Datasets:

id
stringlengths
9
150
url
stringlengths
42
183
title
stringlengths
11
101
summary
stringlengths
45
356
text
stringlengths
439
6.59k
a_g20-toronto-canada-meeting-06-28-10-97331599_1460839
https://amharic.voanews.com/a/g20-toronto-canada-meeting-06-28-10-97331599/1460839.html
የG20 አገሮች መሪዎች በቶሮንቶ ካናዳ ተሰባሰቡ
በሶስት ዓመታት ውስጥ የባጀት ኪሳራቸዉን በግማሽ እንዲቀንሱ ፣ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር እስከ 2016 ደግሞ ከኢኮኖሚ እድገታቸዉ ጋር በማጣመር ተጨማሪ የባጄት ኪሳራ ቅነሳ ማድረግ አለባቸዉ አሉ።
የዓመት የባጄት ኪሳራቸውን እየቀነሱ የኢኮኖሚ እቅዳቸውን ከግብ የማድረስ ግዴታ እንዳለባቸው መክረዋል ስምንት በኢኮኖሚ ከበርቴ የሆኑ እና ኢኮኖሚያቸዉ እየመጠቀ ያለ እንደ ቻይናና ህንድ ያሉ ታዳጊ አገሮችን የጠቀለለ የ G 20 መሪዎች ጉባኤ በቋፍ ያለ የዓለም ኢኮኖሚ አሁንም ማነቃቂያ እንደሚያሰፈልገውና የበጀት ኪሳራቸውን ለመቀነሰ ግን የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ እንዳለባቸው ተስማምተዋል። ጉባኤዉን ባስተናገደችው አገር ካናዳ ባቀረበችው እቅድ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ስቲቨን ሀርፐር የኢኮኖሚ ተሃድሶው እንዲቀጥል፣ አገሮች ባለፈዉ ዓመት ጉባኤ በፒትስበርግ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ፣ የዓለም ገበያን ለማረጋጋት መሪዎቹ የተቀነባበረ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። የG 20 አገሮች የዓመት የባጄት ኪሳራቸውን እየቀነሱ የኢኮኖሚ እቅዳቸውን ከግብ የማድረስ ግዴታ እንዳለባቸው መክረዋል። የG20 እና G8 መሪዎች በጉባኤዉ ፍጻሜ ላይ ያወጡት መግለጫ በአያሌ አገሮች የስራ አጡ ህዝብ ቁጥር ከሚገባው በላይ ከፍተኛ ስለሆነ፣ የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ማገገም በቋፍ ያለና ኑሮ ላይ ያስከተለው ቀውስም እንደሃገሮቹ የተለያየ ነው ይላል። የግል ንግዶችን የብድር ፍላጎት ለማሙዋላትና ኢኮኖሚውን እንደገና ለማንሰራራት የማነቃቂያ እርምጃ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸዉ ተጠቅሷል። በዓለም እኩል የማይራመዱና ወጣ ገባ የኢኮኖሚ አያያዞች፣ በተለይም የአገሮች የባጄት ኪሳራ ወደ ማገገም የተያዘዉን አቅጣጫም ሊቀለብሱ እንደሚችሉ የG20 መሪዎች ይናገራሉ። ፕሬዚደንት ኦባማና ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት፣ የኢኮኖሚ እድገቱ አንድ ተጨባጭ ውጤት ሳያሳይ፣ በመንግስታት የሚወሰዱ የማነቀቂያ እርምጃዎች እንዳይቋረጡ ፣ ያ ከሆነ ግን እንደገና የዓለም ዋጋ ግሽበት እንደሚከስት ያስጠነቅቃሉ። በጉባኤዉ ፍጻሜ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ በዚህ ነጥብ ላይ ስላለዉ የሃሳብ ልዩነት ፕሬዚደንት ኦባማ ተጠይቀዉ በተለያዩ አገሮች የሚታየው የኢኮኖሚ ማገገም አሁንም በቋፍ ያለ እንደሆነና ተሃድሶ ላይ ለመድረስም ገና ብዙ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል። የጉባኤዉ መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ የምትከተላችውን ልዩ ልዩ ፖሊሲዎች ያንጸባርቃል የሚሉት ፕሬዚደንት ኦባማም ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ የማንፈልግ ከሆነ ግን “በመካከለኛና ረጅም ጊዜያት በመተመን ከባድ የባጄት ኪሳራ ቅነሳ መጋፈጥ ይኖርብናል፤” ይላሉ። የሚቀጥለዉ የG 20 መሪዎች ጉባኤ በመጪው ህዳር ወር በሶል ደቡብ ኮሪያ ይደረጋል።
a_amnesty-open-letter-to-the-ethiopian-parilament-voa-03-01-18_4276606
https://amharic.voanews.com/a/amnesty-open-letter-to-the-ethiopian-parilament-voa-03-01-18/4276606.html
አምነስቲ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ።
“አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው። አሁን ላለው ችግር መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ።” ሳሊ ሼቲ የአምነስቲ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ለኢትዮጵያ ፓርላማ አባላት ግልጽ ደብዳቤ ልኳል። የምክር ቤቱ አባላት ነገ አርብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ለመምከር እየተዘጋጁ ባሉበት በዚህ ወቅት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ይበልጥ እንዲያስቡ ጥሪ እናቀርባለን፤ ብሏል። በነገው የፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዙሪያ ክርክር የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አብይ ትኩረት እንዲሆን ነው፤ አምነስቲ በግልጽ ደብዳቤው የጠየቀው። የኢትዮጵያ ፓርላማ አዲሱ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀድሞውንም የጠበበውን በሃገሪቱ ያለውን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት፤ የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶች ይበልጥ እንዳያጠፋ ማረጋገጥ አለበት” ሲል የሚንደረደረው የአምነስቲ መግለጫ የብሔራዊው ሸንጎ በነገው ዕለት ሲከፈት አባላቱ በሚያደርጉት ክርክር ወቅት፤ “አሳሳቢውንና የከፋውን” የአገሪቱን ሁኔታ በቅጡ እንዲያጤኑ አሳስቧል። “አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው” ሲሉ፤ የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር ሳሊ ሼቲ ለፓርላማ አባላቱ በላኩት ደብዳቤ “መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ” ያሉበትን አቶ ፍስሃ ያብራራሉ። ይበልጥ የሚያሳስበን ደግሞ የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊ ያሉትን ኃይል እንዲጠቀሙ መታዘዙ ነው፤ ይላሉ አቶ ፍስሃ። “ሁላችሁም” ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ዋቢ ያደረገው የአምነስቲ መግለጫ፤ (የፓርላማ አባላትም ጭምር ማለታቸው ነው) “ሁላችሁም በሕግ እንድተዳደሩ፤ የሕዝቡን ፍቃድ እንድታከብሩና ለሕሊናችሁ እንድትገዙ፤ የሃገሪቱ ሕገ-መንግስት ግድ ይጠይቃል። በአስቸኳይ አዋጁ ጉዳይ ውሳኔ በምትታሳልፉበት ወቅት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊ መብት መከበር ሙሉ ትኩረት መስጠት በእጅጉ አስፈላጊ ነው። ” ብለዋል።
a_india-covid19-surpases-20-million-second-wave-continues-05-04-21_5878097
https://amharic.voanews.com/a/india-covid19-surpases-20-million-second-wave-continues-05-04-21/5878097.html
መቆሚያ ያልተበጀለት የህንዱ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ 19 ማዕበል
“አጋዥ ከማጣት የመጣ አይደለም። ጨርሶ ከመውደቅ ደረጃ መድረሱ እንጂ! ለሌላ ለማዘን ከምንችልበት ቦታ አይደለንም። እዚህ ታካሚዎች እየሞቱብን ነው። ይሄ የተለየ ድብቅ ምክኒያት የከሰተውም አይደለም።በተጨባጭ የሚታይ ነገር ነው። ሁሉም ያውቀዋል፡፡ አገረ ገዥው ያውቁታል። አስተዳደሩም ያውቀዋል። ሁሉም ያውቀዋል፡፡” ዶ/ር ሩሺ ጉብታ በማዕከላዊ ኒው ዴልሂ የሚገኝ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን ሃኪም።
ዋሺንግተን ዲሲ — ህንድን እያናወጠው ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዛሬ 13ተኛ ቀን በተከታታይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ለቫይረሱ መጋለጡ ተዘግቧል። በአንድ ቀን ዕድሜ 357 ሺህ 229 አዲስ ለኮረናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች መዘገባቸውን የጤና ሚንስትር በዛሬው ዕለት አስታውቋል። ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በደቡባዊ እስያዊቱ አገር በኮቪድ-19 ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ከ3449 በላይ ሰዎች ናቸው። በጃን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮረናቫይረስ መረጃ ማዕከል አሃዞች መሰረት ባሁኑ ወቅት በህንድ ለቫይረሱ የተጋለጠው ሰው ቁጥር ሃያ ሁለት ሚልዮን ነጥብ ሁለት በዚያች አገር በኮቪድ ሳቢያ ህይወቱ ያለፈው ሰው ቁጥር 222,408 ደርሷል። ያም ህንድን በወረርሽኙ ጥናት እና ለቫይረሱ በተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ ሁለተኛዋ አገር ያደርጋታል። በሟቶች ቁጥር ደግሞ ሶስተኛዋ አገር ናት። በአንድ የኒው ዲልሂ ሆስፒታል ሃኪሞች የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ቀውስ የሕክምና መስጫ ተቋሙ ከሚችለው በላይ ለማስተናገድ የተገደደበት ሁኔታ መፈጠሩን ይናገራሉ። ዶ/ር ሩሺ ጉብታ በአንድ ማዕከላዊ ኒው ዴልሂ በሚገኝ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን መርጃ ክፍል ሃኪም ናቸው። “አጋዥ ከማጣት የመጣ አይደለም። ጨርሶ ከመውደቅ ደረጃ መድረሱ እንጂ! ለሌላ ለማዘን ከምንችልበት ቦታ አይደለንም። እዚህ ታካሚዎች እየሞቱብን ነው። ይሄ የተለየ ድብቅ ምክኒያት የከሰተውም አይደለም። በተጨባጭ የሚታይ ነገር ነው። ሁሉም ያውቀዋል፡፡ አገረ ገዥው ያውቁታል። አስተዳደሩም ያውቀዋል። ሁሉም ያውቀዋል፡፡ ” ብለዋል። ዶ/ር ጉብታ አክለውም መሠረታዊ የኦክስጂን አቅርቦት ያለመኖሩን እና ያላቸውም በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሊያልቅባቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ትናንት የሆስፒታላቸው የድንገተኛ ክፍል ሞልቶ ስለነበር ከኮቪድ 19 ውጭ ሌሎች የድንገተኛ እርዳታ የሚሹ ታካሚዎችን ተቀብለው መርዳት ሳይቻላቸው መቅረቱን አስረድተዋል። በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሆስፒታሎች የህሙማን መቀበያ እና መርጃ መኝታዎች በመሙላታቸው እና ከፍተኛ የኦክስጂን አቅርቦቶች ዕጥረት በመፈጠሩ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች እንዲጨምር ማድረጉ ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ህንድ በገጠማት ችግር ሳቢያ ለደሃና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገሮች የሚሰራጨውን ክትባት የሚያመርተው የመድሃኒት ኩባንያ ብዙ ተስፋ እንደተጣለበት ማቅረብ በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ ባለመሆኑ የዩናይድ ስቴትሱ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ሞደርና በዓለም ጤና ድርጅት አማካኝነት ለተቋቋመው ዓለም አቀፍ የክትባት ፕሮግራም COVAX የCOVID-19 ክትባቱን መጠኑ 500 ሚሊዮን የሚደርስ ክትባት ለማቅረብ ቃል መግባቱን በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።
a_opposition-wants-new-election-06-03-10-95522759_1458002
https://amharic.voanews.com/a/opposition-wants-new-election-06-03-10-95522759/1458002.html
የኢትዮጵያው ምርጫና የተቃዋሚዎቹ የዛሬ አቋም
የመንግሥት ባለሥልጣናት የገዥው ፓርቲ አጠቃላይ ድል የሕዝቡን ፍላጎት ያሣየ ነው ቢሉም ተቃዋሚዎቹ ግን ምርጫው ተሠርቋል በሚል አቋማቸው እንደፀኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት አዲስ ምርጫ ጠይቀዋል፡፡
"ፍትሐዊ ምርጫ ቀልድ ነበር" - ኢፍዴኃግ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስምምነት የሌላቸው 65 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ከተደረሰባቸው ሰባሪ ሽንፈት ለማገገም እየተፍጨረጨሩ እንደሆነ ይታያል፡፡ ብዙዎቹ ግን በአንድ ጉዳይ ላይ ወደአንድ ሠልፍ እየገቡ ይመስላሉ - በምርጫው ውጤት፡፡ ከ547ቱ የፓርላማ መቀመጫዎች አሥር ከመቶ የማይሞሉትን የተቃዋሚ የሚባሉ መቀመጫዎች በብዙ መንገድ ነው የሚቀራመቷቸው፡፡ የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረቱ የኢትዮጵያ የፍትሕና የዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር አዲስ ምርጫ መካሄድ አለበት የሚለውን አቋም ተቀላቅሏል፡፡ ይህንን አቋም የሚያራምዱት ወገኖች ገዥው ፓርቲ ምርጫውን አጭበርብሯል፤ ዕጩዎቻቸውና ድምፅ ሰጭዎች ተዋክበዋል፤ እንዲሸማቀቁ ተደርገዋል ባይ ናቸው፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ደግሞ ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን መናገር እንደሚችሉ ቢናገሩም ድጋሚ ምርጫ የሚባል ነገር ግን የሚታሰብ ነገር እንዳልሆነ ያሣስባሉ፡፡ - ብለዋል የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትሩ በረከት ስምዖን - ይሁን እንጂ ደርሰዋል የሚባሉ ችግሮችን በገሃድ የሚያሣዩ ቁጥራቸው የበዛ ማስረጃዎች በእጃቸው እንደሚገኙ ታዛቢዎቻቸው ከብዙ የምርጫ ጣቢያዎች መባረራቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ወደምርጫው ፉክክር የገቡት መንግሥት ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ ስለነበረ ቃሉን ይጠብቃል በሚል እምነት እንደነበረ አመልክተዋል፡፡ "ያ የፍትሐዊ ምርጫ ቃል ግን ቀልድ ሆኖ ቀረ" ብለዋል የፍትሕና የዴሞክራሲ ኃይሎች ግንባር ዋና ፀሐፊ ገረሱ ጋሳ፡፡ - ሲሉም አክለዋል፡፡ የምርጫው ሂደት አያያዝና አሠራር እራሱ በተፈጥሮው ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የማይመች፣ ለገዥው ፓርቲ የሚያዳላ እንዲሆን ተደርጎ የተዋቀረ እንደሆነ ይናገራሉ ዋና ፀሐፊው፡፡ ትልልቆቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው የሚባሉት መድረክና የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ባለፈው ሣምንት ጠይቀዋል፡፡ በፓርላማው ውስጥ በንቃት ይሣተፍ የነበረው የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም ቢሆን መንግሥትን አካሂዷል በሚላቸው የሰፉ ችግሮች ሲከስ ተደምጧል፡፡ ሌላ ዙር ምርጫ እንዲካሄድ ከመጠየቅ ግን ተቆጥቧል፡፡
a_amh-horn-drought-moyale-cattle-death-10-11-11-131540858_1462986
https://amharic.voanews.com/a/amh-horn-drought-moyale-cattle-death-10-11-11-131540858/1462986.html
በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በተጨማሪ የዝናብ እጥረት ተባብሷል
በቦረና ዞን ክፉኛ በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የመስከረም አጋማሹ ዝናብ ዘግይቷል
ከአዲስ አበባ 705 ኪሜ ወደ ኢትዮጵያ ኬንያ ድንበር ሞያሌ መንገድ ጸሃይ በርትታለች። ክው ብለው በደረቁት የግራር ዛፎችና ቁጥቋጦዎች ያለከልካይ የሚነፍሰው ንፋስ ደማቅ ብርቱካናማውን አፈር እንዳሻው ይገልጠዋል። ድርቁ አካባቢውን አረንጓዴ ቀለም አይቶ የማያውቅ በረሃ አስመስሎታል። ግራና ቀኝ በቀይ አፈር አጃቢነት ከተነጠፈው አስፋልት ቀለሙ በለቀቀ ጥቁርና ነጭ ቀለም 705 ኪሎሜትር የሚል የኮንክሪት አምድ ቆሟል። ከአዲስ አበባ 705 ኪ.ሜ መሆኑን ከሚያሳየው ምልክት ስር አንዲት ደባራ ላም ወድቃለች። ከወደወገቧ ጥቁር ቡናማ ከወደ እግሮቿ ሳያር የተቆላ ቡና መሰል -- ደባራ ቀለም አላት። መቼ እንደሞተች ባይታወቅም። ስጋዋ በጸሃይ ሃሩር ፈሳሹን አትንኖ ቆዳዋ ከአጽሟ ጋር ተጣብቋል። ሽታ የሚባል ነገር የለም። ቀድሞውንም ለሁለት አመት ያህል የዘለቀው ድርቅና የጸሃዩ ብርታት የሚሞቱትን ከብቶች በቀናት ውስጥ ያደርቃቸዋል። ከብቶቻቸው የሚሞቱባቸው አርብቶ አደሮች ሳር ፍለጋ ከሞት የተረፉትን ለማዳን ስለሚገሰግሱ፤ ቆም ብሎ ቆዳ ለመግፈፍ ጊዜውን አንዳንዴ ደግሞ አቅሙ አይኖራቸውም። 705ኛው ኪሎሜትር በቦረና ዞን የሚታየውን ድርቅና ከፍተኛ የሆነ የእንስሳት ሞት በግልጽ ያሳያል። ከ1.5 ኪሎሜትር እስከ 2 የሚሆን ርቀት ውስጥ 16 የሞቱ የከብት ቅሪቶችን ቆጥረናል። ይሄ እንግዲህ በመንገዱ ዳር ያየንው ብቻ ነው። ውስጣ ውስጡን ያለቀውን፣ ወድቆ የሚታየውን የእንስሳት ቅሪት አድማስ ይቁጠረው። የሚበዛው ነዋሪ ከከብት እርባታ በሚገኙ ተዋጽዖዎች የሚተዳደርበት ቦረና ከ60-75 ከመቶ የሚሆኑ ከብቶች መሞታቸው ይገመታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለው ከሆነ የሚያዝያው ወር የገና ዝናብ ለሁለተኛ ጊዜ ሳይጥል በመቅረቱ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ከብቶች ሞተዋል። “የእንስሳት ሞቱ በከብት ብቻ አልተወሰነም። ግመልም፣ ፍየልም የጋማ ከብቶችም ሞተዋል። ” ይላሉ ሊበን አሬሮ የቦረና ዞን አርብቶ አደር ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ። “በድርቁ ሳቢያ የሞቱትን ከብቶች ጠቅላላ ቁጥር ለማወቅ ጥረት ቢያዝም፤ እስካሁን ይሄን ያህል ለማለት የሚያስችል መረጃ አላሰባሰብንም። የሞቱት ከብቶችን ቁጥር የኢትዮጵያ መንግስት በቁጥር ማስቀመጥ ባይችልም። በአካባቢው ለተረጂነት የተጋለጡ ሰዎችን ቁጥር በአግባቡ ይገልጻል። በአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና በሴፍቲ ኔት ከሚረዱት ሰዎች በተጨማሪ ለእናቶችና ህጻናት፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋዊያን የሚሰጠው እርዳታ ሲጨመር ግማሽ የሚሆነው የቦረና ህዝብ እርዳታ እየተሰጠው ይኖራል። ከ705ኛው ኪሜ ቀድሞ አልፎም እስከ ኬንያ ድንበር እንዲሁ የቀውስ ቀጠና ነው። ሰሜን ኬንያም ቢሆን በዚህ ድርቅ ክፉኛ ተጠቅቷል። በሳምንታት የዘገየው የሃገያ ዝናብ ካልጣለ፤ አካባቢው ወደከፋ የሰብዓዊ እልቂት እንዳያመራ ተሰግቷል።
a_ethiopia-election-re-run_1458682
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-election-re-run/1458682.html
«በአብዛኛው ታዛቢዎቻችን በሌሉበት ተካሄደ፤» ሲሉ፥ የገለፁት የግንቦት 15ቱ ምርጫ እንዲደገም ሁለት ዋነኛ ተቃዋሚ ቡድኖች አስታወቁ።
«ነፃና ገለልተኛ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገርና ታዛቢዎች፤ በተገኙበት ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ እንጠይቃለን፤» - መድረክ
«የምርጫው ሂደትም ሆነ የድምፅ መስጫው ቀን፥ ነፃና ፍትሃዊ ባለመሆናቸው፤ ታዛቢዎቻችን ተደብድበው በመባረራቸው በብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን ውጤት አንቀበልም። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ በተከታታይ በሰጧቸው መግለጫዎች በምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን ውጤት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ይፋ ካደረገና ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም ድሉን ማክበር ከጀመረ በኋላ የመጀመሪያው በሆነው ይፋ የተቃዋሚዎች መግለጫ ሁለቱ ተቃዋሚ ቡድኖች ውጤቱን የማይቀበሉበትን ምክኒያትና አማራጭ ያሉትን በመግለጫቸው ዘርዝረዋል። «የምርጫው ሂደትም ሆነ የድምፅ መስጫው ቀን፥ ነፃና ፍትሃዊ ባለመሆናቸው፤ በመላው አገሪቱ በሚገኙ አብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎችም ታዛቢዎቻችን ተደብድበው በመባረራቸው በብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን ውጤት ላለመቀበል ወስነናል፤» ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በውጭ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ያቆብ ልኬ አማካኝነት አስታውቋል። ይሄንን ውሳኔውን ትላንት ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ለምርጫ ቦርድ ማሳወቁን የገለፀው መኢአድ፥ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫዎችም በተቻለ ፍጥነት በድጋሚ እንዲካሄዱ መጠየቁን አመልክቷል። ኢህአዴግን አሸናፊ ያደረገውንና በቦርዱ ይፋ የሆነውን ውጤት እንደማይቀበል ከመኢአድ በተመሳሳይ ዛሬ ከቀትር በኋላ ያስታወቀው የስምንቱ ተቃዋሚ ቡድኖች ጥምረት መድረክ በበኩሉ፥ ነፃና ገለልተኛ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገርና ታዛቢዎች፤ በተገኙበት ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ጠይቋል። «ከኢህአዴግ ሌላ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ የማይፈልግ ተቃዋሚ ፓርቲ ሊኖር አይችልም፤» ብሎ እንደሚያምን መድረክ በሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አማካኝነት መድረክ ገልጧል።
a_voa-amharic-news-05-22-2020_5442495
https://amharic.voanews.com/a/voa-amharic-news-05-22-2020/5442495.html
ቪኦኤ አማርኛ - የቅዳሜ፤ ግንቦት 22/2012 ዜና
በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ተጋላጭ ከአንድ ሺህ በላይ ሆነ ከቤይሩት ተጨማሪ 323 ሃገራቸው ገቡ የጆርጅ ፍሎይድ መገደል ዓለም አቀፍ ንግግር እየሆነ ነው
ኢትዮጵያ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ስድሣ መብለጡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የኮቪድ 19 ሞት ቁጥር ስምንት መድረሱን በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፊርማ የወጣው የዛሬ መግለጫ ያሳያል። መግለጫው ዛሬ እስከወጣበት ጊዜ በነበሩት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ 5 ሺህ 34 የላብራቶሪ ምርመራዎች ለቫይረሱ መጋለጣቸው የተረጋገጠው ዘጠና አምስት ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች አጠቃላይ ቁጥር ዛሬ 1063 ደርሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮቪድ 19 የዓለም መዛመት ቁጥር ወደ ስድስት ሚሊየን መጠጋቱን ዓለምአቀፉን ሁኔታ በቅርብ እየመዘገበ ያለው የጆንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል ዛሬ አስታውቋል። በማዕከሉ መረጃ መሠረት በዓለም ዙሪያ 365 ሺህ 800 ሰው በኮቪድ 19 ምክንያት ሞቷል። ሠንጠረዡን እየመራች ባለችው ዩናይትድ ስቴትስ የተጋላጩ ቁጥር አንድ ሚሊየን 750 ሺህ፤ የሞቱ ቁጥርም አንድ መቶ ሁለት ሺህ 900 መድረሱን ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል። ከ135 ሺህ በላይ ተጋላጮች እንዳሉባት ዛሬ ጠዋት በተነገረው አፍሪካ ከሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ በላይ ሰው በኮቪድ 19 ምክንያት መሞቱ ተገልጿል። ቤይሩት ውስጥ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ተመዝግበው ሲጠባበቁ የነበሩ ተጨማሪ 323 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ተመልሰዋል። ኢትዮጵያዊያኑ የተመለሱት ለመጓጓዣና ለተለያዩ ወጭዎች የከፈሉት 550 ዶላር ተመልሶላቸው መሆኑን በሊባኖስ የኢትዮጵያ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል አስታውቋል። ከሁለት ቀናት በፊት እንዲመለሱ የተደረገውን ጨምሮ አጠቃላይ ቁጥር 658 መድረሱን የቆንስላ ጄነራል ፅህፈት ቤቱ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባወጣው ዝርዝር መግለጫ ላይ አመልክቷል። ኢትዮጵያዊያኑ ከቤይሩት ከመነሳታቸው በፊት አስፈላጊው የኮቪድ 19 ፍተሻ እንደተደረገላቸውና አዲስ አበባ ሲደርሱም ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚቆዩባቸው ሁኔታዎች የተመቻቹላቸው መሆኑን፤ የአሥራ አራት ቀናት የቆይታ ጊዜያቸውን ከጨረሱ በኋላም እስከመኖሪያ ቀዬዎቻቸው የሚደርሱበትና ከየማኅበረሰባቸው ጋር የሚቀላቀሉባቸው ዝግጅቶች መደረጋቸውንም ፅህፈት ቤቱ ገልጿል። በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ምዕራብ ግዛቷ ሚኔሶታ ከተማ ሜኔአፖሊስ ውስጥ በነጭ ፖሊሶች የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ጊዳይ ባስነሳው ቁጣ ተቃዋሚዎቹ በከተማዪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ተቋማት ላይ እሳት አንስተዋል። በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ባልታየ ሁኔታ አፍሪካ ዋና ከተሞች ውስጥ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች የበረታ ይዘት ያላቸውን መግለጫዎች እያወጡ ናቸው። አሜሪካ ምድር ላይ የተፈፀመው አድራጎት በመላ አፍሪካ ቀጣና ቅሬታን ማጫሩም ተዘግቧል። የኤምባሲዎቹ መግለጫዎች እየወጡ ያሉት የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር መሳ ፋኪ ማሃማት በጆርጅ ፍሎይድ ላይ የተፈፀመውን አድራጎት በዩናይትድ ስቴትስ ጥቁር ዜጎች ላይ እየቀጠለ ያለ የመድልዎ አድራጎት ሲሉ ውግዘት ካሰሙ በኋላ ነው። በኮንጎ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃመር ባወጡት መልዕክት የጆርጅ ፍሎይድ ሜኔአፖሊስ ውስጥ በአሳዛኝ ሁኔታ መገደል የረበሻቸው መሆኑን ጠቁመው የሃገራቸው የፍትሕ ሚኒስቴር ለጉዳዩ ከፍተኛ ቅድሚያ ሰጥቶ ወንጀል ምርመራ እያካሄደበት መሆኑን ገልፀዋል። ኬንያ፣ ዩጋንዳና ታንዛኒያ ያሉት የአሜሪካ ኤምባሲዎችም የየራሳቸውን መልዕክቶች አውጥተዋል። እንድ ነጭ ፖሊስ አንገቱ ላይ በጉልበቱ ተጭኖት በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ጥቁሩ ጆርጅ ፍሎይድ መሞት በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ተቃውሞዎችን እያቀጣጠለ መሆኑ ተዘግቧል። ሰልፈኞቹ ሚኔአፖሊስ ውስጥ የንግድ ተቋማትን፣ ተሽከርካሪዎችንና ፖሊስ ጣቢያ በእሳት አጋይተዋል። በሜኔአፖሊስና በአጎራባቿ ሴንት ፖል ከተሞች 500 ብሄራዊ ዘብ የተሠማራ ሲሆን ነገ ቁጥሩ ወደ 1700 ከፍ እንደሚል ተገልጿል።
a_article----112273904_1460523
https://amharic.voanews.com/a/article----112273904/1460523.html
ሁለት ጥበበኛ እጆች
አብዱረዛቅ ረሽድ ወይንም በመድርክ ስሙ አብዲ ዘ-ጀግለር ታዋቂ የሰርከስ ትርዒት ባለሙያ ነው። ስለትግሉና ስኬቱ ከመስታዎት ዝግጅት ጋር ተወያይቷል።
ተወልዶ ያደገው ናዝሬት ከተማ ነው። አብዱረዛቅ ረሽድ አደም ገና በስምንት ዓመቱ የሰርከስ ልምምድ ለማድረግ ከትምህርት ቤት መልስ ከበጎ ፈቃድ አሰልጣኙ ሙያ ሊቀስም ሲሄድ ቤተሰቦቹ ደስተኞች አልነበሩም። “ይሄንን ቧልትና ዝላይ ትተህ በትምህርትህ በርታ” ነበር የወላጆቹ ምክር። በየቀኑ ወሳኝ ክህሎቶቹን እየተማረ የነበረው አብዲ ግን ተደብቆም ቢሆን ከልምምድ አይቀርም ነበር። “ቤተሰቦቼ ጊዜየን የከንቱ የማሳልፍ ይመስላቸው ነበር” ይላል አብዲ። የኋላ ኋላ ቤተሰቦቹን ከትርዒቶቹ አንዱን እንዲመለከቱለት ጋብዟቸው ስራውን ካዩ በኋላ ድጋፋቸውን ሰጡት። ዛሬ ይሄ ታዳጊ ወጣት የ27 ዓመት ሰው ነው። በስራውም ቢሆን በልጅነቱ ያደረበትን የሰርከስ ፍቅር ወደ ፕሮፌሽናል ሙያ ቀይሮት ታዋቂ ሆኗል። ሲጀምር ሰርከስ ናዝሬት ፥ ከዚያ ሰርከስ ኢትዮጲያ ፥ ዛሬ ደግሞ በዓለም ላይ የታወቀ ባውንሲንግ ጀግለር ወይም በርካታ ኩዋሶችን በማንጠር በቅንብር እየቀለበ በታላላቅ የዝናኛ ማዕከላት እና በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ከተሞች ስራውን ያቀርባል። ለሰርከስ ትርኢቱ ወዲህ ወደዩናይትድ ስቴትስ መጥቶ በዋሽግተን ዲሲ እና በተለያዩ በርካታ ከተሞች እየተዘዋወረ ነው። በታወቀው በኬኔዲ ሴንተር ዝግጅቱን ከአውሮፓ ከተሰባሰብ የሰርከስ ቡድን ጋር አቅርቧል በሌሎችም ከተሞች እንዲሁ እየተዘዋወረ ዝግጅቶቹን ያቀርባል። ከመስታዎት ዝግጅት ጋር ያደረገውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።
a_amh-ethiopians-eritreans-libya-02-25-11-116949553_1458016
https://amharic.voanews.com/a/amh-ethiopians-eritreans-libya-02-25-11-116949553/1458016.html
ሁለት ኢትዮጵያዊያን በሊቢያ መሞታቸውንና በርካታዎች መሰወራቸውን ስደተኞቹ አስታወቁ
በጸረ-መንግስት ተቃውሞ በታወከችው ሊቢያ አፍሪካዊያን ስደተኞች ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰባቸው ይገኛል። በተለይ ከመንግስቱ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ከተሞች ጥቃቱ አይሏል።
የጋዳፊ ቅጥረኞች ናችሁ በሚል ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ጥቃት እየደረሰባቸው ነው በጸረ-መንግስት ተቃውሞዎች የተናወጠችውን ሊቢያ ለቀው ለመውጣት በርካታ ሽህ የውጭ አገር ስደተኞች በአውሮፕላን፤ በመርከብና በእግር እየተመሙ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በከባድ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ግጭት መሀል የተያዙት በሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች የሞማር ጋዳፊ ቅጥረኛ “ጥቁር የውጭ አገር ወታደሮችሁ” ናቸው በሚል ለድብደባ፣ ዘረፋና ግድያ መጋለጣቸውን ይናገራሉ። በጸረ-መንግስት ተቃውሞ በታወከችው ሊቢያ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ከቤታቸው አይወጡም። ወጥቶ ለቤተሰብ፣ በተለይ ለልጆች የሚቀመስ እህል ውሃ መግዛት እንዳልቻሉ ይናገራሉ። እነዚህ ስደተኞች በአንድ በኩል በሁከት በሌላ በኩል የጋዳፊ ቅጥረኛ የውጭ አገር ተዋጊዎች ላይ ባለው ጥላቻ ከባድ ችግር ላይ ወድቀዋል። “ጥቁር መንገድ ላይ ከወጣ መግደል ነው” ይላል በሊቢያ ለ9አመት የኖረው ኢትዮጵያዊ ሳሚ። ወደ ሱቅ ሄዶ ምግብና ውሃ መግዛት በህይወት ዋጋ የሚያስከፍልበት ደረጃ ደርሰናል ይላል። “ለቤተሰባቸው ምግብ ሊገዙ የወጡ ሶስት ኢትዮጵያዊያን አንዱ የአሩሲ ልጅ ነው። እግሩን በጥይት መትተው ይዘውት ሄደዋል” ይላል ሳሚ። በመንግስት ቁጥጥር ስር በማይገኙ ከተሞች። ማለት የጸረ-ጋዳፊ ተቃዋሚዎች ነጻ ባወጧቸው ከተሞች በጥቁር አፍሪካዊያን ላይ ያለው ቁጣ በጣም ያየለ ነው። ሳሚ ሁኔታው ከቆየ ጥላቻ የመነጨ ቢሆንም፤ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ ፓስፖርት ያላቸው ሰዎች በጋዳፊ ቅጥረኛ ተዋጊነት ተጠርጥረው ከተያዙ ወዲህ ቁጣው ወደ ጥቃት ተለውጧል። በጠቅላላው ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ እነዚህ ስደተኞች ከባድ የሆነ ችግርና ጥቃት ይደርስባቸዋል በሚል ተሰግቷል። የሊቢያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች መስሪያቤትን ከሀገር እንዲወጣና ስራውን እንዲያቆም ማድረጉ ይታወሳል። በዚህ እርምጃ ወደ 12ሽህ የሚሆኑ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ሌሎች ስደተኞች አስተባባሪ አጥተው ቆይተዋል። ከነዚህ መከከል በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ይገኙበታል። UNHCR እና ሌሎች አለማቀፍ የስደተኛ ተቆርቛሪ ድርጅቶች በሌሉበት ሁኔታ፤ አገሮች ዜጎቻቸውን በአውሮፕላን በመርከብና በመኪና እያስወጡ ባለበት ወቅት፤ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን፣ ሱዳናዊያን እና ሌሎችም በከባድ ችግር ላይ ናቸው። አንድ በጣሊያን መሰረቱን ያደረገ አጄንሲያ አበሻ የተባለ ማህበር፤ የአውሮፓ ህብረት በተለይ ደግሞ የጣሊያን መንግስት ዜጎቻቸውን ከሊቢያ ሲያወጡ፤ ኢትዮጵያዊያኑንና ኤርትራዊያኑን አብሮ ከሀገር እንዲያወጣ በመማጸን ላይ ነው። “ከአውሮፓዊያን ዜጎች ጋር አብሮ የመውጣት እድል እንዲሰጣቸው ጠይቀናል” የሚሉት አባ ሙሴ ዘርዓይ አጀንሲያ አበሻ የተባለው ማህበር መስራች ናቸው። የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በትሪፖሊ ለሚገኘው ኢምባሲ ሁኔታውን እንዲያሳውቅና የስደተኞቹ ደህንነት እንዲጠበቅ ያቀረቡት ጥያቄ፤ በጣሊያን መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አላገኘም። የስደተኞቹ ቁጥር በርካታ በመሆኑ ከሊቢያ ማውጣቱ ከባድ እንደሆነ መልስ ተሰጥቷቸዋል። አባ ሙሴ ትግላቸውን አላቆሙም። ህጻናት ልጆች ላላቸው ቅድሚያ እንዲሰጥ የተረፉትን ደግሞ ወደ ጎረቤት አገሮች እንዲዛወሩ እየወተወቱ ነው። አባ ሙሴ በዚህ ትግላቸው ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።
a_ethiojazz-music-young-ethiopia-_3187096
https://amharic.voanews.com/a/ethiojazz-music-young-ethiopia-/3187096.html
አዳጊ ወጣት የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋቾች-በካሊፎርኒያ
“Young Ethio-jazz Band” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ተወልደው ያደጉት በዩናይትድ ስቴትስ ኦክላንድ ካሊፎርኒያ ነው። እድሜያቸው ከዐስራ ሦስት እስከ ዐስራ ስምንት የሆኑት አነዚህ ወጣቶች በጋራ ሙዚቃን መጫወት የጀመሩት የዛሬ አራት ዓመት ነው።"ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ" ይላል ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ።
