ ፅፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ግርማ ሚደቅሳ ለቢቢሲ ገልፀዋል። •የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን ከ2009 ዓ.ም የለውጡን እንቅስቃሴ ተከትሎ በተለያዩ በዓላትና አከባበሮች ላይ ደስታንም ሆነ ኃዘንን ለመግለፅ መተኮስ እንደተጀመረ ኢንስፔክተር ግርማ በተጨማሪ ገልፀዋል። ባለፈው አመትም አቅራቢያው በሚገኝ ሌላ አካባቢ አንድ ወጣት የደስደስ ጥይት ሲተኩስ ጓደኛውን በመግደሉ መልሶ ራሱን እንዳጠፋ ኢንስፔክተር ግርማ ያስታውሳሉ። ኦሮምኛ ሙዚቃዎችን የሚጫወተው ዳዲ አስከሬን ለምርመራ ተልኮ ከነበረበት ጳውሎስ ሆስፒታል ዛሬ ከሰዓት በኋላ የትውልድ ቀዬው አሹፌ መድረሱን ኢንስፔክተሩ ገልፀውልናል። \n\nGive me a good title for the article above.
ኦሮምኛ ዘፋኙ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን አጣ
amh_Ethi
train
goodtitle
GEM/xlsum
amharic
223
Given the below title and summary of an article, generate a short article or the beginning of a long article to go along with them. Title: ፍሬዲ ብሎም፡'የዓለማችን የእድሜ ባለፀጋ' ደቡብ አፍሪካዊ በ116 ዓመታቸው አረፉ\nSummary: የዓለማችን በዕድሜ ትልቁ ሰው ይሆናሉ ተብለው የታሰቡት ደቡብ አፍሪካዊ በ116 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።\nArticle (Max 500 characters):
እኝህ የእድሜ ባለፀጋ ፍሬዲ ብሎም፤ በምስራቅ ኬፕ ግዛት በጎርጎሮሳዊያኑ ግንቦት ወር 1904 እንደተወለዱ የግል መረጃቸው ያሳያሉ። ይህ ግን በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ የተረጋገጠ አይደለም። በጎርጎሮሳዊያኑ 1918 በተከሰተው በስፓኒሽ ጉንፋን ወረርሽኝ (የኅዳር በሽታ) ምክንያት በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ላይ እያሉ ጠቅላላ ቤተሰባቸውን አጡ። የሚገርመው ከወረርሽኙ ያመለጡት ፍሬዲ፤ ለበርካቶች ሞት ምክንያት ከሆኑት ሁለት የዓለም ጦርነቶችና እና ከአፓርታይድ ጭፍጨፋም ተርፈዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት ረዥም እድሜ ለመቆየታቸው ሚስጥሩ ምንድን ነው ? ተብለው የተጠየቁት የዕድሜ ባለፀጋው ለቢቢሲ ሲናገሩ "ምንም የተለየ ሚስጥር የለውም" ብለዋል። " አንድ ነገር ብቻ ነበር። ይህም ከፈጣሪ የተሰጠ ፀጋ ነው። ሁሉም ኃይል ያለው እሱ ነው። እኔ ምንም የለኝ። በማንኛው
amh_Ethi
train
xp3longgenarticle
GEM/xlsum
amharic
149