ዋሽንግተን ዲሲ — ኢትዮጵያዊ ዜማዎችን በተለያዩ መድረኮች በመጫወት ለውጭው አድማጭ ኢትዮጵያዊነታቸውና ባህላቸውን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ። በተለይም የኢትዮ-ጃዝ የሙዚቃ ስልት የሆነውን የዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ ሙዚቃዎችን በመድረክ በመጫወት ይታወቃሉ። 'Young Etho-jazz band' ያንግ ኢትዮ-ጃዝ ባንድ የተመሰረተው በአዳጊዎቹ ወላጆች የጠነከረ ጓደኝነትና ኢትዮጵያዊነትን ለልጆቻቸው ለማስተላለፍ ካላቸው ፍላጎት ነበር። ከሙዚቃ ባንድ አባላቱ የአንዱ ልጅ አባት የሆነው አቶ ሲራክ ተግባሩ በተለየ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለወጣቶቹ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል። ​ የሳክስፎን የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች የሆነው አቶ ሲራክ ልጆቹን በማሰባሰብና በመኖሪያ ቤቱ የሙዚቃ ልምምድ እንዲያደርጉበት ከማዘጋጀት ጀምሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ፣ አጠቃላይ የሙዚቃን ህግና የሙዚቃ መሳሪያውን በማስተማር ላይ ይገኛል። በቅርቡም ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴት አዳጊ ወጣቶችን በማሰባሰብ የኢትዮጵያን ሙዚቃ የማስተማር እቅድ አለው። “መሆን የምትመኙትን ለመሆን ጣሩ፤ ራሳችሁን ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ። ” ዮሃንስ ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ የተናገረው ነው። መስታወት አራጋው የሙዚቃ ባንድ አባላቱን አነጋግራቸዋለች። ሙሉ ዝግጅቱን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ።
a_amh-unsc-eritrea-react-12-6-11-135127608_1458866
https://amharic.voanews.com/a/amh-unsc-eritrea-react-12-6-11-135127608/1458866.html
ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ተጨማሪ ማእቀብ የጣለብኝ ለዩናይትድ ስቴይትስ ስለማላጎበድድ ነው አለች
ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ የምትፈጥረውን አለመረጋጋት ለመግታት በሚል ያለፈው ውሳኔ 2023 በኤርትራ የማእድን ኢንዱስትሪና በውጭ አገር የሚኖሩ ኤርትራዊያን የሚከፍሉት ቀረጥ ለአፍራሽ ተግባር እንዳይውል ያቅባል።
ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቪዛ ማግኘታቸውን ዩናይትድ ስቴይትስ ገለጸች በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማእቀብ ከመጣሉ በፊት የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ህብረት IGAD መሪዎችና ተወካዮቻቸው በአዲስ አበባ በቪዲዮ መልእክት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ማእቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል። የጸጥታው ምክር ቤት አባላት አንዲያስቡበትና ድምጻቸውን እንዲሰጡበት የረፍት ጊዜ ከወሰደ በኋላ በናይጀሪያና ጋቦን አርቃቂነት የቀረበው ስምምነት 2023 በ13 የድጋፍ ድምጽና በቻይናና ራሻ ተአቅቦ ጸድቋል። በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴይትስ አምባሳደር ሱዛን ራይስ ይሄ ስምምነት ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ የምትፈጥረውን አለመረጋጋትና ለአሸባሪዎች የምትሰጠውን ድጋፍ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደሚያወግዝ ያሰምርበታል ብለዋል። “ከዚህ በፊት የነበረውን ስምምነት 1907 ያጠናክራል፥ እናም በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማእቀቦችን ይጥላል። ከዚያም በተጨማሪ ከማእድን ዘርፍና በውጭ አገር ከሚኖሩ ኤርትራዊያን የሚሰበሰበውን ቀረጥ ላልተፈለገ ለእኩይ ተግባር እንዳታውል ያቅባል” ብለዋር አምባሳደር ራይስ። ጀርመንም በዚሁ ውሳኔ ላይ የኤርትራ መንግስት የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ህብረት IGAD ለመግባት ያቀረበው ጥያቄ ተፈጻሚ እንዲሆን ጠይቃ፤ ኤርትራ በበኩሏ ከጎረቤቶቿ ጋር እንድትስማማ ገልጻለች። ውሳኔ 2023 ለኤርትራ ይፋ የፖለቲካ መልእክት የያዘ ነው ያሉት በተ.መ.ድ የጀርመን ቋሚ ልዑክ ፔትር ዊቲግ ኤርትራ “ጎረቤቶቿ መረጋጋት እንዳይኖራቸው የምታደረገውን እንቅስቃሴ ትታ፤ በትብብር መኖር አለባት” ብለዋል። ቻይናና ራሻ በውሳኔው እጃችን የለበትም ሲሉ በውሃ ታጥበው የተዓቅቦ ድምጽ ሰጥተዋል። የጸጥታው ምክር ቤት የወቅቱ ፕሬዝደንት የራሻ ፌደሬሽን አምባሳደር ቭ መንግስታቸው በኢጋድ አባሎች የቀረቡት አቤቱታዎች እንደሚያሳስቡት ገልጸው ቪታሊ ቸርኪን በአንዳንድ ለውሳኔ የቀረቡ ጉዳዮች ላይ ግን በቂ ማስረጃ አልነበረም፤ በተለይ ኤርትራ በአዲስ አበባ የአፍሪክ ህብረት ስብሰባ ላይ ፈንጅ ለማፈንዳት አሲራለች የተባለው የተረጋገጠ መረጃ የለውም ብለዋል። “ምርመራው እንዴት እንደተከናወነ አናውቅም፣ እንዴት እንድተጠናቀቀና በዚህ ጉዳይ ላይ የፍርድ ሂደት ስለመኖሩ የምናውቀው ነገር የለም። ስለዚህ እንዲህ ያለ ከባድ ውንጀላ ለማካተት የተረጋገጠ ማስረጃ ያስፈልግ ነበር። አንድ የሁኔታ አጣሪ ቡድን ይሄን አረጋግጧል ተብሎ ያለበቂ ማስረጃ ማቅረብ ተገቢ አመለካከት አይደልም። በዚያ ላይ የኛ ባለሙያዎች የሁኔታ አጣሪውን ብቃት ሙሉ ድጋፍ አልሰጡትም። አምባሳደር ቼርክን አክለውም ምንም እንኳ ራሻ በውሳኔው ገለልተኛ ብትሆንም፤ ለኤርትራ የተሰጠው ጊዜና ውሳኔው የተላለፈበት መንገድ፤ ህጋዊ ነው አሰራሩም ፍትሃዊ ነው ብለዋል። “ኤርትራ በስልክም ቢሆን አቋሟን እንድታሳውቅ እድሉ ተሰጥቷት ነበር። ይህንን እድል ሊወስዱ በቻሉ ነበር። የአካባቢው መሪዎች በቪዲዮ መልእክታቸውን አሳልፈዋል። ወይንም ደግሞ እዚህ ባሉት ቋሚ መልእክተኛቸው በኩል ተቃውሟቸውን ሊያሰሙ ይችሉ ነበር። እነርሱ ሃሳባቸውን ለመናገር አልፈለጉም፤ ውሳኔው የራሳቸው ነው” ብልዋል ቸርኪን። የጸጥታው ምክር ቤት ኤርትራ አቋሟን እንድታስረዳ በማሰብ ነበር ለባለፈው ሳምንት ታቅዶ የነበረውን የድምጽ መስጫ ቀነ ቀጠሮ ለሰኞ ያዛወረው። ኤርትራም አስቀድማ በፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኩል መልእክት ለማሳለፍ ጠይቃ ነበር። የመንግስቱ ቃል አቀባይ አቶ አሊ አብዱ እንደሚሉት የኤርትራ ባለስልጣንት አስመራ በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ቪዛ ማግኘት አልቻሉም። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሱዛን ራይስ አገራቸው ለልዑካኑ በ24 ሰዓት ውስጥ ቪዛ መስጠቷል ይናገራሉ። “አርብለት አስመራ በሚገኘው ኢምባሲያችን ለ13 ሰዎች ቪዛ ጠየቁን። አስሩን ቪዛዎች ወዲያውኑ ሰጠናቸው። የተቀሩትን 3 ቪዛዎች በማግስቱ ከአራስት ሰዓት በፊት ሰጠናቸው። ሁሉም ቪዛዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ተሰጥተዋል። የፕሬዝደንት ኢሳያስ ቪዛ ወዲያውኑ በሰዓታት ውስጥ ነው የተሰጠው። የኤርትራ መንግስት እነዚህን ሁሉ ከእውነት የራቁ ናቸው ይላል።
a_eritrean-sanctions-united-nations-07-21-10-98943239_1460405
https://amharic.voanews.com/a/eritrean-sanctions-united-nations-07-21-10-98943239/1460405.html
የኤርትራ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጣለባትን ማእቀብ እንዲያነሳ ጠየቀች
ኤርትራ ይህንን ጥያቄዋን ያቀረበችው ከጅቡቲ ጋር ያላትን የድንበር ግጭት በውይይት ለመፍታት የጀመረችውን ጥረት ካወደሰ በኋላ ነው።
አንድ የዩናይትድ ስቴይትስ የረጅም ጊዜ የህግ አውጭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራን አሸባሪዎችን ከሚረዱ አገሮች ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንድትገባ ጠይቀዋል ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን-ኪሙን ቢሮ የወጣው ሪፖርት ኤርትራ ከጎረቤቶቿና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ እየተነጋገረች መሆኑን ጠቁሟል። በተለይ ኤርትራ ከጅቡቲ ጋር ያላትን የድንበር ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት መወሰኗ ይበል የሚያሰኝ ጅምር መሆኑን አትቷል። የጸጥታው ምክር ቤት በኒው ዮርክ ሲሰበሰብ በጉዳዩ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሀፊ ሊን ፓስኮ ኤርትራ ወታደሮቿን ከአወዛጋቢው ድንበር ማስወጣቷንና አደራዳሪዋ ቃታር ወታደራዊ ታዛቢዎችን በቦታው ማስፈሯን አረጋግጠዋል። “ኤርትራና ጅቡቲ የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት በቃታር መንግስት አደራዳሪነት የወሰዷቸውን ወሳኝ እርምጃዎች እናደንቃለን። ዋና ጸሀፊው የተባበሩት መንግስታት እርዳታ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፤ ሊረዳ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፣” በማለት ሊን ፓስኮ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር አርአያ ደስታ ከጅቡቲ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ጉልህ እመርታ ነው ብለውታል። ነገር ግን የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለው ማእቀብ ፍትሃዊ አይደለም በማለት አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “ኤርትራ ለሰላምና ደህንነት ከፍተኛ አትኩሮት ትሰጣለች። በዚህ ምክንያት በአካባቢዋ በሚደረጉ ፍሬአማ ውይይቶች ትርጉም ባለው መልኩ ተሳትፎ እንዳታደርግ መታገድ የለባትም። ዘለቄታ ያለው ሰላምን በሚያመጡ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የኤርትራ ተሳትፎ መረጋገጥ አለበት፣” ብለዋል አምባሳደር አርአያ ደስታ። “ከጅቡቲ ጋር በቃታር መንግስት ሸምጋይነት ያገኘናቸው የዲፕሎማሲ ፍሬዎችን ማጤን ያስፈልጋል። በሶማሊያ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን የምናደርገውን ጥረትም ተመልክቶ የጸጥታው ምክር ቤት የጣለብንን መአቀብ እንዲያነሳ እንጠይቃለን። በአስተርጓሚ የተናገሩት የጅቡቲ ተወካይ ካድራ አህመድ ሃሰን በኤርትራ ላይ የተጣለው ማእቀብ የሰላም ውይይት እንዲጀመር በር ከፍቷል ብለዋል። “የተያዘው ጥረት አበረታች ቢሆንም፤ ረጅም መንገድ ይጠብቀናል። በሚቀጥሉት ወራት በሁለታችንም በኩል ቀጣይነት ያላቸው ስራዎችን መስራት ይጠበቃል። የተወያየንባቸው ነጥቦች በእጅጉ ወሳኝ ናቸው፤ የምርኮኞች ጉዳይ፣ የጠፉ ሰዎች ጉዳይና ድንበሩን በካርታ አስምሮ በምድር በችካል እስከመከለል ይሄዳል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን ጊ-ሙን ቢሮ ያወጣው ሪፖርት ኤርትራ የጀመረቻቸውን ጥረቶች አበረታች ናቸው ቢልም፤ የጸጥታው ምክር ቤት ማእቀቡን ሲጥል ያስቀመጣቸውን ሁኔታዎች ለማሟላት ብዙ መስራት እንደሚጠበቅባት ጠቁሟል። ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤርትራ መልካም ጅምሮቿን የሚያበረታቱ ምላሽ ብታገኝም ከዩናይትድ ስቴይትስ በኩል ግኝ ተጨማሪ ጫና እንዲደረግ የህግ አውጭዎች እየወተወቱ ነው። በዩናይትድ ስቴይትስ የህግ አውጭ ክፍል ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ኮንግረስማን ኤድ ሮይስ ኤርትራ አሸባሪዎችን ከሚረዱ አገሮች ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንድትገባ ጠይቀዋል። ኮንግረስ ማን ሮይስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በጻፉት ደብዳቤ በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ ሀምሌ 4 ቀን የደረሰውን ፍንዳታ ያቀነባበሩ የአል-ቃይዳ አጋሮች ጋር ይሰራል ያሉት የኤርትራ መንግስት ላይ ጫና እንዲደረግ ጠይቀዋል። በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አል-ሸባብ የተባለ የአሸባሪዎች አንጃ በዩጋንዳ ለ76 ሰዎች ህይወት መጥፋት መንስኤ የሆኑትን ጥቃቶች ማከናወኑን አስታውቋል። ድርጊቱም የተከናወነው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል አብዛሀኛው ወታደሮች ከዩጋንዳ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ነው። ታዲያ በኮንግረሱ የሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የጸረ-ሽብርተኝነት፣ የጸረ-ኑክሌር ግንባታና የንግድ ንኡስ ኮሚቴ ተሰሚነት ያላቸው ኮንግረስማን ሮይስ በጻፉት ደብዳቤ “ኤርትራ ለአልሸባብ የምትሰጠው ድጋፍ በአግባቡ በመረጃ የተረጋገጠ ነው” ሲሉ አልሸባብ በአሜሪካ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። ኤርትራ አሸባሪዎችን ከሚደግፉት አገሮች መካከል ከተፈረጀች ከኩባ፣ ኢራን፣ ሱዳንና ሶሪያ ጋር ትቀላቀላለች። በእነዚህ አገሮች የተጣሉ የዲፕሎማቲክ፣ ኢኮኖሚና የጦር መሳሪያ ማእቀቦች በኤርትራ ላይ ሊጫኑባት ይችላሉ። ኤርትራ ለሶማሊያ ሸምቅ ተዋጊዎች እርዳታ ትሰጥ እንደነበረ መረጃዎች አሉ። ነገር ግን በናይኖቢ የInternational Crisis Group ስራአስኪያጅ E.J. Hogendoorn ኤርትራ የኢትዮጵያን ወታደሮች ይዋጉ ለነበሩ ሸማቂዎች እርዳታ መስጠቷ ቢታወቅም፤ በቀጥታ ለአሸባሪዎቹ የአል-ሸባብ ተዋጊዎች የምታደርገው እርዳታ የለም ይላሉ። “በዚህ ጊዜ ኤርትራ አል-ሸባብን እንደምትረዳ የሚያሳይ ትንሽ እንኳን ማረጋገጫ አልተገኘም። በሶማሊያ የነበረውን የኢትዮጵያን ጦር በእጅ አዙር የሚወጉ ሀይሎችን ታስታጥቅ እንደነበረ መረጃ አለ። ያሉን መረጃዎች የሚጠቁሙት ኤርትራ ሂዝቡል-ኢስላምን እንጂ አል-ሸባብን አትደግፍም። የሂዝቡል ኢስላም እንቅስቃሴዎች በእርግጥ አሳሳቢ ናቸው። ነገር ግን ሂዝቡል ኢስላም በቀጥታ በጎረቤት አገሮች ላይ የሽብር ጥቃቶችን ማቀነባበሩን የሚያሳዩ መረጃዎች የሉም። ሂዝቡል ኢስላም ከአል-ሸባብ ጋር ግንባር ፈጥሮ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለውን የሶማሊያ መንግስት ይወጋል። ሁለቱ ቡድኖች በሶማሊያ እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ይንቀሳቀሱ እንጂ አብዛሃኛውን የሶማሊያ አካባቢዎች የሚያስተዳደረው አል-ሸባብ ነው። አልሸባብ በዩናይትድ ስቴይትስ ጥቅሞች ላይ ከዚህ በፊት ይዝት እደነበር የገለጹት በናይኖቢ የInternational Crisis Group ስራአስኪያጅ E.J. Hogendoorn እሳካሁን ድርጅቱ ከዩናይትስ ስቴይትስ ጥቅሞች ይልቅ የምስራቅ አፍሪካ አገሮችን ሰላምና ጸጥታን በማወክ ረገድ አፍራሽ ሚና መጫወቱን ይገልጻሉ።
a_rockwell-exhibit-contest10-13-10-104895464_1460770
https://amharic.voanews.com/a/rockwell-exhibit-contest10-13-10-104895464/1460770.html
የአሜሪካዊያን ኑሮ በየኖርማን ሮክዌል ስእሎች
በእርሳስና በዘይት በሚስላቸው እውነት መሰል ስእሎች በዋሽንግተን ዲሲ በመታየት ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ የጥበብ ውድድር ከፍቷል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናትድ ስቴይትስ ኢምባሲ በሚቀጥለው አመት የሚከበረውን የፕሬዝደንት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት “የአራቱ ነጻነቶች” ንግግር አስመልክቶ የጥበብ ውድድር አዘጋጅቷል። የፕሬዝደንቱ ንግግር የመሰጠው አሜሪካዊ ሰአሊ ኖርማን ሮክዌል በ1935 ዓ.ም “የአሜሪካ ኑሮ” በሚል አራት የስእል ራብአይ ለትእይንት አብቅቷል። እነዚህ ታዋቂ ስእሎች በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ እየታዩ ይገኛሉ። በዋሽንግተን ዲሲ እምብርት የሚገኘው የስሚትሶኒያን ማእከል የታዋቂውን አሜሪካዊ ሰአሊ ኖርማን ሮክዌል ስራዎች ለትእይንት አቅርቧል። “የአሜሪካ ኑሮ” በሚል የተሳሉት አራቱ ስእሎች በፕሬዝደንቱ “የአራቱ ነጻነቶች” ንግግር የተቃኙ ናቸው። የሃይማኖት ነጻነት፣ የመፈልግ ነጻነት፣ ከፍራቻ ነጻ መሆንና የመናገር ነጻነት ናቸው አራቱ ነጻነቶች። አንደኛው ስእል በህዝብ መካከል አንድ ሰው ተነስቶ ሲናገር ያሳያል። ሰዎች ተሰባስበው ሲጸልዩ፣ ቤተሰቦች በምግብ በተሞላ የምግብ ገበታ ላይ ተቀምጠውና ባልና ሚስት ልጆቻቸውን ሲያስተኙ የሚያሳዩ ናቸው ስእሎቹ። አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ የፕሬዝደንት ሩዝቬልት ንግግር የተደረገበትን 70ኛ አመት በሚቀጥለው አመት መከበሩን አስመልክቶ ነው ይሄንን የስእል ውድድር የሚያካሂደው። በኤግዚቢሽኑ ከቀረቡት የኖርማን ሮክዌል ስራዎች በርካታዎቹ በአሜሪካዊው ፊልም ሰሪ ጆርጅ ሉካስ ባለቤትነት ያሉ ናቸው። “ስለእውነተኛ በየለቱ የምናያቸው ሰዎች ነው የሚያወራው በፍሬም ውስጥ የሚያሳየን” ይላላ ጆርጅ ሉካስ “ይሄንን ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ታዋቂው የፊልም ሰሪ ስቲቨን ስፒልበርግም የኖርማን ሮክዌል አድናቂ ነው። ይህወትን በሲኒማ እንደምናሳየው ሮክዌል በእርሳስ በሚሞነጫጭራቸውና በዘይት ቀለም በሚስላቸው ስራዎቹ ኑሮን ቅልብጭ አድርጎ ያሳያል ይላል። በተለይ አሜሪካዊያኑን ኑሮ። ፕሬዝደንት ሩዝቬልትና ሰአሊው ኖርማን ሮክዌል ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ነበራቸው። አጼ ሃይለ-ስላሴ በ1935ዓም ለፕሬዝደንት ሩዝቬልት አሁን በሽሮሜዳ የሚገኘውን የአሜሪካ ኢምባሲ እንዲሰራ መሬቱን ሰጥተዋል። ሰአሊው ሞርማን ሮክዌል ወደ ኢትዮጵያ በ1945ዓም ተጉዞ ነበር። በዚያን ጊዜ በሰላም ጓድነት ይሰሩ የነበሩ አሜሪካዊያንን ስራ በቡርሹ ለማስቀረት ነበር ሮክዌል ወደ ኢትዮጵያ ያቀናው። በደሴ ከተማ አቅራቢያ አንድ አሜሪካዊ የሰላም ጓድ የቤተሰቡ አካል ሆኖ በሚኖርበት መንደር እርሻ ከሚያርስ ኢትዮጵያዊ ገበሬ ጋር ሆኖ የሳለው ስእል ከፍተኛ አድናቆት የተቸረው ስራው ነው። ወደ ኋላ ስእሉ በዩናይትድ ስቴይትስ የፖስታ ድርጅት ቴምብር ሆኖ ወጥቷል። ያሜሪካ ኢምባሲ ለዚህ ውድድር የ25ሽህ ብር ሽልማት አዘጋጅቷል። የማመልከቻ ቀኑ የሚያልፈው በአውሮፓዊያኑ አመት 2010 የመጨረሻ ቀን ዲሴምበር 31 ቀን ነው።
a_amh-ak-us-midterm-elections-global-implications-analysis-106476383_1458441
https://amharic.voanews.com/a/amh-ak-us-midterm-elections-global-implications-analysis-106476383/1458441.html
የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤቶች ምርጫና ዓለም አቀፍ አንድምታው
ሪፐብሊካኖች ምርጫውን አሸንፈው ሁለቱንም ምክር ቤቶች ወይም አንዱን ብቻ እንኳን ከቆጣጠሩ፥ የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች አስመልክቶ በርከት ያሉ ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ።
በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ማክሰኞ ጥቅምት 23 የሚካሄዱት Midterm Elections በመባል የሚታወቁት የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በአሁኑ ወቅት አብላጫውን የሁለቱን ምክር ቤቶች የኅግ አውጪውንና የእንደራሴዎች ምክር ቤቶች፤ መቀመጫዎች ለያዘው የፕሬዝዳንት ኦባማ የዲሞክራቶች ፓርቲ ፈተና ይደቅናል፤ ተብሎ ተገምቷል። የሪፐብሊካኑ ፓርቲ የብልጫውን ድምፅ ያገኝ ይሆናል፤ የሚል ሠፊ ግምት በተያዘባቸው በእነኚህ የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በርካታ መቀመጫዎችን ያጡ ይሆናል የተባሉት ዲሞክራቶች፥ ከተቀናቃኛቸው በሚገጥማቸው ፈተና፥ ከዲሞክራቱ ፓርቲ የሆኑት ፕሬዝዳንት ኦባማ በቀጣዩ የሁለት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው ለማሳካት ያቀዷቸው ውጥኖች «ይደናቀፋሉ፤» የሚል ግምት አሳድሯል። እንደ ቅድመ ምርጫ ትንበያዎቹ ሪፐብሊካን የሁለቱንም ምክር ቤቶች አብላጫ መቀመጫዎች ከያዙ፥ የተባሉት ለውጦች፥ በአገር ውስጥ ጉዳዮች ብቻ ሳይወሰኑ፥ የዩናይትድ ስቴትስን የውጭ ፖሊሲ ጨምሮ፥ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምታጨወታቸው «ዋና ዋና የሚሰኙ ሚናዎቿም ይንፀባረቃሉ፤» እየተባለ ነው። በርዕሱ ዙሪያ ትንታኔ የሚሰጡን የፖለቲካ ሳይንቲስት ጋብዘናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የህግ ባለ ሞያ ናቸው።
a_osaman-mohammed092910-104029894_1460868
https://amharic.voanews.com/a/osaman-mohammed092910-104029894/1460868.html
የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን መሀመድ ሳለህ የኤርትራ መሬት በኢትዮጵያ በህገ ወጥ ሲያዝ ባለማስለቀቅ የመንግስታቱን ድርጅት ወነጀሉ
ዉዝግቡ የሚመለከታቸዉ አካላት ሃላፊነት ካልሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማደራደር ስልጣን የለዉም ብለዋል አቶ ስዩም መስፍን ።
አቶ ኦስማን የግጭት መቀጠል ለኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች ከባድ ሸክም ከመሆኑም በላይ የአካባቢዉን ሁኔታ የሚያወሳስብ ነዉ ሲሉ,የኢትዮጵያዉ አቻቸዉ አቶ ስዩም መስፍን በበኩላቸዉ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንበሩን ለማካለል ያቀረበዉ ዉሳኔ ላይ ”አልወያይም” ያለችዉ ኤርትራ ናት ብለዋል። የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን መሀመድ ሳለህ የኤርትራ መሬት በህገ ወጥ በኢትዮጵያ ሲያዝ፣ አይቶ እንዳላዬ ቸል በማለት የመንግስታቱን ድርጅት ከሰዋል። ኢትዮጵያ የኤርትራን ነጻ ግዛት እንደያዘች ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዚህን እርምጃ አሳሳቢነት ቸል ማለቱን መርጦአል። የኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር አካላይ ኮሚሽን ዉሳኔዉን ከሰጠ ስምንት ዓመታትና ኮሚሽኑ ሃላፊነቱን አጠናቆ ያካለለዉን ካርታ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካሳወቀ በሁዋላ፣ የኢትዮጵ ከህግ ዉጭ የኤርትራን ግዛት መቆጣጠርና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩን ቸል ማለት፣ የሁለቱ አገሮች ግጭት መቀጠል ለኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች ከባድ ሸክም ከመሆኑም በላይ የአካባቢዉን ሁኔታ የሚያወሳስብ ነዉ ብለዋል። የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ዛሬ በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ከ1990 ዎቹ ወዲህ ኤርትራ በርካታ ጎሬቤቶችን ወራለች፣ የመንግስታቱ ድርጅት ድረ ገጽ የኤርትራ መንግስት ያለ ምንም ትንኮሳ ኢትዮጵያን ወሮ ኢትዮጵያ ተከላክላ የኤርትራን ሰራዊት መመለስዋን ያሳያል ሲሉ በዋቢነት ጠቅሰዋል። ምንም እንክዋን የተባባበሩት መንግስታትን ህግ ጥሳ ኢትዮጵያን ብትወርም ኤርትራ ዛሬ ኢትዮጵያ ወረረችኝ የሚል ዘመቻ ይዛለች ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንበሩን ለማካልል ያቀረበዉ ካርታ ላይ፤ ቁጭ ብለን እንወያይ በሚለዉ የኢትዮጵያ ጥያቄ ያልተስማማችዉም ኤርትራ ናት ብለዋል። ”ድንበሬ ተያዘ” የሚለዉ የኤርትራ ግምት ነዉ ያሉት አቶ ስዩም መስፍን ዉዝግብ ካለ፣ ዉዝግቡ የሚመለከታቸዉ አካላት ሃላፊነት ካልሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማደራደር ስልጣን የለዉም ብለዋል። ዘገባውን ያድምጡ!
a_amhara-landslide-08-24-10-101405284_1461942
https://amharic.voanews.com/a/amhara-landslide-08-24-10-101405284/1461942.html
በአማራ ክልል የመሬት መንሸራተት 19 ሰዎችን ገደለ
በመርሳ ከተማ በደረሰው የመሬት መንሸራተት 14 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ 24 ቆስለዋል። በውርጌሳ ዙሪያ አምስት ሰዎች ሞተዋል።
አከታትሎ የጣለ ዝናብ ያደረሰው የጎርፍ አደጋ በሀብሩ 2ሽህ ሰዎችን አፈናቅሏል አቶ አሰፋ ነጋሲ በሀብሩ ወረዳ በመርሳ ከተማ ለረጂም ጊዜ የኖሩ የአገር ሽማግሌ ናቸው። አበይ ተራራ በሚባለው ስፍራ ከሰሩት ቤታቸው ቁልቁል ከተማዋን እየተመለከቱ የህዝቡ ብዛት ከጥቂት ሽዎች ወደ አስር ሽዎች ሲያድግ ተመልከተዋል። በግብርና ስራ የተሰማሩት አቶ አሰፋ ቤት እሁድ ሌሊት በመሬት መንሸራተት ፈርሷል። አቶ አሰፋ ምሽቱን አነስ ባለች ቤት ስላሳለፉ በአደጋው ጉዳት አልደረሰባቸውም። በዋናው ቤት ውስጥ የነበሩት ባለቤታቸው፣ ልጃቸውና የልጅ ልጃቸው ገበሬያቸውን ጨምረው ህይወታቸው አልፏል። የድረሱን ጥሪ “እሪታውን” ጎረቤቶች ሲያሰሙ፤ የአካባቢው ሰውና ወዳጅ ዘመዶች ለእርዳታ ወደ አቶ አሰፋ ቤት ፍርስራሽ የተቀበሩ ሰዎችን ሊያድኑ ያመራሉ። በዚህ ጊዜ ነው ትልቁና ብዙዎችን የጎዳው መንሸራተት የደረሰው። “እንደ ደማሚት መሬቱ ተገምሶ እላያችን ላይ ወደቀ ሲሉ” ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ተናግረዋል። የመሬት መንሸራተቱ 14 ሰዎችን ሲገድል ከ24 ያላነሱ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ አስከትሏል። “ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በወልዲያ ሆስፒታልና በመርሳ ጤና ጣቢያ በመታከም ላይ ይገኛሉ” ሲሉ የመርሳ ከተማ አስተደደር ባለስልጣን አቶ ሙሀመድ ያሲን ተናግረዋል። “በአካባቢው የጎርፍ አደጋም ደርሷል… በተለይ በቡሆሮና በውርጌሳ አካባቢ ባለው ተደምሮ ከሁለት ሽህ በላይ ህዝብ የተፈናቀለ መሆኑን ነው መረጃው የሚያሳየው። ” ብለዋል አቶ ሙሀመድ። በጎርፉ ለተጎዱ ገበሬዎች የእርዳታ አቅርቦትና የመልሶ ማቋቋም ስራን ለማስተባበር እየጣረ መሆኑን የአካባቢው አስተዳደር ይናገራል። በወረዳው ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ችግር ደርሶ ስለማያውቅ አቅርቦት ለማዳረስ የሚያስችሉ መሰረቶችና ልምዶች የሉም። ይሄም የእርዳታ አቅርቦቱን ሊያጓትተው ይችላል በሚል ስጋት አለ። የአካባቢው አስተዳደር ግን በቀጣይነት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል።
a_ethiopia-press-review-8-23-13_1735792
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-press-review-8-23-13/1735792.html
ኢትዮጵያ በጋዜጦች
የሱዳንና የሶማልያ ፕረዚዳንቶችን የመሳሰሉት በዝክረ መለስ ስነ-ስርአት የተሳተፉት የአፍሪቃ መሪዎች “የአፍሪቃ ድምጽ” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርን አሞግሰዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ — ዋሽንግትተ ፖስት ጋዜጣ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርመለስ ዜናዊ ህልፈት አንደኛ አመትን ለማሰብ ስለተደረገው ስነስርአት ባወጣው የአሶሼተድ ፕረስ ዘገባ አቶ መለስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ አንድ አመት ቢያልፍም የተለወጠ ነገ የለም ይላል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አመቱን ሙሉ ሲሞገሱ ቆይተዋል። ምስላቸውም በሀገሪቱ ዙርያ በሚገኙት የመንግስት መስርያ ቤቶች እንደተሰቀለ ነው ይላል ጋዜጣው ላይ የወጣው ዘገባ። በሀገሪቱ ዙርያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርአት ተደርጎላቸዋል። ለሳቸው ማስታውሻም ከአርባ ስምንት በላይ የመናፈሻ ቦታዎች ተመስርተዋል። በመዲናይቱ አዲስ አበባም የሳቸው ስራዎች የሚዘከሩበት ቤተ መዘክር ለመገንባት መሰረተ-ዲንጋይ ተጥሏል። የሱዳንና የሶማልያ ፕረዚዳንቶችን የመሳሰሉት በዝክረ መለስ ስነ-ስርአት የተገኙት የአፍሪቃ መሪዎች “የአፍሪቃ ድምጽ” በማለት አቶ መለስን እንዳሞገሱ ዋሽንግትተ ፖስት ጋዜጣ ላይ የወጣው የአሶሼትድ ፕረስ የዜና አገግሎት ዘገባ ጠቅሷል። ሌሎች ርእሶችም ተካተዋል። ከሚቀጥለው ድምጽ ያድምጡ።
a_the-idea-series-ethiopian-history-selective-memory-a-historian-view-voa-dr-shimelis-bonsa-with-alula-kebede-july-2017_3968766
https://amharic.voanews.com/a/the-idea-series-ethiopian-history-selective-memory-a-historian-view-voa-dr-shimelis-bonsa-with-alula-kebede-july-2017/3968766.html
ታሪክ ‘ባስታዋሹ’ መነጽር እና ...በታሪክ ምርምርና ፋይዳ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሌሎች ወጎች
“ክርክሩ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን መነጋገሪያ መድረክ የት ነው? እያንዳንዱ ሰው ከራሱ መንገድ ነው የሚጽፈው። በታሪክ ሞያ ውስጥ ይሄን ምንድን ነው የምንለው? መርጦ ማስታወስ እና መርጦ መርሳት። የተወሰኑ ነገሮች ተመርጠው ይታወሳሉ። ተመርጠውም ይረሳሉ። ታዲያ እነኚህ ጨርሶ እውነታ የላቸውም ማለት አይደለም። ነገር ግን ጎዶሎ እውነታዎች ነው የሚሆኑት። የራስን ፍላጎት ለማስፈጸም ነው የሚውሉት።” ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ።
አዎን! ይህም “ሃሳብ እንደ መንገድ .. በማስረጃ የተደገፉ ጠቃሚ ወጎች” በሚል አብይ ርዕስ የተጀመረው አዲስ ተከታታይ ወግ አካል ነው። የታሪክ ትንተና በፈቃድና ከጥቅም አንጻር ሲተረጎም? ... ታሪክ ባስታዋሹ መነጽር ነገር ግን በብዙዎች ህይወት ላይ የሚኖረው አንድምታ እንደምን ይታያል? የታሪክ ምርምር ተጨባጭ ፋይዳስ በእርግጥ ምንድን ነው? እንግዳችን ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ ናቸው። በState University of New York - Stony Brook የአፍሪካ ዘመናዊ ታሪክና ፖለቲካ እንዲሁም የከተማ ጉዳዮች መምህር ናቸው። በፕሬስ፥ በሴቶች ጉዳይ፣ ፍልሰት፣ በከተሜነትና ከተማ ነክ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረጓቸው በርካታ ጥናትና ምርምሮች ለህትመት በቅተዋል። “ከተማ እንደ አገር” የሚለውን ጨምሮ በከተማ በመንግስትና በሕብረተሰብ መሃል ያለውን መስተጋብር በሚመረምሩ የጥናት ሥራዎቻቸው፤ በሰሞንኛ አነጋጋሪ ታሪክ ቀመስ ጉዳዮች እና በታሪክ ምርምርና ፋይዳ ዙሪያ የተካሄደውን ባለ ሦሥት ክፍሎች ተከታታይ ውይይት ከዚህ ያድምጡ።
a_article-------------114307439_1460381
https://amharic.voanews.com/a/article-------------114307439/1460381.html
ቻይና ከዩናይትድ ስቴይትስ ጋር የጠበቀ የንግድ ግንኙነት እንጂኖራት ፕሬዝደንት ሁ ጥሪ አቀረቡ
ዩናይትድ ስቴይትስን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ጂንታው አገራቸው ከአሜሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራት እንደምትፈልግ ገልጸው፤ ቻይና አጋር እንጂ ስጋት አይደለችም ብለዋል።
የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ጂንታው በዩናይትድ ስቴይትስ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ1989ወዲህ በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስታዊ ልዑካንን በመምራት የቻይና ፕሬዝደንት ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ ሲጓዝ ሁ የመጀመሪያው ናቸው። በዚህ ጉብኝታቸው ሚስተር ሁ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአንድሩውስ ወታደራዊ የአውሮፕላን ማረፊያ በምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ዛሬ በዋይት ሀውስ ቤተ-መንግስት ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። የአሜሪካ ኩባንያዎችና ድርጅቶች ዋጋው ከወረደው የቻይና ገንዘብ ጋር በዶላር ለገበያ ውድድር መቅረብ ከብዶናል በሚል ሮሮ ማሰማት ከጀመሩ ቆይተዋል። በይፋ የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስትና የመገናኛ ብዙሃን ችግሩን አስመልክቶ መላ መምታት ከጀመሩ አንድ አመት አልፎታል። እስካሁን የተለወጠ ነገር የለም። የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ከዩናይትድ ስቴይትሱ አቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር በንግድ ዙርያ ሲመክሩ ሰንብተዋል። በሰፊው ውይይት ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቀው ጉዳይ ቻይና የሀገር በቀል ድርጅቶቿን ታበረታታለች ለውጭ ሀገር ኩባንያዎች ገበያ በተለያዩ የቢሮክራሲና የህግ ማነቆዎች ገበያ እንዳያገኙ ትጥራለች በሚል አሜሪካዊያን ነጋዴዎች ያማርራሉ። በተለይ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በማደግ ላይ ያለውን ያቻይናን ኢንዱስትሪ የገበያቸው መዳረሻ ለማድረግ ይፈልጋሉ፤ ግን ማነቆዎቹ በዝተውባቸዋል። ሚስተር ኦባማ ያቻይናንና አሜሪካን የትምህርት፣ የቴክኖሎጂ፣ የንግድና የቱሪዝም ግንኙነት መጠናከር አስመልክተው፤ በብዙዎቹ መስኮች ተወዳዳሪዎች ብንሆንም በብዙዎቹ ደግሞ አብረም መስራት እንችላለን ብለዋል። ሚስተር ሁ ጂንታውም በበኩላቸው ወደ ዩናይትድስቴይትስ የመጡት የሁለቱን አገሮችና ህዝቦች ትብብር፣ አጋርነት፤ እንዲሁም እርስ-በርስ መተማመን ለማጠናከር መሆኑን ተናግረዋል። ሚስተር ሁ ይሄ ግንኙነት በጸና መሰረት ላይ መቆም ያለበት መሆኑን ገልጸዋል።
a_the-purpose-of-education-experts-discuss-the-state-of-education-in-ethiopia-with-voa-alula-kebede-march-1-2021_5799589
https://amharic.voanews.com/a/the-purpose-of-education-experts-discuss-the-state-of-education-in-ethiopia-with-voa-alula-kebede-march-1-2021/5799589.html
ለምን እንማራለን?
"..ራሳችን በራሳችን የመሠረትነው ትምህርት ከኖረን ቆይቷል።.." ዶ/ር ሃዋኒ ንጉሴ "የራሳቸው ነጻነት ኖሯቸው ማሰብ መፈተሽ እንዲችሉ - ተዓማኒነት ያለውን ከሌለው መለየት የሚያስችል የአስተሳሰብ ችሎታ፥ የሰው መብት የሚያከብር ፍጡር እንዲሆኑ ለማድረግ የምንጠቀምበት ሂደት ነው።" ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ። "..ከዛሬ የተሻለ ነገ እንዲኖረን የሚረዳ እና ችግርን የሚፈታ መሆን አለበት ብዬ ነው የማምነው።.." ዶ/ር ፋንታሁን አድማስ።
ዋሽንግተን ዲሲ - ሎሳንጀለስ - ሺካጎ - አዲስ አበባ — በዝግታ … በጊዜ ውስጥ በሚገበይ እውቀት ሁነኛ ለውጥ ማምጣት ቻሉና “ለአንዳች ቁም ነገር ማብቃቱ” የታወቀና ሁሌም የሚጠበቅ ትሩፋቱ ይመስላል። ኑሮን ለማሸነፍ የሚበጅ ክህሎት ማጎናጸፉና የሰው ልጆችን ህይወት ለማሻሻል ዓይነተኛ መንገድነቱ ሳይሆን ዕድሉን ማግኘት ያለማግኘት ነው ጥያቄው። የመልካም ፍሬዎቹን መበርከት: የመንገዱን ማለቂያ ያለው ያለመምሰል እና ጉዞው የዕድሜ ልክ የሆነውን ያህል ግን አንዳንዶች በዙሪያቸው ያለውን ዓለም አይተው መለስ ሲሉ “በእርግጥ ከትምህርት የጠበቅነውን እያገኘን ነው? ” በሚል መጠየቃቸው አልቀረም። ለመሆኑ መላውስ ምን ይሆን? ፍለጋው ቀጥሏል። የትምህርት ጥራት ወይም ይዘት እዚህ ውስጥ ድርሻው ምን ይሆን? ሦስት የትምህርት ጉዳይ አዋቂዎች ለውይይት ጋብዘናል። ዶ/ር ሃዋኒ ንጉሴ ከሎሳንጀለስ ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ ከሺካጎ እና ዶ/ር ፋንታሁን አድማስ ከአዲስ አበባ ናቸው። የትምህርትን ትርጏሜ: ፋይዳ እና ጥራት ይፈትሻሉ።
a_amh-ned-havel-1-11-2012-137122993_1460387
https://amharic.voanews.com/a/amh-ned-havel-1-11-2012-137122993/1460387.html
በኢትዮጵያ መንግስት የሚዋከቡና የሚታሰሩ ተጠቂዎች ቢመስሉም አሸናፊዎች ናቸው ሲሉ ብርቱካን ሚደቅሳ ተናገሩ
በዋሽንግተን ዲሲ በተሰናዳ የቀድሞው የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ቫትስላቭ ሃቨል መታሰቢያ የብርማዋ አንሳንሱቺ፣ ፕሬዝደንት ኦባማ፣ ዳሊ ላማና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች መልእክት አስተላልፈዋል
በታህሳስ ወር በህመም የሞቱት የቀድሞው የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ቫትስላብ ሃቨል፤ ቼኮስላቫኪያን ከኮሚውኒስት አገዛዝ ነጻ ለማውጣት “የቬልቬት አብዮት” በመባል በሚታወቀው ሰላማዊ ትግል በ1981ዓም የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ሆኑ። በ1985 ቼኮዝላቫኪያ ለሁለት ተከፍላ ስሎቫኪያና ቼክ ሪፐብሊክ ስትባል፤ የመጀመሪያው የቼክ ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። ቫትስላቭ ሃቨል በመላው አለም የሚታወቁት በፖለቲካቸው ብቻ አይደለም። እንዲያውም ሃቨል ከምንም በላይ እራሳቸውን የሚገልጹት፤ ጸሃፊ ተውኔት አድርገው ነው። የሃቨል ተውኔቶች ታዲያ፤ ፍሬ ከርስኪ አልነበሩም፤ መሰረታቸው እውነት ሆኖ የቼኮችን ህዝና የዓለምን ህዝብ አንድ የሚያደርጉ ሰብዓዊ ባህርያትና ፍላጎቶች ጣራና ድግድዳ ሆነው የተዋሃዱባቸው ናቸው። የተውኔቶቹ ክዳን ደሞ፤ ነጻነት፣ ተስፋና ዴሞክራሲ ነበሩ። ቼኮዝላቫኪያ የተፈጠረችው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ሲሆን፡ አስቀድማ በጀርመኖች ጠንካራ እጅ ትገዛ የነበረችው የምስራቅ አውሮፓ አገር፤ ቀጥላ በራሻ ኮሚኒስቶች እጅ ወደቀች። በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ቼኮዝላቫኪያ የምእራባዊያንና የምስራቅ ሶሻሊስቶች የመቆራቆሻ ሜዳ ነበረች። በዚህ የቁርሾ ጊዜ የኖሩት ሃቨል፤ ስራዎቻቸው የጊዜውን ሁኔታዎች ያሳዩ ነበር። ይሄ ታዲያ በሶሻሊስቶቹ አልተወደደላቸውም። በተለይ ስለ ግለሰቦች ነጻነት፣ እኩልነትና ዜጎች እራሳቸውን ለማስተዳደር ያላቸውን መብቶች የሚያሳዩ መልእክቶች ለተደጋጋሚ እስራትና ወከባ ዳርጓቸዋል። በ1980ዎቹ ሃቨልና መሰል ዜጎቻቸው በሰላማዊ መንገድ የሶሻሊዝም አስተዳድርን ለመጣል ተደራጅተው ተንቀሳቀሱ። መሳሪያቸው ንግግር፣ ብእርና ጠብቆ የህዝቡን ብሶት የማደራጀት ብቃት ነበር። ተሳካላቸው። አንድም ሰው ሳይሞት “በቬልቬት አብዮት” የሰላማዊ ትግል ሶሻሊስቶችን አሽቀንጥረው ጣሉ። በዚያን ወቅት በቼኮዝላቫኪያ የዩናይትድ ስቴይትስ አምባሳደር ዊሊያም ሉርስ፤ ሃቨል ፕሬዝደንት ከመሆናቸው አንድ ቀን አስቀድሞ አብረዋቸው እራት በልተው ነበር። “የቆዳ ጃኬት ለብሰው በየመንገዱ ሰልፍ ያስተባብሩ የነበሩ የፋብሪካ ሰራተኞች፤ በአዲሲቱ ቼኮዝላቫኪያ የካቢኒ ሚኒስትሮች ሆኑ” ብለዋል። ለዴሞክራሲ በሚሰራው National Endowment for Democracy ባሰናዳው የሃቨል መታሰቢያ ፕሬዝደንት ኦባማ በአካል ባይገኙም በቢል ክሊንተን አስተዳድር ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት ማድሊን ኦልብራይት መልእክታቸውን እንዲያነቡ ጠይቀዋቸዋል። “ሁላችሁም ጋር በአንድነት የቫትላቭ ሃቨልን ህይወትና ስራዎች ስዘክር ደስታ ይሰማኛል። ከጸሃፊ ተውኔትነት፣ ወደ ፖለቲካ እስረኛነት፣ ከዚያ ወደፕሬዝደንትነት ያደረጉትጉዞ፤ ነጻነትን ለሚሹ የአለም ህዝቦች አርዓያ ሆኗል። በዋሽንግተን ዲሲ ሃቨልን ለማስታወስ በተሰናዳው ዝግጅት በርካታ የአለም ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎችና መልእክተኞች ተገኝተዋል። ከኩባ፣ እስከ ሞንጎሊያ፣ ቲቤት፣ በርማ፣ ኢትዮጵያ፣ አሜሪካና ቼክ የታወቁ ስሞች ይህንን የነጻነት ሰው ዘክረዋል። የቲቤት ህዝቦች የመንፈሳዊ መሪ ዳሊ ላማ በጽሁፍ መልእክታቸውን ልከዋል። “ከቲቤታዊያን ጎን ተሰልፈዋል። በጋራ ያረቀቁት የሰብዓዊ መብት ቻርተር 77 በአገራቸው ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ዜጎችም ትልቅ ለውጥ ያመጣ ነው። በቅርቡ ቻርተር 8 የሚባል ተመሳሳይ ህግ በቻይና ረቋል። በቃላት ብቻ ሳይሆን ጓደኝነታቸውን በተግባር አሳይተዋል። የቻይና ተቃዋሚ ሉ ሻቦ ከእስር እንዲፈታም ተከላክለዋል” ይላል የዳሊ ላማ መልእክት። ቫትስላቭ ሃቨል የጤንነት ሁኔታቸው እያስቆለቆለ ባለበት ወቅት በጋዜጠኞች ተከበው ፕራግ ለሚገኘው የቻይና ኢምባሲ ሉ ሻቦን መንግስቱ እንዲለቅ ደብዳቤ አስገብተዋል። ሃቨል ጤንነታቸው እያሽቆለቆለ በመጣበት ጊዜም የሌሎችን ህዝቦች ትግል አልረሱም። በበርማ ከወታደራዊ አገዛዝ ጋር ተፋጠው በእስርና በወከባ የሚጎሳቆሉት አን ሳን ሱቺ ሃቨል ካረፉ ከሁለት ቀናት በኋላ ደብዳቤ ደረሳቸው። “ለ50 አመታት ከዘለቀ አምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ ወጥቶ ሁሉን አቀፍ፣ ዴሞክራሲያዊ አስተዳድር የመመስረቻው መንገድ ከባድ ነው። እኛም 50 ዓመታት በጭቆና ኖረናል። መጀመሪያ ጀርመኖች፤ ከዚያ ኮሚኒስቶች። የቬልቬት አብዮት ከተሳካ ከ22 ዓመታት ቢያልፉም አሁንም የፈለግንው ቦታ አልደረስንም። በዚህ የመታሰቢያ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያዋ አን ሳን ሱቺ በመባል ወደ መድረክ የተጠሩት ለዴሞክራሲ በሚሰራው National Endowment for Democracy ጥናት በማድረግ ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊት ተቃዋሚና የዴሞክራሲ አቀንቃኝ ብርቱካን ሚደቅሳ፤ የኢትዮጵያን ጉዳይ ከአለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር በማጣቀስ ንግግር አድርገዋል። ወይዘሪት ብርቱካን የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን በምርጫ 97 ከመሩ በኋላ ለሁለት አመት ያህል በታሰሩበት፤ ቆይቶ ደግሞ የይቅርታ ወረቀታቸው ተቀዶ ለብቻቸው በታሰሩትበ ወቅት፤ ተስፋ ይሰጣቸው የነበረው የቫትስላቭ ሃቨል ጽሁፎች እንደሆኑ ያስታውሳሉ። “ጉልበት የሌላቸው ህዙሃን ሃይል The powerof the Powerless በሚል ቫትስላቭ ሃቨል የጸፉት መጽናኛና መበረታቻዪ ነበር። ነጻና የተከበረ የሰው ይህወት ለመምራት ያለኝን ቁርጠኝነት አጠንክሮታል። አንድ ግለሰብ ጭቆናን እምቢ ሲል፤ የሚያሳልፈው መልእክት ከተሳካ አብዮት ጋር የሚስተካከል ትርጉም አለው። አንድም ሰው ሆነ ብዙ ሰዎች ያለውን ስርዓት ማንገጫገጫቸው፤ የእንቅስቃሴዎች ሁሉ የመጀመሪያ እርምጃ ነው” ብለዋል ብርቱካን ሚደቅሳ። ወይዘሪት ብርቱካን፤ የሃቨልን የሰላማዊ አብዮትና የዴሞክራሲ ፍልስፍናዎች ከኢትዮጵያ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታዎች ጋር አነጻጽረዋል። “የኢትዮጵያ መንግስት የሚቃወሙትን ሁሉ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ብዙ ሳይተች በጭካኔ ቢያዋክብም፤ እነዚህ ተጠቂዎች ደካማና ረዳት አልባ ቢመስሉም፤ ለኔ አሸናፊዎች ናቸው። ምክንያቱም በውሸት አንኖርም ሲሉ ስርዓቱን በመቃወማቸው። በኢትዮጵያ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና መሰሎቹ ይፈቱ ሲሉ ወይዘሪት ብርቱካን በንግግራቸው ጠይቀዋል። በዚህ ስነስርዓት ከኩባ ኦስዋልዶ ፓያ፣ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማድሊን ኦልብራይት፣ ከቻይና ሊ ሻሮንግ፣ እንዲሁም ከሌሎች ለዴሞክራሲ ትግል ከሚደረግባቸው አካባቢዎች “ተቃዋሚዎች” ንግግር አድርገዋል።
a_ethiopia-health-11-12-10-109949584_1458542
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-health-11-12-10-109949584/1458542.html
የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ለማሳደግ ዩናይትድ ስቴይትስ ተጨማሪ እገዛ እያደረገች ነው
ኢትዮጵያ በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት የግሎባል ሄልዝ ኢኒሺየቲቭ በጤና ዙሪያ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው ከተመረጡ ጥቂት አገሮች አንዷ ነች።
በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን በሚገኘው የባቲ የጤና ጣቢያ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኛ የሆነችው ዘቢባ ሰይድ መድሃኒቶችን ከመድሃኒት ቤት ለመውሰድ መጥታለች። መድሃኒት ቤቱ ተጨናንቋል። ከኦሮሚያ ዞንና ከቅርበቱ አንጻር ከአፋር ክልል የሚመጡ ተገልጋዮች በጤና ጣቢያው ይገኛሉ። ይሄንን መሰል የጤና ጣቢያ በተለይ በገጠር አካባቢ ማግኘት አይቻልም። ለዚህ ነው የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ምንስቴር የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ያሰማራው። እንደ ዘቢባ መሰል ከ32ሽህ በላይ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በመላው ኢትዮጵያ ከወረዳ እስከ ጎጥ ድረስ ከማህበረሰቡ ጋር እየኖሩ ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል፤ አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት በመስጠትና ከአቅማቸው በላይ የሆኑትን ጉዳዮች ወደ ክሊኒኮች፣ ጤና ጣቢያና ሆስፒታሎች መላክ ነው ስራቸው። ይሄ ስልት የተዋጣለት እንደሆነ በባራክ ኦባማ አስተዳድር በጤና ጉዳዮች የዋይት ሃውስ የበጀት አማካሪ ዶክተር ዝክየል ኢማኑዌል የተናገሩት። “እዚህ በአግባቡ እየሰሩና ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ነገሮችን አስተውያለሁ። በተለያዩ የጤና ኬላዎች ብዙ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን ተመልክቻለሁ። ይሄ በእውነቱ በኢትዮጵያ ከሚታዩ ትልቅ እመርታዎች አንዱ ነው። ውጤታማ ነው። ሀገሪቱ 32 ሽህ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን በአጭር ጊዜ አሰልጥና ወደ ገጠር ቀበሌዎች በመላክ የሚደነቅ ስራን ሲሰሩ ተመልክተናል። ማህበረሰቡን ያስተምራሉ፣ መሰረታዊ የጤና አገልግሎትም ይሰጣሉ። የወባ በሽትን በመከላከል ረገድና የቤተሰብ ምጣኔን በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች በእጅጉ የሚደነቁ ናቸው” ብለዋል። ዶክተር ዚክ ኢማኑዌል በጎበኟቸው የአመያና ዎንጭ ወረዳዎች ከአንደ አመት በፊት የወባ መከላከያ አጎበሮች ተከፋፍለው ነበር፣ የወባ በሽታ መለላከልና ህክምና አገልግሎትም በዚሁ አመት ተስፋፍቷል። ውጤቱ በወባ በሽታ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር በ90 ከመቶ ቀንሷል፤ ከሁለት አይነት የወባ ተውሳኮች ማለት ከቫይቫክስና ፋልሲፋረም የሚሞቱ ሰዎችም ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል። “በግልጽ እንደሚታየው የአልጋ አጎበሮች ስርጭት፣ የማህበረሰቡ ግንዛቤ መጨመር፣ መድሃኒት መርጨት፣ ፈጣን የምርመራ አገልግሎቶች መስፋፋት ለተገኘው ውጤት ተጠቃሽ ናቸው። አስቀድሞ በሽታው ከታወቀና የመከላከያ መንገዶች ካሉ፤ የወባ በሽታን መቀነስ ይቻላል” ሲሉ ዶክተር ኢማኑዌል ተናግረዋል። ሌላኛው በጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የተገኘው ለውጥ የወሊድ መቆጣጠርና የእናቶችና ህጻናት በእርግዝና ጊዜ፣ በወሊድና፣ ከወሊድ በኋላ የሚኖር የጤና ክትትል ነው። ይሄንን ስራ ነው የኦባማ አስተዳድር የጤና አማካሪ የሆኑት ዶክተር ዚክ ኢማኑየል ያወደሱት። “በጣም የሚያስመሰግንና የሚያኮራ ነው። ይሄ የሚያሳየው የተሟላ መርሃ ግብር ተቀርጾ በስራ ላይ ከዋለ የሚያስገርም ለውጥ እደሚያመጣ ነው። ዶክተር ኢማኑዌል ይህንን ይበሉ እንጂ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ጥራት ዙሪያ የሚያሳስቧቸው ነገሮች እንዳሉ ሳይጠቁሙ አላለፉም። ከጤና ጥበቃ ምኒስትር ዶ.ር. ቴድሮስ አድሃኖም ጋርም በተገናኙበት ወቅትም ይህንንኑ ማሳባቸውን ገልጸዋል። “በሳምንቱ መጀመሪያ ከሚኒስትሩ ጋር ስንገናኝ ያለምንም ገደብ የማይሰራውንና ሊሻሻል የሚገባ የምለውን እንድነግራቸው አበረታተውኝ ነበር” ይላሉ የቀድሞው የዋይት ሀውስ ቺፍ ኦፍ ስታፍ ራም ኢማኑዌል ወንድም ዚክ ኢማኑዌል ። “ያም ሆኖ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ከፍተኛ እንቅፋቶች ተጋርጠውበታል። የመጀመሪያው መሰረተ-ልማት ነው። ይሄንን ስል የጤና መሰረቶች=ማለት የጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች እንዲሁም ዶክተሮችና ነርሶች ብዛት ሳይሆን፤ ሌሎችንም ያካትታል። መንገዶች፣ የውሃ የመብራትና የመሳሰሉት አገልግሎቶች አለመኖር አሁንም ከፍተኛ ችግር ነው። ከዚህም በተጨማሪ በመላው ኢትዮጵያ የመከላከልና የመጀመሪያ ደረጃ ህክምናን ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም የጤና ዘርፉ አሁንም ቢሆን ከፍተኛ የጥራት ችግሮች ይታዩበታል ሲሉ ዚክ ኢማኑዌል ተናግረዋል። ዶክተሮች፣ የጤና መኮንኖችና ነርሶች ቁጥር መጨመር እንዳለበትና ፤ ሀገር ለቀው በሚሄዱ ልምድ ባላቸው ሃኪሞች እግር ሌሎችን ለመተካት የተሻሉ ባለሙያዎችን ማሰልጠን እደሚሻ ተናግረዋል። ለሁሉም የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። “በዚች አገር ከፍተኛ መዋእለ-ንዋይ እያፈሰስን ነው። በየአመቱ ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ዶላር ለጤና እንሰጣለን። ይች አገር ቁልፍ አጋር ነች። ብዙዎቻችሁ አንደምታውቁት ባለፈው አመት ፕሬዝደንት ኦባማ የግሎባል ሄልዝ ኢኒሺየቲቭን መስርተዋል። የዚህ መርሃ-ግብር አንዱ አሰራር በጤና ዙሪያ ከፍተና ለውጥ ያመጣሉ ብለን ያሰብናቸውን ጥቂት አገሮች እንድንመርጥ ነው። ኢትዮጵያ በዚህ መርሃ ግብር ከተመረጡት ጥቂት አግሮች አንዷ ናት። ተጨማሪ ገንዘብና የቴክኒክ እገዛም ለማድረግ ተዘጋጅተናል። በዚህም ጠንካራ እመርታዎችን ለማግኘትና የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል ከመንግስቱ ጋር አብረን እንሰራለን። በጤና አገልግሎቱ ዙሪያ በወባ በሽታ፣ በኤች አይ ቪ ኤድስ፤ በእናቶችና ህጻናት ጤና ጥበቃ ዙሪያ የመረጃ ማሰባሰብ ስራዎች አሁን ካሉበት ዝቅተኛ ደረጃ እንዲሻሻሉም ዚክ ኢማኑዌል አሳስበዋል።
a_unga-obama-ahmadinejad--103885994_1461881
https://amharic.voanews.com/a/unga-obama-ahmadinejad--103885994/1461881.html
"ታሪክ የነፃነት ወገን ነች" - ፕሬዚዳንት ኦባማ ለተመድ ያደረጉት ንግግር
"በመስከረም 94ቱ ጥቃት ውስጥ የአሜሪካ መንግሥት እጅ አለበት" - ፕሬዚዳንት አሕመዲነጃጅ ለተመድ ያደረጉት ንግግር
ኒው ዮርክ ላይ ሲካሄድ በሰነበተውና 14ዐ የሚሆኑ የመንግሥታትና የሃገሮች መሪዎች በተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሐሙስ ውሎ ላይ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፕሬዚዳንቶች ተናግረዋል፡፡ ኒው ዮርክ ላይ ሲካሄድ በሰነበተውና 14ዐ የሚሆኑ የመንግሥታትና የሃገሮች መሪዎች በተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሐሙስ ውሎ ላይ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፕሬዚዳንቶች ተናግረዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሃገራቸውን ሠላም፣ የውጭ ፖሊሲና ሰብዓዊ መብቶችን ያካተተ ሰፊ አድማስ ያለው ንግግር ነው ያደረጉት፡፡ በዚህ ንግግራቸው ፕሬዚዳንቱ በሴቶች ላይ የሚካሄደው አመፃ እንዲያከትም ዓለም እንዲተባበር አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ለያዙት የመካከለኛው ምሥራቅ የሠላም ጥረትም መሪዎቹ ድጋፍ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል፡፡ ከሁሉም ዓይነት የአስተዳደር ሥርዓቶች አሸናፊው ዴሞክራሲ መሆኑን ታሪክ እንደሚመሰክርም ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ መድረክ ላይ የተናገሩት የኢራን ፕሬዚዳንት ማኅሙድ አሕመዲነጃድ በመስከረም 1994ቱ ጥቃት ውስጥ የራሷ የዩናይትድ ስቴትስ እጅ አለበት ብለው ብዙ አሜሪካዊያንና ብዙ መንግሥታትም እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ ይህ የኢራኑ መሪ ንግግር በዩናይትድ ስቴትስ፣ በብዙ የአውሮፓና የሌሎችም አካባቢዎች ልዑካን ዘንድ ቁጣን አጭሯል፡፡ ብዙዎቹም ንግግራቸውን እየረገጡ ከአዳራሹ ወጥተዋል፡፡ ዝርዝሩን በ"የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባዔ ያድምጡ፡፡
a_article----------amh-ak-crossfire-freedom-of-speech-2-18march2011-118338139_1458396
https://amharic.voanews.com/a/article----------amh-ak-crossfire-freedom-of-speech-2-18march2011-118338139/1458396.html
የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ የዛሬ ይዞታውና አካሄዱ፤ ከየት ወደ የት?
«እኔ ባለኝ ግንዛቤ፥ የንግግር ነፃነት ዛሬ በኢትዮጵያ አለ፤» አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ። «የንግግር ነፃነት ለተወሰኑ ብቻ የተሰጠ የኢህአዴግን ዓላማ ለማስፈፀም ብቻ የዋለ እንጂ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የለም፤» አቶ ግዛው
«የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፤ ወቅታዊ ይዞታና አንድምታው፤» በእሰጥ አገባ የተጀመረው የሁለት ወገን ክርክር ቀጥሏል። የክርክሩ ተሳታፊዎች፥ አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ከአዲስ አበባ፤ አቶ ግዛው ለገሰ ደግሞ ከዚህ ከዋሽንግተን ዲሲ ናቸው። አቶ ተስፋዬ ”የንግር ነፃነት“ ዛሬ በኢትዮጵያ «ተረጋግጧል፤» ሲሉ፤ አቶ ግዛው በበኩላቸው፤ ከዓመታት በፊት ብልጭ ብሎ የነበረውና እንዲያድግ፥ እንዲጎለብት ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ዛሬ ጨርሶ ተዳፍኗል፤ ይላሉ። የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ ከማጡ ወደ ድጡ? ወይስ በእርግጥ «ሁነኛ፤» የሚሰኝ ነፃነት ዕውን እየሆነ ይሆን? የማይመሳሰሉና ፍፁም የተለያዩ ዕይታዎች የተንፀባረቁበት የሁለት ወገን ክርክር እንደጦፈ ቀጥሏል። ለዝርዝሩ የሳምንቱን ምጥን ዝግጅት ያዳምጡ፤
a_obama-african-youth-leaders-white-house-08-04-10-99977454_1460122
https://amharic.voanews.com/a/obama-african-youth-leaders-white-house-08-04-10-99977454/1460122.html
ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ሀገሮችን የወከሉ ወጣት መሪዎችን ተቀበሉ
ወጣቶቹ ከሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን እና ከአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን ጋር ጀምረው ከቀትር በኋላ ደግሞ በዋይት ሃውስ ከፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ጋር በዋይት ሐውስ ምስራቅ ክፍል ውይይት አድርገዋል።
ከአሜሪካውያን አቻዎቻቸው ጋር እየተወያዩ ራዕያቸውን እያካፈሉና ልምድም እየቀሰሙ ናቸው በዚህ መልክ ነበር ፕሬኢዘንት ባራክ ኦባማ ወደ መቶ ሃያ የሚደርሱት እና በየሀገሮቻቸው የባህል ልብሶች ደምቀው በማራሹ ዙሪያ ተቀምጠው የጠበቋቸውን ወንዶችና ሴቶች የአህጉረ አፍሪካ ወጣት መሪዎች የተቀበሏቸው። ፕሬዚደንት ኦባማ ለዚህ መወያያ መድረክ ወጣቶቹን የጋበዟችው ይህ የአውሮፓውያን ሁለት ሺህ አስር ዓመተ ምህረት አስራ ሰባት የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ አገዛዝ ተላቀው ነጻነታችውን የተጎናጸፉበትን ሃምሳኛ ዓመት መታሰቢያ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ከወጣቶቹ ጋር እናንተስ የቀጣዮቹ ሃምሳ ዓመታት ራዕያችሁ ምንድነው? በሚለው ዙሪያ ለማወያየት ነው። የሃይማኖታዊ ተቋማት ፥ የሲል ማህበረሰባት የልማት እንዲሁም የንግድ ስራዎች መሪነታችሁን አስመስክራችኋል። ታላቅ ተስፋም ይጠብቃችኋል ። አያሌ እሪካውያን ለብዙ ጊዜ ያከናወኑትን የምትወክሉ ናችሁ። በርግጥም አፍሪካ ብዙ ጊዜ ልብ የማይባልላትን ወደሃያ አንደኛው ምዕተ በምታደርገው ግስጋሴ ያላትን ተስፋ የምታሳዩ ናችሁ ብለዋቸዋል። ስለዚህም አሉ ጠንካራ እና በራሱዋ የምትተማመን አፍሪካ ታስፈልገናለች። ዓለምን የናንተን አፍሪካ ዓቅም ትፈልጋለች ፥ ሸሪካችሁ ለመሆንም ብለዋል። ስለዚህም ዛሬ በመካከላችን ያን ሽርክና ለማጠናከር የሚሰሩ የአስተዳደሬ አባላትም አሉ። ደስ ብሎኛል። ለዚህ ለዛሬው ስብሰባችን ካሁን የሚመረጥ ጊዜ አይኖርም ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚደንት በአፍሪካ ዙሪያ አስራ ሰባት ሀገሮች የቅኝ ገዥዎች ባንዲራ ወርዶ የራሳቸው የነጻነት ሰንደቅ ዓላማቸውን በማውለብለብ በደስታ የፈነደቁበት ሃምሳኛ ዓመት ታሪካዊ ክብረ በዓል በመሆኑ ነው ብለዋል። ፕሬዚደንቱ አያይዘው ዛሬም ቢሆን በአህጉሪቱ ዜጎች በፈታኝ ህይወት ውስጥ እንደሚያልፉም አንክድም ። ለልጆቻችን የለት ጉርስ እና ስራ ለማግኘት ያለባቸው ውጣ ውረድ እናውቃለን ብለው አዘውትሮ በዓለም መድረኮች የሚንጸባረቀው የአፍሪካ ገጽታም ይህ መሆኑንን እንረዳለን ብለዋል። በጋና እና ቦትስዋና ብልጽግና እየተመዘገ ነው ሲሉም ፕሬዚደንት ኦባማ ተናግረዋል። ደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን በስኬት ማከናወኑዋም አሉ ፕሬዚደንት ኦባማ ምንም እንኩዋን ወደአሸናፊነት የዘለቁት አውሮፓውያን የእግር ኳስ ቡድኖች ይሁኑ እንጂ የዓለም ዋንጫው ባለድል ግን አፍሪካ መሆንዋ ሲወሳላት እንደቆየ አስታውሰዋል። ወጣቶቹን መሪዎች የቀጣዮቹን ሃምሳ ዓመታት አፍሪካን የመገንባት ኃላፊነት የናንተ ነው ሲሉ ኣሳስበዋቸዋል ። አሜሪካ አብራችሁ ትቆማለች በማለትም ለአህጉራችሁ ግልጽነትንና ሙስናን ለማስወገድ እንዲሰሩ አሳስበዋቸዋል። መጪዎቹ የአፍሪካ መሪዎች እንዲህ ያለውን ግልጽነት ከልባቸው በመከተል ሙስና አስወጋጅ ርምጃዎችን የሚወስዱ ናችው። እንደHIV AIDS ካሉ በሽታዎች ራሳቸውን የሚጠብቁ የዜጎቻችን ሁሉ በተለይም የሴቶችን መብት የሚያስከብሩ ናቸው በማለት ካስገነዘቡ በኋላ የወደፊት ዕጣ ፈንታችሁ በናንተው ስራ ላይ ነው ብለዋል። ፕሬዘንት ኦባማ ከወጣት አፍሪካውያኑ መሪዎች በርካታ ጥያቄዎችን በመቀበል አስተናግደዋል ፥ HIV AIDS ወረርሺኝ ፥ የአፍሪካ ሀገሮች የተማሩ ዜጎች ከሀገር ተሙዋጦ መውጣትን ፥ የሴቶች መብትንና ሌሎችንም ጥያቄዎችን አንስተውባባቸዋል። ደካማ አፍሪካ እና ብርቱዋ አሜሪካ ዕውን በዕኩልነት ላይ የተመሰረተ ሽርክና ሊኖራቸው ይችላል የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸዋል። አፍሪካውያኑ ወጣት መሪዎች ዛሬም በተሰናዱላቸው ልምድ መቅሰሚያ ራዕይ መጋሪያና ትውውቅ መፍጠሪያ ፕሮግራሞች መካፈላችውን ቀጥለዋል። ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ፥ በአሜሪካ የሰላም ጉዋድ እና በተለያዩ ህዝባዊ ድርጅቶች መርሃ ግብሮች የነበሩዋቸው ሲሆን ነገ ሐሙስም ይቀጥላሉ።
a_th-annual-golden-globe-jan-7-2018-voa-alula-kebede_4198709
https://amharic.voanews.com/a/th-annual-golden-globe-jan-7-2018-voa-alula-kebede/4198709.html
ኦፕራ ዊንፍሬ በዘንድሮው የምርጥ-ምርጥ የቴሌቭዥንና የሲኒማ ሥራዎች ሽልማት ጎልደን ግሎብ
“እነኚያ ሬሲ ቴይለር’ን ሊያጠፉ የሞከሩ ሰዎች በሕግ ሳይጠየቁ ቀርተዋል። ሬሲ ቴይለር ዘጠና ስምንተኛውን የልደት በዓሏን ለማክበር ጥቂት ሲቀራት ከአሥር ቀናት በፊት ነው ያረፈችው። አይደፈሬ ነገር ግን ርሕራሄ በሌላቸው ወንዶች በተደፈረ ባሕል ውስጥ አያሌ ዓመታት ኖራ አለፈች። በእነኚያ አይጠየቄ ወንዶች የደረሰባቸውን ጥቃት ለመናገር የደፈሩ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶችም ሰሚ ሳይኖራቸው ለረዥም ዘመናት ዘለቁ። ዛሬ ግን ያ ሰዓት ያበቃ ይመስላል።” ኦፕራ ዊንፍሬ።
ዋሺንግተን ዲሲ — በቀይ ምንጣፍ ላይ የተንጣለለ የጥቁር ባሕር ተመስሏል። በሆሊውድ እና በመላዋ አገሪቱ በተለያዩ የሥራ ቦታዎች በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ሥር የሰደደ ወሲባዊ ወከባ ለመፋለም ለሚንቀሳቀሰውን ታይም ኢዝ አፕ የተባለውን የመብት ተሟጋች ቡድን በመደገፍ ጥቁር የለበሱ በሥነ ሥርዓቱ የተገኙ ሴቶች የለበሱት ልብስ የከሰተው ገጽታ ነው። በቴሌቭዥን እና በሲኒማው መስክ ባለፈው ዓመት የተሰሩ ምርጥ ሥራዎችን የሚዘክረው የሆሊውዱ የውጭ ፕሬስ ማኅበር የሚያሰናዳውና እንደ ወትሮው ሁሉ ለየት ባለ ጉጉት የተስተናገደው የትላንቱ የጎልደን ግሎብ ሥነ ሥርዓት፤ ሆሊውድ በሴቶች ላይ በሚፈጸሙት እና ለዓመታት በዘለቁት የወሲባዊ ወከባ ጥቃቶች ቅሌት ከተናጠች ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑ ነው። የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ባለፈው የጥቅምት ወር አስገድዶ የመድፈር ጥቃትን ጨምሮ በያኔው ገናና እና ከፍተኛ ተሰሚነት የነበረው የፊልም አቀናባሪ ሃርቬይ ዋይንስቲን “ተፈጽመዋል” በተባሉ ለአሥርት ዓመታት የዘለቁ፤ ወሲባዊ ወከባዎች ውንጀላ ያተተ ዝርዝር ዘገባ ተከትሎ፤ ሌሎች በርካታ ገናናዎችንና አይደፈሬዎችን ያንበረከኩ ያልተጠበቁ ድምጾች፤ ክሶችና ስሞታዎች በየቀኑ ይዥጎድጎዱ ጀመር። በትላንቱም ጎልደን ግሎብ የሥነ ሥርዓቱ አስተናጋጅ፤ ታዋቂ የምሽት የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና ኮሜዲያን ሲት ማየር ይሄንኑ የወሲባዊ ቅሌት ሥሜት ባዘሉ የሰሉ ሥላቆች የምሽቱን መድረክ መጋረጃ እንዲህ ሲል ከፈተ። “በዚህ ክፍል ውስጥ የሌለውን ግዙፍ ጉዳይ የማስተዋወቂያው ሠዓት ይመስለኛል። ሃርቬይ ዋይንስቲን በዛሬው ምሽት ከዚህ የለም። እንደ ሰማሁት ጭምጭምታ ከሆነ እብድና አብረውት መሥራት የሚቻል ሰው አይደለም። ሃሳብ አይግባችሁ ከአንድ ሃያ ዓመታት በኋላ ተመልሶ ይመጣል። በሕልፈታቸው መታሰቢያ በታዳሚው ጩኰት ከመድረኩ እንዲወርዱ በመጠየቅ የመጀመሪያው ሰው ይሆናሉ። እንዲያ ነው የሚመስለው ነገሩ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1914 እስከ 1958 በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ70 በላይ ፊልሞችን በሰራውና የአሜሪካ የፊልም አባት በሚል ቁልምጫ በሚታወቀው ዕውቁ የፊልም ዲሬክተር እና አቀናባሪ ሴሲሊ ቢ ዴሚሌ ሥም የተሰየመውን ለዕድሜ ልክ ሥራዎች የሚሰጥ ሽልማት የዘንድሮ ተሸላሚ የፊልም ተዋናይዋ አቀናባሪና የቴሌቭዥን ሠው ኦፕራ ዊንፍሬ ሽልማቱን በተቀበለችበት ወቅት ያሰማችውም ንግግር አዳራሹን ከዳር እስከ ዳር ያቀጣጠጠለ ነበር። ኦፕራ በዚያ የብዙዎችን ቀልብ በልዩ ሥሜት በናጠ ንግግሯ ከሰባ ዓመታት በፊት በነጭ አሜሪካውን ወረበሎች በቡድን የተደፈረች አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት አስታወሰች። “እነኚያ ሬሲ ቴይለር’ን ሊያጠፉ የሞከሩ ሰዎች በሕግ ሳይጠየቁ ቀርተዋል። ሬሲ ቴይለር ዘጠና ስምንተኛውን የልደት በዓሏን ለማክበር ጥቂት ሲቀራት ከአሥር ቀናት በፊት ነው ያረፈችው። አይደፈሬ ነገር ግን ርሕራሄ በሌላቸው ወንዶች በተደፈረ ባሕል ውስጥ አያሌ ዓመታት ኖራ አለፈች። በእነኚያ አይጠየቄ ጉልቤ ወንዶች የደረሰባቸውን ጥቃት ለመናገር የደፈሩ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶችም ሰሚ ሳይኖራቸው ለረዥም ዘመናት ዘለቁ። ዛሬ ግን ያ ሰዓት ያበቃ ይመስላል። የእነኚያ ጉልበተኞች ጊዜ አለፈ። አዎን! አለፈ። ” ብላለች። በርካታ እንስት ተዋናዮች ከሴቶች መብት ተሟጋቾችና የዘር ልዩነትን በመቃወም የፍትሕ ጥሪ ለማሰማት ከተሰለፉ ብዙዎች ጋር በመሆን ነው። አነጋጋሪውና ቀልብ ሳቢያ የኦፕራ ንግግራ የመጪዋ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የመሆን ዕቅድ መጀመሪያ አድርገውም ወስደውታል። ይህን አስመልክቶ በኦፕራ በኩል የተባለ ነገር በሌለበት በእርግጥ የሚሆነው ወደፊት ይሆናል የሚታወቀው።
a_covid-main_5545788
https://amharic.voanews.com/a/covid-main/5545788.html
የኮሮናቫይረስ የምራቅ ምርመራ ጸደቀ
የዩናይትድ ስቴትስ የሳይንስ ምሁራን ሆስፒታል ከሚገኙት የኮቪድ 19 በሽተኞች በ 4.8 ሜትር ርቆ የቫይረሱን አካል ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ የሚለው እምነት የተሳሳተ መሆኑን የሳይንስ ጠቢባኑ ሲያስረዱ የነበረው የተሳሳተ ግንዛቤ ብዙ ሰዎችን ለቫይረሱ እያጋለጠ ሳይሆን አንዳልቀረ ጠቁመዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ — ጥናቱ የተካሄደው በፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ክፍል ሲሆን ገና በሌሎች የሙያው ምሁራን እንዳልተገመገመ ተገልጿል። የአሜሪካው የል ዪኒቨርሲቲ ያፈለቀውን የኮቭድ 19 ቫረስን በምራቅ የመመርመሩ ዘዴ በአስቸኳይ ጊዜ ወቅት እጥቅም ላይ እንዲውል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ትላንት አጸደቀው። በምራቅ የሚደረገው ምርመራ ከ 24 ሰአታት ባነሰ ፍጥነት ውጤቱ ሊገኝ እንደሚችል ዋጋውም ርካሽ እንደሆነ ወደ $10 ዶላር ገደማ መሆኑ ተገልጿል። አዲሱ የምርመራ ዘዴ የፀደቀው አንዳንድ የፌደራልና የጤና ባለስልጣኖች በሀገሪቱ የቫይርሱ ምርመራ እንዲበራከት እየጠየቁ ቢሆንም በየቀኑ የሚደረግ የቫይረሱ ምርመራ እንደቀነሰ በተገለጸነት ወቅት ነው። ዩናይትድ ስቴትስ በኮቪድ-19 ህሙማንና በሙታኑ ብዛት ከአለም ቀዳሚ ቦታ መያዝዋ በቀጠለበት ወቅት ነው ይህ የሆነው። በአለም ደረጃ የኮቪድ 19 በሽተኞች ብዛት እስከ ዛሬ ንጋት በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ 21 ሚሊዮን በላይ መሆኑን ስለጉዳዩ የሚከታተለው የጆንስ ሆፕኪንስ ዪኒቨሲቲ አስታውቋል። ከ5.3 ሚልዮን በላይ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ3.3 ሚልዮን ደግሞ በብራዚል መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው አሀዝ አመልክቷል። የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በገለጸው መሰረት ህንድ ከ 2.5 ሚልዮን በላይ በኮቪድ የተያዙ በሽተኞች አሏት። ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች በሞት ተለይተዋል።
a_hr-128-ethiopian-human-rights-us-congressman-cofman-01-30-18_4231874
https://amharic.voanews.com/a/hr-128-ethiopian-human-rights-us-congressman-cofman-01-30-18/4231874.html
በUS ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ረቂቅ ሕግ ቀጣይ እጣ እና ሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች
“ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ላላት በብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ላተኮረ ግንኙነቷ ቅድሚያ በመስጠት ለረዥም ጊዜ በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አይታ እንዳላየች ስታደርግ ቆይታለች። ያ ፍጹም የተሳሳተ ነገር ነው። በመሆኑም ይሄ ያን ስህተት የማመን የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ዜጎቹ ላይ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።” ኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን የUS የተወካዮች ምክር ቤት አባል።
ዋሽንግተን ዲሲ — በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ግፊት ለማድረግ በሚል ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ሕግ ቀጣይ ሂደት ዙሪያ የተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባኤ ነው የቀጣዩ ዘገባ መነሻ። ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ሁኔታ ካልተለወጠ HR-128 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሙሉ ምክር ቤቱ የሚተላለፍና ሊጸድቅ የሚችል መሆኑ ነው፤ በምክር ቤቱ የብዙኃኑ ፓርቲ ተጠሪ በተገኙበት በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባኤ የተገለጸው። በኢትዮጵያ ተፈጽመዋልና እየተፈጸሙ ናቸው የሚላቸውን የመብት ጥሰቶች የሚያወግዘው ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ የቀረበው ይህ የሕግ ረቂቅ፤ በኢትዮጵያ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ከበሬታ መረጋገጥ እና ብሎም ሁሉን አቀፍ አስተዳደር መፈጠር የታለመ መሆኑን ይዘረዝራል። ኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን በUS የተወካዮች ምክር ቤት የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ስድስተኛው የምክር ቤታዊ የአስተዳደር ክልል ተወካይ ናቸው። ረቂቅ ሕጉ ያለበትን ሁኔታ እንዲያስረዱ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ፤ ከምክር ቤቱ አመራር አባላት ጋር ባደረግናቸው ንግግሮች “በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትና አስተዳደር ጉዳዮች ያሉትን አማራጮች ለማየት ከሚያስችለን ስምምነት ላይ ደርሰናል፤” ይላሉ። “የኢትዮጵያ መንግስት እስረኞችን እየፈታ ነው፤ አንዳንድ መሻሻሎችንም እያደረገ ነው፤ እናም በረቂቅ ሕጉ ላይ ድምጽ ከመ’ሰጠቱና ከመጽደቁ አስቀድሞ ነገሮችን ወደሚፈለገው አቅጣጫ ይወስዳል፤” የሚል አስተያየትም ተነስቷል። በእርግጥ እኔ በዚያ ግምት አልስማም። ለሁሉም የምናየው ይሆናል። ካልሆነም ረቂቅ ሕጉ እውን ወደሚሆንበት መንገድ እናመራለን። ” የሚሉት ኮንግሬስማን ኮፍማን የጊዜ ገደቡ እየተጤነ መሆኑንም ጨምረው ገልጠዋል። ሁኔታዎች ተሥፋ እንደተጣለባቸው ባይይዙና ቀደም ብለው እንደገለጹት የሕግ ረቂቁን ተፈጻሚ ወደሚያደርገው አማራጭ የሚኬድ ቢሆን፤ በእርግጥ ሕጉ ምን ዓይነት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት ያስገኝ ይሆን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም ኮፍማን እንዲህ ይመልሳሉ። “ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ላላት በብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ለሚያደርገው ግንኙነቷ ቅድሚያ በመስጠት በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለረዥም ጊዜ አይታ እንዳላየች ስታደርግ ቆይታለች። ያ! ፍጹም የተሳሳተ ነገር ነው። በመሆኑም ይሄ ያን ስህተት የማመን የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ዜጎቹ ላይ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የመቶ ሚልዮን ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው፤ በአፍሪቃ ቀንድ ዋነኛዋ የዩናይትድ ስቴትስ ሃጋር የሆነችው ኢትዮጵያ፥ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መሆኗ እየተዘገበ ነው። ለመሆኑ ያች ሃገር ቀውሱ ተባብሶ የከፉ ሁኔታዎች ውስጥ እንዳትወድቅ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሊወስዳቸው የሚችላቸው እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን? ለሚለውም ኮፍማን ጥረታቸው ያ እንዳይሆን መሆኑን ያስረዳሉ። “ቀውስ በተንሰራፋበት የሚሆነውን እናውቃለን። እርግጥ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የገዛ ዜጎቹ ላይ ሽብር እየፈጸመ ነው። መንግስት አልባነት በኢራቅ ይሁን በሊቢያ ያደረገው ቢኖር፤ የአሸባሪዎች መፈልፈያ መሆን ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታዎቹን መለወጥ አለበት። የዚህ ረቂቅ ሕግ መመሪያም ሆነ ሌላው እየሠራን ያለነው ያን ለመከላከል ነው። ” ይላሉ።
a_amh-wfp-horn-drought-9-12-11-125447933_1461018
https://amharic.voanews.com/a/amh-wfp-horn-drought-9-12-11-125447933/1461018.html
በደቡብና ምስራቅ ኢትዮጵያ ከተራቡ ሰዎች በተጨማሪ ሶማሊያዊያን ስደተኞች እርዳታ ይሻሉ
በምስራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ የተራቡ ዜጎችና ስደተኛ ሶማሊያዊያንን ህይወት ለማዳን ከፍተኛ እርዳታ እንደሚያስፈልግ WFP አስታወቀ። ኬንያን ጨምሮ 10 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በ60 አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ ተመትተዋል፡፡ በዚህም መሰረት በአደጋው የተጋለጠውን ህዝብ ለመታደግ ከፍተኛ እርዳታ እንደሚያስፈልግ WFP ገልጿል። በአፍሪቃ ቀንድ በተከሰተው ድርቅ ለከፋ አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን ለመድረስ የያዘውን ጥረት መጨመሩን የተባበሩት መንግስታት ድርግት የምግብ ፕሮግራም WFP አስታወቀ። የአሜሪካ ድምጹ ጋቢ ጆስሎ ከናይሮቢ ባጠናቀረው ዘገባ እንደጠቆመው፤ የተጎዱትን ወገኖች በአስቸኳይ ለመድረስ የሚያስፈልገውን እርዳታ ለማሟላት ድርጅቱ ለተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ጥሪ አቅርቧል። ይህን ያስታወቁት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስነህዝብ የስደተኞችና የፍልሰት ጉዳይ ጽ/ቤት ም/ል ረዳት ጸሃፊ ዶ/ር ሪበን ብርጌቲ ናቸው፡፡ ከዶናልድ ቡዝ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደርና ከዶናልድ ስታይበርግ የአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ተራዲኦ ድርጅት ም/ል አስተዳዳሪ ጋር በጋራ ትላንት አመሻሹ ላይ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያ ውስጥ እየተባባሰ በመጣው ድርቅና ጦርነት የተነሳ ብዙ ሱማሊያውያን ወደኢትዮጵያና ኬንያ እየተሰደዱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ረዳት ጸሃፊው በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በዶሎ አዶ የሰደተኞች ካምፖች የተመለከቱትን ገጽታ አስረድተዋል፡፡ “ዛሬ በዶሎ አዶ የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ የስደተኞች ቁጥር ወደመቶ ሺህ ይጠጋል፡፡ የስደተኞች ጎርፍ በዚሁ ከቀጠለ በአመቱ መጀመሪያ ላይ በእጥፍ ይጨምራል፡፡ ወደ ካምፑ የሚመጡትም በአካልና በጤና የተጎሳቆሉ ናቸው፡፡ በአልተመጣጠነ ምግብ ምክንያት የሚደርሰው ጉዳትም ከ45 እስከ 50 በመቶ ይሆናል፡፡ ይህ በህጻናቱ መካከል 20 በመቶ ይደርሳል፡፡ በሱማሊያ ያለው ግጭት ድርቁን እንዳባባሰውም ተናግረዋል፡፡ አሁን በምስራቅ አፍሪካ የደረሰው ድርቅ በ60 አመታት ውስጥ ያልታየ መሆኑን በመግለጫው ላይ ተገልጿል፡፡ ይህ መቅሰፍት እንደሚመጣም በአሜሪካ መንግስት አስቀድሞ ይታወቅ እንደነበረ የአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ተራዲኦ ድርጅት ም/ል አስተዳዳሪ ዶናልድ ስታይበርግ ተናግረዋል፡፡ ይህ የታወቀውም በሳተላይትና ምድር ላይ በተገኙ መረጃዎች ሳይንሳዊ ትንታኔ መሰረት ነው፡፡ የተፈራው ድርቅም ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ መከሰት ጀመረ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ እርዳታ የሚሹ ዜጎች ቁጥር በሚሊዮኖች መቆጠር ጀምሯል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዶሎ አዶ የሱማሊያ ስደተኞች ጣቢያዎች ውስጥ በየቀኑ ከ2-3 ወይም ከ10 ሺዎች ውስጥ 7 ህጻናት እንደሚሞቱ ተናግረዋል። የዶሎ አዶ ጣቢያዎች ከአሜሪካ ባለስልጣናት በተጨማሪ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ተወካዮች፥ የኢትዮጵያ መንግስት የስደተኞችና ስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ተወካዮች፥ የዩናይትድ ኪንግደም አለማቀፍ ክፍል፥ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እንዲሁም የሲዊዲንና የጃፓን መንግስት ተወካዮች ጎብኝተዋቸዋል።
a_election-followup-opposition-06-08-10-95900214_1462506
https://amharic.voanews.com/a/election-followup-opposition-06-08-10-95900214/1462506.html
ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላም ወከባና እንግልቱ ቀጥሏል፤ በሚለው ተቃዋሚና መንግስት አሁንም እየተወዛገቡ ነው
«ማንም ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዳይዋከብ፤ የልማት ሥራው እንዳይስተጓጎል ግልፅ የመንግስት መመሪያ ወጥቷል፤» አቶ መስፍን አሰፋ።
የምርጫው ማግስት ወከባና እንግልት እንደቀጠለ ነው፤ ሲል የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ገዢውን ኢህአዴግን ይወነጅላል። ኢህአዴግ በበኩሉ «ከምርጫው ጋር በተያያዘ በማንም ላይ እየተወሰደ ያለ ዕርምጃ የለም፤» ሲል ያስተባብላል። ብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መሠረት ምርጫው ሙሉ በሙሉ በኢህአዴግ አሸናፊነት ቢጠናቀቅም፤ «ለታዛቢነት ያቀረብኳቸውና ደጋፊዎቼ ከሥራ መታገድ፥ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ነው፤» ሲል፥ ተቃዋሚው የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ገዢውን ኢህአዴግን ወንጅሏል። ችግሮቹ ተከሰቱ የተባለበት የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር በበኩሉ፥ «ለተቃዋሚው ወገን በምርጫ ታዛቢነት መንቀሳቀስም ሆነ ደጋፊ ወይም አባል መሆን የዜጎች መብት ነው፤ እናም በዚህ ሳቢያ በማንም ላይ ዕርምጃ አልተወሰደም፤» ሲል ውንጀላዎቹን አስተባብሏል። «ማንም ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዳይዋከብ፤ የልማት ሥራው እንዳይስተጓጎል ግልፅ የመንግስት መመሪያ ወጥቷል፤» ሲሉ፥ መንግስታቸውን የተከላከሉት የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ የመረጃና ኅዝብ ግንኙነት ሥራ ሂደት መሪውን አቶ መስፍን አሰፋን ናቸው። «ደጋፊዎቻችን ለስራ አጥነት እየተዳረጉ ነው፤» የሚሉት የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ዋና ፅህፈት ቤት ረዳት ኃላፊ አቶ ኦልባና ሌሊሳ ግን፤ ባለሥልጣናቱ ሳያውቁ የሚፈፀም ምንም እንደሌለ ተናግረው፤ ለችግር የተጋለጡት ወገኖች ከአንዱ የመንግስት ቢሮ ወደ ሌላው ለአቤቱታቸው ሠሚ ሳያገኙ እየተንከራተቱ ነው ብለዋል። የተቃዋሚ ዕጩዎች፥ ስለ ተሸነፉበት ምርጫ ነፃና ትክለኛነት እንዲመሰክሩ፤ በተቃዋሚ የምርጫ ታዛቢነት የተሳተፉት ደግሞ ይቅርታ ጠይቀው ከፈረሙ ብቻ ስራቸውን የሚያገኙ መሆናቸው እየተገለፀላቸው መሆኑን አቶ ኦልባና ዘርዝረዋል። «ለምሳሌ ያህል አቶ ጣሂር ደርሲሶ የተባሉ ታዛቢያችን በምርጫው ዋዜማና በዕለቱ ዕለት በወረዳው የኦህዲድ ፅ/ቤት የታዘዙ ሠዎች በአባታቸው ቤት ውስጥ በሰንሰለት አስረው በታዛቢነታቸው እንዳይሰሩ አድርገዋቸዋል፤» ሲሉ ከምርጫው አስቀድሞም ለተመረጡበት የታዛቢነት ሚና እንዳይበቁ በደጋፊቸው ላይ «ደረሰ፤» ያሉትን ህገ ወጥ ዕርምጃ የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬሱ ተጠሪ በዋቢነት አንስተዋል። ከምርጫው በፊትም ሆነ በምርጫው ወቅት እንዲህ ያሉት ተመሳሳይ ክሶች በተቃዋሚዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፤ ነገር ግን ወደ ማጣራቱ ሲኬድ ዕውነተኛ ሆኖ አይገኝም፤ የሚሉት የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ የመረጃና ኅዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መስፍን ደግሞ «የክሶቹን መሠረተ ቢስነትም ህዝቡ ያውቃል፤» ይላሉ። በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች «እየተፈፀሙ ናቸው፤» የተባሉትን አንዳንድ ክሶች የሚያጣሩ መሆናቸውን አቶ መስፍን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል አመልክተዋል።
a_uganda-blast-0712-10-98264739_1462920
https://amharic.voanews.com/a/uganda-blast-0712-10-98264739/1462920.html
በዩጋንዳ በደረሰ ፍንዳታ 74 ሰዎች ተገደሉ
በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በደረሱ ተከታታይ ፍንዳታዎች ከ70 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ።
አስር ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን መሞታቸው ተዘግቧል ትናንት እሁድ ማታ የአለም ዋንጫ ፍጻሜን በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ሲመለከቱ ነበር ተከታታይ ፍንዳታዎች የኳስ አፍቃሪዎቹ የተሰበሰቡባቸውን ሁለት ስፍራዎች ያናወጡት። አንደኛው የዩጋንዳ ራግቢ ክበብ ሲሆን፤ ሁለተኛው በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን፣ የሌላ አገሮች ዜጎችና ዩጋንዳዊያን የተሰባሰቡበት የኢትዮጵያዊያን የገጠር ምግብ ቤት ነበር። “የመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታ በማብቃት ላይ ሳለ ነው ፍንዳታው የተከሰተው…ወዲያው ሰው መጮህ ጀመረ፣ ከአካባቢው ለመራቅ በነጫጭ የፕላስቲክ ወንበሮች ላይ እየዘለለ ነበር የሚሄደው፣” ሲል ላለፉት ስድስት ወራት በካምፓላ የኖረውና ለጋዜጠኝነት ትምህርት ወደዚያው ያመራው ተስፋለም ወልደየስ ለቪኦኤ ተናግሯል። በተመሳሳይ ሰአት በዩጋንዳ ራግቢ ክበብ የደረሱ ፍንዳታዎችም እንዲሁ በርካታዎችን አቁስለዋል። ዛሬ ማለዳ የዩጋንጋ ፖሊስ ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫ የሟቾቹ ቁጥር 74 ሲደርስ ከሰባ የማያንሱ ደግሞ ቆስለዋል። መሟቾቹ መካከል ወደ አስር የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን እንደሚገኙበት ታቋል። በተለያዩ ዜጎች የሚዘወተረው የኢትዮጵያ ምግብ ቤት የደረሰው ፍንዳታ አንድ-አሜሪካዊ መግደሉም ተዘግቧል። “አንድ አሜሪካዊ ሞቷል። ጉዳት የደረሰባቸውን አሜሪካዊያን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማጠያየቅ እየሞከርን ነው፣” ሲሉ በካምፓላ የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ ቃል አቀባይ ጆዋን ሎካርድ ተናግረዋል። ጥቃቱን ተከትሎ በርካታ መሪዎች መግለጫ አውጥተዋል። የዩናይትድ ስቴይትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ “አሳፋሪ የፈሪዎች ተግባር ሲሉት” የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን የዩጋንዳ መንግስት ወንጀለኞቹን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል-አቀባይ በረከት ስም-ኦን በአልሸባብ የተሰነዘረ “የፈሪ ዱላ” ብለውታል። የዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አገራቸው በሞቃዲሹ ካላት ሀላፊነት አታፈገፍግም ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ይህንን የተናገሩት አስቀድሞ የነበረውን ጥርጣሬ በመመርኮዝ ነው። ጉዳቱ እንደደረሰ- በአል-ቃይዳ የሚታገዘው የሶማሊያ የሽብርተኞች ቡድን አል-ሸባብ የአጥፍቶ ማጥፋት ጥቃቱን በማቀነባበር በመጠርጠሩ ነው። ከአል-ቃይዳ ጋር ግንኙንት እንዳለው የሚነገረው የሶማሊያ አንጃ አል-ሸባብ ጥቃቱን መፈጸሙን ሰኞለት አምኗል። “በካምፓላ የተከሰተው አገሪቱ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ስራ ላይ ከመሰማራቷ ጋር የተያያዘ ነው፣” ሲሉ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽነር ራምታኔ ላማምራ ዛሬ በአዲስ አበባ ተናግረዋል። ሚስተር ላማምራ ጥቃቱ የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ በአስቸኳይ ሊያሰፍር ያሰባቸውን የ2ሽህ ወታደሮችና አጠቃላይ የ8ሽህ ግብረ-ሀይል እቅድ አያስተጓጉለውም፤ እንዲያውም ከምን ጊዜውም በበለጠ ሁኔታ በሶማሊያ የሚኖረንን ስራ ያጠናክረዋል ብለዋል። በካምፓላ ከደርግ አስተዳደር ጀምሮ በአሁኑ መንግስትም ጭምር በፖለቲካ ስደትና በንግድ የሚኖሩ በሽዎች የተቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ይገኛሉ።
a_amh-debt-us-7-20-11-125912468_1459491
https://amharic.voanews.com/a/amh-debt-us-7-20-11-125912468/1459491.html
የዩናይትድ ስቴይትስ የብድር ጣራ በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካኖች መካከል ያስነሳው ውዝግብ ቀጥሏል
የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት እንዲበደር የሚፈቀድለት የ14.3 ትሪሊየን ዶላር ጣራ እንዲነሳለት የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አስተዳድር የህዝብ ተወካዮችን በኮንግረስ በመጠየቅ ላይ ነው
የዩናይትድ ስቴይትስ የብድር ጣራ መነሳትና አለመነሳት የሰሞኑ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት ሆኖ ነው የሰነበተው። የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በበጀት መጓደል የገጠሙትን እክሎች ሊያስተካክል፤ የመንግስቱን ወጭ በመቀነስ ላይ ባለበት ወቅት፤ አገሪቱ ተጨማሪ ብድር የምታገኝበትና፤ ከዚህ ቀደመ የቆዩ ብድሮቿን ለመክፈል እንድትችል፤ ተጨማሪ ብድር የማግኘት እድሏ በህግ ቋጠሮ ተበጅቶለታል። የባራክ ኦባማ አስተዳድር የአሜሪካ የብድር ጣራ ካልተነሳ አገሪቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ትወድቃለች በሚል አምርሮ በመከራከር ላይ ይገኛል። የህዝብ ተወካዮች በሚገኙበት ኮንግረስም ክርክሩ በዴሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች ጦፏል። ዴሞክራቶቹ ከኦባማ ጎን ተሰልፈዋል፤ ሪፐብሊካኖቹ የብድር ጣራውን አናነሳም ብለዋል። በትናንትናውለት ፕሬዝደንት ኦባማ በዋይት ሃውስ ቤተመንግስት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ አስተዳደራቸው ከኮንግረስ መሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት መጠነኛ እመርታዎች ቢታዩም፤ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ነገሮች እየጠበቡ መሄዳቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ለሳምንታት የዘለቀው ክርክር በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካኖች በይፋ በመገናኛ ብዙሃንና በዝግ በሚደረጉ ድርድሮችና ስብሰባዎችም ጭምር ሲስተጋቡ ቆይተዋል። የዩናትድ ስቴይት የነጻነት ቀን በሰኔ ወር ማብቂያ ላይ ሲከበር ፕሬዝደንት ኦባማ በብድር ጣራው ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሄ ያሻዋል ብለዋል። “ባለፉት አስርት አመታት ዋሽንግተን የአገሪቱን ብድር ጣራዊን ካስነካችው በኋላ፤ አሁን ተቀማጭ ገንዘባችንን መጨመር ይገባናል” ብለዋል ኦባማ። ፕሬዝደንቱ አክለውም ሁሉንም ዘርፎች ተመልክቶ የቀረጥ እፎይታ በበጀቱ መካተት እንደሚገባውና አስተዳደራቸው ሁሉንም ተመልክቶ ገንዘብ የሚባክንባቸውን ፕሮጀክቶች በማቆም ገንዘብ እንደሚቆጥብ ገልጸዋል። የዩናይትድ ስቴይትስ ኢኮኖሚ ከአለም የገንዘባ ውድቀት ወዲህ ከገባበት አዘቅት ለመውጣት በሚፍጨረጨርበት ወቅት፤ መንግስቱ የበጀት አለመመጣጠን ገጥሞታል፣ በዚያ ላይ የብድር ጣራው ሰማይ ነክቷል። ሪፐብሊካኖች ለዚህ ችግር መፍትሄው፤ መንግስት ወጭውን መቀነሱ ነው ይላሉ። “የሌለንን ገንዘብ ልናወጣ አንችልም። ከዋሽንግተን የሚመጣ አንድ ዶላር ውስጥ 42 ሳንቲሙ በብድር የተገኘ ነው። ከዚህ ውስጥ 47 ከመቶው ከውጭ የተገኘ ብድር ነው፤ ቻይና ቁጥራ 1 አበዳሪያችን ናት” ብለዋል በኮንግረስ የበጀት ኮሚቴ ሊቀ-መንበር ሪፐብሊካን ፖል ራያን። ዴሞክራቶቹ በበኩላቸው የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት የቀረጥ ገቢ ከ1950ዎቹ ወዲህ በጣም ዝቅ ያለ መሆኑን ይጠቅሳሉ። “በምናደርጋቸው ድርድሮች እንዳየንው፤ ሪፐሊካን ጓዶቻችን የአገሪቱን ኢኮኖሚ አዝቅት ውስጥ ማስገባት ግድ አይሰጣቸውም። እንዲያውም ባንጻሩ የቀረጥ እፎይታዎች እንዲነሱ ፈጽሞ አይፈልጉም” ብለዋል የኒውዮርኩ ዴሞክራት ሴናተር ቻርልስ ሹመር። ሪፐብሊካኖች የመንግስትን ገቢ ለመጨመር ቀረጥ መጨመር የሚለውን አሳብ አይደግፉትም። የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት ያለበትን የ1.5 ትሪሊየን የበጀት መጓደል ከማሟላት ይልቅ፤ የቀረጥ ገቢው ሲጨምር ተጨማሪ ገንዘብ ያወጣል ሲሉ አጥብቀው ይከራከራሉ። “ችግራችን ትንሽ ቀረጥ መክፈላችን አይደለም። ከዚህ ሁሉ የፖለቲካ ክርክር በኋላ አሜሪካኖች ከሀምሌ 26 በፊት ውሳኔ ማሳለፍ ይኖርባቸዋል። የብድር ጣራውን ማንሳት፤ አለማንሳት፤ የበጀት መጓደሉ እንዴት እንደሚስተካከልና የቀረጥ ጉዳይ ከዚች ቀን በፊት ውሳኔ ማግኘት ይገባቸዋል። ፕሬዝደንት ኦባማና አስተዳደራቸው ተስፋ ሰንቀዋል። ከምርጫና ከድምጽ ማግኘት አንጻር የሚደረጉ የፖለቲካ ክርክሮች ቢበረቱም፤ በስተመጨረሻ የብድር ጣራው እንደሚነሳ እምነት አላቸው። “ዴሞክራሲ ሁሌ የተዋበ አሰራር አይደለም። እንከራከራለን በሃሳብ አንስማማም፤ ነገር ግን በተደጋጋሚ ያረጋገጥንው ነገር ቢኖር ችግሮችን ለመፍታት አብረን እንደምንሰራ ነው። በሁሉም ጉዳዮች ላይ አይን ለአይን ባንተያይም አገራችንን እንወዳለን፣ በወደፊት ተስፋዋም የጋር እምነት አለን። ይሄንን ስሜት ነው አሁን ልናስተጋባ የሚገባን” ብለዋል ፕሬዝደንት ኦባማ። በሴኔቱ ተቀባይነት ያላቸው ፖለቲከኞች ተሰባስበው ጉዳዮን ለመሸምገል ጥረት ይዘዋል። እነዚህ ፖለቲከኞች የመንግስቱን ወጭ ለመቀነስና ዩናይትድ ስቴይትስ ብድሯን የምትከፍልበትን መንገድ ለማመቻቸት ጥረት ይዘዋል።
a_eu-election-observers-report-05-25-10-94872039_1458991
https://amharic.voanews.com/a/eu-election-observers-report-05-25-10-94872039/1458991.html
የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ሰላማዊ ቢሆንም በእኩል ሜዳ አለመደረጉን ገለጸ
ምርጫው ከፍተኛ ብዛት ያላቸው መራጮች የተሳተፉበትና ሰላማዊ ቢሆንም እየጠበበ በሄደው የፖለቲካ ምህዳርና እኩልነት በጎደለው የመወዳደርያ ሜዳ መዘፈቁ አልቀርም ሲሉ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ገለጹ።
ባለፈው እሁድ ግንቦት 15 ቀን 2002 አም በኢትዮጵያ የተካሂደውን ምክር ቤታዊ ምርጫ የተከታተለው የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ታይስ በርማን የምርጫውን ሂደት ጠንካራና ደካማ ጎን ሲገመግሙ አራተኛው አጠቃላይ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ባለድርሻ አካላት በአንድነት ተቀብለውታል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድም ምርጫውን በበቂ ሁኔታ አስተዳድሯል። ይሁንና በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚነሱትን የኢወገኝተኛነት ጥያቄን ለመመለስ አልቻለም ብለዋል በርማን። ታይስ በርማን ይህን ያሉት ዛሬ ማክሰኞ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ከእኩለ ቀን በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ሚስተር በርማን በተጨማሪም “በገዢው ፓርቲና በመንግስታዊ አስተዳደር መካከል መኖር የሚገባው ልዩነት በብዙ የተለያዩ ቦታዎች ደብዝዞ ታይቷል። የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን የመንግስት ንብረቶች ለገዢው ፓርቲ የምርጫ ዘመቻ መገልገያነት መዋላቸውን አስተውሏል። ቡድኑ የ 2002 የምርጫ ሜዳ በበቂ ሚዛን አልጠበቀም። በብዙ ቦታዎች ለገዢው ፓርቲ ያጋደለ ነበር የሚል እምነት አለው። ” በማለት ገምግመዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ቴክኒካዊ ችግሮችን ብቃት ባለው ሙያዊ ተግባር ተወጥቷል። በማለትም አመስግነዋል። ሙሉ የምርጫ ጣብያዎች ዝርዝርን የመሳሰሉት መረጃዎች አለመኖራቸው ግን በሂደቱ ግልጽነት ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ብለዋል። ስለሚድያ ሲናገሩ ደግሞ የአሜሪካ ድምጽ ሪድዮ የአማርኛ አገልግሎት መታፈንም የመራጮችን ከዘርፈ ብዙ ምንጮች ኢንፎርመሻን የማግኘት ዕድል ቀንሷል ብለዋል የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ታይስ በርማን።
a_oromya-flood-08-27-10-101798503_1459111
https://amharic.voanews.com/a/oromya-flood-08-27-10-101798503/1459111.html
በኦሮሚያ ክልል የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪዎች በጎርፍ ተጠቃን ይላሉ፤ አስተዳደሩ ጉዳቱ መጠነኛ ነው ብሏል
በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ በአማራ ክልል ከ37 ሰዎች በላይ የገደለው የጎርፍ አደጋ በኦሮሚያም ተከስቷል።
በኦሮሚያ በህይወት ላይ ጉዳት አልደረሰም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ጎርፍ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። በአካባቢው የሚገኝ የሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤት ክፉኛ በጎርፍ መመታቱን ቦሩ ሮባ የተባሉ የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪ ለቮኦኤ ገልጸዋል። “የደረሰው ጉዳት በጣም ከባድ ነው። ጉዲና ቱምሳ GTS የተባለ ሃይስኩል (ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) አለ። ያን ትምህርት ቤት እንዳለ ወስዶታል (ጎርፍ)” ብለዋል አቶ ቦሩ ሮባ። የምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳድር በበኩሉ መጠነኛ ጎርፍ በመተሃራ ከተማ አቅራቢያ እንደነበረና ያስከተልው ከፍተኛ ጉዳት እንደሌለ ለቪኦኤ አብራርቷል። የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብራሃም አዱላ ጉዳቱ መጠነኛ ነው ብለዋል። “የፈንታሌ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው መተሃራ አቅራቢያ በሰቃ ሀይቅ የሚባል የተፈጥሮ ሃይቅ አለ። በበጋው ወር ውስጥም አልፎ አልፎ ዝናብ ይዘንብ ስለነበረ፤ መጀመሪያ ካለው የውሃ ይዘቱ የጨመረበት ሁኔታ አለ፤” ብለዋል። በመተሃራ የስኳር ፋብሪካና በግል የከብት ማደለቢያ አካባቢ የተወሰነ ጥፋት መድረሱንና የሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤት በጎርፍ መጥለቅለቁን የተናገሩት አቶ አብርሃም አዱላ፤ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጠዋል። ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል አከታትሎ የጣለው ዝናብ በአምስት ወረዳዎች 37 ሰዎችን ሲገድል ከ6ሽህ በላይ ሰዎችን ማፈናቀሉን የክልሉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የአስቸኳይ ጊዜ ሰራተኞች የተጎጂዎቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል በመግለጽ ላይ ናቸው። የክረምቱ ዝናብ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ድርጅት አስታውቋል።
a_henok-youth-white-house-08-03-10-99888544_1460928
https://amharic.voanews.com/a/henok-youth-white-house-08-03-10-99888544/1460928.html
ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ከወጣት የአፍሪካ ሃሳብ አፍላቂዎችና መሪዎች ጋር ተገናኙ
የአፍሪካ የወደፊት የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የምህበራዊ ተቋማት መሪ የሆኑ ወጣቶች እርስ በርስ ልምድ ይለዋወጣሉ፤ ከታላላቆቻቸውም ተሞክሮ ይካፈላሉ።
ጉባኤው እስከ ሀሙስ ድረስ ይቀጥላል ከ45 የአፍሪካ አገሮች የተሰባሰቡት 115 ወጣቶች ዛሬ ማለዳ በውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ለአራት ቀናት የሚዘልቀውን ውይይታቸውንና የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብራቸውን ጀምረዋል። እነዚህ በሚኖሩበት አገር በአነስተኛና ከፍተኛ የማህበራዊ መሪነት ጉልህ ሚና የተጫወቱ ወጣቶች ለአፍሪካ የወደፊት ተስፋዎቿ፣ አሁን ደግሞ የእድገት ክንዶቿ ናቸው ሲሉ የዩናይትድ ስቴይትስ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን በስብሰባው መክፈቻ ተናግረዋል። በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ-ግዛት ነጻ የወጡበትን 50ኛ አመት በማክበር ላይ ባሉበት ወቅት የወደፊትና የአሁን የአህጉሪቷን መሪዎች አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አምነው ነው ፕሬዝደንት ኦባማ በዋይት ሃውስ እነዚህን ወጣቶች ለውይይት የጠሩት። ወደ ዋይት ሃውስ ከማምራታቸው በፊት ግን እነዚህ ወጣቶች እርስ በርስ በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይተዋል። በርካታ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና ልምዶችን ከየአገራቸው ይዘው የመጡት ወጣቶች እርስ በርስ እየተማማሩ ችግሮቻቸውን ከባለሙያዎች ጋር እየተወያዩ አርፍደዋል። ከኢትዮጵያም 4 ተሳታፊዎች መጥተዋል። አንዳንዶቹ በወጣቶች ማህበር የተሰባሰቡ አቀንቃኞች ሲሆኑ፤ ሌሎቹ ደግሞ እጅጊያቸውን ሰብስበው በስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው። ይሄ ስብሰባ ታዲያ ለሁሉም ነው። ግንዛቤ መፍጠር፣ አቅም መገንባትና የተሰሩ ተግባራዊ ስራዎችን ደግሞ ለሌሎች ማሳየት ነው አላማው። እኛ የወጣት ጉዳይን ይዘው በየስብሰባው ለሚሳተፉ ቦታ የለንም፤ በስራ የተሰማራችሁ ካላችሁ ግን ስራችሁን አሳዩንና ወደ ትልቅ ደረጃ እናድርሰው ሲሉ የተናገሩት ደግሞ TED የተባለው የፈጣሪ ጭንቅላት ያላቸውን አፍሪካዊያን ወጣቶች የሚያግዝ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ለምሳሌ በመንደራቸው ከንፋስ መዘውር የሚሰራ የሀይል ማመንጫ እንደገነባው የማላዊው የ12 አመት ወጣት ዊሊያም ኳምክእ`ምባ አይነት ፈጣሪዎችን ያግዛል። በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚገኙ እድገቶችን፣ ማህበራዊ ችግሮችን የመፍቻ አዲስ መንገዶችን፤ ሰርቶ የማደርና ኑሮን የማሸነፍ ውጤቶችን ያበረታታል። በዚህ ጉባኤ የሚሳተፉት ወጣቶች ታዲያ እንዲህ ያለ ድጋፍ ከሚሰጡ ድርጅቶች ተወካዮችም ጋር ይወያያሉ፣ ሃሳብ ይለዋወጣሉ፣ ተዋውቀውም ወደፊት ለሚሰሩት ስራ ድጋፍ ያመቻቻሉ። ይህንን ነው ፕሬዝደንት ኦባማም የአፍሪካ ወጣቶች እንዲያደርጉ አስበው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የጠሯቸው።
a_amh-wfp-famin-7-21-11-125957683_1459934
https://amharic.voanews.com/a/amh-wfp-famin-7-21-11-125957683/1459934.html
በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ከብቶች እየሞቱ ነው
በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ፣ በሶማሊያና በኬንያ የተከሰተው ድርቅ ወደርሃብ በመሸጋገር ላይ በመሆኑ ከፍተኛ እልቂት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ የዓለም የምግብ ድርጅትና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስጠነቀቁ።
በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ ወደርሃብ መሸጋገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ እርዳታ በማይደርስባቸው የሶማሊያ ደቡባዊ ቀጣናዎች ድርቅ ያስከተለው ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት ዕለቂት ሊያስከትል ወደሚችል ርሃብ መሽጋገሩን የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይፋ አደረጉ። የአፍሪካ ህብረትና የዓለሙ ድርጅት የደረሰውን ሰባዊ ቀውስ ለመታደግ በትብብር እንዲንቀሳቀሱ ጠየቁ። የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጆሴት ሽራም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ኢራስተስ ሞኤንቻ ጋር በመሆን በአፍሪካ ህብረት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው ድርቅና ያስከተለው ቀውስ መከታተል ድርጅታቸው በዓለም ላይ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። ድርቁ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶማሊያ ኬንያና ኡጋንዳ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። የዚህ ሰባዊ ቀውስ ዋና ተጠቂ የደቡብ ሱማሊያ ክፍል ነው ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። “ ሁኔታው ከባድ ጥፋት እያስከተለ ነው። ሆኖም በቁጥጥር ስር ነው። የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ እየጨመረ ነው። ስለሆነም በማንደርስባቸው አካባቢዎች ካልሆነ በስተቀር የሰው ህይወት አልጠፋም” ብለዋል ሽራም። “እንዳለን መረጃ ከሆነ ሰባ በመቶ የሚሆነው የሶማሊያ ህዝብ ዕርዳታ ማግኘት በሚችልበት ሁኔታ ላይ አይደለም። ይህ ደግሞ ሰባዊ ቀውስ ፈጥሯል። በታሪክ እንደታየው ድርቁ እየከፋ በሄደ ቁጥር ሰባዊ ቀውሱ እየከፋይሄዳል ይላሉ ሽራም። በአፍሪካ ቀንድ ድርቁ በስፋት የደረሰ ቢሆንም የሰው ህወት አልጠፋም ያሉት ጅሴት ሽራም መድረስ ያልተቻለባቸው የሱማሌ አካባቢዎች ግን ድርቁ ወደርሃብ ተሸጋግሯል። “የአሰራር ፕሮቶኮል የምንመሰርትበትን ብልሃት በማፈላለግ ያስቸኳይ ጊዜ እርዳታዎች አከማችተን በደቡብ ሱማሊያ የችጋር ቀጣናዎች ተብለው ወደተለያዩ አካባቢዎች ለመድረስና ሕይወት ለማዳን እየሞከርን ነው። ሚስ ሽራም ይህን ቀውስ ለመፍታት የሚያስፍልገውን እርዳታ ለመሰብሰብ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይገባል ብልዋል። “የእርዳርታውን ቁሳቁስ ባስቸኳይ ማሰባሰብ ያስፈልጋል። አሁን ያለን ጉድለት $190 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይሄ ደግሞ ለተጠበቀው 6 ሚሊዮን እርዳታ ጠባቂ ህዝብ ነበረ። በግንቦትና ሰኔ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ስላልጣለ ይህ የርዳታ ጠባቂ ቁጥር ወደ 11 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይጠበቃል። ይሄ በደቡብ ሶማሊያ ያሉትን ለመድረስ ተስፋ በማድረግ ነው። ድርቁ በኢትዮጵያ ያስከተለውን ችግርም በጥልቀት ዘርዝረዋል። “በኢትዮጵያ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ በሚገኙ ሰፊ አካባቢዎች ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በተለይም አርብቶ አደሩ በቀውስ ውስጥ ይገኛል። ይኽ ቀውስ ለረጅም ጊዜ የቆየ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታትም ብዙዎች ከብቶቻቸውን አጥተዋል። ሌሎች በርካቶችም ያላቸውን ሁሉ ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ አጥተዋል። እናም በአርብቶ አደሮች ላይ የደረሰው ቀውስ በጥልቁ ያሳስበናል። ዳይሬክተሯ ድርቁ ያስከተለውን ቀውስ ለመቋቋም ከአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጋር በጥልቀት ተወያይተዋል። የህብረቱ ረዳት ኮሚሽነር ኢራስተስ ሞኤንቻም ስለውይይታቸው ትኩረት ይህን ብለዋል። “ትኩረታችን አሁን በምናየው ቀውስ ላይ ብቻ አይደለም። እንዲህ አይነት ሁኔታን እንዴት መከላከልና ማለዘብ እንችላለን በሚለው የወደፊቱን ጊዜ ጭምር ነው። አቅምን በመገንባት ላይ ዘላቂነት ያላቸው መፍትሄዎች በመዘርጋት ላይ ነበር አተኩረን የተነጋገርነው። 13 የድርጅቱ ሰራተኞች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በስራላይ እንዳሉ መገደላቸውን ጆሴት ሽራም አውስተው የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተባብረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል
a_voa-radio-mag-stories-with-alula-kebede-and-addisu-abebe-11-22-15_3073955
https://amharic.voanews.com/a/voa-radio-mag-stories-with-alula-kebede-and-addisu-abebe-11-22-15/3073955.html
የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች፥ አዲሱ ሰባት ኪሎ መጽሔት፥ እና ሌሎች ሙዚቃ ነክ ወጎችና የሃሳብ መስመሮች፤
የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
“ሰባት ኪሎ” የሚል ሥያሜ ስለ ሰጡትና በቅርቡ ለንባብ ስለ በቃው መጽሔታቸው፥ ጋዜጠኝነት በስደትና መንገዶቹ የሚያወጉን እንግዶች፤ ከቀድሞዎቹ አዲስ-ነገሮች ሁለቱ ለራዲዮ መጽሔት ወግ ተሰይመዋል። ከዓመታት በፊት “መርካቶ ሰፈሬ፤” በተሰኘችው ዜማው ከሙዚቃ አድናቂዎች ጋር የተዋወቀው ድምጻዊ አብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ” በሚል ሥም ያወጣውን አዲስ አልበም ይዞ ብቅ ብሏል። በእንግሊዥናው ምሕጻረ ቃል AFRIMA በመባል ለሚታወቀው “የመላው አፍሪቃ ዓመታዊ የሙዚቃ ሽልማት” ለሁለተኛ ጋዜ ከተመረጠችው ድምጻዊት ጸደኒያ ገብረማርቆስ ስለ ሽልማቷ፥ የውድድሩ ሂደትና ሌሎች ተዛማች ርዕሶች እንነጋገራለን። “የሃሳብ መስመር” ... የተለያዩ ጉዳዮችንና ሁኔታዎችን የሚመለከቱ ጭብጦች መናሃሪያ ነው። እውነት ምንድ ናት? በሚል ጥያቄ ዙሪያ ያጠነጥናል። ሕዳር ይታጠናል። የዕለቱ የታሪክ ማስታወሻ ከአዲስ አበባ ተቀናብሯል። የሳምንቱን የራዲዮ መፅሔት ወጎች እነሆ፤
a_a-53-2008-04-30-voa2-93031129_1457722
https://amharic.voanews.com/a/a-53-2008-04-30-voa2-93031129/1457722.html
African Athletics Championships DAY 1: Ethiopia Sweeps Medals in the Men’s 10,000 meters
Gebreegziabher Gebremariam led the Ethiopian trio to victory and finishing the10,000 meteres in 28:17.11.
10,000 m - MENS FINAL RANK NAME NAT 1. Gebregziabh. GEBREMARIAM ETH 28:17.11 2. Ebrahim JEILAN ETH 28:30.66 3. Eshetu WONDEMU ETH 28:56.36 4. John KORIR KEN 29:07.33 5. Bernard SANG KEN 29:47.61 6. Julius KIPTOO KEN 30:12.10 SHOTPUT - MENS FINAL RANK NAME NAT RESULT 1. Abdu Moaty MOUSTAFA EGY 18.06 2. Yasser IBRAHIM EGY 17.39 3. Janus ROBBERTS RSA 16.44 HAMMER - WOMENS FINAL RANK NAME NAT RESULT 1. Marwa HUSSIN EGY 62.26 2. Florence EZEH 61.26 3. Funke ADEOYE NIG 57.02
a_inventions-for-though-times-3d-printers-ppe-faruk-mubarek-with-voa-alula-kebede-may-2020_5437346
https://amharic.voanews.com/a/inventions-for-though-times-3d-printers-ppe-faruk-mubarek-with-voa-alula-kebede-may-2020/5437346.html
ሕይወት ለማዳን የዋለ ጥበብ እና አሳቢነት
“እንደሚታወቀው አገራችን ደካማ የሚባል የጤና ሥርዓት ነው ያላት አገር ነች። ከዚህ በፊት በተክለምዶ የተለያዩ እርዳታዎች ከውጭ ይመጡ ነበር። አሁን ግን ያደጉትን አገሮች ብንመለከት አራቸውን ዘግተው ራሳቸውን ለማዳን እየተረባረቡ ናቸው። ‘የስሪ ዲ ኮሚኒቲዎች’ እና ቴክኖጂውንም ሳይ ደግሞ ብዙው የውሚሰሩት ራሳቸውን ለመጥቀም ነው። ስለዚህ እኛም ለምን ይሄንን ወስደን ራሳችንን ለምን አናድንም ከሚል ነው የተነሳሁት።” ፋሩቅ ሙባረክ።
ዋሽንግተን ዲሲ - አዲስ አበባ — ክፍል ሁለት ከጊዜያችን ብርቱ ፈተናዎች አንዱ ለሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ የሚውሉ ሁነኛ መላ ፍለጋ የሚደረገው ጥረት በሁሉም አቅጣጫ ቀጥሏል። በዚህ መላውን የሰው ልጆች በገጠመ ፈተና እንደየተሰማሩበት ሞያና እንደየክህሎቶቻቸው የተያዘው ጥረት አጋዥ ለመሆን የበኩላቸውን ለማድረግ ደፋ ቀና የሚሉት ብዙዎች ናቸው። የወረርሽኙን የጥድፊያ መዛመት ለመግታትት ሁነኛ የመከላከያ ብልሃቶችን በመቀየስ አገራዊውን ጥረት ከሚያጎለብቱት፤ ከፍተኛ እጥረት የሚታይባቸውን አስፈላጊ ቁሳቁሶች እጥረት ለመቀነስ የሚያግዙ መላዎችን እስከሚፈነጥቁት ይዘልቃሉ። የኮቪድ 19 ህሙማንን ለመርዳት በግንባር የተሰለፉትየሕክምና ባለሞያዎች ለበሽታው እንዳይጋለጡ ለማድረግ በታለመ ጥረት '3D ፕሪንተር' በመባል የሚታወቀውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የመከላከያ ቁሳቁሶችን በመስራት ላይ የሚገኝ ወጣት ነው። ፋሩቅ ሙባረክ ይባላል። ስለ ስራውና ለዚህ መልካም ዓላማ ያነሳሱትን ምክኒያቶች ጨምሮ ሊያጫውተን ከአዲስ አበባ በስልኩ መስመር ብቅ ብሏል። የቃለ ምልልሳችንን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ። ክፍል አንድ
a_south-sudan-independence-7-11-2011-125348308_1459557
https://amharic.voanews.com/a/south-sudan-independence-7-11-2011-125348308/1459557.html
የደቡብ ሱዳን አስተዳድር ከጎረቤቶቹ ጋር አብሮ ለመስራት እጁን ዘረጋ
ሀምሌ 2 ቀን 2003ዓም የአለማችን አዲሲቱ አገር ደቡብ ሱዳን ተወለደችበት እለት ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ባሰሙት ንግግር አገራቸው የመልካም ጉርብትናና የትብብር እጇን እንደምትዘረጋ ገልጸዋል።
ቅዳሜለት በመዲናዋ ጁባ በተደረገ ስነስርዓት በአስር ሽዎች የተቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ዜጎች በአለም መሪዎች ታዛቢነት የአዲስ አገር ምስረታ በዓላቸውን አክብረዋል። ከዋዜማው ጀምሮ ማምሻውን በጸሎትና በባህላዊ ጭፈራዎች ደምቆ ያመሸው የነጻነት ዋዜማ፤ ቅዳሜ ማለዳ ባንዲራ ይዘው ለነጻነት ክብረበዓሉ በወጡ ዜጎች ታጅቦ፣ በአለም መሪዎች ታዛቢነት ተበስሯል። የደቡብ ሱዳን አስተዳድር ፕሬዝደንት የነበሩት ሳልቫ ኪር፤ የአዲሱቱ አገር ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ ማሃላ ፈጽመዋል፤ ሃገሪቱ የምትተዳደርበትን ህገ-መንግስትንም በፊርማቸው አጽድቀዋል። ፕሬዝደንት ኪር በትረ-ስልጣኑን ከተረከቡ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ ደቡብ ሱዳናዊያን ለዛሬዋ የነጻነት ቀን እውን መሆን ለከፈሉት መስዋእትነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተለይ የሱዳን ህዝቦች የነጻነት ጦር (SPLA) ን የመሰረቱትን ጆን ጋራንግ አመስግነዋል። “ለ56 ዓመታት የጠበቅናት ቀን ናት። ህልማችን ዛሬ እውን ሆኗል” ብለዋል ኪር “ውድ ጓዶቼ የዛሬዋ ቀን ለነጻነት ለወደቁ ጀግንኖቻችን ልባዊ የሆነ ምስጋናና አክብሮት የምናቀርብበት ሊሆን ይገባል። ከዚህ ንግግር አስቀድሞ የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽር ባሰሙት ንግግር፤ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክን እውቅና የሰጠችው የመጀመሪያዋ አገር ሱዳን መሆኗን ተናግረዋል። ለአዲሲቷ አገር መልካም እድል የተመኙት አል-በሽር፤ መንግስታቸው አሁን ጎረቤት ከሆነችው ደቡብ ሱዳን መልካም ንግኙነት እንደሚሻም ይፋ አድርገዋል። ደቡብና ሰሜን ሱዳን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍርጫቸው የቆየ ነው። ሱዳን ከግብጽና ከብርታንያ ጥምር የቅኝ አገዛዝ እንደ እ.ኤ.አ በ1956 ዓም ነጻ ከወጣች ወዲህ በሱዳን ሰላም አልታየም። የቀደሙ የትጥቅ ትግሎችን ተከትሎ የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጭ ጦር (SPLA) በዶ.ር ጆን ጋራንግ ከተመሰረተ ወዲህ፤ ከሁለት አስርት አመታት በላይ በደቡብና ሰሜን ሱዳን መካከል መሪር ውጊያ ተካሂዷል። በነዚህ የጦርነት ዘመን ደቡብ ሱዳናዊያን ተሰደዋል፣ ተርበዋል ተጠምተዋል። “ይቅር እንላለን ግን አንረሳም! ” ብለዋል ኪር። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር አክለውም ከጎረቤቶቻቸው ጋር በሰላም፣ በልማትና አብሮ በመስራት የሚያተኩር ግንኙነት ለመፍጠር መንግስታቸውና ህዝቦቻቸው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። “ከሱዳን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር እንዲሁም ከሁሉም ጎረቤቱቻችን ጋር በህብረት ከህዝባችን ጋር በጸባይም ሆነ በምግባርም የሰመረ ግንኙነት እንዲኖረን፣ በሰላም መልካም የጉርብትና እጆቻችንን እዘረጋለን” ብለዋል ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር። በደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የነጻነት በአል ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪሙን፣ የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽርና ሌሎችም የአለም መሪዎች ተገኝተዋል።
a_usaid-officials-ethiopia-127886433_1462105
https://amharic.voanews.com/a/usaid-officials-ethiopia-127886433/1462105.html
የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት አሞገሱ
የ United States የአለም አቀፍ ረዴት ባለስልጣን በኢትዮጵያ ረሀብ እንዳልጋባ ገለጹ
የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ገለጹ። አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎችም እርዳታውን እያገኙ ናቸው ብለዋል ባለስልጣናቱ። በ United States አለም አቀፍ የተራዶ ድርጀት ከፍተኛ ምክትል የእርዳታ አስተባባሪ Gregory Gotlied በአዲስ አበባ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሲም አልሱ፣ “በኢትዮጵያ ረሃብ የለም እንላለን። አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በሱማልያ ያለውን ሁኔታ አይመስልም። ያ ረሃብ ነው። የእነዚህ በተመጣጠነ ምግብ እጦት ከሚታይ ጉዳት በላይ ነው። እዚህ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ አይነት ሁኔታ የለም። እና በዚያ ረገድ እዚህ ይሻላል። " ሲሉ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ አብራርተዋል። ኤቶጵያ ውስጥ በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጎዱ ህጻናት ክሊኒክ ሄደው ተገቢውን ህክምና እንደሚያገኙ ከምግብ ዋስትና አኳያም ተስፋ የሚያሳድሩ አዝማምያዎች አሉ ሲሉ የአሜሪካው ባለስልጣን አስገንዝበዋል።
a_meles-press-conference-05-27-10-95042384_1462514
https://amharic.voanews.com/a/meles-press-conference-05-27-10-95042384/1462514.html
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችን ነቀፉ፤
"የምርጫው ውጤት ትብብራችንን ለመቀጠል የሚያስችል አይደለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ - መልካም፤ እስከዛሬ ላደረጉልን እርዳታ እያመሠገንን ወደፊት መቀጠል ነው፡፡" መለስ ስለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አቋም ሲናገሩ፡፡
መለስ ዜናዊ “የአውሮፓ ኅብረት ታዛቢዎች የፖለቲካ ድምዳሜውን ለራሣቸው ዓላማ በሚመጥን መልኩ የሰፉት ስለሆነ እኛ ልንለብሰው አንችልም’ አሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ትላንት በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርተዋል፡፡ የሃገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች ያነሷቸው ጥያቄዎች ከምርጫው ጋር የተያያዙ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ካለፉት ምርጫዎች ሁሉ በተለየ ሁኔታ ገዥው ፓርቲ ከሁለት መቀመጫዎች በስተቀር የፓርላማውን መቀመጫዎች ጠቅልሎ መውሰዱ "በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደትና በብዙኅነት አቅጣጫ ላይ አደጋ የለውም ወይ? " የሚል ነበር፡፡ እንዲያውም በቻይና እንደሚታየው ዓይነት የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ሊፈጠር እንደሚችልም ተመላክቷል - በጥያቄዎቹ፡፡ ይህንን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችም ሲሉት ነበረ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን በዚህ ፈፅሞ አይስማሙም፡፡ "በኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ሥርዓት ሊፈጠር የሚችልበት ሁኔታ ፈፅሞ የለም፡፡ በሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ መኖር ምክንያት ይህ በምንም ዓይነት ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ ምናልባት እንደስዊድን ያለ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ወይም እንደጃፓኑ ሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ተፅዕኖ የሠፈነበት ሥርዓት ለአንድ አሠርት ዓመት ወይም ወደዚያ የሚጠጋ ጊዜ ሊኖር ይችላል፡፡ ግን በምንም ዓይነት በኢትዮጵያ የአንድ ፓርቱ ሥርዓት ሊፈጠር አይችልም፡፡ የዘንድሮው ምርጫ ውጤት በሠላማዊና ሕጋዊ መንገድ በሃገሪቱ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ኃይሎችን የሚያዳክምና ፅንፈኛ ለሚባሉ የፖለቲካ ኃይሎች አመቺ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል የሚለውን ክርክርም አቶ መለስ ዜናዊ ጨርሶ አይቀበሉትም፡፡ እንዲያውም ፓርቲያቸውም ሆነ የሚመሩት መንግሥት የሚከተሏቸው ፖሊሲዎች ፅንፈኛ የሚባሉ ኃይሎችን እንኳ እያለዘበ ወደ ሕጋዊና ሠላማዊ የፖለቲካ መስመር እያስገባ መሆኑን በመግለፅ ይከራከራሉ፡፡ እንደምሣሌም ከጥቂት ወራት በፊት ከመንግሥት ጋር የተፈራረመውን የምዕራብ ሶማሌ ነፃነት ግንባርና በቅርብ ጊዜ ደግሞ ተመሣሣይ ስምምነት ሊፈርም ነው ያሉትን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር አንድ አንጃም ይጠቅሣሉ፡፡ የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ግንቦት 18 ቀን 2002 ዓ.ም ካወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀበሉት የተዘረዘሩትን "ጥሬ ሃቆች" ያሏቸውን ብቻ ነው፡፡ በእነርሱም ላይ እንኳ አንዳንድ የተዛቡ ነገሮች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ መደምደሚያውን በተመለከተ ያላቸውን ቅሬታ ግን አልሸሸጉም፡፡ "ከሞላ ጎደል በትክክል አስቀምጠውታል፤ ድምዳሜውን ከፖለቲካ ዓላማቸው ጋር አብሮ በሚሄድ ልክ ሰፍተው አስቀምጠውታል፡፡ የፖለቲካ ድምዳሜውን ለራሣቸው ዓላማ በሚመጥን መልኩ የሰፉት ስለሆነ እኛ ልንለብሰው አንችልም፡፡ ጥሬ ሃቁ ግን ጥሬ ሃቅ ስለሆነ ልንቀበለው የምንችል ነው፡፡ " ብለዋል፡፡ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ አስተያየቱን የሰጠው የአውሮፓ ኅብረት ታዛቢ ቡድን ብቻ አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው ከሚባሉት መንግሥታት መካከል የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትም አስተያየቱንና ውጤቱ ያሣሰበው መሆኑን ገልጿል፡፡ ደግሞም የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሰብዓዊ እርዳታ በሰፊው ይለግሣል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን እንዴት እንደሚመለከቱትም ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ሃገሪቱ ያላት ግንኙነት በሁለቱም ሃገሮች የጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ መሆኑን አበክረው ያስረዱት አቶ መለስ ይህ መልካም ግንኙነት ወደፊትም እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ አረጋግጠዋል፡፡ "ግን - አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ - ኢትዮጵያ በሞግዚት የምትተዳደር ሃገር አይደለችም፡፡ ዩናይትድ ስቴትስም በዚህ ረገድ አንድ ጥርጣሬ የላትም፡፡ "ዩናይትድ ስቴትስ የታክስ ከፋዮቿን ገንዘብ ይሆናል እርሷ ባሻት ሁኔታ ልትጠቀምበት ሙሉ መብቷ ነው፡፡ የምርጫው ውጤት ትብብራችንን ለመቀጠል የሚያስችል አይደለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ - መልካም፤ እስከዛሬ ላደረጉልን እርዳታ እያመሠገንን ወደፊት መቀጠል ነው፡፡ ይሁንና ' ከዚህ ወይም ከዚያ ሃገር የሚመጣው የእርዳታ እህል ከቆመ የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሃብ ያልቃል' ብለው የሚያስቡ ሰዎች ካሉ ይህቺ ሃገር እንደት እንደምትተዳደር ምንም የማያውቁ ናቸው፡፡ ረቡዕ መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ አልነበሩም፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን መግለጫዎችን ሰጥተዋል፡፡ ሁሉም በምርጫው ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡ ከአፍሪካ ሕብረት ታዛቢዎች በስተቀር የተቃዋሚዎቹና የመንግሥት ባለሥልጣናቱ መግለጫዎች ቢያንስ መንፈሣቸው የሚጣጣም አይደለም፡፡ ይህ አለመጣጣም እንዲረግብ የማንም ጤናማ ሰው ምኞት ነው፡፡ ታሪክ ግን በምኞት አይሠራም፡፡ መለስካቸው አምሃ - ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ከአዲስ አበባ፡፡
a_amh-onlf-sweeds-ethiopia-7-5-11-125030254_1463114
https://amharic.voanews.com/a/amh-onlf-sweeds-ethiopia-7-5-11-125030254/1463114.html
ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በኦጋዴን በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ቆስለው ታሰሩ
በሰሜናዊቷ የሶማሊያ ራስ ገዝ ፑንትላንድ በኩል ድንበር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ያቀኑት ስዊድናዊ የፎቶ ጋዜጠኞች በኦብነግ አማጺያን አጃቢነት ድንበር ሲሻገሩ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ቆስለው ታስረዋል።
ሰኔ 23 ቀን ኢትዮጵያን በሚያዋስነው የፑንትላንድ ድንበር በጋልቃዮ በኩል ሁለቱ ስዊድናዊ ጋዜጠኞች ከከኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጭ ግንባር (ኦብነግ) ታጣቂዎችና ሌሎች አጋዦቻቸው ጋር ሲጓዙ ነበር የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በደረሳቸው መረጃ መሰረት ተከታትለው ያገኟቸው። ወዲያውኑ ተኩስ ተከፈተ። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ስምዖን የሆነውን ለVOA እንዲህ ያስረዳሉ። “ተኩስ ነበር። በዚህ የተኩስ ልውውጥ 15 የአሸባሪ ድርጅቱ ታጣቂዎች ወዲያውኑ ተገድለዋል። ስድስቱ ተማርከዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሁለት የውጭ አገር ዜጎች ተይዘዋል” ብለዋል አቶ በረከት ስምዖን። አቶ በረከት “ሁለቱ የውጭ አገር ዜጎች” ያሏቸው ዮሃን ፐርሰን እና ማርትን ሽቢየ የተባሉ የስዊድን ዜጎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በፑንትላንድ በኩል ጋዜጠኞቹን ለማሳለፍ አጃቢዎችና መሪዎች መላኩን ያስታወቀው በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጭ ግንባር (ኦብነግ) ከጋዜጠኞቹ ጋር ከሰኔ 24 ቀን ወዲህ ግንኙነቱ መቋረጡንና፤ የኢትዮጵያ ሃይሎች የጋዜጠኞቹን ረዳቶች ገድሎ፤ ስዊድናዊ ጋዜጠኞቹን አስሯል ሲል በዛሬውለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አቶ በረከት ስምዖን የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ሁለቱን ጋዜጠኞችና ሌሎች 21 ሰዎች ከማግኘታቸው በፊት በጋልቃዮ በኩል ወደ ኦጋዴን ለመግባት ሲሞክሩ በጀሌዎና በሊወርድ የአካባቢው ፖሊስና የጸጥታ ሃይሎች ድርሰው ተኩስ እንደከፈቱባቸው ነው የተናገሩት። በዚህ የተኩስ ልውውጥ መካከል ሁለቱም ጋዜጠኞች ቆስለዋል። “በተኩስ ልውውጡ አንዱ….በእርግጥ ሁለቱም በመጠኑ ቆስለዋል። አንዱ ትንሽ ጠለቅ ያለ ቁስል አለው፤ ግን ለሞት የሚያበቃው አይደለም” ብለዋል አቶ በረከት። በዛሬውለት መግለጫ ያወጣው ኦብነግ በኢትዮጵያ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀ ነው። ድርጅቱ እንደሚለው ሁለቱ ጋዜጠኞች “ኮንቲነንት ፎቶጆርናሊስት ኤጀነሲ” ለተባለ የፎቶ አንሽ ጋዜጠኞች ድርጅት የሚሰሩ ናቸው። በፑንትላንድ በኩል ጋዜጠኞቹ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞች ወደ ኦጋዴን ሄደው እንዳይዘግቡ በመከልከሉ እንደሆነ ኦብነግ አስታውቋል። ይሄም የሚደረገው የኢትዮጵያ ወታደሮች በኦጋዴን የሚፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ረገጣና ግድያ ለማድበስበስ እንደሆነ ኦብነግ በመግለጫው አስታውቋል። አቶ በረከት ስምዖን መንግስታቸው ለውጭ አገር ጋዜጠኞች የሚሰጠው የዘገባ ፈቃድ እንዲህ ያለ መንግስታቸው እንደሚያምነው “የልዖላዊ ድንበርን የመሻገር ወንጀል አያካትትም” ብለው ጋዜጠኞቹ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ገልጸዋል። “እነዚህ ሰዎች ህጋዊ ፓስፖርት የላቸውም። ከዚያ በተጨመሪ ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ሲሰሩ ተይዘዋል። ስለዚህ ህጉ በሚደነግገው መሰረት፤ ህገ-ወጥ ናቸው ስለዚህ እንደ ህገወጥ እናያቸዋለን” ብለዋል አቶ በረከት ስምዖን። አቶ በረከት አክለውም ከሁለቱ ጋዜጠኞች መካከል ዮሃን ፐርሶን ከዚህ በፊት በኦጋዴን መያዙን ተናግረዋል። “ሚስተር ጆን በድንበሩ በኩል ተሾልኮ ሲገባ ይሄ ሶስተኛ ጊዜው ነው። ይሄን አምኗል። በ2000ዓም በአካባቢው ፖሊስ ተይዞ ነበር። ለአካባቢው ፖሊስ የነገረውን ከግምት በማስገባት ወዲያውኑ ተለቋል። ከዚያም በኋላ ስለ ኦብነግና የኢትዮጵያ መንግስት የተሳሳተ መረጃ ሲያሰራጭ ቆይቷል። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ለኢትዮጵያ መንግስት መረጃውና አቀብሏል ያለው የፑንትላንድ አስተዳድርና የኢትዮጵያ መንግስት ላይ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድርጊቱን በማውገዝ መተባበር አለበት ብሏል። የኢትዮጵያ መንግስትም ታጋቾቹን እንዲለቅ ጫና ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል ኦብነግ። ኢትዮጵያ በቅርቡ ባወጣችው የጸረ-ሽብር ህግ፤ መንግስቱ አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ነፍጥ ካነሱ አንጃዎችና ከተወሰኑ ተቃዋሚዎች ጋር ጋዜጠኞች እንዳይሰሩ ይከለክላል። ባለፈው ሳምንት የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬና የፍትሕና አዲስ ፕሬስ ጋዜጦች፣ የፖለቲካ አምደኛ ወይዘሪት ርዕዮት ዓለሙ ታስረው ለፍርድ ቀርበዋል። በኒውዮርክ መሰረቱን ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲ.ፒጄና የመብት ተሟጋች ቡድኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችን “አሸባሪዎች” በሚል እንዲያስር የሚያደርገው ህግ ለመብት ረገጣና ለአፈና የተመቼ ነው ሲሉ ጉዳዩ በብርቱው እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል። ሲ.ፒ.ጄ በጸረ-ሽብር ህግ ጋዜጠኞችን አሸባሪዎችን አነጋግራችኋል አብራችሁ ሰርታችኋል በማለት ማዋከብና ማሰር በኢትዮጵያ እንዲቆም ጠይቋል።
a_ethiopia-edp-election-95273224_1458296
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-edp-election-95273224/1458296.html
የ2002ቱ አጠቃላይ ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ አልነበረም፤ በበርካታ ችግሮች የተሞላም ነበር፤ ሲል ኢዴፓ አስታወቀ
ምርጫው ተመልሶ ቢደገምም፤ በዴሞክራሲ ተቋማቱ የሚታዩ ግድፈቶች በድጋሜ ለገዥው ፓርቲ ያዳላሉ ሲሉ የኢዴፓ አመራሮች አስታውቀዋል።
ከህግ ውጭ ከአንድ በላይ የኢህአዴግ ወኪል ታዛቢ በየምርጫ ጣቢያዎች ተመድቦ እንደነበር ይላል ኢዴፓ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ 547 መቀመጮች ካሉት የአገሪቱ ፓርላማ ከ99.6 በመቶ በላይ የሚሆነውን ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ተቃዋሚዎች ውጤቱን አስመልክቶ ያላቸውን አስተያየት በመግለጫዎች ጭምር እያስታወቁ ነው። በሸንጎው ወንበሮች ባያሸንፉም የተሻለ ድምፅ ማግኘታቸው ከተነገረላቸው ሁለት ዋነኛ ተቃቃሚዎች አንዱ የሆነው ኢዴፓም በዛሬው ዕለት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ አቋሙን ይፋ አድርጓል። የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ልደቱ አያሌው፥ ዋና ፀሃፊው አቶ ሙሼ ሰሙና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ መስፍን መንግስቱ በተገኙበት ኢዴፓ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ጋዜጠኞች በሠጠው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫው፤ ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ፥ ገዢው ኢህአዴግ የፈፀማቸው ስህተቶችና ድክመቶች ዋነኞቹ መንስኤዎች ናቸው፤ ብሏል። «መራጮች አስቀድሞ በተወሰነላቸው ሠዓት፥ በአምስት ሠው ተቧድነውና ማንን መምረጥ እንዳለባቸው አለቃ ተመድቦ በጫና እንዲመርጡ መደረጋቸው፤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎችም ቀድሞ ከተመዘገበው በላይ ድምፅ የተሰጠበት ሁኔታ መከሰቱ፤» በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ከተፈፀሙ የህዝብን የመምረጥ መብት ከሚጋፉ ሁኔታዎች ውስጥ መሆናቸውን ኢዴፓ ገልጧል። «በአንዳንድ አካባቢዎች ከህግ ውጭ ከአንድ በላይ የኢህአዴግ ወኪል ታዛቢ በየምርጫ ጣቢያዎች እንዲመደብ መደረጉና በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎችም የተቃዋሚ የምርጫ ታዛቢዎች ያለ አግባብ እንዲባረረሩ መደረጉ፤ ከእንከኖቹ ጥቂቶቹ ናቸው፤» ሲል ኢዴፓ አመልክቷል። የገዢው ፓርቲ ድክመቶችና ስህተቶች ያላቸውን በአሃዝ ሠላሳ አንድ ያደረሳቸውን ነጥቦች የዘረዘረው ኢዴፓ በችግሮቹ ስፋትና ተቋማዊ ይዘት ምክኒያት ድጋሚ ምርጫ መፍትሄ አያመጣም ሲል ይልቁን ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ድርድር በተቋማቱ ላይ እንዲጀመር ጠይቋል።
a_amh-somalia-un1-13-11-137287513_1458998
https://amharic.voanews.com/a/amh-somalia-un1-13-11-137287513/1458998.html
የአፍሪካ ቀንድ ድርቅና ረሃብ ጋብ ቢልም ሊያገረሽ ይችላል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት አሳሰበ
በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን ድርቅና ረሃብ ለመታደግ የተደረገው አለም አቀፍ ትብብር፤ ብዙ ህይወት ማትረፉን የተባበሩት መግስታት ድርጅት አስታውቋል።
በአፍሪካ ቀንድ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ከታዩ ሁሉ የከፋ የተባለው ድርቅና ረሃብ ወደ 13 ሚሊዮን ህዝብን ለአስቸኳይ እርዳታ ባጋለጠበት ወቅት፤ በድርቁ ክፉኛ በተጎዳችው ሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚያቀርበውን እርዳታ የሚያስተባብሩት ማርክ ቦደን” ለቪኦኤ ሲናገሩ፤ የአለም አቀፍ እርዳታ ለውጥ ማምጣቱን አስምረውበታል። “የከፋው የረሃብና ቸነፈሩን ጊዜ ለመከላከል ችለናል። በሃምሌ ወር በሶማሊያ ረሃብና ቸነፈር ተስፋፍቷል ብለን ስናውጅ ወደ 8 የሚሆኑ ክፍለ-ሃግሮች ይራባሉ ብለን አስበን ነበር። ከጥር ወር በፊት ባለው ጊዜ በረሃብና ቸነፈር ሞት ተጋርጦባቸው የነበሩትን ሰዎች ቁጥር ከ750ሽህ ወደ 250ሽህ ዝቅ ማድረግ ችለናል” ብለዋል ቦደን። የህጻናትና የእናቶች ሞትም በሶስቱ የረሃብና ቸነፈር ቀጠናዎች በእጅጉ መቀነሱን ነው ባለስልጣኑ የሚናገሩት። ያም ሆኖ ሁኔታው አሁንም አስጊና ሊያገረሽ የሚችል እንደሆነ ቦደን ያሳስባሉ። አሁንም 4 ሚሊዮን ሰዎች በሶማሊያ ውስጥ አስቸኳይ እርዳታ ይሻሉ። እነዚህ ሰዎች የምግብ እርዳታና የኑሮ ማቋቋሚያ ካላገኙ ተመልሰው ወደ ረሃብ ሊወድቁ እንደሚችሉ ቦውደን ይናገራሉ። የመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪው ቦውደን በዩናይትድ ስቴይትስና አውሮፓ፤ በቀጣይነት ሶማሊያዊያንን መልሶ ለማቋቋም የታሰበ የ1.5 ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ በጀትን ለማሟላት፤ መንግስታትን በመማጸን ላይ ናቸው። በድርቁ በተጠቁ የሶማሊያ አካባቢዎች፣ በደቡብና ምስራቅ ኢትዮጵያ እንዲሁም በሰሜን ምስራቅ ኬንያ በመስከረምና ጥቅምት አጭር የዝናብ ወቅት፤ በቂ ዝናብ ተገኝቷል። የተገኘውን ዝናብ ተጠቅመው ገበሬዎች ሰብሎች እንዲዘሩ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እየጣረ ይገኛል። ገበሬዎች ምርታቸውን ወደ ጎተራ፤ ወይም መሬት እንደሰጠው ወደ ኬሻ እስኪያስገቡ ድረስ ግን፤ አሁንም በድርቁ የተጠቁ አካባቢዎች አስቸኳይ እርዳታ ያሻቸዋል። ወትሮውንም በደህናው ጊዜ የጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ መጋቢት ድረስ፤ የድርቅ ወቅት በመሆኑ፤ ከአሁኑ ወቅታዊ ምርት ጋር ቀጣዩ የዝናብ ወቅትም ወሳኝ እንደሚሆን የእርዳታ ሰራተኞቹ ያብራራሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ከአገር በቀል ድርጅቶችና መንግስታት ጋር በቅንጅት የሚያደርጓቸው እንቅስቃሲዎች በሶማሊያ ላለፉት 20 ዓመታት የዘለቀው ጦርነት ሲያጨናግፈው ይታያል። በድርቁ ከተጎዱ ሰዎች መካከል ወደ 60ከመቶ የሚሆኑት የሚኖሩት በእስልምና አማጺው ቡድን አልሸባብ ቁጥጥር ስር የሚገኙ አካባቢዎች ነው። በዚህ የተነሳ እርዳታ ላማዳረስ የሚያስችሉ መንገዶችና የፖለቲካ ፈቃደኝነቶች ፈታኝ ችግሮች ነበሩ። የምእራባዊያን መንግስት በጽኑ የሚቃወመው አልሸባብ፤ እርዳታ በችግር ላይ የሚገኙ ሶማሊያዊያንን እንዳይደርስ በተደጋጋሚ ያግዳል። በተለይ ሞቃዲሹ የሚገኘውን የሽግግር መንግስት የሚያግዘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአሜሪካ እርዳታ በሸባብ በተያዙት ማእከላዊና ደቡባዊ ሶማሊያ እንዲደርሱ አማጺያኑ አይፈልጉም። በዚህ እክል የተነሳ የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል በዚህ ሳምንት (ባለፈው ሳምንት) ለ1.1 ሚሊዮን ሶማሊያዊያን ያቀርብ የነበረውን እርዳታ አቋርጧል። ይሄም ሊሆን የቻለው የአልሸባብ ባለስልጣናት ድርጅቱ በማእከላዊና ደቡብ ሶማሊያ እርዳታ እንዳያከፈፍል በመከልከላቸው እንደሆነ አስታውቋል። ሁኔታው የእርዳታ አሰጣጡን ክፉኛ እንዳይጎዳው ተሰግቷል። የተባበሩት መንትስታት ድርጅት የሶማሊያ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ቦደን የቀይ መስቀል ውሳኔ ጊዚያዊ እንደሚሆን ይናገራሉ። “ሳነጋግራቸው ሁኔታው ጊዚያዊ እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸውልኛል። ሆኖም የማህበረሰቡን የምግብ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉን ሌሎች መንገዶች አሉ፤ ዋናው ነገር እርዳታውን ለማድረስ የሚያስችሉ መንገዶችን ማፈላለጉ ነው። ከነዚህ መንገዶች አንዱ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አጋሮችን ማፈላለግ ነው። “አብረናቸው የምንሰራው ከ200-300 የሚሆኑ አገር በቀል አጋሮች አሉን” ይላሉ ቦደን። “ሰፊ የሆነ የመረጃ መቀባበያና ሁኔታ የመገምገሚያ መንገዶች አሉን። ከነዚህ አጋሮቻችን ጋር ሆነን ክፍተቶቹ በየትኞቹ አካባቢዎች እንዳሉና እንዴት እርዳታ ማድረስ እንደሚቻል እንመካከራለን። እርዳታውን ወደ ሶማሊያ ለማድረስ የተደቀኑ የደህንነት ጥያቄዎች በአሁኑ ወቅት በአልሸባብ ላይ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪዎች፣ የጎረቤት ኬንያና ኢትዮጵያ ወታደሮች የጀመሩትን ጥቃት ተንተርሶ፤ እርዳታ ለማከፋፈል የሚያስችል ጸጥታ ይኖር ይሆን? “በእውነቱ ይሄንን አላውቅም። የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን በአንድ በኩል ወይ በሌላ ይለውጠዋል ብየ መናገር አልችልም። ዋናው ተስፋችን ግጭቱ አቢይ የምግብ እርዳታ ማሰራጫ መንገዶችን አይዘጋም የሚል ነው። ግጭቶቹም ተጨማሪ ሰዎችን ለስደት እንዳያጋልጡ በሁሉም ወገኖች ጥረት እንዲደረግ ጥሪ እናስተላልፋለን። ሚስተር ቦድን በዚህ ሳምንት በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ በሶማሊያ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ ለመሪዎች ለማሳወቅና፤ ተጨማሪ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና የመልሶ ማቋቋሚያ ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ ናቸው። በሶማሊያ ያለው ድርቅና ረሃብ እስከ መጨው ነሃሴ ወር ሊቀጥል እንደሚችልም አሳስበዋል።
a_Ethiopia-joint-statement-by-high-representative-vice-president--_5770135
https://amharic.voanews.com/a/Ethiopia-joint-statement-by-high-representative-vice-president--/5770135.html
የአውሮፓ ኅብረት ሰለ ትግራይ ክልል ሁኔታ መግለጫ ሰጠ
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ሰብዓዊ ቀውስ አሳዛኝ መሆኑንና በቀጣናው ላይ ሊያሳድር የሚችለው አንድምታ በጥልቅ እንደሚያሳስበው የአውሮፓ ኅብረት አስታውቋል።
ዋሺንግተን ዲሲ — መግለጫውን በጋራ ያወጡት የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ተጠሪና ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቦሬል፣ እዲሁም የኅብረቱ ኮሚሽነሮቹ ዪታ ኡርፒላይነን እና ያኔዝ ሌናርቺች ናቸው። ትግራይ ክልል ውስጥ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ለማድረስ የሚያስችል ሁኔታ በመጠኑ የተከፈተ መሆኑን የጠቆመው የኮሚሽነሮቹ መግለጫ ግጭቱ ሦስተኛ ወሩን ባስቆጠረበት ጊዜ የበረታ ቸነፈርንና ተጨማሪ የህይወት ጥፋትን ለማስቀረት እንዲቻል በከበደ ችግር ላይ ለሆኑ ሰዎች ለመድረስ ሁኔታው አሁንም አዳጋች መሆኑን አመልክቷል። በማዕከላዊና ምዕራባዊ ትግራይ አብዛኛው አካባቢ ለመድረስ አስቸጋሪ መሆኑንና ክልሉ ውስጥ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች የተጠለሉባቸው ሁለት ሠፈሮች ሙሉ በሙሉ እንደማይደረስባቸው ኮሚሽነሮቹ ተናግረዋል። ኮሚሽነሮቹ በዚሁ የጋራ መግለጫቸው አክለው ትግራይ ክልል ውስጥ ችግር ላይ ላሉትና ክልሉ ከአማራና ከአፋር ክልሎች ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች ወገንተና ያለመሆንን፣ ሰብዓዊነትን፣ ገለልተኝነትንና ነፃነትን በሚጠይቁትው የሰብዓዊነት መርኆች መሠረት እርዳታ መድረሱን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። የሲቪሎች እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ጥበቃ ጉዳይም የአውሮፓ ኅብረትን ይበልጥ እያሳሰበው መሆኑን ኮሚሽነሮቹ አስታውቀዋል። በሲቪሎችና በስደተኞች ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን፣ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች፣ እንዲሁም ስደተኞችንና ሰብዓዊነትን የሚመለከቱ ዓለምአቀፍ ህግጋት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየደረሷቸው መሆኑንም ኮሚሽነሮቹ አመልክተዋል። ስደተኞች በዓለምአቀፍ የስደተኛ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊነት ህግጋት መሠረት ከማናቸውም ጉዳት መጠበቅ እንዳለባቸው መግለጫው አስታውሶ ኤርትራውያን ስደተኞችን በማስፈራራት ወይም በግዳጅ ወደ ኤርትራ ለመመለስ ከሚደረግ ማናቸውም አድራጎት ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስቧል። "የአውሮፓ ኅብረትም ትግራይ ክልል ውስጥ ግጭቶችን የሚያባብሱ፣ የጭካኔ አድራጎት እንደሚፈፅሙና በብሄር ማንነት ላይ የተመሠቱ ሁከቶችንን እንደሚያደርሱ የሚከሰሱት የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ከሚጠይቀው የዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ ጎን ይቆማል" ብለዋል ኮሚሽነሮቹ። የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እያከናወነ ያለውን ተግባር እንደሚደግፍ ኮሚሽነሮቹ ገልፀው 'ይፈፀማሉ' በተባሉት የሰብዓዊ መብቶች እና የዓለምአቀፍ ህግ ጥሰቶች ላይ ምርመራውን እንዲቀጥል እንደሚያበረታቱ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ኮሚሽኑ ያቀረባቸውን ምክር አዘል ሃሳቦች እንደሚቀበልና ጥፋተኞች ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግም የቀረቡት የነፃ ምርመራና የፍትኅ ሂደቶች መከናወናቸውን ሙሉ በሙሉ በተግባር እንደሚያውል ተስፋ እንደሚያደርጉ የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ኮሚሽነሮች በጋራ መግለጫቸው ተናግረዋል። የዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ክልል እንዲገቡ እንዲፈቀድ የጠየቁት ኮሚሽነሮች ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞችም የደህንነት ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስበዋል። በሌላ በኩል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ መርኃግብር ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ ከኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ጋር ሆነው ከትናንት በስተያ ቅዳሜ መቀሌን ጎብኝተዋል። ዴቪድ ቢዝሊ በትዊተር ገፃቸው "ዛሬ በኢትዮጵያ ትልቅ ርምጃ ተመዝግቧል" በሚል ርዕስ ባሠፈሩት ቃል ድርጅታቸውና የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ከልል ውስጥ ሰብዓዊ ረድዔት የሚደርስበትን ሁኔታ ለማስፋፋት የሚያስችል ተጭባጭ እርምጃ ለመውሰድ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። "ቁጥሩ ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ ሰው እርዳታችንን እየጠበቀ በመሆኑ ድርጅታችን እንቅስቃሴውን ያጠናክራል፤ የምናባክነው ጊዜ የለም" ብለዋል ቢዝሊ። የመንግሥታቱ ድርጅት ዓለም የምግብ መርኃግብር ባወጣው መግለጫም የረድዔት ሠራተኞች ወደ ትግራይ ለመግባት ፈቃድ ለማግኘት ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተፋጠነ መንገድ ለማስተናገድ መስማማታቸውን አመልክቷል። ትግራይ ውስጥ ለአንድ ሚሊዮን ሰው አጣዳፊ እርዳታ እንዲያቀርብና ለመድረስ አዳጋች ወደሆኑ የክልሉ ገጠራማ አካባቢዎችም መድረስ እንዲቻል የማጓጓዣ ድጋፍ እንዲያደርግ ከኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበለትን ጥያቄ መቀበሉንም መርኃግብሩ አስታውቋል።
a_ramadan-washington-09-9-10-102562794_1458547
https://amharic.voanews.com/a/ramadan-washington-09-9-10-102562794/1458547.html
ረመዳን በዋሽንግተን ዲሲ
በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ሙስሊሞች በፈረስት ሂጂራ መስጊድ በየምሽቱ ተሰባስበው ያፈጥራሉ።
መስጊዱ “ፈርስት ሂጂራ” ይባላል። በጆርጂያ አቨኑ ላይ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ የመኖሪያ አካባቢ ነው ያለው። ስፍራው በርካታ አፍሪካ አሜሪካዊያን የሚኖሩበት፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሌሎች ስደተኞችና አሜሪካዊያኑም እየሰፈሩበት የመጣ በከተሜዎቹ አጠራር እያደገ የመጣ “አፕ ኤንድ ካሚንግ” አይነት ነው። በዚህ ሰፈር ከአምስት አመታት ሀፊት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መስጊድ ሲከፍቱ፤ በራቸው ለሁሉም ክፍት ነበር። በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የአካባቢው አፍሪካ አሜሪካዊያን ወደዚህ መስጊድ እየመጡ አብረዋቸው ፈጣሪን እንዲያመልኩ፡ ኢትዮጵያዊያኑም እርስ በርስ እንዲተጋገዙና እንዲፈቃቀሩ መንገድ ሆኗል ሲሉ ኢማሙ ነጂብ መሀመድ ይናገራሉ። “ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆኑ እዚህ አካባቢ ያሉ አፍሪካን አሜሪካንስ፣ አፍሪካኖችም እየመጡ እኛ ጋር ጾም ይፈታሉ። ከቅርብና ከሩቅ የተሰባሰቡት እስከ 200 የሚደርሱ ሙስሊሞች በየቀኑ የረመዳን ጾማቸውን የሚፈቱት ማለት የሚያፈጥሩት በፈርስት ሂጂራ መስጊድ ነው። አፍሪካን አሜሪካዊው መሀመድ ተወልዶ ያደገው መስጊዱ በሚገኝበት ፔትወርዝ ሰፈር ነው። በዚህ አካባቢ ከ10-15 ደቂቃ ተነድቶ የሚኬድባቸው መስጊዶች እንደነበሩ ይገልጻል። አሁን ግን ከቤቱ የመጣው በእግሩ ነው። ቅርበቱ ጥሩነው፤ መስጊዱም የሁላችንም ነው ይላል። “አላህ ሁላችንም ሙስሊም የሆንን ሁሉ መጥተን በቤቱ ተቀምጠን እንድናመሰግነውና እንድንደሰት ፈቅዶልናል። ይሄ የአላህ ቤት ነው” ብሏል። “የኢትዮጵያዊ ወይንም የአሜሪካዊ ቤት አይደለም። የአላህ ቤት ነው። ሰላት ከተሰገደ በኋላ ታዳሚዎች እርስ በርስ እየተጨዋወቱ እራታቸውን በልተው የሚቸኩሉ ወደ ቤታቸው፤ ጊዜ ያላቸውና ለጾሙ ሲሉ ከስራቸው እረፍት የወጡ ደግሞ በመስጊዱ ጸሎታቸውን እያደረጉ ረመዳንን በያመቱ ያከብራሉ።
a_kebele-lives-10-18-10-105186339_1459692
https://amharic.voanews.com/a/kebele-lives-10-18-10-105186339/1459692.html
የአዲስ አበባ ግንባታና ማህበራዊ ስንክሳሩ
በአዲስ አበባ በስፋት የሚካሄዱ የግንባታ ስራዎች በርካታ ቤተሰቦችን ወደሌላ አካባቢ እያዛወሩ ነው።
አዲስ አበባ ፈርሳ እየተገነባች ነው። ለዘመናት የማይነቃነቁ የሚመስሉት አፈርማ ቀለም ያላቸው የቆርቆሮ ቤቶች በልደታ፣ በካሳንችስ፣ በአራት ኪሎ አካባቢና በሌሎችም ያረጁ የአዲስ አበባ አካባቢዎች እየፈረሱ ናቸው። በምትካቸው ረጃጅም ህንጻዎች ለሆቴል፣ ለቢሮና ለሌሎች አገልግሎቶች ይገነባሉ። እነዚህ ግንባታዎች የከተማዋን ገጽታ እየቀየሩ ቢሆንም፤ ለረጂም ጊዜ የኖሩበትንና ያደጉበትን ሰፈል ለሚለቁ ቤተሰቦች ግን አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሯል። አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የከሳንችስ ነዋሪ ኢትዮጵያም ሆነች አዲስ አበባ ማደጋቸውን እንደሚፈልግ ይናገራል። በዚህ ሳቢያ ግን በርካታ ቤተሰቦች ከኑሯቸውና ከቤታቸው መፈናቀላቸው ሊታይ ይገባል ሲል ያሳስባል። ቤተሰቦቹ የመንግስት ሰራተኞች መሆናቸውን የሚናገረው ወጣት በተለዋጭ የተሰጣቸው ቦታ ከከተማዋ በየቀኑ የ20 ብር የመጓጓዣ ወጭ የሚያስወጣ ይሆናል ይላል። ከገንዘቡ በላይ መንገላታት አለ ስለዚህ “እናቴ ከዚያ እዚህ ድረስ መጥታ ለመስራት አቅሙም አይኖራትም። ወጭውም አይኖራትም እና ብዙ ስለሆንን ቤተሰብም ስለማይሸፍንልን የግድ ታቆማለች። እዚያ ሰፈር ስንሄድ ምን አይነት ሰው እንደምንሆን አላውቅም” ብሏል። የልማት ስራዎቹ በርካታ ቤተሰቦችን ከሚኖሩበት ስፍራ አፈናቅለዋል፤ እያፈናቀሉም ይገኛሉ። አቶ ካሳ ወልደሰንበት የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ቃል-አቀባይ ሰዎች ከለመዱት ስፍራ ሲነሱ ቅር መሰኘታቸው ያለ ነው ይላሉ። “ሼራተን ሲሰራ ሰዎች ተነስተው ሲ.ኤም.ሲ ሲሄዱ ከከተማ አውጥተው ጣሉን የሚሉ ሰዎች ነበሩ። ዛሬ አንደኛ ቦታ ነው” ይላሉ አቶ ካሳ። የሶስት ልጆች እናት የሆነች በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ጀርባ የምትኖር ሴት ገላን ወደሚባለው አዲሱ ሰፈር የምትገባ ከሆነ፤ የልጆቿ ትምህርት እንደሚቋረጥ ትናገራለች። በግንባታዎቹ ሳቢያ ወደ ሌላ ስፍራ የሚነሱ ሰዎች በተሰሩ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው አቅሙ ኖሯቸው 20 ከመቶ የቤቱን ዋጋ መክፈል ከቻሉ፤ እንደ አንደኛ አማራጭ ተቀምጧል ይላሉ አቶ ካሳ ወልደሰንበት። አቅሙ ከሌላቸው ሌላ የቀበሌ ቤት እደሚሰጣቸውና የግል ቤት ያላቸው ካሳ እንደሚከፈላቸው ቃል-አቀባዩ ተናግረዋል።
a_usavoters-politicswrap_5621278
https://amharic.voanews.com/a/usavoters-politicswrap/5621278.html
ትራምፕ እና ባይደን በአሻሚዎቹ ግዛቶች ዘመቻቸውን ቀጥለዋል
ለኮቪድ 19 ቫይረስ ተጋልጠው ህክምናቸው ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ፣ በዶክተራቸው ከቫይረሱ ነጻ በመሆናቸው ሌሎችን ሊበክሉ አይችሉም የተባሉት ፕሬዚዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ወደ ምረጡኝ ዘመቻቸው ለመመለስ የመጀመሪያው ሳምንታቸውን ይዘዋል፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ — ምርጫው ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት የቀሩት ሲሆን ፕሬዚዳንታዊ እጩዎቹ ትራምፕና የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ጆ ባይደን ብርቱ ፉክክር ወደሚጠይቁት የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች በመዘዋወር ደጋፊዎቻቸውን ሊያነቃቁም ተነሳስተዋል፡፡ የቪኦኤ ሪፖርተር ኤልዛቤጥ ሊ የሚከተለውን ዘገባ አዘጋጅታለ፡፡ ምርጫው እየተቃረበ መጥቷል፡፡ ከፍሎሪዳ እስከ ኦሃዮ ያሉ ደጋፊዎች ከእጩዎቻቸው ዙሪያ ተሰልፈዋል፡፡ አሻሚና አፎካካሪ በሆነችው ፍሎሪዳ የፕሬዚዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ ከተጠቁ በኋላ፣ አገግመው ወደ ምርጫ ዘመቻው የተመለሱትን ፕሬዚዳንት ትራምፕን ለማድመጥ ወደ ስፍራው የሚያስገባቸውን የትኩሳት መጠን እየተለኩ ገብተዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አሉ! ወደ ምርጫ ዘመቻው መመለሴን በይፋ ለማወጅ ቤቴ ወደ ሆነችው ፍሎሪዳ ተመልሼ መምጣቴ ደስ ይላል! ! አገግመው ስለተነሱበት የኮረና ቫይረስም የሚከተለውን ተናገሩ አሁንማ ኮረና አይነካህም ብለውኛል፡፡ ይሰማኛል! መጠንከሬ በጣም ይሰማኛል፡፡ ወደ ታዳሚዎቼ መራመድ እችላለሁ፡፡ ወደ መካከላችሁ መምጣት እችላለሁ፣ እዚህ ያላችሁትን ሁሉ አንድ በአንድ መሳም እችላለሁ፡፡ በኮኮቪድ 19 አይነኬ ስለመሆን ሳይንስ ግን፣ ገና እርግጠኛ አይደለም፡፡ ለማንኛውም ጆ ባይደንን ለመደገፍ በኦሃዮ የተሰባሰበው የደጋፊዎች ሁኔታ ግን የተለየ ነው፡፡ ይህ እኚህ ሰው ታመውና ተመርምረው ከወጡ በኋላ እንኳ የሚያሳዩት አደገኛ ባህርይ ነው፡፡ ጨርሶ እማይገባ ነገር ነው፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በፕሬዚዳንትነቱ እየቆዩ በሄዱ ቁጥር የበለጠ አደገኛ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ ትራምፕ ምናልባት ሊያሳዩ የፈለጉት ጠንካራ ሆኖ መታየትን ነው ይላሉ፣ የስታንፎርድ ዩኒንቨርስቲ ፖለቲካ ሳይንቲስት ብሩስ ኬን “እኔ እንጃ ከዚህ በላይ በሌላ መንገድ መግለጽ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ እንዴ! በጣም ደካማ ተጠቂና ታማሚ መስለው ከታዩ እኮ ለሳቸውም ጥሩ አይደለም፡፡ “ይሁን እንጂ” ይላሉ ኬን፣ ትራምፕ ህመማቸውንና ማገገማቸውን የሚያስተናግዱበት መንገድ ተመልሶ ሊጎዳቸው ይችላል፡፡ “ለኮቪድ የሚሰጡት ምላሽ፣ ወይም ስለኮቪድ የተናገሩት በሙሉ እኔን አይነካኝም ይኸው ሊያጠቃኝ አልቻለም የሚለው አባባላቸው በአረጋውያኑ መራጮች ዘንድ እየተወደደላቸው አይመስለኝም፡፡ በተለይ በፍሎሪዳ ያሉት በርካታ ጡረተኞችና የኮቪድ ተጠቂዎች ለቫይረሱ በአደገኛ ሁኔታ የተጋለጡ ብቻ ሳይሆኑ በኮቪድ ሊሞቱ የሚችሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ትራምፕ በ2106 ፍሎሪዳን ያሸነፉ ቢሆንም፣ በ2020 ግን ፍሎሪዳ አሻሚ ናት፡፡ በቅርብ የወጣው የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ እንደሚገልጸው ባይደን ትራምፕን በጥቂት ይቀድማሉ፡፡ ያ ለሁለቱም እጩዎች ከፍለግዛቲቱን አሻሚ ያደርጋታል፡፡ “ትራምፕ ለማድረግ የሚሞክሩት ነገር ደጋፊዎቻቸው ወጥተው ድምጽ እንዲሰጡ ማነቃቃት ነው፡፡ ምክንያቱም በተለይ ነጮቹ ወንዶች ወደ ምርጫው ቦታ በርከት ብለው ቢወጡላቸው፣ ከሴቶችና አረጋውያን መካከል ሊያጧቸው የሚችሉትን ድምጽ ሊያክሳክስላችው ይችላል፡፡ በባይደን የምርጫ ዘመቻ በኩልም ያለው ትኩረት በክሊንተን ጊዜ የተሠራው ስህተት እንዳይደገም ማድረግ ነው፡፡ የላቲን አሜሪካ ዝርያ ያላቸውና ላቲኖስ የሚባሉት ከነጭ አሜሪካውያን ቀጥለው በአሜሪካ ትልቁን የመራጮችን የማህበረሰብ ክፍል ድርሻ የያዙ ናቸው፡፡ በመሆኑም በምርጫው ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በብሄራዊ ደረጃ ሁለት ለአንድ በሆነ ብልጫ ከትራምፕ ይልቅ ባይደንን የሚደግፉ ቢሆንም፣ በፍሎሪዳ በሚገኙና አብዛኞቹ መራጮች በሆኑት የኩባ ተወላጅ በሆኑ አሜሪካውያን ዘንድ፣ ትራምፕ የተሻለ ድጋፍ አላቸው፡፡ በአገሪቱ ለመራጮች ዋነኛ የትኩረት ጉዳይ ሆኖ የሚወጣው የኮቪድ 19 ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም መላ አሜሪካውያን ወረርሽኙን እየተፋለመች ያለቸው አገራቸው፣ በማን መመራት እንደሚገባት በድምጻቸው ያረጋግጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
a_us-defended-its-libya-policy-118907289_1458667
https://amharic.voanews.com/a/us-defended-its-libya-policy-118907289/1458667.html
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት Barack Obama የአሜሪካን በሊቢያ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ተከላክለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል በሊቢያ የዓለምአቀፉ ዘመቻ አካል እንዲሆን የወሰኑትም የአገራቸው ጥቅሞችና እሴቶች ስጋት ላይ በመውደቃቸው መሆኑን አስረድተዋል።
ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በንግግራቸው፥ በሊቢያ ላይ ለምን ከዚህ ውሳኔ እንደደረሱ፥ እስካሁን ስለተገኙ ስኬቶችና ለአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል ይሰጣል ስላሉት ጥቅምና ዩናይትድ ስቴትስ በስፋት ስለምትጫወተው መሪ ሚና አብራርተዋል። ዩናይትድ ስቴትስና ሸሪኰቿ በሊቢያ ጣልቃ የገቡት አሉ ፕሬዘዳንት ኦባማ፥ ጣልቃ የገቡት የሞዓማር ጋዳፊ ኃይሎችን «አረመኔአዊ ጭቆናና» በሲቪሎች ላይ እያደረሱ የነበረውን ፍጅት ለማስቆም እንዲሁም አገሪቱ ላይ ያንዣብብ የነበረውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመከላከል ነው ብለዋል። ሚስተር ኦባማ ንግግራቸውን በመቀጠል፥ ዩናይትድ ስቴትስ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን ስፋት ያለው ጥምረት ለማቋቋም፥ የሊቢያ ሲቪሎችን ደህንነት መጠበቅ የሚያስችል የዓለሙን ድርጅት ሥልጣን ለማግኘትና ከበረራ የተከለከለ ቀጣና ለመመሥረት ችላለች ብለዋል። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በትላንቱ ንግግራቸው ታዲያ ምንም እንኳ ሊቢያና ዓለማችን ያለ ሞዓማር ጋዳፊ የተሻሉ መሆናቸው ባያጠያይቅም በወታደራዊ ኃይል የመንግሥት ለውጥ ለማምጣት እንደማይፈልጉ ግን አስረድተዋል። « ጋዳፊን በኃይል ለመጣል ብንሞክር ኖሮ፥ ህብረታችን ይሰነጣጠቅ ነበር። የዩናይትድ ስቴትስ እግረኛ ወታደሮችን መመደብ ደግሞ በሠራዊታችን ደህንነት ላይ ከፍተኛ አደጋን መጋበዝ ይሆናል። ዩናይትድ ስቴትስ አሉ ፕሬዘዳንት ኦባማ በዚያ የከፋ ገዳና አልፋለች። በኢራቅ በሺዎች የሚቆጠር ያሜሪካና ኢራቃውያን ዜጐች ሕይወት ጠፍቷል። በገንዘብም አንድ ትሪሊዮን ዶላር ተከፍሏል። እናም ይህን ጐዳና በሊቢያም ደግመን አንጓዝም። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ቀደም ሲል ከፈረንሳዩ አቻቸው ኒኰላስ ሳርኰዚ፥ ከጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርክል እና ከብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምረን ጋር መነጋገራቸውን የዋይት ሐውስ ቤተ መንግሥት አስታውቋል። መሪዎቹ ሚስተር ጋዳፊ ሥልጣን መልቀቅ እንዳለባቸውና የሊቢያ ሕዝብ መፃዒ የፖለቲካ ዕድሉን እራሡ ሊወስን እንደሚገባ መስማማታቸውን ያወጡት መግለጫ ያስረዳል።
a_us-budget-debate-8-2-11-126611193_1461811
https://amharic.voanews.com/a/us-budget-debate-8-2-11-126611193/1461811.html
የአሜሪካን የብድር ጣሪያ የሚያነሳውና መንግስት ወጪወችን እንዲቀንስ የሚደነግግ ህግ ጸደቀ
የዩናይትድ ስቴትስን የብድር ጣሪያ ከፍ የሚያደርገውንና በምትኩ ደግሞ መንግስት ወጪ እንዲቀንስ የሚደነግግ ህግ በሁለቱም ምክር ቤቶች ካለፈ በኋላ ፕሬዚዳንት ኦባማ በፊርማቸው አጽድቀውታል።
የዩናይትድ ስቴይትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአገሪቱን የብድር ጣሪያ ከፍ የሚያደርገውንና በምትኩ ደግሞ መንግስት ወጪ እንዲቀንስ የሚደነግግ ህግ ሰኞ አመሻሹ ላይ አጸደቀ። ህጉ የጸደቀው አገሪቱ የተቆለለባትን 14.3 ትሪሊዮን ብድር መክፈል ከማያስችላት ቀውስ ከመግባቷ አንድ ቀን ቀድማ ነው። ኦባማ የአገሪቱን የብድር ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፤ በዚህም አገሪቱ ልትገባበት የነበረውን ዕዳን ያለ መክፈል ቀውስ አስወግዳለች። የተፈረመው ህግ የአገሪቱን የመበደር ገደብ ከ14.3 ትሪሊዮን በላይ ሲያደርግ የመንግስት ወጪ ደግሞ እንዲቀንስ ይደነግጋል። የሁለቱም ፓርቲወች በሚያስማማ ሰጥቶ መቀበል መርህ የተረቀቀውና በፕሬዚዳንት ኦባማ የጸደቀው ይህ ህግ ወደ አልተጠበቀ ቀውስ አገሪቱ እንዳትገባ ያደርጋል ተበሎ ይታመናል። የዩናይትድ ስቴይትስ ሴኔት በዛሬውለት የአገሪቱን የበጀት መጓደል ለማስተካከል መንግስት ወጭውን እንዲቀንስና ተጨማሪ ብድር እንዲያገኝ የሚያስችል ህግ አጸደቀ። ሃምሌ 26 2003ዓም የዩናይትድ ስቴይትስ የገንዘብ ግምጃ ቤት ተጨማሪ ብድር ካላገኘ፤ አገሪቱን የሚያንቀሳቅስበትና ብድሩን የሚከፍልበት የገንዘብ አቅሙ እንደሚሟጠጥ ካስታወቀ ቆይቷል። ዩናይትድ ስቴይትስ ልትበደር የምትችለው የ14.3 ትሪሊዮን ዶላር ጣራ ላይ በመድረሷ፤ ተጨማሪ ብድር ለማግኘትና የቆዩ ብድሮችን ለመክፈል የባራክ ኦባማ አስተዳድር በኮንግረስ የብድር ጣራው እንዲነሳለት ጠይቋል። አሜሪካ ይሄን ማድርግ ካልቻለች ተበድራ በዚህ ቀን እከፍለዋለሁ ያለችውን ገንዘብ፤ ቃሏን ጠብቃ በቀኑ መክፈል ይሳናታል። የኦባማ አስተዳድር፤ የሄ ከሆነ የዩናይትድ ስቴይትስ ብቻ ሳይሆን የአለም ኢኮኖሚ ይናጋል እያለ ሲከራከር ቆይቷል። ሪፐብሊካኖች በበኩላቸው፤ መንግስቱ በዜጎች ላይ ቀረጥ እንዳይጭንና የበጀት መጓደሉን፤ ተጨማሪ የበጀት ቅነሳ በማድረግ ሊያስተካክል ይገባዋል ሲሉ ሲከራከሩ ሰንብተዋል። በትናንትናውለት በህግ መምሪያው የህዝብ ተወካዮች የብድር ጣራውን የሚያነሳና፤ የመንግስቱን በጀት የሚቀንስ ህግ አሳልፏል። ዛሬ የህግ መወሰኛው ሴኔት ውሳኔውን አጽድቋል፤ ፕሬዝደንት ኦባማ እንዲፈርሙት ባስተላለፈው መሰረት በፊርማቸው ዛሬ አጽድቀዋል። በዚህ አወዛጋቢ የበጀት ጉዳይ የባለሙያ አስተያየት ይዘናል። በሃርፐር ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር የሆኑ ጌታቸው በጋሻው ማብራሪያ ይሰጡናል።
a_djibouti-ethiopia-china-gasdeal-ogaden_3229505
https://amharic.voanews.com/a/djibouti-ethiopia-china-gasdeal-ogaden/3229505.html
ኢትዮጵያ፣ጅቡቲና ቻይና በጋራ የነዳጅ ፍለጋ ግንባታ ስራ ላይ ተስማሙ
የጅቡቲ መንግስት ከኢትዮጵያና ከቻይና ጋር ያደረገችው የነዳጅ ፍለጋ ግንባታ ስምምነት በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙትን የሱማሊያ አማፂ ቡድን አስቆጣ።
ዋሽንግተን ዲሲ — ጅቡቲ ስፋቷ አነስተኛ ቢሆንም ለቀይ ባህር ባላት የወደብ ቅርበት በብዙዎች የውጭ ባለሃብቶች ንግድ እንቅስቃሴ ተፈላጊ ያደርጋታል። ባለፈው ሳምንት የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር፤ በኦጋዴን ለታቀደው የነዳጅ ማውጣት ስራ መጀመር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። ይህ ግንባታ ጋዝን ወደ ፈሳሽነት የሚቀይር ፋብሪካን የሚጨምር ነው። የግንባታው ስፍራም ከጅቡቲ 16 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው። ከኢትዮጵያ እስከ ጅቡቲ ወደብ ወደ 800 ኪሎሜትር የሚጠጋው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መዘርጋትም በስምምነቱ ተካቷል። የዚህ ግንባታ ስራ ወደ 4 ቢልየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚፈጅ የጅቡቲው የተፈጥሮ ሃይል ሚኒስትር አቶ አሊ ያኮብ ማህሙድ ገልፀዋል። Poly-GCL የተባለው ስምምነቱን የፈረመው የቻይና ድርጅት ለግንባታው የሚያስፈልገውን ወጪ እንደሚሸፍንና ነዳጁ ወደ ቻይና እንደሚላክ አስታውቋል። ይህ የነዳጅ ፍለጋ ስራ፤ ጅቡቲ ከአንድ የቻይና የግል ድርጅት ጋር ያደረገችው ስምምነት ነው። በእቅዱ መሰረት ከተከናወነ እ.አ.አ 2018 የግንባታው ስራ ተጠናቆ ነዳጅ የማውጣት ስራው ይጀመራል። የጅቡቲው የተፈጥሮ ሃይል ሚኒስትር ይህ ለሃገሪቱ የመጀመሪያው ከፍተኛውና የግል ፕሮጀክት እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ ወገን የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር በመባል የሚታወቀው ONLF አማፂ ቡድን ግንኙነት ሃላፊ አብድራህማን ማሃዲ የተደረገው ስምምነት ተቀባይነት የለውም ብለዋል። እሳቸው እንደሚሉት ስምምነቱ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑትን የደቡብ ኦጋዴን ጎሳዎችን አላካተተም። ስለዚህ መቀጠል የለበትም ብለዋል። ከኢትዮጵያ መንግስት እስከአሁን ምንም አይነት መግለጫም ሆነ አስተያየት ስለስምምነቱ አልተሰጠም። የቪኦኤው ሃሩፍ ማሩፍ የዘገበውን መስታወት አራጋው ታቀርበዋለች። ለማዳመጥ ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት ይጫኑ።
a_ungass-ethiopia-eritrea-mdg-103555919_1459922
https://amharic.voanews.com/a/ungass-ethiopia-eritrea-mdg-103555919/1459922.html
የሚሌንየሙ የልማት ግቦች አካሄድ በየሃገራቸው አበረታች መሆኑን ኢትዮጵያና ኤርትራ አስታወቁ፡፡
"የሚሌንየሙን የልማት ግቦች ለመምታት እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም አቅጣጫዎች ትርጉም ያላቸው ውጤቶችን አስመዝግበናል፡፡ የራሣችንን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን በሙሉ አቅም እየተንቀሣቀስን ነው፡፡" - መለስ ዜናዊ፤
140 መሪዎች የተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘንድሮ ጠቅላላ ጉባዔ ለሚሌኒየሙ የልማት ግቦች አያያዝ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየመከረ ነው፡፡ የሚሌኒየሙን የልማት ግቦች በተያዘላቸው ጊዜ ለመምታት እየተንቀሣቀሱ መሆናቸውን ኢትዮጵያና ኤርትራ አስታወቁ፡፡ ኒውዮርክ ላይ በመካሄድ ላይ ባለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ትናንት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዓለምአቀፉ ቃል እየሄደ ያለበት ፍጥነትና ጥራት አምስት ዓመታት ብቻ የቀሩትን የሚሌኒየሙን የልማት ግቦች መምታት ይቻል እንደሆነ ግልፅ ማረጋገጫ መስጠት እንደማይቻል አመልክተዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሚሌኒየሙን የልማት ግቦች በመንግሥታቱ ድርጅት ሥርዓት ውስጥ አንድነትን በመፍጠር ተመሣሣይ የሌላቸው መሆኑን የጠቆሙት የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሣለህ ግቦቹን የመምታት ጉዳይ አሁንም ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊቀጥል የሚገባው መሆኑን አሣስበዋል፡፡ የዘንድሮው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተነጋገረ ያለው ድህነትን፣ ረሃብና በሽታዎችን ከዓለም በማስወገድ አጀንዳ ላይ ሲሆን ሊጠናቀቅ አምስት ዓመታት ብቻ የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች ዕቅድ አካሄድን እየገመገመ ይገኛል፡፡ በጉባዔው ላይ የተገኙት የመንግሥታት መሪዎች እና ተጠሪዎቻቸው የየሃገራቸውን የልማት ግቦቹን አካሄድ የሚገመግሙ ንግግሮችና ሪፖርቶችን አቅርበዋል፡፡ በጉባዔው ላይ የኢትዮጵያን ግምገማ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃገራቸው ግቦቹን ለመምታት አበረታች በሆነ መንገድ ላይ የምትገኝ መሆኑን ጠቁመው ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ቃሉን እንዲያጠናክርና ቁርጠኝነቱንም በድጋሚ እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል፡፡ የኤርትራን ሪፖርት ያቀረቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አቶ ኦስማን ሣለህም ሃገራቸው የሚሌንየሙን የልማት ግቦች በ2015 ለመምታት የተቻላትን ሁሉ ለማድረግ መቁረጧን ተናግረዋል፡፡ "ረሃብን ያለፈ ታሪክ ለማድረግም በተለይ በመሠረተ-ልማትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አፍስሣለች" ብለዋል፡፡ በያዝነው ሦስተኛው ሚሌኒየም መባቻ ላይ እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ መከናወን አለባቸው ብሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ2000 ዓ.ም ያፀደቃቸው ስምንቱ ግቦች፡- - የበረታ ድህነትና ረሃብን ማስወገድ፤ - የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ለሁሉም ማዳረስ፤ - የፆታ እኩልነትን ማራመድ እና የሴቶችን አቅም ማጎልበት፤ - የሕፃናትን ሞት መጠን መቀነስ፤ - የእናቶችን ጤና ማሻሻል፤ - ኤችአይቪ/ኤድስን፣ ወባንና ሌሎችም በሽታዎችን መዋጋት፤ - የተፈጥሮ አካባቢን ደህንነት ማረጋገጥ፤ - ለልማት ዓለምአቀፍ አጋርነትን ማጠናከር ናቸው፡፡ የእነዚህን ግቦች ያለፉ አሥር ዓመታት ጉዞ በሚገመግመው በዘንድሮው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ 140 የሚሆኑ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ለዝርዝሩ ዘገባውን ያድምጡ፡፡
a_a-53-2008-05-01-voa1-93030769_1459031
https://amharic.voanews.com/a/a-53-2008-05-01-voa1-93030769/1459031.html
African Athletics Championships DAY 2: Ethiopia Tops Medals Count with Victory in the Women’s 5,000 m
Meselech Melkamu of Ethiopia clinched the gold medal beating the World and Olympic champion Meseret Defar by one fifth of a second.
RANK SILVER BRONZE TOTAL 1. ETHIOPIA 2 2 1 5 NIGERIA 2 2 1 5 3. EGYPT 2 2 - 4 4. 1 1 2 4 5. ALGERIA 1 - 1 2 6. TUNISIA 1 - - 1 GUINEA 1 - - 1 RANK NAME NAT 1. Meselech MELKAMU ETH 15:49.81 2. Meseret DEFAR ETH 15:50.19 3. Grace MOMANYI KEN 15:50.19 4. Belaynesh FEKADU ETH 15:50.49 100 m- MEN FINAL RANK NAME NAT 1. Olusoji FASUBA NIG 10.10 2. Uchenne EMEDOLU NIG 10.21 3. Hannes DREYER RSA 10.24 100 m- WOMEN FINAL RANK NAME NAT 1. Damola OSAYOMI NIG 11.22 2. Vida ANIM GHA 11.43 3. Delphine ATANGANA CAM 11.46 110 m- HURDLE WOMEN FINAL RANK NAME NAT 1. Fatmata FOFANAH GUE 13.10 2. Toyin AUGUSTUS NIG 13.12 3. Carole M. KABOUD ME BAM CAM 13.52
a_ethiopia-new-education-guideline-102308249_1460449
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-new-education-guideline-102308249/1460449.html
የግል ከፍተኛ የትምህር ተቋማት ማህበር ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ያወጣዉን መመሪያ ተቃወመ!
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራት አልተጠበቀም በማለት አዲስ መመሪያ አዉጥቷል፥ ከፍተኛ የግል ተቋማት ግን መመሪያዉ ድንገተኛና የግል ተቋማት ባለሃብቶችን አመለካከት ያላገናዘበ ነዉ ሲሉ ተቃዉመዋል።
የኢትዮጵያ ትምህት ሚኒስቴር ያወጣዉ መመሪያ የግል ከፍተኛ ተቋማት የህግና የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ ያግዳል። በአገሪቱ የርቀት ትምህርትም እንዲቆም አድርጓል። የህዝብ ግንኙን ዳይሬክተር አቶ አበራ አባተ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ምክንያቱን ሲያብራሩ፣ እርምጃዉ የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ነዉ ብለዋል። ሁሉም ባይባሉ አብዛኞች የግል ከፍተኛ የትምህት ተቋማት የትምህርት ሚኒስቴርን ግብአት አያሙዋሉም፣ ለቴክኒክና ሙያ የተቀመጡ መስፈርቶች ስራ ላይ አያዉሉም ብለዋል። የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማህበር ስራ አስኪያጅ ዶክተር ነጋ ናማጋ በበኩላቸዉ፣ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት መዉደቁን አምነዉ፣ አንድ በቅርቡ የተካሄደ አንድ ጥናት፣ ለትምህርት ጥራት መጉዋደል አንዳንድ የመንግስት ተቋማትንም ሃላፊ እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል። ይልቁንስ ጥራታቸዉን የጠበቁ ተብለዉ አምስት ከፍተኛ የግል ተቋማት በጥናቱ መለየታቸዉን ተናግረዉ መመሪያዉ ተቋማቱን በጅምላ መፈረጁን ተቃዉመዋል። መመሪያዉ የወጣዉ፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ለመስከረም ትምህርት ጅማሮ ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜና ሳይታሰብ በድንገት በመሆኑም ባለሃብቱና የአገሪቱ ትምህርት ስርአት ላይ ጉዳት ያስከትላል ብለዋል። ከመሆኑም በድንገት ሰለወጣ ለግል ተቋማት ጉዳት እንደሚያስከትል የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበራ አባተ፣ የከፍተኛ ትምህርት አቅርቦት በአገሪቱ ክልሎች ሁሉ ከመቸዉም ጊዜ የተስፋፉና፣ እርምጃዉ ወደፊትም ስለሚቀጥል ጥራት የጎደለዉ ትምህርት በግል ተቋማት መሰጠቱ አስፈላጊ አይደለም ብለዋል። ለሰማኒያ ሚሊዮን ህዝብ ትምህርትን ያዳርሳሉ ብሎ መገመት አይቻልም ብለዋል። ሁለቱ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት መዉደቅ መፍትሔ ያሉትን ጥቁመዋል። ዉይይታቸዉን አዳምጡ።
a_ask-the-doctor-understanding-anti-social-personality-disorder-voa-amharic-dr-yonas-endale-gede-1-2-3-alula-kebede-july-11-2017_4107075
https://amharic.voanews.com/a/ask-the-doctor-understanding-anti-social-personality-disorder-voa-amharic-dr-yonas-endale-gede-1-2-3-alula-kebede-july-11-2017/4107075.html
የማኅበራዊ ግንኙነት አዋኪነት ዝንባሌ የአዕምሮ ሕመም ወይስ እኩይ ጠባይ?
“bio-psycho social model ይሉታል። በተፈጥሮ በዘር የሚተላለፍ፣ ስነ ልቦናዊው እና ማሕበራዊ ይዘት ያለውም አለ። አንዳንድ ጊዜ ቤተሰብ ውስጥም ይሁን ጎረቤት ያንን ልጅ ክፉኛ እያዋከበ፥ ክብሩን እየናቀና እያዋረደና እያጥላላ የሚያድግበት ሁኔታ የሚፈጥር አዝማሚያ ወደማመጽና በሕብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ቁርሾ ወደመያዝና ብሎም ሲብላላ ኖሮ ንጹሃንን በግፍ በማሰቃየት ወደሚደሰት ሥብዕና ሊያመራ ይችላል።” ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ ልብ የነርቭና የአዕምሮ ሃኪም።
ለሌሎች ክብር ማጣት፤ ትክክለኛውን ከስሕተቱ ያለመለየት ያለመቻል። ምክኒያት የለሽ በሆነ የበረታ ጥላቻና ክፋት መጠመድና ንጹሃንን የመበደል ፍላጎት ከዋነኞቹ ምልክቶች ውስጥ ናቸው። ሁሉን አዋቂ ነኝ ባይነትና አንዳንዴም እውነተኛ ጠባይን በመሸሸግ መልካም የሚመስል ጠባይ በማሳየት ሌሎች በማደናገር ለግል ጥቅም አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ማውጠንጠን ይገኙበታል። ይህ ታዲያ እኩይ ጠባይ ብቻ አይደለም። የአእምሮ ሕመም ጭምር እንጂ። በሕምናው ቋንቋ በእንግሊዝኛ antisocial personality disorder በመባል ይታወቃል። ለመሆኑ የዚህ ሕመም ምንጩ ምን ይሆን? በሕክምና ይረዳል? ሥር ከመስደዱ አስቀድሞስ መከላከል ይቻል ይሆን? በተከታታይ የሚቀርበው የሃኪምዎን ይጠይቁ ቅንብር የህመሙን ምንነት፥ ዓይነተኛ መለያዎች፥ የሕክምና አማራጮች ጨምሮ ይዳስሳል። ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ፥ በሜዮ ክሊኒክ፥ የነርቭና የአዕምሮ ሃኪም ናቸው።
a_amh-awolia-police-7-14-12-162471466_1492799
https://amharic.voanews.com/a/amh-awolia-police-7-14-12-162471466/1492799.html
በአዲስ አበባ አወሊያ መስጊድ ፖሊስና ሙስሊሞች ተጋጩ
አርብ ለቅዳሜ አዳር በፖሊስና በአወሊያ መስጊድ ዙሪያ በተሰባሰቡ የሙስሊም ማህበረስብ አባላት መካከል ግጭት ተቀስቅሶ ከመቶ በላይ ታሰሩ 16ሰዎች መቁሰላቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ አድርጓል።
ፖሊስ የአስለቃሽ ጋዝ በመተኮስ በመስጊዱ የተሰባሰቡትን ሰዎች ሲበትን መመልከታቸውን ምስክሮች ገልጸዋል፤ የኢትዮጵያ መንግስትም መግለጫ ሰጥቷል የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን በማስተናገድ ላይ በምትገኘው አዲስ አበባ ትናንት ማምሻውን ፖሊስና በአወሊያ መስጊድ አቅራቢያ የተሰባሰቡ ሰዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ከመቶ በላይ መታሰራቸውንና መቁሰላቸውን፤ የእስልምና ኮሚቴው ገለጸ። የኮሚቴውን ቃል አቀባይ አህመዲን ጀበል ጠቅሶ የብሉምበርግ የዜና አውታር እንደዘገበውና፤ የዝግጅት ክፍላችን ያናገራቸው የአይን ምስክሮችና አንዳንድ የኢንተርኔት ፎቶዎች እንደሚያሳዩት፤ ግጭቱ ጥይት፣ ቆመጥ፣ ድንጋይና አስለቃሽ ጋዝ የተተኮሰበት ነው። በዚህ ግጭት አንድ ሰው ሳይገደል እንዳልቀረ ኮሚቴው አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚንስትር ድዔታ አቶ ሽመልስ ከማል ለብሉምበርግ የዜና አውታር፤ በግጭቱ 72 ሰዎች መታሰራቸውንና ስድስት የፖሊስ ባልደረባዎችን ጨምሮ 10 ሰላማዊ ሰዎች የቆሰሉበት መሆኑን ይፋ አድርገዋል። አቶ ሽመልስ አክለውም በአወሊያ ት/ቤትና መስጊድ አቅራቢያ መንገድ በመዝጋት የፖለቲካ መፈክር ያሰሙ የነበሩትን ሰዎች ፖሊስ በአስለቃሽ ጋዝ መበተኑን ተናግረዋል። ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጥይት አለመተኮሱን አቶ ሽመልስ ገልጸዋል። በአወሊያ መስጊድ የተሰባሰቡ ሰዎችን ወክለው ለብሉምበርግ የዜና አውታር መግለጫ የሰጡት አህመዲን ጀበል ፖሊስ በአወሊያ መስጊድ ተሰባሰበው በሰላይ የተቀመጡ ሙስሊሞች ላይ አጥር ጥሶ በመግባት፣ ጥቃት ማድረሱን ተናግረዋል። “በሩን ሰብረው ገብተው በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ተኩስ ከፈቱ” ብለዋል አቶ አህመዲን። በኢትዮጵያ መንግስትና በእልምና ምክር ቤቱና ደጋፊዎቹ መካከል ግጭቱ የተባባሰው፤ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ እየገባ ነው በሚል በምክር ቤቱ በተነሳ ቅሬታ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት የሃይማኖት ጉዳዮችን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ይተው፤ መሪዎቻችንን እራሳችን እንምረጥ ይላል፤ ምክር ቤቱ። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ምክር ቤቱ በውስጡ የፖለቲካ ተልእኮ ያላቸውና ኢትዮጵያን በእስላማዊ ህግ የምትመራ አገር የማድረግ ጽንፍ የረገጠ አክራሪነት ያለባቸው አካላትን አካቷል ሲል ወንጅሏል። ይሄ አስተያየት የተሰማው በሚያዝያ ወር በአርሲ አሳሳ ከተማ ውስጥ አንድ የእስልምና አባት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ይመራሉ በሚል በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተቀሰቀሰ ግጭት 4 ሰዎች ከተገደሉና በርካቶች ከታሰሩ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል በአዲስ አበባ ትናንት ማምሻውን የተቀሰቀሰው ግጭት መብረዱንና ሁኔታው በቁጥጥር ስር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መሪዎችን በምታስተናግድበት ወቅት አንዳንድ ሃይሎች ብጥብጥ ለመፍጠር እየጣሩ ናቸው በለዋል አቶ ሽመልስ ከማል።
a_sudan-bashir-icc-chad-07-22-10-99054789_1462672
https://amharic.voanews.com/a/sudan-bashir-icc-chad-07-22-10-99054789/1462672.html
የሱዳኑ ፕሬዝደንት ለቀረበባቸው የዘር ማጥፋት ክስ ምላሽ እንዲሰጡ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች
ጥሪው የቀረበው የሱዳኑ መሪ የICC አባል አገር የሆነችውን ቻድን ከጎበኙ በኋላ ነው።
የቻድ የአገር ውስጥ ሚኒስትር አል-በሽር እንደማይታሰሩ ማረጋገጫ ሰጥተዋል የቻድ መንግስት የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወይንም ICC አባል አገር በመሆን የተፈረመውን ስምምነት ባለማክበር ኦማር አልበሽርን ባለማሰሩ የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያወጣው ወቀሳ ወይንም መቆላጨት የለም። ነገር ግን በሱዳን ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲሰፍን ፕሬዝደንት አልበሽርም ሆኑ ሌሎች ክስ የተመሰረተባቸው ባለስልጣናት ለICC ምላሽ መስጠት አለባቸው ትላለች ዩናይትድ ስቴይትስ። ዛሬ ፕሬዝደንት አልበሽር ክስ ከተመሰረተባቸው ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የICC ስምምነትን ከፈረሙ አገሮች መካከል አንዷ የሆነችውን ቻድን ጎብኝተዋል። በዳርፉር ግዛት ለሰባት አመታት ያህል በዘለቀው ጦርነት ኢሰብአዊ ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ፕሬዝደንቱን ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ መሪዎችን በወንጀል ከሶ ICC፤ በተገኙበት እንዲታሰሩ ማደኛ አውጥቶባቸዋል። ባለፈው ሳምንት በጦር ወንጀለኝነት ከወጣው ክስ በተጨማሪ በሄግ የሚገኘው ፍርድ ቤት በአል-በሽር ላይ የዘር ማጥፋት ክስ ጨምሮባቸዋል። የዳርፉር ግጭት 300 ሽህ ሰዎችን ሲገድል ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሌሎችን ደግሞ ማፈናቀሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይተምናል። ስደተኞቹ ብዙውን ጊዜ ወደ ጎረቤት ቻድ ያመራሉ። የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ለአመታት የሻከረ ሲሆን አንደኛው መንግስት ሌላኛውን “ወታደሮች ያሰለጥናል፣ በእጅ አዙር ይወጋኛል” በማለት እርስ-በርስ መወነጃጀልም ይታያል። በእንጃሚና ንግግር ያደረጉት አል-በሽር የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ተሻሽሏል ብለዋል። የቻድ የአገር ውስጥ ሚኒስትርም አል-በሽር እንደማይታሰሩ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ዛሬ በዋሽንግተን የጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል-አቀባይ ፒ.ጄ ክራውሊ ቻድ ለምን የፈረመችውን የICC ግዴታ አልተወጣችም ሲሉ ጠይቀዋል። የሱዳኑ መሪ በስተመጨረሻ ለፍርድ እንደሚቀርቡም ክራውሊ ተናግረዋል።
a_ethiopians-abroad-protest-elections-06-14-10-96328819_1461710
https://amharic.voanews.com/a/ethiopians-abroad-protest-elections-06-14-10-96328819/1461710.html
በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የምትከተለውን ፖሊሲ እንድትቀይር ጠየቁ
«ሠልፉ፥ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በቅርቡ ያወጣውን መግለጫ በመደገፍና ተጨባጭ የፖሊሲ ለውጥ ዕርምጃዎች እንዲታገዝ ለመጠየቅ የተዘጋጀ ነው፤» ዶ/ር ካሳ አያሌው፤ ከሠልፉ አስተባባሪዎች አንዱ።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት የምርጫውን ሂደትና ውጤት አስመልክቶ በቅርቡ ያወጣውን መግለጫ የሚደግፉ መሆናቸውን የሚናገሩት ሠልፈኞች በተጨባጭ የፖሊሲ ለውጥ ዕርምጃዎች እንዲታገዝ ጥረት መጀመራቸውን ገልፀዋል። በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ኢህአዴግን ሙሉ በሙሉ አሸናፊ ያደረገውን የ2002ቱን ብሄራዊ ምርጫ ሂደትና ውጤት በመቃወም፥ ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የምትከተለውን ፖሊሲ እንድትቀይር ለመጠየቅ ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴርና በዋይት ሃውስ ደጃፍ ሰላማዊ ሠልፍ አድርገዋል። «ቃልዎን ይጠብቁ። » ሲሉ የዩናይድ ስቴትሱን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ያሳሰቡት ሠልፈኞች «ነፃነትና ዲሞክራሲ በሌለባት ኢትዮጵያ ሠላም የለም። » የሚሉ መፈክሮችንም ሲያሰሙ ተደምጠዋል። ሠልፉ፥ «የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት በቅርቡ ያወጣውን መግለጫ በመደገፍና በተጨባጭ የፖሊሲ ለውጥ ዕርምጃዎች እንዲታገዝ ለመጠየቅ የተዘጋጀ ነው፤» ያሉት ከአስተባባሪዎች አንዱ ዶ/ር ካሳ አያሌው ናቸው። ለውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሄላሪ ክሊንተን እንዲደርስ የተፃፈውና ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዕጅ የገባው ደብዳቤ፥ “ገዢው ፓርቲና አጋሮቹ 99.6 በመቶውን የአገሪቱን ሸንጎ መቀመጫዎችና የክልል ምክር ቤቶችን ሙሉ መቀመጫዎች የተቆጣጠሩበት፥ ”በእጅጉ የተዛባ፤” ያለው ምርጫ ውጤት፤ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ከታዩ ሌሎች “የተዛቡና የተጭበረበሩ ምርጫዎች፤” አንፃር እንኳን ሲታይ፥ ወደር የማይገኝለት አሳዛኝ የምርጫ ታሪክ የተዘገበበት ነው፤ ሲል ኮንኗል። «በኢትዮጵያ ከአምባገነን አገዛዝ ወደ መልካም አስተዳደር ሰላማዊ ሽግግር ይደረግ ዘንድ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በዲፕሎማሲያዊም ሆኑ በሌሎች መንገዶች ግፊት እንድታደርግ፤» ሲል የቀረበው ይህ ደብዳቤ፣ «በዚያች አገርና በአካባቢው አገሮች ዕውነተኛ፥ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ሊመጣ የሚችለው፥ ከኢትዮጵያ ኅዝብ ወገን እንጂ ኅዝቡን ከሚጨቁን ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ጎን ሲሰለፉ አይደለም፤» ሲል የዩናይትድ ስቴትስን መንግስት አሳስቧል። ደብዳቤውን ከተቀበለው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርም ሆነ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሰልፉን አስመልክቶ ለጊዜው የተሰጠ አስተያየት የለም። “March for Freedom” የተባለው የፖለቲካና የማኅበራዊ ለውጥ አቀንቃኝ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን የተሰባሰቡበት ቡድን በጠራው በዚህ ሠልፍ በመቶዎች የሚገመት ኅዝብ ተሳትፏል።
a_meles-presser-08-11-10-100467279_1457993
https://amharic.voanews.com/a/meles-presser-08-11-10-100467279/1457993.html
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕጋዊ ካሏቸው ተቃዋሚዎች ጋር እንደሚደራደሩ ገልጹ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለአገር ዉስጥ ጋዜጠኞች ረቡእ በሰጡት መግለጫ ከተቃዋሚዎች ጋር መንግስታቸዉ ስለሚደራደርበት መስፈርትና፣ የአሸባሪዎችን ጥቃት ስለመከላከል ገልጸዋል።
ህገ መንግስቱንና ህግ መንግስታዊ ስርዓቱን መቀበልና ዓላማቸዉን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ማራመድን እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል። የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዛሬ ለአገር ዉስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ለተለያዩ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። በሶማሊ ክልል ከሚንቀሳቀስ ታጣቂ ሃይል ጋር በቅርቡ የተፈረመዉን ስምምነት መነሻ ያደረገዉ ጥያቄ አንዱ ነዉ። መንግስታቸዉ የሚደራደረዉ መሳሪያ ካነሱት ጋር ብቻ ነዉ? ወይስ ካኮረፉትም ጭምር እንደሆነ የተጠየቁት አቶ መለስ፣ “መሳሪያ ለማንሳት ያዉ የመጀመሪያዉ እርምጃ ማኩረፍ ነዉ ስለዚህ ለድርድር ዝግጁ የምንሆነዉ መሳሪያ ቢያነሱም ባያነሱም ካኮረፉት ሁሉ ጋር ነዉ“ ብለዋል። ለምሳሌ አገር ዉስጥ ያሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በህጉ መሰረት መሥራት የሚፈልጉ እስከሆኑ ድረስ አኩርፈዋል የማይባሉ ስለሆነ መንግስታቸዉ በተከታታይ ድርድር እንዳደረገ ገልጸዉ፣ ያኮረፉና መሰሪያ ያላነሱም ካሉ መንግስት ለመደራደር ዝግጁ ነዉ ብለዋል። ከተቃዋሚዎች የሚጠበቅ ግን አንደኛ፣ ህገ መንግስቱና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን መቀበልና ማክበር፣ ሁለተኛ የመሰላቸዉን ዓላማ በዚህ ማእቀፍ ዉስጥ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ማራመድ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ታጣቂ ድርጅት፣ ከመንግስት ጋር ድርድር ሲያደርግ እነዚህን መስፈርቶች ተቀብሎ ነዉ ሲሉም አክለዋል። በኡጋንዳ ካምፓላ ዉስጥ የተፈጸመዉን ጥቃት ተከትሎ ተመሳሳይ ሁኔታ በኢትዮጵያ እንዳይከሰት፣ ምን ዝግጅት እንዳለ ተጠይቀዉም ጥንቃቄዉ የተጀመረዉ ከዚያ ቀድም ብሎ እንደሆነ አብራርተዋል። ለዝርዝሩ የእስክንድፍ ፍሬዉን ዘገባ ያዳምጡ።
a_howard-rally-04-11-2011-119628784_1458522
https://amharic.voanews.com/a/howard-rally-04-11-2011-119628784/1458522.html
ኢህአዴግ በሰሜን አሜሪካ ያካሄደው ስብሰባ ተቃውሞ ገጠመው
በ12 የዩናይትድ ስቴይትስና በሁለት የካናዳ ከተሞች በሳምንቱ መጨረሻ በኢህአዴግ የአምስቱ አመት የእድገትና የልማት ትራንሽፎርሜሽን እቅድ ዙሪያ የተካሄዱት ስብሰባዎች ድጋፍም ተቃውሞም ተስተናግዶባቸዋል።
ከታቀደለት ጊዜ ወደ ሰዓት ገደማ ዘግይቶ ነበር የተጀመረው ስብሰባ «በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ላይ ከኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ጋር ለመወያየት የተዘጋጀ መድረከ ነበር። በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ መንግሥት አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ አጠር ያለ የማስተዋወቅ ገለጻ በኋላ፣ ስለ ፭ ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ በትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኰንን ገለጻ ሊቀጥል ሲል፣ አንድ ድምፅ ከሕዝቡ መካከል፣ «ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን የህሊና ጸሎት ይቅደም» አለ። «አይሰማም» በሚል ዓይነት፣ መልስ አላገኘም። ግን በድጋፍ መልክ ብዙ ድምጾች ተሰሙ፣ የዩኒቨርሲቲው ፖሊሶች መጡ የቻሉትን እያስነሱና መሬት ላይ እየጎተቱ አስወጡ። አምባሳደር ግርማም፣ እየተጎተታችሁ ከምትወጡ የ«አርፋችሁ ተቀመጡና አድምጡ» ማሳሰቢያ ቢያቀርቡም፣ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰሚ ጠፋ። በመላ አገሪቱ ከ34ሺህ የጤና ኤክስቴንሺን ባለሙያዎች ካሉበት ከጤናው ጀምሮ፣ በመንገዱ፣ በቴሌኮሚኒኬሽኑ፣ በግብርናው፣ በመልካም አስተዳደሩ፣ ወዘተረፈ ያሉትን 10 የልማትና ትራንስፎርሜሽን ግቦች፣ እንዲሁም አራት ዋና ዋና ዕቅዶች፣ እኒሁ የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ፣ ሰሌዳው ላይ በእንግሊዝኛ በተጻፈው ፓወር ፖይንት እየታገዙ፣ ከአንድ ሰዓት በላይ የፈጀ ንግግራቸውን አቅርበዋል። በኃፊነት ባሉበት የትምህርት ዘርፍም አንዳንድ ነጥቦችን ሳያነሱ አላለፉም። በሃዋርድ ዩኒቨርስቲ የክራምተን አዳራሽ ፊትለፊት በመቶዎች የተቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ ነው ያመሹት። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ ኢህአዴግ አሉታዊ ሚና ተጫውቷል ይላሉ ሰልፈኞቹ። የሙስና ጉዳይ የሚያሰጋቸው “በላባችን ያገኘንውን ገንዘብ ለስዊዝ ባንክ አንሰጥም” የሚል መፈክር አንግበው፤ የሰብዓዊ መብት የሚያሳስቧቸው ደግሞ በምርጫ 97 እና ከዚያ ወዲህ በኢህ አዴግ የተገደሉ ናቸው ያሏቸውን ሰዎች ፎሮግራፎች በትላልቅ ፖስተሮች ሰቅለው ድምጻቸውን አሰምተዋል። ወደ ስብሰባው አዳራሽ የሚያመሩትን ሰዎችን በስም እየጠሩ ማሳፈር ነበረበት። በጠቅላላው ወደ ስብሰባው አዳራሽ ለመግባት በደብዳቤ የተጠሩ ሰዎች ከቀጥር በኋላ ወደ ስብሰባው አዳራሽ መግባት ጀምረዋል። በበር ላይ ያስተባብሩ የነበሩ ሰዎች የሚያውቋቸውን ሰዎች ያለ መጥሪያ ደብዳቤ የሞቀ-ሰላምታ ሰጥተው ሲያስገቡ፤ ሌላውን ሰው ደግሞ ደብዳቤ ሲጠይቁና ያልፈለጓቸውንና ጥሪ የነበራቸውን ሰዎች ሲመልሱ ውለዋል። ሙሉ የሬድዮ ዘገባውን ያዳምጡ
a_mbeki-sudan-referendum-06-21-10-96827074_1460372
https://amharic.voanews.com/a/mbeki-sudan-referendum-06-21-10-96827074/1460372.html
የሱዳን የህዝብ ውሳኔ ተቀባይነት ካላገኘ የአካባቢ አለመረጋጋት ሊፈጥር ይችላል ተባለ
“የኢጋድ ተረኛ ሊቀ-መንበርነቱ በኢትዮጵያ እጅ ስለሚገኝ፤ በሰፊው በዚህ ሂደት ይሳተፋሉ፣” ታቦ ምቤኪ
በመጭው አመት የሚካሄደው የደቡብ ሱዳን ህዝበ ውሳኔ ተቀባይነት ባለው መልኩ ካልተካሄደ በአካባቢው አለመረጋጋትን ሊፈጥር እንደሚችል የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ከፍተኛ ልኡክ ታቦ ምቤኪ ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት ከዩናይትድ ስቴይትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ጋር በዋሽንግተን በተለይ በሱዳን ጉዳይ የተነጋገሩት ፕሬዝደንት ምቤኪ የሱዳንን የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክቶ የሚታየው አለም አቀፍ ድጋፍ እንዳበረታታቸው ይናገራሉ። የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስትና ህዝብ የደቡብ ሱዳን የህዝብ ውሳኔ በቀነ-ቀጠሮው እንዲካሄድ የገንዘብ፣ የፖለቲካና የሰው ሀይል እገዛ በሰፊው መኖሩንና ይሄም ተጠናክሮ አንዲቀጥል ሚስተር ምቤኪ ለፕሬዝደንት ኦባማ አሳስበዋል። በደቡብ አፍሪካ በመካሄድ ላይ ባለው የአለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ የነበሩት ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደንንም አግኘተው በሱዳን ጉዳይ እንዳወያዩአቸውም ሚስተር ምቤኪ ተናግረዋል። ለአስርት አመታት የዘለቀው የሰሜን-ደቡብ ሱዳን ውጊያ በ1998 በተፈረመው የCPA ስምምነት ሲፈታ በስምምነቱ ከተካተቱት መስፈርቶች አንዱ የውሳኔ ህዝብ እንደነበር ይታወቃል። በደቡብ ሱዳን ህዝብ ውሳኔ የአፍሪካ ህብረት አባላት የማያሻም ስምምነት አላቸው ያሉት ታቦ ምቤኪ፣የአፍሪካ ህብረት የሱዳንን ውሳኔ ህዝብ እንደሚደግፍና ሱዳንን የሚያዋስንኑት 9 አገሮች በተለይ በቅርበት የጋር መፍትሄ ለማበጀት መስራት እንዳለባቸው አክለው ጨምረዋል። ከነዚህ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ እንዳለችበትም ሚስተር ምቤኪ ይናገራሉ። “የኢጋድ ተረኛ ሊቀ-መንበርነቱ በኢትዮጵያ እጅ ስለሚገኝ፤ በሰፊው በዚህ ሂደት ይሳተፋሉ” ሲሉ የተናገሩት ምቤኪ ሰኔ 14 ቀን በአዲስ አበባ በቅድመ-ሬፈረንደምና ከዚያ በኋላ በሚነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር ስብሰባ ጠርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም በሱዳን ፖለቲካ ዙሪያ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ሚስተር ምቤኪ ተናግረዋል። “ውጤቱ ምንም ይሁን ምን፤ ወደ ውጥረትና ግጭት ሊያመራ አይገባውም። ትንሽም ይሁን ትልቅ የሆነ መተናኮስ ወይንም ጦርነት ተቀባይነት የሌላቸው አካሄዶች ናቸው፣” ብለዋል። አንዳንድ ተንታኞች የሱዳን የህዝበ-ውሳኔ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና የህዝቡን ድምጽ በሚያስከብር መልኩ ካልተካሄደ ግጭቱ ለጎረቤት አገሮችም የራስ ምታት ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። ያ’ እንዳይሆን የጎረቤት አገሮች፣ የአፍሪካ ህብረትና የአለም-አቀፉ ማህበረሰብ ከሱዳን የፖለቲካ ሀይሎች ጋር አብረው እየሰሩ እንደሆነ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የሱዳን ልኡክ ታቦ ምቤኪ ተናግረዋል።
a_burundi-to-cooperate-with-au-on-mediation-but-frowns-on-au-sanctions_3014114
https://amharic.voanews.com/a/burundi-to-cooperate-with-au-on-mediation-but-frowns-on-au-sanctions/3014114.html
ቡሩንዲ የአፍሪካ ኅብረትን የማዕቀብ ሃሣብ ተቃወመች
ቡሩንዲ “የአፍሪካ ህብረት በሚያካሂደው ምርምራ እተባበራለሁ፤ ማዕቀብ ግን ቀውሱን ያባብሳል እንጂ መፍትኄ አያመጣም” እያለች ነው፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ — የቡሩንዲን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት በሚካሄደው የሽምግልና ጥረት “ማዕቀብ እንጥላለን ብሎ ማስፈራራት አይገባም፤ ማዕቀብ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለውን ቀውስ ከማባባስ በስተቀር መፍትኄ አያመጣም” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልየን ኛምዊትዌ አሳስበዋል። መንግሥት ‘በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተፈፅሟል’ የተባለውን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣም ሆነ ሌሎች የመብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ የአፍሪካ ኅብረት በሚያካሂደው ምርመራ ይተባበራል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል ገብተዋል። ኛምዊትዌ ይህን የተናገሩት ባለፈው ሣምንት መጨረሻ አዲስ አበባ ላይ ስብሰባውን ያካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ኮሚሺን “ሁከቱን የሚያራግቡና ቀውሱን እንዲያከትም የሚያደርግ መፍትሄ ለማግኘት የተያዘውን ጥረት የሚያደናቅፉ ሰዎችን ዒላማ ያደረገ ማዕቀብ እንጥላለን” ሲል ያሳለፈውን ውሣኔ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ ነው። "የፕሬዚዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ መንግሥት ቡሩንዲ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይሟገታሉ። “ስለመግለጫው እናውቃለን፤ ትልቅ ትኩረትም ሰጥተነዋል። ምክንያቱም መንግሥቱን እንታገላለን ብለው የዛቱ አንዳንድ ሰዎች የፖለቲካ ግባቸውን ለማሣካት የኃይል መንገድን፣ ግድያን ጭምር ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ስለዚህም ማዕቀቡ እነርሱ ላይ ማነጣጠር ይኖርበታል” ብለዋል ኛምዊትዌ፡፡ ሚኒስትሩ አያይዘውም ከመንግሥትም በኩል ቢሆን በሁከት የተሣተፈ አባል ካለ ማዕቀቡ እርሱንም ሊመለከት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡ “አፍሪካ ውስጥ ብትመለከቱ በማዕቀብ የተፈታ አንድም ቀውስ አታገኙም። የደቡብ ሱዳን ሳይቀር፤ አስታውሣለሁ የሰላምና የፀጥታ ኮሚሺኑ ‘ማዕቀብ ለመጣል አንቸኩል…..ምክንያቱም ሁኔታው በጣም ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለሆነ በዚያ መንገድ ከሄድን ይብሱን ሊያቆለቁል ይችላልና’ ሲል ነበር” ብለዋል፡፡ “ከኛ በባሰ ቀውስ ውስጥ የነበሩ ሃገሮች ጉዳይ በታየበት መንገድ መታየት ይገባዋል” ብለዋል የቡሩንዲው ሚኒስትር። የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶችና የሕዝብ መብቶች ኮሚሺን ጉዳዩን መርምሮ በአንድ ወር ተኩል ጊዜ ውስጥ ሪፖርት እንዲያቀርብ የኅብረቱ የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ጠይቋል። “መንግሥት አጥፊ ሳይጠየቅ እንዲቀር አይፈልግም፤ ስለዚህም በምርመራው ይተባብራል” ብለዋል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ። የቡሩንዲ የፖለቲካ ቀውስ የቡሩንዲ ፕሬዚደንት ንኩሩንዚዛ ተቃዋሚዎች ‘ህገ መንግሥቱን የጣሰ ተግባር ነው’ ብለው ባወገዙት እርምጃ ለሦስተኛ ጊዜ ከተመረጡ ወዲህ ሁከቱ ቀጥሏል። የአፍሪካ ኅብረት የቡሩንዲ መንግሥትና ተቃዋሚ ቡድኖችን የሚያሣትፍ ንግግር በአንዱ የአፍሪካ ሃገር ዋና ከተማ እንዲካሄድ ጥሪ አስተላልፏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አለን ኛምዊትዌ “እኛ ለንግግር ዝግጁ ነን የቡሩንዲያውያን ብሄራዊ ኮሚሺን ብለን ያቋቋምነው እኮ ማናቸውም ዜጋ ስለሀገሩ ቀውስ መናገር እንዲችል መድረክ ለመፍጠር ነው” ብለዋል። ሙሉውን ዘገባ ለመስማት ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
a_adoption-ethiopia-success-_3192024
https://amharic.voanews.com/a/adoption-ethiopia-success-/3192024.html
"በመላው አፍሪካ ላሉ ሕፃናት አሁንም ከፍተኛ እርዳታ ያስፈልጋል" አምበር ስታይም
አምበር ስታይም የተወለደችው በጎንደር ደብረታቦር ከተማ ነው። የ3 አመት ልጅ እያለች ከመሬት መጫወቻ መስሏት ያነሳችው ቦንብ ፈንድቶ ሁለት እጆቿን አሳጥቷታል።
ዋሽንግተን ዲሲ — ወደ አሜሪካ በማደጎ የመጣችው እ.አ.አ በ1970 ነው። ለስራ ወደ ኢትዮጵያ በመጡ አሜሪካውያን። ያኔ የስምንት አመት ልጅ ነበረች። አምበር ስታይም የተወለደችው በጎንደር ደብረታቦር ከተማ ነው። የ3 አመት ልጅ እያለች ከመሬት መጫወቻ መስሏት ያነሳችው ቦንብ ፈንድቶ ሁለት እጆቿን አሳጥቷታል። በዚህ ምክንያት የተለየ አርዳታ ፈላጊ ሆነች። ኢትዮጵያ በሚገኘው የክርስቲያን የህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ከኖረች በኃላ ለስራ ኢትዮጵያ ይኖሩ ከነበሩት ከአሜሪካውያኑ የማደጎ ወላጆቿ ጋር ወደ አሜሪካ መጣች። የመጀመሪያ ዲግሪዋን በማህበራዊ ጉዳይ አጠናቃ ለተወሰነ አመት በሙያዋ ካገለገለች በኃላ የከፍተኛ ትምህርቷን በመቀጠል በማህበራዊ ጉዳይ ሙያ አጠናቃለች። "እናም ትምህርቴን ስጨርስ በሲያትል ለሚገኙ በጎዳና የሚኖሩ ህፃናትና ሴቶችን በመርዳት ስራዬን ጀመርኩ" ትለናለች አምበር ስታይም። "በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ከፍተኛ እርዳታ አሁንም ያስፈልገናል፡ በረሃብ በበሽታና በተፈጥሮ መዛባት ምክንያት ብዙ ሕጻናትና ሴቶች እርዳታ ይፈልጋሉ። በማደጎ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡ አዳጊ ኢትዮጵያውያን ዋነኛው ችግር ሊኖሩበት ስለመጡበት ሃገር ትክክለኛ መረጃን አለማግኘት ሲሆን የልጆቹን ደህንነት የሚከታተል አለመኖሩም ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው። አምበር እንዳለችው የኢትዮጵያ መንግስት ወይም የሚመለከተው አካል በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ መስራት ይገባዋል። ​
a_kerry-hilemariam-igad_1973217
https://amharic.voanews.com/a/kerry-hilemariam-igad/1973217.html
የ United States የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና ከኢጋድ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ
ጆን ኬሪ ትላንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝንና የኢጋድ ማለት የምስራቅ አፍሪቃ የልማት ትብብር በይነ-መንግስታት መሪዎችን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መስርያ ቤታቸው ተቀብለው ሲያነጋግሩ ኢትዮጵያን በክልሉ መሪነት ሚናዋ አሞግሰዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ — የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን ተቀብለው ሲያነጋገሩ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከኛ ጋር በጣም ብዙ ሰርተዋል ብለዋል። “ በኢትዮጵያ ስላለው የጤና ጥበቃ ጉዳይ ብዙ ተነጋግረናል። በደቡብ ሱዳን ያለውን ሂደት ስለማንቀሳቀስ ጉዳይም ተወያይተናል። ኢትዮጵያ በተለይም ሀገሮችን በማቀራረብ ተግባር፣ ተኩስ እንዲቆም በማድረግና ተቀናቃኝ ወገኖች ወደ ድርድር እንዲያመሩ በማግባባት ረገድ የመሪነት ቦታ ይዛ ቆይታለች። ሶማልያ ውስጥ በተካሄደው የሽግግር ጉዳይም ኢትዮጵያ ለኛ ቁልፍ ሚና ነው ያላት። ለዚህ ተግባርዋም እጅግ እናመሰግናለን። በእውነቱ የክልሉ መሪ ናት። ” ሲሉ አሞግሰዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው የኢትዮጵያና የ United States ግንኙነት እየሰረጸ ሄዷል ብለዋል። " በአከባቢው ሰላም፣ መራጋጋትና ጸጥታ እንዲሰፍን ማድረግ የወቅቱ የትብብራችን ምሰሶ ነው። ከዛ ሌላ ደግሞ United States እና ኢትዮጵያ የአሜሪካ መዋዕለ-ነዋይ ፍሰት ኢትዮጵያ እንዲገባ አበክረን እየሰራን ነው። በዚህ መድረክና ጉባኤ ላይም ትልቅ እድል አግኘተናል። በሀገሪ መዋዕለ-ነዋይ የማፍሰስ ፍላጎት ካላቸው በርካታ የ United States ኩባንያዎች ጋር ስንሰራ ቆይተናል። " ማለታቸው ተጠቅሷል።
a_hrw-lefkow-105943744_1460318
https://amharic.voanews.com/a/hrw-lefkow-105943744/1460318.html
የሂዩማን ራይትስ ዋች ከፍተኛ አጥኝ ስለኢትዮጵያ ሪፖርቱ ተናገሩ
ሂዩማን ራይትስ ዋች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያወጣው ሪፖርት ትክክል ነው ሲሉ አንድ ከፍተኛ ኃላፊው ክሱን አጠናክረዋል፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዋች በቅርቡ የኢትዮጵያን መንግሥት ከእርዳታ ጋር በተያያዘ በአፈና ተግባር የከሰሰበትን ሪፖርት ወደማውጣት የወሰደውን ምክንያት የድርጅቱ የአፍሪቃ ፕሮግራም ከፍተኛ የጥናት ኃላፊ ሌስሊ ሌፍኮው ሲናገሩ “የኢትዮጵያ መንግሥት ለብዙ ጊዜ እርዳታን ለፖለቲካ ጭቆና ይጠቀማል ተብሎ ሲከሰስ ቆይቷል፤ ጥናቱንም ለማካሄድ ያነሳሳን ይህ እውነት መሆኑን ለማወቅ ነው። እውነት ከሆነስ በአገሪቱ የተንሰራፋ ነው ወይስ በአንድ አካባቢ የተወሰነ? ብለን ነበር፡፡ የሚያሣዝነው ግን ከገመትነው በላይ በብዙ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የሚሠራበት ሆኖ ማግኘታችን ነው። ” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ ተቃውሞን ለማፈን ከለጋሾች የሚሰጠውን እርዳታ እንደመሣሪያ ይጠቀማል ሲል ዓለምአቀፍ የስብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ባለፈው ሣምንት መባቻ “Development without Freedom: How Aid Underwrites Repression in Ethiopia” “ልማት ያለ ነጻነት፤ በኢትዮጵያ እርዳታ እንዴት ለጭቆና እንደሚውል” በሚል ርዕስ ባወጣው ሪፖርት መክሰሱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሪፖርቱ “የመንግሥትን ስም የማጉደፍ ዓላማ አለው” ሲሉ ክሱን አስተባብለዋል። ለኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ የሚሰጡ መንግሥታትና ድርጅቶች ተወካዮች ሪፖርቱ በጥልቁ እንደሚያሳስባቸው ገልፀው በእርዳታ እደላ ላይ ችግር አይኖርም ብሎ ማስተባበል ባይቻልም ሆን ተብሎ ለፖለቲካ ጭቆና ግል አይውልም ብለዋል። ሂዩማን ራይትስ ዋች በኢትዮጵያ ላይ ስላወጣው ሪፖርት ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ትዝታ በላቸው የድርጅቱን የአፍሪቃ ፕሮግራም ከፍተኛ የጥናት ሃላፊ ሌስሊ ሌፍኮውን አነጋግራለች፡፡ ዓለም አቀፉ የስብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች በዚህ ሪፓርቱ በኢትዮጵያ ገጠሮች የሚኖሩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች ብዙ ጊዜ ብድር፣ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የምግብ እርዳታና የመጠለያ ድጋፍ ይከለከላሉ ሲል ነው የኢትዮጵያን መንግሥት የሚከስሰው። ሌስሊ ሌፍኮው ድርጅታቸው እዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ጥናቱን እንዴት እንዳካሄደ ሲያስረዱ “የኢትዮጵያ መንግሥት ለብዙ ጊዜ እርዳታን ለፖለቲካ ጭቆና ይጠቀማል ተብሎ ሲከሰስ ቆይቷል፤ ጥናቱንም ለማካሄድ ያነሳሳን ይህ እውነት መሆኑን ለማወቅ ነው። እውነት ከሆነስ በአገሪቱ የተንሰራፋ ነዉ ወይስ በአንድ አካባቢ የተወሰነ? ብለን ነበር፡፡ የሚያሳዝነው ግን ከገመትነው በላይ በብዙ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የሚሠራበት ሆኖ ማግኘታችን ነው። ” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን “ሂዩማን ራይትስ ዋች እንደፈለገው ባለፈው ምርጫ ተቃዋሚዎች ሥልጣን ስላልያዙ ተስፋ ቆርጦ የመንግሥትን ስም ለማጉደፍ ያቀደው ነው፡፡ ” ብለዋል ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የእንግሊዘኛው ቋንቋ ሥርጭት በሰጡት መልስ። “ዘገባው አይታመንም፤ ሂዩማን ራይትስ ዋችም በኢትዮጵያ መሠረት የለውም፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዋችዋ የአፍሪካ ፕሮግራዋ ዋና አጥኚ ግን “ይህ አዲስ ነገር አይደለም - ይላሉ - ብዙውን ጊዜ ጨቋኝ መንግሥታት የሪፖርታችንን ይዘት አይቀበሉም፣ በጣም የምያሣዝን ነዉ፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ችግር በመሆኑ መንግሥት ይህን ተቀብሎ የራሱን ምርመራ ያደርጋል፣ ችግሩንም ይፈታል የሚል ነው የኛ ተስፋ። ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች የኢትዮጵያ መንግሥት ከውጭ የሚሰጠውን እርዳታ ለፖለቲካ ጭቆና ያውላል በማለት ባወጣው ሪፖርት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት USAID እና የካናዳው ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት CIDA ባወጧቸው መግለጫዎች ሪፓርቱ በጥልቅ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል። “በኢትዮጵያ በእርዳታ እደላ ላይ ችግር የለም ለማለት ባይቻልም ችግሩ በአሠራር ደረጃ ወይም ሆን ተብሎ በተቀናጀና በመንግሥት መመሪያ የሚካሄድ አይደለም” ብለዋል። ካሁን በፊት ተመሣሣይ ክስ ተነስቶ እንደነበርና ምርመራ ተካሄዶ ያገኙት ጭብጥ ከድርጅቱ ድምዳሜ የተለየ መሆኑንም ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ የሚገኘው Development Assistant Group (የልማት እርዳታ ቡድን) 24 ለጋሽ አገሮችና ድርጅቶችን አስተባብሮ የሚመራው የልማትና የተራድዖ ቡድን በግሉ ያካሄደው ጥናት፣ ሂዩማን ራይትስ ዋች ደረስኩበት ካለው ድምዳሜ ጋር እንደማይጣጣም በመጥቀስ መግለጫ አዉጥቷል፥ የድርጅቱ ፕሮግራም አቀናባሪ ቪክቶሪያ ቺሣላ እንዲያነጋግሩን ጠይቀን ፈቃደኛ አልሆኑም። ሆኖም የልማት እርዳታ ቡድኑ ባወጣው መግለጫ ላይ መልስ እንዳላቸው የሂዩማን ራይትስ ዋችዋን ሌስሊ ሌፍኮውን ጠይቀናል። በቡድኑ የታቀፉት ድርጅቶች “ከቢሯቸው ጠረጴዛ ስላካሄዱት ጥናት ነው የሚናገሩት፤ ወደ ኢትዮጵያ ገጠሮች ሰው ልከው አራሾችን አነጋግረው ያጠናቀሩት ጥናት አይደለም። የሚጠቀሙበት የእርዳታ አስጣጥ ቁጥጥር ሥርዓት በትክክል ይሥራ አይሥራ የገመገሙበት ነው። እሱም ቢሆን፣ የእርዳታ አስጣጥ ሥርዓቱ ከፍተኛ ድክመት እንዳለው ነው የጠቆማቸው፡፡ መሻሻል የሚያስፍልጋቸው ብዙ ክፍተቶች እንዳሉት ጥናቱ በእርዳታ አሰጣጥ ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑንና ወደፊት ግን ጠለቅ ያለ ምርመራ እንደሚያስፈልግ ነው ውጤቱ የጠቆመው። ሆኖም ግን ይህ ውጤት በእጃቸው እያለ የኛን ጥናት ውጤት መቃወማቸው ያስገርማል። ” ብለዋል፡፡ ሚስ ሌፍኮው አክለውም “እንዲህ ዓይነቱን የእርዳታ እህል ለፖለቲካ ተቃዋሚ መቅጫ መጠቀም ክልልም ባይሆን በጣም ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ባለባት አዲስ አበባና በሦስት ክልሎች፣ ማለትም በኦሮሚያ፣ በአማራና ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች ላይም ሪፖርት ማድረጋችን፣ በጣም ሰፊ በሆነ ጂኦግራፊያዊ ክልል ከሃምሣ በላይ በሚሆኑ ቀበሌዎች ማየታችን የችግሩን ስፋትና ተደጋጋሚነት ያሳያል። እኛ እንዲሁ ክልል ላይ አምባገንን የሆኑ ግለስቦች በግላቸው ተነሳስተው የሚፈጽሙት ወንጀል አይመስለንም፤ ተያያዥነት አለዉ” ብለዋል፡፡ ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
a_colors-of-voices-conversation-with-an-author-air-force-pilot-and-a-humanitarian-radio-magazine-with-alula-kebede-and-addisu-abebe-july-01-20_4466020
https://amharic.voanews.com/a/colors-of-voices-conversation-with-an-author-air-force-pilot-and-a-humanitarian-radio-magazine-with-alula-kebede-and-addisu-abebe-july-01-20/4466020.html
የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች
"ድንገት "ቷ" የሚል ድምፅ ሰማሁ። እጄ ተንቀጠቀጠ። ጮኹኩ። .. "መቱት፣ መቱት!" እል እንደነበረ ትዝ ይለኛል።.. ዜና አንባቢው ተመልሶ መጥቶ በቦንብ ፍንዳታ የተጎዱ ጥቂት ሰዎች መኖራቸውን ሲናገር መሬት ላይ ተጣጥፌ ቁጭ አልኩ።..”የቅዳሜው ድንገት በአድማጭ ማስታወሻ። “በሥልጣን ላይ ያሉትና ለሥልጣን የሚዘጋጁ መሪዎቻችን ይህን መጽሐፍ በጥሞና ቢያነቡ ምን ያህል ትምህርት ባገኙበት?” አልሁ። 'ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይና በበጎም በጥርጣሬም ዙሪያቸውን ለተሰለፉ ሁሉ ቀበቶዬን አስሬም ቢሆን መጽሐፉን ገዝቼ ልላክላቸው?' የሚል ነገርም ዳዳኝ።” ይልማ አዳሙ።
ዋሺንግተን ዲሲ — የአድማጮች ማስታወሻ ነው። በሁለት የዓለም ጫፎች ያሉ (በሃሳብም ወደ ቀያቸው የሚጣሩ) የሁለት ዘመናት ለየቅል ገጠመኞች ትርክት ነው። እንደ አድራሽ መልዕክተኛም ከሁለቱ ቀዬዎች የሚያውሉን። አንድም ከምንኖርበት ሁለትም ከምናስበው። በቀዳሚው የራዲዮ መጽሔት ገጽ (ከድምጹ ማጫወቻ) የሚያነቡት የቅርብ ሩቅድምጽ አሳዛኝም ተስፋ ለማድረግም በቂ ምክኒያት ያዘለ ከሚመስል ሰሞንኛ ጉዳይ ዙሪያ የሚያጠነጥን አንዲት የመካከለኛው ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሚነሶታ ክፍለ ግዛት ቤተኛ አድማጫችን ያደረሰችን ከማስታወሻዋ የሰፈረ ስዕል ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል የጦር ተዋጊ ጄት አብራሪ (ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደሕንነት አገልግሎት የመስክ አስተባባሪ መኮንን ናቸው። ) ዳዊት ወንድይፍራው ይባላሉ። ከተወለዱና ካደጉባት የአራት ኪሎዋ ግንፍሌ .. የዓየር በረራ ሃሁ እስከ ቀሰሙባት ክራስኖዳር ሶቭየት ሕብረት የዓየር ኃይል ኮሌጅ፤ የደብረዘይቱ የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል ካምፕ .. ድሬዳዋ… ጎዴ .. አስመራ እና ሌሎች የተለያዩ የጦር አውድማዎች ..ከከሸፈው የመንግስት ግልበጣ ጉዳይ .. የስደት ሕይወት እና ለስደተኞች ደራሽ የመሆን ሥራ .. በሊቢያ .. ሶሪያ .. ቱርክ እና ሌሎች የዓለም አካባቢዎች .. “ያልታለመው የሕይወት መንገድ” በተሰኘው መጽሃፋቸው ያጏጉዙናል። ይኽኛው ደግሞ ብዙ ዘመናት ወደ አንድ ወደ ራቀና ለብዙዎች አድማጮቻችንም እንግዳ የሆነ የታሪክ የሚወስድ ነው። ሃሳቡ ግን ቅርብም የራስም ሊያደርጉት የሚጋብዝ ነው .. የባላንጣዎች ቡድን። ይልማ አዳሙ ከምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የሎሳንጀለስ ከተማ ያደረሱን መጣጥፍ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ 2005ዓም የታተመ እና ለPultizer ሽልማት የበቃ መጽሃፍ ነው። .. “Team of Rivals: The Political Genius of Abraham Lincoln” ይሰኛል።
a_osama-africa-react-5-2-11-121102499_1460698
https://amharic.voanews.com/a/osama-africa-react-5-2-11-121102499/1460698.html
በኦሳማ ቢን ላድን ግድያ አፍሪካዊያን የተቀላቀለ ምላሽ ሰጡ
በርካታ የአፍሪካ መንግስታት የአል-ቃይዳውን ቁጥር አንድ ኦሳማ ቢን ላድን መገደል አወድሰዋል፤ አንዳንድ ግለሰቦች ደግሞ ኦሳማ ለፍርድ መቅረብ ነበረበት ሲሉ ተደምጠዋል።
ኦሳማ ቢን ላድን በአፍሪካ ላይ ካነጣጠራቸው የሽብር ስራዎች፣ ብዙ ሰዎችን የገደለው በ1990 ዓም በኬንያና ታንዛንያ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲዎች የደረሰው ፍንዳታ ነው። በጥቃቱ 224 ሰዎች ተገድለዋል። የኬንያ ፕሬዝደንት ምዋይ ኪባኪ የኦሳማ ቢን ላድንን በአሜሪካ ልዩ ሃይሎች መገደልን ተከትሎ በሰጡት አስተያየት “ፍትህ ሚዛኗን አደላደለች” ሲሉ ተናግረዋል። በናይሮቢ ቦምብ ጥቃት ላይ የተባበሩን ሁሉ የሚይዙ መንግስታትን ፕሬዝደንት ኪባኪ አወድሰዋል። ባለፈው ሳምንት በአልቃይዳ ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባት ሞሮኮ ደግሞ የማስታወቂያ ሚኒስትር ኻሊድ ናችሪ በቢን ላድንና በድርጅቱ ያልተነካ የአለማችን ክፍል አይገኝም ብለዋል። ናችሪ አክለውም የሞሮኮ ህዝብ በንጹሃን ግድያ የማያምን መሆኑንና ሁከት ፈላጊነትን አገሪቱ አጥብቃ እንደምታወግዝ ገልጸዋል። የደብቡ አፍሪካ መንግስት ደግሞ ጥንቃቄ የተመላበት መግለጫ አውጥቷል። ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ዜናውን ለአለም ህዝብ ይፋ ካደረጉ በኋላ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በአጭሩና በደፈናው “ምንም አይነት የሽብርተኝነት ተግባርን በምንም አይነት ገጹ እንደማይቀበለው” የውጭ ጉዳዮችና ትብብር ሚኒስቴር አስታውቋል። ይሄንንም ለመታገል አለም አቀፍ ስምምነትና ትብብር ሊኖር እንደሚገባም አሳስቧል። በናይጀሪያ የደህንነት ማካሪ የሆነው ኢቫወሬ ኦይዴ በኦሳማ ቢን ላድን ግድያ አፍሪካዊያን ያላቸው ምላሽ የተዘበራረቀ ነው ይላል። “አንዳንድ ሰዎች ይሄንን እንደ እፎይታ ይመለከቱታል። ሌሎች ደግሞ ምእራባዊያንን አጥብቆ የሚቃወምና የሚዋጋ ሰው ብለው ያስቡታል። ለብዙ ሰዎች ኦሳማ ጀግናቸው ነው። አሜሪካ ባላት የደህንነትና የወታደራዊ አቅም ለአስር አመት ልትይዘው ያልቻለች ሰው ነው በሚል ያደንቁታል። በናይጀሪያ በንግድ የሚተዳደረው አንድሩ ኢጂሮ ክሮስ ደግሞ ኦሳማ ቢን ላድን መገደል አልነበረበትም ይላል። እንዲያውም ትጥቁን አስፈትተው እጁን ይዞ የኦባማ አስተዳድር ለፍርድ ሊያቀርበው ይገባ ነበር ይላል። ከሶቪየት ህብርት ጋር ባደረጉት ጦርነት ኦሳማን ለዚህ እንዲበቃ የደገፉት አሜሪካኖቹ እራሳቸው ናቸው ይላል ክሮስ፤ በዚህም አሜሪካን ተጠያቂ ያደርጋል። “ኦሳማ ቢን ላድን ገንዘብ ይፈልግ የነበረ ነጋዴ ነበር። አሜሪካኖቹ ተጠቀሙበት። የፈለጉትን ካደረጉ በኋላ አሁን ደግሞ ገደሉት። መግደሉ ለምን አስፈለገ? አሜሪካ ከጠላችህ በቃ አለቀልህ፤ ይገድሉሃል። የዩጋንዳ መንግስት በበኩሉ የኦሳማን መገደል “የምስራች” ብሎታል። የመንግስቱ ቃል አቀባይ ፍሬድ ኦፖሎት በሶማሊያ በሰላም ማስከበር ስራ የተሰማሩ የዩጋንዳ ወታደሮች ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላቸው ያሉትን አል-ሸባብን በርትተው እንዲዋጉ ጥሪ አስተላልፈዋል። በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የኦሳማ ቢን ላድንን ደም እንደሚበቀል አንድ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የኬንያ መንግስት የደህንነት ጥበቃውን ማጠናከሩንና በተለይ ከሶማሊያ ጋር በሚዋሰነው ግዛቱ ስጋቱ የጠነከረ ስጋት እምዳለው መንግስቱ አስታውቋል።
a_ethiopia-ogaden-somal-shinn-uwsuf-08-10-10-100346109_1460569
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-ogaden-somal-shinn-uwsuf-08-10-10-100346109/1460569.html
ዴቪድ ሺን ስለ ኦጋዴን፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ኦብነግ
"ያ ቡድን ኦጋዴን ውስጥ በስፋት የሚንቀሣቀስ አይደለም፡፡ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ድምፁን አጥፍቶ ቆይቷል፡፡"
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) በሶማሌ ክልል ማዕከላዊቱ ደገሕቡር አካባቢና በስተደቡብ ባለችው ቀብሪደሃር በሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃቶችን ማድረሱን በቅርቡ አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የተባበረው የምዕራብ ሶማሌ ነፃነት ግንባር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት መፈረሙና ንግግሮቹ አሁንም እንደቀጠሉ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡ እንዲያውም በቅርቡ ተከታይ ውይይታቸውን ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ በአንድ በኩል የሰላም ድርድርና ስምምነት ከኦጋዴን አካባቢ ሲሰማ በሌላ በኩል ደግሞ የጥቃትና የግጭት ዜናም እየወጣ ነው፡፡ ስለመጠነ ሰፊው የኦብነግ ጥቃት የተናገሩት ለንደን የሚገኙት የኦብነግ የውጭ ግንኙነቶች ፀሐፊ አብዲራህማን ማኅዲ ሲሆኑ መግለጫው መሠረት የሌለው ነው ሲል ደግሞ አንድ ለጊዜው ማንነቴ አይገለፅ ያለ ለኢትዮጵያ መንግሥት ቅርበት ያለው ምንጭ አመልክቷል፡፡ ምንጩ የኦብነግን አብዛኛውን አመራርና ሠራዊቱን የሚወክሉ ቡድኖች ከመንግሥት ጋር የዕርቅና የሠላም ድርድር ላይ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ አክሎም ኦብነግ በአሁኑ ሰዓት በማንም ላይ ጥቃት ማድረስ በሚችልበት ሁኔታ ላይ የሚገኝ ኃይል አለመሆኑን አመልክቶ "አንዳንድ በሕገወጥ እንቅስቃሴ ለመቀጠል የወሰኑ ሦስት እና አራት እየሆኑ በተበታተነ ሁኔታ የሽብር ተግባር የሚፈፅሙ የጉዳትና የውድመት ዜና በማውጣት በመገናኛ ብዙኃኑ ትኩረት ውስጥ ለመቆየት ያልያዙትን ያዝን፣ ያልማረኩትን ማረክን ከሚሉ በስተቀር አድርሰናል የሚሉት ጥቃትም ሆነ ጉዳት ውሸት ነው" ብሏል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካን በተለይም ደግሞ ይህንን የኢትዮጵያ ሶማሌ የፖለቲካ ጉዳይ በቅርብ ከሚከታተሉ ምሁራንና ዲፕሎማቶች ዴቪድ ሺን አንዱ ናቸው፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ጉዳዮች መምህርና ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር ሚስተር ዴቪድ ሺን ስለእነዚህ መግለጫዎችና በአሁኑ ወቅትም በአካባቢው ስላለው ሁኔታ አጠር ያለ ግምገማ ለአሜሪካ ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ ሚስተር ሺን በዚሁ ግምገማቸው ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትና የተባበረው የምዕራብ ሶማሌ ነፃነት ግንባር የሰላም ስምምነት መፈረማቸውና እርሣቸው በወቅቱ በአጋጣሚ አዲስ አበባ ውስጥ ስለነበሩ ከፊርማው ሥነ-ሥርዓት በኋላ ከግንባሩ መሪ ሼኽ መሐመድ ሁሴን ጋር መነጋገራቸውን አመልክተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በአጠቃላይ "ሰላም አለ ወይም የለም" ለማለት አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው የሚናገሩት አምባሣደር ሺን ሁኔታው በሰፊው የኦጋዴን ክልል ውስጥ ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ዛሬ የተሻለ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ኦብነግ ሰሞኑን አድርሻቸዋለሁ የሚላቸውን ጥቃቶች እውነትነትና ሃሰትነት ለማረጋገጥ እንደሚከብዳቸው የሚናገሩት አምባሣደር ሺን ምን ያህል ክብደት ያለውና ለምን ያህል ጊዜ የተራዘመ ውጊያ ማካሄድ ይችላል የሚል ጥያቄ ካልተነሣ በስተቀር በተለይ በሞሐመድ ዑማር ኦስማን የሚመራው ቡድን ጥቃት የመሠንዘር አቅም አሁንም እንዳለውና ብዙውን ጊዜም አደጋ ስለመጣሉ የሚናገረው እርሱው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ስለመሰል ጥቃቶች መግለጫ በሚሰጡበት ጊዜ የኦጋዴኖቹ አማፂያንም ሆኑ መንግሥት የማጋነን አዝማሚያ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ እነዚህ የኦጋዴን አማፂያን ከኤርትራ የተወሰነ ድጋፍ እንደሚያገኙም ዴቪድ ሺን ጠቁመዋል፡፡ አምባሣደሩ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚታየውን "ተገቢነት ያለው" የሚሉት ቅሬታ አስመልክቶ ሲናገሩም በዚያ ይበልጥ ልማት፣ ይበልጥ ዴሞክራሲና እስከ ታች የወረደ የሥልጣን ክፍፍል መኖር እንዳለበት ገልፀው የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር አንጃዎች የሚያራምዱትን የመገንጠል ሃሣብ እንደማይደግፉና ብልህነት ነው ብለውም እንደማያምኑ ተናግረዋል፡፡
a_oromya-corruption-chages-03-15-11-118029634_1457732
https://amharic.voanews.com/a/oromya-corruption-chages-03-15-11-118029634/1457732.html
ኦሕዴድ ከ120 በላይ አባላቱን በሙስና ጠርጥሮ አገደ
ከ120 በላይ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ከፍተኛና ባለስልጣናት በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል፤ ክድርጅቱ አባልነትና ከስልጣንም ተወግደዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በክልሉ ማረሚያቤቶች ያለ ጠያቂ በእስር ላይ ናቸው ከአንድ ሳምንት በላይ የፈጀው የኦሕዴድ ድርጅታዊ ግምገማ ከ120 በላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ባለስልጣናትን የሙስና ጉዳይ መርምሯል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ማረሚያ ቤቶች ቁጥጥር ስር የሚገኙት ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱና ለፍርድ እንዲቀርቡ መወሰኑን በስብሰባው የተሳተፉና መግለጫ የመስጠት ስልጣን የሌላቸው የኦሕዴድ አባላት ገልጸውልናል። ከታሳሪዎቹ የሚበዙት በከተማ ከንቲባነትና በቀበሌ አስተዳድር ውስጥ የሚሰሩ ቢሆኑም የክልሉ ካቢኔ አባላት የነበሩ ከፍተኛ አመራሮችም እንደሚገኙበት ታውቋል። በተለይ በሰበታ፣ አለምገና ናዝሬት (አዳማ) ደብረ ዘይት (ቢሾፍቱና) በጠቅላላው በአዲስ አበባና በአካባቢዋ የሚገኙ ከተሞች ሹማምንት በሙስና ተጠርጥረው ከታሰሩት የሚበዙት ናቸው። ከህዝብን መሬት ለባላሃብቶችና ለግለሰቦች፤ በጥቅም በመደለል የሚዘርፉ ባለስልጣናት መበራከታቸውን ጠንቅቀው እንደሚያውቁ፤ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሳምንቱ መጨረሻ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል። “መሬት የዘረፉም ያልዘረፉም ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን። ዋናው አደጋ ዘራፊው ሳይሆን አዘራፊው ነው” ብልዋል አቶ መለስ። መሬት ከዘረፉት ባለሃብቶች ጥቂቶቹ ለፍርድ እንደሚቀርቡና የተቀሩት ደግሞ ምህረት ተደርጎላቸው በከባድ አስተዳድራዊ ቅጣት ይቅርታ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል። “ያዘረፉት የመንግስት ሰራተኖች በሙሉ ግን፤ በሙሉ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ። ትልቁ አደጋ የመንግስት ሙስና ነው። በናዝሬት ከተማ ለረጂም ጊዜ የኖረውና ሙሉ ስሙን እንዳንጠቅስ የጠየቀን ነዋሪ በኦሮሚያ ክልል፤ በተለይ በናዝሬት የሙስና ችግር አዲስ አይደለም ይላል። መንግስት እያወቀ፤ ህዝቡን የቀበሌ ሹማምንት፣ የከተማ ከንቲባዎች መሬቱን እየሸጡ፣ ከቤቱ እያፈናቀሉ ሲያጎሳቁሉት፤ መንግስት የት ነበር? ብሎ ይጠይቃል የናዝሬቱ ነዋሪ። ነዋሪው የሚናገረው መንግስት ሁኔታውን ላለፉት አምስት አመታት ጠንቅቆ እንደሚያውቀው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሙስና ኢህ አዴግ በምርጫው ወቅት ከህዝቡ ከተጠቆሙ ድክመቶቹ አንዱ መሆኑን ያምናሉ። በኦሮሚያ ምክር ቤት የተካሄደውን ስብሰባ የመሩት የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን የአዲስ አበባው ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ናቸው።
a_ethnic-federalism-or-multinational-politics-for-ethiopia-discussion-10-15-16_3553853
https://amharic.voanews.com/a/ethnic-federalism-or-multinational-politics-for-ethiopia-discussion-10-15-16/3553853.html
ፌደራል ሥርዓቱና የኢትዮጵያ ፖለቲካ
አቶ ገለታው ዘለቀ ያጠኑትና የድኅረ-ምረቃ ዲግሪ ያገኙበት መስክ ልማት ነው። በኢትዮጵያ ወቅታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሣትፎ ያደርጋሉ። “የኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች” በሚል ርዕስ ለንባብ ያበቁትን ጹሑፍ መሠረት አድርገን ለውይይት ጋብዘናቸዋል።
ዋሺንግተን ዲ.ሲ. — ኅብረብሄር ፖለቲካ? ወይስ የብሔር-ብሔረሰቦች ፌደራሊዝም? - ውይይት ከአቶ ገለታው ዘለቀ ጋር፡፡ አቶ ገለታው ዘለቀ ያጠኑትና የድኅረ-ምረቃ ዲግሪ ያገኙበት መስክ ልማት ነው። ከደቡብ ኮርያ ጓንጁ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ በልማት ጥናት ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው። በኢትዮጵያ ወቅታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሣትፎ ያደርጋሉ። “የኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች” በሚል ርዕስ ለንባብ ያበቁትን ጹሑፍ መሠረት አድርገን ለውይይት ጋብዘናቸዋል። አቶ ገለታው “በብሔር-ብሔረሰብ መደራጀትን የሚመርጡ ኢትዮጵያዊያን በሕገ-መንግሥቱ የተደነገገውን ገዥው ፓርቲ ባለማክበሩ እንጂ የፌዴራል ሥርዓቱ የምንመርጠው ነው” እንደሚሉ ይናገራሉ፡፡ ኅብረብሔር ሆነው የተደራጁ ደግሞ “ፌዴራል ሥርዓቱ ለሀገሪቱ ፖለቲካ መመሳቀል ምክንያት ነው” እንደሚሉ አቶ ገለታው ዘለቀ ይጠቁማሉ፡፡ በአመለካከት ወደ እነዚህኞቹ ወገን ያደላሉ፡፡ የሕወሓት መሥራችና ከፍተኛ የአመራር አባላትም በቅርቡ ኢትዮጵያን ከገጠማት ቀውስ ጋር አያይዝው ስለ ኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ሥርዓት የተናገሩት አለ፡፡ ሁለቱን ሃሳቦች የተጣቀሱበትን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
a_meles-presser-08-12-10-100576419_1460253
https://amharic.voanews.com/a/meles-presser-08-12-10-100576419/1460253.html
ኢትዮጵያ የስዊድን ኢምባሲዋን ልትዘጋ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መግለጫ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመጭው ጥቅምት አካሂዳለሁ ባሉት የመንግስት ለውጥ፤ እየተቀያየረ የሚሄደውን የኢትዮጵያን የወዳጅነት አቅጣጫ ተከትለው የሚዘጉና አዲስ የሚከፈቱ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች እንደሚኖሩ አስታወቁ። ከሚዘጉት መካከል የመጀመሪያ የሚሆነው በስዊድን የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንደሚሆን ተናግረዋል። "በኛና በስዊድን መካክል ትርጉም ያለው የልማት ትብብር መርሃ ግብርም ሆነ የንግድ ልውውጥ የለም፤ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ የጎላ ኢንቨስትመንትም የለም" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ። "ብራዚል ወደ ብልጽግናው አለም እየዘለቀች ያለች ግዙፍ አገር ሆና በዚያ ግን ኢምባሲ የለንም። ስለዚህ የስዊድን ኢምባሲያችን ከሚዘጉት ቀዳሚው ነው። ምክንያቱም ኤምባሲ በዚያ መክፈት ጥቅም ያለው ጉዳይ አይደለም፣" ብለዋል። በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ መካከል ያሉት ግንኙነቶች ለወራት በውጥረት ውስጥ ከቆዩ በኋላ አሁን እየተጠገኑ ነው ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስታወቁ፡፡ ያ ከዋሽንግተን ጋር በአስቸጋሪ ሁኔታ የተወጠረ ያሉት የግንኙነት ሁኔታ ዛሬ ያለፈ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አመልክተዋል፡፡ "ባለፉት ስድስት እና ሰባት ወራት ገብተንበት የነበረው አስቸጋሪ መካረር በብዙ ርቀት ወደኋላ የቀረ ይመስለኛል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በተለየ ሁኔታና አክብደው የሚያይዋቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ በእነዚያ በማንስማማባቸው ጉዳዮች ላይ ላለመስማማት እንስማማለን፤ የጋራ ጥቅሞቻችንን በሚያገለግሉ ጉዳዮች ላይ ደግሞ አብረን ለመሥራት እንስማማለን፡፡ " ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ ለአንድ ዓመት ክፍት ሆኖ የቆየው በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሣደር ቦታም በመጭው ጥቅምት ወር አጠቃላይ ለውጥ አድርገው አዲስ መንግሥት ሲመሠርቱ በሚሾም አምባሣደር እንደሚሞላ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጠቁመው የካቢኔ ለውጡ የሃገሪቱን የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖችም እንደሚያጠቃልል ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ ይፋ ስለተደረገው የአምስት ዓመት የኢኮኖሚ ዕቅድ ሲናገሩም የሃገሪቱ የውጭ የምግብ ዕርዳታ ጥገኝነት እንዲያበቃ የሚያደርግ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጠቁመው በተባለው ጊዜ ኢኮኖሚው ከ11 እስከ 14 ከመቶ የሚደርስ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ ተናግረዋል፡፡
a_usethiopia-relations-05-19-10-94321429_1462285
https://amharic.voanews.com/a/usethiopia-relations-05-19-10-94321429/1462285.html
የኢትዮ-አሜሪካ ግንኙነት በዚህ በምርጫ አመት እንዴት ይገመገማል?
የዴሞክራሲ ጉዳይ ፈተና ከሆነባት ኢትዮጵያ ጋር ዩናይትድ ስቴትስ አስቸጋሪ፣ ግን ደግሞ ለእርሷ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ግንኙነት ውስጥ መግባት መገደዷን አሜሪካዊያን የአፍሪካ ጠቢባን እየተናገሩ ነው፡፡
"ኢትዮጵያ ተግባሯን ታስተካክል ዘንድ ከሞራል ጫና በላይ አንዳች ኃይል ማሣረፍ ለዩናይትድ ስቴትስ ከባድ ይሆንባታል" ኢቭ ሣንድበርግ በ1997 ዓ.ም በኢትዮጵያ የደመቀ የምረጡኝ ዘመቻ ውስጥ እንዲያ የበረታ ፉክክር ሲደረግ በዴሞክራሲ ገፅታዋ ለይ የተሃድሶ ነፋስ ያድራል ሲሉ ተስፋ የጣሉ ብዙ አሜሪካዊያን የዴሞክራሲ ተሟጋቾች ነበሩ፡፡ የተቃዋሚው ጎራ መሪዎችም እጅግ የበዙ ደጋፊዎቻቸውን ደጋግመው ወደ አደባባይ ማውጣት ችለው ነበር፡፡ ምርጫው ተጠናቅቆ ውጤት ሲወጣ ገዥው ፓርቲ በሰፋ አብላጫ ማሸነፉ ተነገረ፤ ተቃዋሚዎቹም 'ምርጫው ተጭበርብሯል' ብለው እሮሮ ሲያሰሙ ደጋፊዎቻቸው ዋና ዋና በሚባሉ ከተሞች ወደ ጎዳና ወጡ፡፡ ከመሃላቸው ወደ 200 የሚጠጋ ሰው በወቅቱ በተቀሰቀው ግጭት ውስጥ የጥይት ሰለባ ሆነ፡፡ ብዙዎች፤ የተቃዋሚ መሪዎችም፣ በምርጫው ያሸነፉም ሳይቀሩ በየእሥር ቤቱ ታጎሩ፡፡ ያ ነገር ከሆነ እነሆ አምስት ዓመት ሆነ፡፡ ዛሬ ታዲያ የውጭ የምርጫ ተንታኞች የፊታችን ዕሁዱን ምርጫ በከፋ ጥርጣሬ እያዩት ነው፡፡ 'ይህ ምርጫ ፍትሐዊ ይሆናል ማለት መዘባበት ነው' ሲሉ ከወዲሁ ይናገራሉ፡፡ ገዥው ፓርቲ መገናኛ ብዙኃኑን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን፣ በአሠርት የሚቆጠሩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች ዘብጥያ መውረዳቸውንና ገለልተኛ የሆኑ የምርጫ ታዛቢዎች አለመኖራቸውን ጭምር እየዘረዘሩ የምርጫው ዝግጅት እራሱ በችግር የተዋጠ መሆኑን ታዛቢዎች ይጠቋቁማሉ፡፡ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤትም ብርቱ ወቀሣ እያሰማ መሆኑ ይወራል፡፡ ብዙ ቁጥር ያላቸው እንደራሴዎች 'የኢትዮጵያ መንግሥት እያደር አምባገነን ሆኗል' እያሉ እያሳሰቡ ነው፡፡ በቅርቡ ለኢትዮጵያ የተላኩት የአሜሪካ አምባሣደር ዶናልድ ቡዝ በዚያች ሃገር ዴሞክራሲ እንዲጠናከር፣ ሰብዓዊ መብቶችም እንዲከበሩ ለማስቻል እንደሚጥሩ ቃል መግባታቸውን የኦበርሊን ኮሌጅ የፖሊሲ መምህር ኢቭ ሣንድበርግ ተናግረዋል፡፡ "ይሁን እንጂ - ይላሉ ፕሮፌሰር ሣንድበርግ በመቀጠል - ኢትዮጵያዊያኑ ከቀደሙት አምባሣደሮችም እንዲህ ዓይነቶቹን ቃላት ሰምተዋል፡፡ አሁን ጥያቄው ቡዝ እውን አቅም አግኝተው የኢትዮጵያ መንግሥት ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶችን ያከብር ዘንድ አንዳች ተግባር ማከናወን ይችላሉ ወይ? ነው፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና ወደፊት እንድትራመድ ለማድረግ ምን ያህል መጓዝ ወይም መግፋት እንደሚችል ግራ የተጋባ መንታ መንገድ ላይ ቆሟል፡፡ ኢትዮጵያ እኮ በጣም አስፈላጊ ሸሪክ ነች - ይላሉ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ አማካሪ ሆነው የሠሩት እኒሁ ፕሮፌሰር ኢቭ ሣንድበርግ፡፡ "በአንድ በኩል - አሉ ሣንድበርግ - በምዕራቡ ዐይን ኢትዮጵያ ከአጋንንቱ ብዙም ያልገነነውን የሶማሊያን መንግሥት አቋቁማለች፤ እየጠበቀችውም ነው፡፡ በዚህም በብዙ ኃላፊነት ተሸክማለች፡፡ ምክንያቱም ያንን መንግሥት የሚቃወመው'ኮ በአልቃይዳ ሠልፍ ውስጥ የቆመ አማፂ ቡድን ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደአስፈላጊ ሸሪክ የምትታይበት ሌላው ጉዳይ በቀንዱ አካባቢ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ለማወቅ በብዙ የምንጠቀመው የእነርሱን የስለላ መዋቅር ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያዊያኑ እኛ እንደምንፈልጋቸው ያውቃሉ፡፡ ከዚህ የፕሮፌሰር ሣንድበርግ አባባል ጋር በቅርቡ ኢትዮጵያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የሚሲዮኑ ምክትል ኃላፊ የነበሩት ቶማስ ሃልም ይስማማሉ፡፡ 'ኢትዮጵያ ቁልፍ የሆነች መልክዓ ምድራዊና ፖለቲካዊ ሥፍራ ነች' የሚሉት ሃል በዚያ ላይ የአፍሪካ ኅብረት ዋና ፅ/ቤትም የሚገኘው በዚያው እንደሆነ ያስታውሱናል፡፡ "በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ ተግባሯን ታስተካክል ዘንድ ከሞራል ጫና በላይ አንዳች ኃይል ማሣረፍ ለዩናይትድ ስቴትስ ከባድ ይሆንባታል፡፡ " ብለዋል ዲፕሎማቱና አሁን በሣይመንስ ኮሌጅ የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ፕሮፌሰር ቶማስ ሃል፡፡ ፕሮፌሰር ሃል እንደሚሉት አሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ ያሏት ተፎካካሪ ጥቅሞች መንግሥቷ የበረታ ጫና እንዳያሣድርም መሰናክል ይሆኑበታል፡፡ "የንግድ ግንኙነቶቻችን በመጠን አንፃር ሲታይ እምብዛም አይደሉም፡፡ " ይላሉ ሃል፤ የገበያ ግንኙነቱን በንፅፅር ሲያስቀምጡም " ቻይናዊያኑ፣ ሕንዳዊያኑና ሣዑዲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሠሩ ካሉት ጋር ሰነፃፀር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ብዙው ለሃገሪቱ የምናደርገው ሰብዓዊ ልገሣ ነው፤ የምግብ፣ ፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስን የመሣሣሰሉ..." ብለዋል፡፡ የጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ቴሬንስ ሊዮንስ ግን የኦባማ አስተዳደር ግንኙነቶቹን የቡሽ ከነበረበት ዓይነት ለመለወጥ እየጣረ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ ሊዮንስ እንዲህ ይላሉ፡- "ባለፈው አስተዳደር ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ ጋር ለነበሯት ግንኙነቶች የፀጥታ ሥጋቶቿና ፀረ-ሽብር ጉዳዮች ዋነኛ ሚዛን ነበሩ፡፡ አሁን ግን እኔ እንደማስበው አስተዳደሩ ይህንን ግንኙነት እደገና እየፈተሸ ነው፡፡ ምንም እንኳ የፀጥታው ጉዳይ ባለበት ቢቀጥልም ዋናው ግን ዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብቶችና ከእነዚህ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮች ናቸው፡፡ ሊዮንስ እንደሚሉት ግንኙነቱን ለመለወጥ አሥር ዓመትና ከዚያም በላይ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በእርሣቸው እምነት 'የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ከአዳዲሶቹ የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ባለሥልጣናት ጋር መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡
a_amh-voa-ethiopia-10-4-10-104305154_1463110
https://amharic.voanews.com/a/amh-voa-ethiopia-10-4-10-104305154/1463110.html
የአሜሪካ ድምጽ፣ የኢትዮጵያ መንግስትና የመገናና ብዙሃን ነጻነት
የአሜሪካ ድምጽ ለምን በዩናይትድ ስቴይትስ እንዳይሰማ በህግ ተከለከለ? የኢትዮጵያ መንግስት ሬድዮውን ሲያፍን የሚሰጠው አስተያየት ከአገሪቱ ህገ-መንግስት አንጻር እንዴት ይታያል?
“የአሜሪካ ድምጽ ወደ ኢትዮጵያ በሚገባው ህገ መንግስቱ ስለሚፈቅድ ነው” የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ በኢትዮጵያ እንዲሰራጭ እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። አቶ መለስ ቪኦኤ በአሜሪካ እንዲያሰራጭ በህግ አይፈቀድለትም፤ እኛም በተለይ አማርኛ አገልግሎቱን በኢትዮጵያ እንዲያሰራጭ አንፈቅድም ሲሉ ይደመጣሉ። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ በ1935 በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ከተቋቋመ ወዲህ የተለያዩ ተቋማዊ ሃላፊነቶች ነበሩበት። የዜና ማሰራጫው አሁን ያለበትን ህልውናና ተግባራዊ ቅርጽ የያዘው ከ1940 ጀምሮ በየጊዜው በወጡ ህጎች ነው። በሪፐብሊካኑ ኮንግረስማን ካርል መንት ጠንሳሽነትና በኒውጀርሲው የፓርቲ አጋራቸው አሌክሳንደር ስሚዝ ድጋፍ በ1940 ህግ ሆኖ የወጣው በሰፊው “የስሚዝ-መንት አዋጅ” ተብሎ የሚጠራው ህግ ለአሜሪካ መንግስት መረጃ የማሰባሰብና የማሰራጨት መብት ሰጠ። ለቲሻ ኪንግ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ናቸው። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የተቋቋመው “ነጻ መረጃን ያለምንም ቅድመ-ምርመራ ለተለያዩ የአለም ክፍሎች ለማድረስ ነው ይላሉ። ነገር ግን የአገሪቱ መንግስት ይሄንን የመገናኛ መንገድ በአገር ውስጥ የህዝብ አስተያየትን ለመለወጥና ፕሮፓጋንዳ እንዳይነዛ በማሰብ በመረጃ ስርጭቱ ላይ “የስሚዝ-መንት” አዋጅ መጠበቂያ አብጅቷል ይላሉ። የአሜሪካ መንግስት በዜጎቹ ላይ መረጃን እንደፈለገው እያሰራጨ ነጻ የመገኛኛ ብዙሃንን ስራም እንዳይጠቀልል ታስቦ በህግ ቪኦኤም ሆነ ሌሎች የማሰራጫ ጣቢያዎች በዩናይትድ ስቴይትስ እንዳይሰሙ ታግዷል። የአሜሪካ ድምጽ በዩናይትድ ስቴይትስ ቢደመጥ በስልጣን ላይ ያለው አስተዳደር በምርጫ ወቅትና በሌሎች ጊዚያት የህዝብን ድጋፍ ለማግኘት እንዳሻው እንዳያዘውና እንዳይጠቀምበት፣ እና የመሳሰሉ ተቋማዊ ነጻነትን የሚንዱ ተግባሮች እንዳይኖሩ ለመከላከል ነው ገድብ ማብጀት ያስፈለገው ይላሉ የቪኦኤዋ ለቲሻ ኪንግ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዛሬ በ42 ቋንቋዎች በአለም ዙሪያ መረጃን ይሰጣል። በእርግጥ በሬድዮና በቴሌቪዥን ጣቢያዎች በአገር ውስጥ ባይሰራጭም፣ ህጉ ሲወጣ ኢንተርኔት ስላልነበረ አሜሪካዊያን ዛሬ በድረ-ገጽ መረጃውን ማግኘት ይችላሉ። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምርጫ በቀረበ ቁጥር የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮን ያፍናሉ በሚል በጋዜጠኛ መብት ተሟጋች ቡድኑ ሲፒጄና ሌሎች ድርጅቶች ይወቀሳል። አቶ መለስ ከ2002 የሀገር አቀፍ ምርጫ በፊት መንግስታቸው ቪኦኤን ለማፈን አቅም እየገነባ መሆኑንና ያን አቅም ገንብቶ ሲጨርስ “አፍኑ” የሚል ትእዛዝ እንደሚሰጡ በይፋ ተናግረዋል። በቅርቡ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲም ቪኦኤ በኢትዮጵያ እንዳይሰማ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። “የአሜሪካ ድምጽ በአሜሪካ በህግ እንዳይተላለፍ ተከልክሏል….እኛም ከዚህ ከዩናይትድ ስቴይትስ ፖሊሲ አንድ ገጽ ወሰድንና ቪኦኤ በኢትዮጵያ አይሰማም አልን” ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀጽ 29 ንኡስ አንቀጽ 2 እንዲህ ይላል “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ-ገብነት ሃሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሁፍ ወይንም በህትመት፡ በስነጥበብ መብት ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም አይነት ሃሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል። በካሊፎርኒያ ስቴይት ዩኒቨርስቲ የህግ መምህር እና ጠበቃ የሆኑት አለማየሁ ገብረ-ማርያም የአቶ መለስ አባባል ህገ-መንግስቱ ጋር ይጋጫል ይላሉ። “የአሜሪካ ድምጽ ወደ ኢትዮጵያ በሚገባው ህገ መንግስቱ ስለሚፈቅድ ነው” ይላሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ።
a_ethiopia-boston-london-marathon-120091729_1461220
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-boston-london-marathon-120091729/1461220.html
ኬንያዊው ጀፍሪ ሙታይ በአለም ፈጣኑን ማራቶር በቦስተን ሮጠ
በዛሬው 115ኛው ዓመታዊ የቦስተን ማራቶንና በትላንቱ ታላቁ የለንደን ማራቶን ኬንያውያን በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል።
በለንደኑ ማራቶን በሁለተኛና ሦስተኝነት የሀገሩን ልጆች አስከትሎ የሥፍራውን ጊዜ በማሻሻል ጭምር በአንደኛነት የገባው የ 26 ዓመቱ ኢማኑኤል ሙታኢ 2 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ 400 ሴኮንድ አስመዝግቧል። በዚህ ውድድር ያሸንፋል ተብሎ ቅድሚያ ግምት የተሰጠው ያምናው ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊው ፀጋዬ ከበደ በአምስተኝነት ፈጽሟል። በሴቶቹ በ 2 ሰዓት 19 ደቂቃ ከ ሴኮንድ ፈጣን ጊዜ ያሸነፈችው ኬንያዊት ሜሪ ኬይታኒ በማራቶን ስትሳተፍ ትላንት የመጀመሪያዋ መሆኑ ተዘግቧል። በትላንቱ የለንደን ማራቶን ድል ይቀዳጃሉ ተብለው ከተጠበቁ መካከል የኢትዮጵያ አትሌቶች ይገኙበታል። ከምን ገቡ? አሰልጣኝ ገመዱ ደደፎ ባጭሩ ውድድሩን ገምግመዋል። በሌላ በኩል የዓለም ማራቶን ክብረወሰን ባለቤት አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንት በቪዬና ግማሽ ማራቶን በድንቅ አሯሯጥና በፈጣን ጊዜ አንድ ሰዓት ከ18 ሴኮንድ አስመዝግቦ ድል ተቀዳጅቷል። ኃይሌ በዛሬው ዕለት 38ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከብራል። በዚሁ ዕለት በተካሄደ ሙሉ ማራቶን፥ በሴቶች ፋጤ ቶላ ከኢትዮጵያ በወንዶች ጆን ኪፕሮቲች ከኬንያ አሸንፈዋል። በእግር ኳስ ዜና የስፔን ላ ሊጋና የእንግሊዙን ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች የተወሰኑትን ባጭሩ እናያለን። ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ
a_amh-ethiopia-students-1-10-12-137045348_1457827
https://amharic.voanews.com/a/amh-ethiopia-students-1-10-12-137045348/1457827.html
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ተማሪዎች የመብት ጥያቄዎችን አንስተው ተቃውሞ አሰሙ
የትምህርት ነጻነታችን ይከበር በሚል አዲስ አበባ የሚገኘው የአወሊያ ት/ቤት፣ በወለጋ ዩኒቨርስቲ የምግብ ጥራት መጓደል፣ በሆሳእና ደግሞ የስራ መጥፋት ተማሪዎችን ለተቃውሞ አነሳስተዋል።
የተማሪዎቹ ጥያቄዎች የተለያዩ መልክ ያላቸው ናቸው። ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ነጻነታችንን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተጋፍቶናል ሲሉ በመቶዎች የተቆጠሩ የአወሊያ የመለስተኛ፣ ሁለተኛ ደረጃና ኮሌጅ ተማሪዎች ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው። ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱ ወደቤታችን አንሄድም በሚል በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ዛሬ ሊያድሩ የወሰኑት ተማሪዎች፤ ቁጥራቸው ከ600 በላይ እንደሆነ ይናገራሉ። ለአንድ ሳምንትም ትምህርት ተቋርጧል። “ምንም አይነት ችግር ሳይፈጠር ኮሌጁን የእልምና ጉዳዮች ዘግቶብናል፣ የኮሌጁ መምህራንና ዲኖች ከስራ ተሰናብተዋል፣ እንዲሁም የአወሊያ መስጊድ ኢማም የሆኑት ሼክ ይማም ተባረዋል” ስትል አንዲት ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች የአረቢኛ ቋንቋ የኮሊጅ ተማሪ ገልጻለች። የጸጥታ ሃይሎች የትምህርት ቤቱን ግቢ ከበዋል፤ እስካሁን ሰልፉን ለመበተን ከማስፈራራት በስተቀር በተማሪዎቹ ላይ የደረሰባቸው ጥቃት የለም። በወለጋ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ተማሪዎች የምግብ ጥራት መጓደል አሳስቧቸዋል፤ አልፎም ለተቃውሞ አድርሷቸዋል። ከለት ወደለት የደፈረሰ የጎርፍ ውሃ የመሰለ ሽሮ መብላት ታከተን፤ በአግባቡ ያልተበጠረና አሸዋ ያለበት እንጀራ መብላት እስከመቼ? የሚመደብልን በጀት በቂ ሆኖ ሳለ፤ የምግብ ጥራት ማሽቆልቆሉ ለምን? እያሉ ውስጥ ውስጡን ሲያጉተመትሙ የነበሩት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች፤ የገና ለት ነው አንጀታቸው ለይቶለት የተቆረጠው። ከቤተሰባቸው ተለይተው በዓሉን የሚያከብሩት ተማሪዎች እልቅ ቅጠል የማይል ምግብ ቀረበልን ሲሉ፤ ምግብ ላለምብላት ይወስኑና፤ በምግብ ቤቱ ዙሪያ ይሰባሰባሉ። ተማሪዎቹ የምግብ ጥራት እንዲሻሻል ሲጠይቁ የመጀመሪያቸው አልነበረም። ወዲያውኑ የጸጥታ ሃይሎች በአካባቢው ተገኝተው ተማሪዎቹ ጋር ግብ ግብ ይገጥማሉ። የታጠቁ ሃሎች በከፈቱት ተኩስ አንድ ተማሪ መቁሰሉንና ሌሎች ደግሞ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ይናገራሉ። ጥቃት ከደረሰባቸው አንዱ በአሁኑ ወቅት የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለት በነቀምት ሆስቲታል ውስጥ ይገኛል። የፌዴራልና የኦሮሚያ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝተው በወሰዷቸው እርምጃዎች ድብደባ ደርሶባቸው በሆስፖታል የሚገኙ ተማሪዎች እንዳሉም ተገልጿል። የሶስተኛ አመት ተማሪ ተስፋየ ደገፋ በአካዳሚክ ፕሬዝደንቱ ዶር ኤባ ሚጀና ስለተደበደብ ለህይወቱ አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገን ተማሪዎቹ ለኦሮሚኛ ዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። የተማሪው የጤና ሁኔታ አስጊ በመሆኑ ለተጨማሪ የህክምና እርዳታ ወደ አዲስ አበባ ከአቅም በላይ ተብሎ ሊላክ እንደታሰበ ተማሪዎቹ ይናገራሉ። በወለጋ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ሂደቱ በከፊል ቀጥሏል። የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ የዝግጅት ክፍላችን በተደጋጋሚ ደውሎላቸው ስልካቸውን አያነሱም። የምስራቅ ወለጋ የፖሊስ ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ኦላና ጌታቸው የተጎዱ የሚባሉት ተማሪዎች ማን እንደደበደባቸውና ጥቃቱን እያደረሰባቸው እንደሆነ አልታወቀም ብለዋል። እስካሁን የታሰሩ ተማሪዎች አለመኖራቸውን ነው ኢንስፔክተር ኦላና የገልጹት። በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን ደግሞ፤ በሆሳእና ከተማና አካባቢዋ የሚገኙ ከ429 በላይ ተማሪዎች ትምህርታችንን አጠናቀን ስራ አጥተናል በሚል የዞኑ መስተዳድር የስራ እድል እንዲከፍትላቸው ጠይቀዋል። ተማሪዎቹ ተወካዮች መርጠው ከመስተዳድሩ ጋር ለረጅም ጊዜ ሲደራደሩና ሁኔታውን ሲከታተሉ መቆየታቸውን ነው የሚናገሩት። በስተመጨረሻ ተወካዮቻቸው ከዞኑ መስተዳድር ጋር ለመነጋገር ገብተው ባለመመለሳቸው ተቃውሞው መባባሱን አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ተማሪ ገልጾልናል። የሃዲያ ዞን የፖሲስ አዛዥ ኮማንደር አዲሴ ፈይሳ ግጭቱ መፈጠሩን ገልጸው፤ ከታሰሩ ተማሪዎች መካከል ሁሉም ትምህርት ተሰጥቷቸው መፈታታቸውን ተናግረዋል።
a_amharic-radio-mag-show-sunday-05-17-2020_5423669
https://amharic.voanews.com/a/amharic-radio-mag-show-sunday-05-17-2020/5423669.html
ራዲዮ መፅሔት - ዕሁድ፤ ግንቦት 9-2012 ዓ.ም.
ከአሜሪካ ድምፅ የዕሁድ፤ ግንቦት 9-2012 ዓ.ም.ዜናና የራዲዮ መፅሔት ሙሉ ዝግጅትን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ዋሺንግተን፤ ዲሲ - አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ጊዜ መቀየሩ የፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ሕገመንግሥታዊ ትርጓሜ መጠየቅ ሕጋዊ አማራጭ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል። የባለሙያዎቹን አስተያየት የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ትናንት፤ ቅዳሜ አዳምጧል። ዝርዝሩን የያዘውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው ከተገጋገጠ የዛሬ አሥራ አንድ ሰዎች ጋር አጠቃላዩ ቁጥር ውድ 317 ከፍ ማለቱን የጤና ሚኒስቴር በትዊተር ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። 113 ሰዎች ከሕመሙ ስሜት የወጡ ሲሆን ከዚህ በጎ ዜና ጋር በተጨማሪ ሃገሪቱ አሁን ባለው ጊዜ በኮቪድ-19 በጠና የታመመ ሰው የላትም፤ አዲስ የኮቪድ-19 ሞትም የለም። በሌላ በኩል ግን ባለፉት ከሃያ አራት ሰዓታት በላይ ለሆን ጊዜ ይህ ዜና እስከተጠናቀረ ድረስ የተሻለው ተጨማሪ ሰውም አልተመዘገበም። በጤና ሚኒስቴሩ መግለጫ መሠረት ኢትዮጵያ እስካሁን በአጠቃላይ 317 ሰው ለአዲሲ ኮሮናቫይረስ ተጋልጦባታል፤ ሁለት ሰዎች ወደ ሃገራቸው ተሸኝተዋል። ዓለምአቀፍ መረጃዎች የአጠቃላዩን ተጋላጭ ቁጥር 319 ብለው የመዘገቡ ሲሆን ሁለቱን ተሸኚዎች ጨምሮ ይሁን አይሁን ግን የጤና ሚኒስቴሩም፣ ዓለምአቀፍ ሠንጠረዦቹም አይናገሩም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመላው ዓለም ለአዲሱ ኮሮናቫይረስ የተጋለጠው ሰው ቁጥር 4 ሚሊየን 664 ሺህ 486 ሲሆን 312 ሺህ 327 ሰው በኮቪድ-19 ምክንያት መሞቱን የጃንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል አስታውቋል። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 11 ሚሊየን 77 ሺህ 179 ሰው ተመርምሮ 1 ሚሊየን 471 ሺህ 674 ሰው ለቫይረሱ መጋለጡ የተረጋገጠ ሲሆን 88 ሺህ 811 ሰው በኮቪድ-19 ምክንያት ሞቷል። ዩናይትድ ስቴትስን ተከትለው እንግሊዝ 34 ሺህ 546 ሰው፤ ኢጣልያ 31 ሺህ 763 ሰው ሞተውባቸዋል። ስፓኝ ከ27 ሺህ በላይ በተመዘገበ የኮቪድ-19 ሞት ሠንጠረዡ ላይ በአራተኛነት ሠፍራለች። ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ በተፈፀመ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት በፑንትላንድ አስተዳደር ውስጥ የምትገኘውን ሙግዱድ ክልል ገዥን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገድለዋል። በቦምብ የታጨቀ መኪናውን አገረገዥ አህመድ ሙሴ ከነበሩበት መኪና ጋር ሆን ብሎ ባጋጨው አጥቂ አብረዋቸው የነበሩ ወንድማቸውና ሁለት ጠባቂዎቻቸው፣ እንዲሁም መንገድ ላይ ቆሞ የነበረ አንድ ሲቪልም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን አደጋው የተጣለባት የጋልካዮ ከተማ ከንቲባ ሰይድ ሙሃሙድ አሊ ለቪኦኤ ገልፀዋል። ለጥቃቱ አልሻባብ ኃላፊነት ወስዷል። የእሥራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዛሬ ለአዲስ አስተዳደራቸው ቃለመሃላ ፈፀሙ። ኔታንያሁ የመጭ ጊዜ ሥራቸውን ዛሬ የጀመሩት ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ከተጓተተ የፖለቲካ አጣብቂኝና ውዝግብ በኋላ መሆኑ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ሥልጣናቸውን ከእርሣቸው ሊኩድ - የብሔራዊ አርነት ንቅናቄ ጋር ጋር ጥምር መንግሥት ለፈጠረው ሰማያዊና ነጭ ፓርቲ መሪ ቤኒ ጋንትዝ እንደሚያስረክቡም ታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር መለዋወጥ ሕገወጥ ነው ብለው የሚከራከሩ ተቃዋሚዎች እየተሰሙ ሲሆን ካቢኔው እስካሁን ታይቶ የማይታወቅ የሚኒስትሮች ቁጥር - ሰላሣ ስድስት ሚኒስትሮች የሚገኝበት እንደሆነ ተገልጿል። የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ቤተእሥራዔላዊ ሚኒስትርም መሾማቸው ተሰምቷል። በእሥራዔል የቻይና አምባሳደር ዱ ዌዪ ሄርዚልያ በሚገኘው መኖሪያ ቤታችው ሞተው መገኘታቸውን የእሥራዔል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። አምባሳደር ዌዪ የተሾሙት ባለፈው የካቲት ነበር። ጀሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ ሃምሣ ሰባት ዓመት ዕድሜአቸው ላይ የነበሩት የቻይና አምባሳደር የሞቱት “በድንገተኛ የልብ መታወክ ነው” ብለው መርማሪዎቹ እንደሚያምኑ ፅፏል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከትናንት በስተያ ዓርብ ምሽት ላይ ማባረራቸውን ተከትሎ ዴሞክራቲክ እንደራሴዎች ምርመራ ጀምረዋል። አቃቤ ሕጉ ስቲቭ ሊኒክ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፔዮ ላይ ምርመራ ከፍተው እንደነበረ ታውቋል። በፕሬዚዳንቱ ላይ ተከፍቶ የነበረው የተወካዮች ምክር ቤቱ የክሥ ሂደት እርሣቸውን ነፃ በማውጣት ከተጠናቀቀ ወዲህ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ያሉ የመንግሥቱን ተቆጣጣሪዎች ሲያባርሩ ሊኒክ ሦስተኛው መሆናቸው ነው። ሊኒክ የተሾሙት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ነበር። ዋይት ሃውስ ከሊኒክ መባረር ጋር የተያያዙ ሠነዶችን ሁሉ እንዲያቀርብ እንደራሴዎቹ ጠይቀዋል።
a_amh-afar-fed-killings-7-5-12-161499275_1492845
https://amharic.voanews.com/a/amh-afar-fed-killings-7-5-12-161499275/1492845.html
በአፋር የፌዴራል ፖሊስ ሁለት ሰዎችን ከእስር ቤት አውጥተው መግደላቸውንና አንድ ማቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
በአፋር ክልል ማክሰኞና ረቡዕለት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበሩ ተጠርጣሪዎች፤ በፌዴራል የፖሊስ ሃይል ተገድለዋል በሚል የአካባቢው ማህበረሰብ ቁጣውን ገልጿል።
በአፋር ክልል ዱብቲ ከተማና በሎጊያ የሰሞኑ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ ህዝብ ውጥረት፤ የክልሉ ነዋሪዎችና ባለስልጣንት የመወያያ ርእስ ሆኖ ነው የሰነበተው። ሁኔታው በአፋሮች ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን ነው፤ ከግማሽ ደርዘን የሚበልጡ አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሰጡ ነዋሪዎች የገለጹት። የጸጥታ ውጥረቱ የተጀመረው እንዲህ ነው፤ በሳምንቱ መጀመሪያ አንድ የፌዴራል ፖሊስ ባልደረባ ከባለቤቱ ጋር በሚኒባስ ሲጓዝ ሁለቱም ተገደሉ። ከዚህ ግድያ አስቀድሞ ከሁለት ሳምንታት በፊት አንድ የ17-ዓመት የአፋር ተወላጅ በፌዴራል ፖሊስ አባላት መገደሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ግድያው በተካሄደበት የሸንኮር አገዳ ልማት ጣቢያ በጥበቃ ስራ የተሰማራው ወጣት የተገደለውም ትጥቁን እንዲፈታ በፖሊስ ተጠይቆ፤ ትእዛዙን ባለመቀበሉ እንደሆነ ምስክሮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በሚኒባስ ሲጓዝ የነበረ የፌዴራል ፖሊስ ባልደረባ ከነባለቤቱ ከተገደለ በኋላ፤ ገዳዮቹ በበቀል ደም ለመመለስ የፈለጉ የ17-ዓመቱ ሟች ቤተሰቦች ናቸው በሚል ጥርጣሬ፤ ወዲያውኑ ከ9በላይ የቤተሰብና የጎሳ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ። በትናንትናውለት መገደላቸው የተረጋገጠው ሁለት ሰዎችና ክፉኛ የቆሰለው ሌላ ግለሰብ፤ በእስር ቤት የህግ እስረኛ ሆነው ሳለ፤ በጥይት ተመተው የተገደሉና የቆሰሉ ናቸው። ሁኔታው እንዴትና መቼ አንደተፈጠረ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን አብራርተዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዱብቲ ከተማ ነዋሪ የሚከተለውን ቃል ለቪኦኤ ሰጥተዋል። በአካባቢው የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ቁጣ ተከትሎ ከፍተኛ የፌዴራል ጉዳዮችና የፖሊስ ባለስልጣናት ወደ አፋር ተንቀሳቅሰዋል። የአፋር ክልል ባለስልጣናት በጉዳዮ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን፤ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢስማኤል አሊ ሴሮ ጀምሮ በተዋረድ የደህንነትና የጸጥታ ባለስልጣናትን ለማግኘት ያደረግንው ጥረት አልተሳካም። ጥረታችንን ቀጥለን ወደ ዱብቲ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ ደውለን ስብሰባ ላይ እንዳሉና ሊያናግሩን እንደማይችሉ ገልጸዋል። የወረዳው አስተዳዳሪም በስፍራው የለሁም፤ በመኪና እየተጓዝኩ ስለሆነ ላነጋግራችሁ አልችልም ብለውናል። ወደ ባለስልጣኑ መልሰን ብንደውልም መልስ አላገኘንም። ቀጥለን ከምስክሮች ያገኘንውን አስተያየት እናቀርባለን። ከዚያ በፊት ግን የክልሉ ወይንም የፌዴራል ባለስልጣናት ሊመልሷቸው የሚገባቸው ጥያቄዎች አሉ። 1ኛ የህግ ታሳሪዎች ከህዝባዊ ፖሊስ እጅ ወጥተው፤ ለምን ለፌዴራል ፖሊስ አልፈው ተሰጡ? እንዴትስ በህግ ጠለላ ስር ሳሉ ተገደሉ? 2ኛ በሚኒባስ ሲጓዝ የነበረው የፖሊስ ባልደረባንና ባለቤቱን ማን እንደገደለ የሚደረገው ምርመራ በምን ሂደት ላይ ይገኛል 3ኛ ከሁለት ሳምንት በላይ የተገደለው የ17 ዓመት የአፋር ወጣት ግድያ ማጣራት በምን ላይ ይገኛል። የአካባቢው ማህበረሰብ ገዳዮ የፖሊስ ባልደረባ አሁንም በስራው ላይ ይገኛል፤ ፍትህና ተጠያቂነት ጠፍቶ፤ በወንጀል ተጠያቂ ሰው በነጻነት ይኖራል ሲሉ ያማርራሉ። እነዚህ ጥያቄዎች መልስ ያሻቸዋል። የአፋር ባለስልጣናት እንዲመልሷቸው እንጠይቃለን።
a_how-did-we-get-here-voices-of-reason-yilma-adamu-mulegeta-aregawi-dereje-demissie-bulto-with-voa-alula-kebede-july-august-2020_5529553
https://amharic.voanews.com/a/how-did-we-get-here-voices-of-reason-yilma-adamu-mulegeta-aregawi-dereje-demissie-bulto-with-voa-alula-kebede-july-august-2020/5529553.html
"እንደምን ከዚህ ደረስን?" .. ሁከት፡ ፈተናና ዘላቂ የሰላም መንገዶች
አመዛዛኝ ድምጾች:- የዛሬውን የውይይቱ የመጨረሻ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።
ዋሽንግተን/ አዲስ አበባ/ ሎሳንጀለስ/ ቦስተን — “… እርግጥ ያንን ሕግ ሲያወጡ 'በዚህ መልክ ነው አብሮ መኖር የሚያስችለን' ብለው ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አንድን አገር እንደ እንዳትኖር ለማድረግ ከፈለግክ የምታመጣው የሕገ መንግስት መመዋቅር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዓይነት ነው። ...” አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ። “…ብልህ ቤተሰብ፥ ብልህ መሪ ያለው አገር ከዚህ አሰቃቂ ሁኔታ .. ከዚህ ጥፋት ምንድነው የተማርኩት ብሎ ይጠይቃል። …”አቶ ይልማ አዳሙ። “…የኢትዮጵያ ህግ ሁሉም ሰው በህግ ዓይን እኩል ነው ይላል። 'ጠንካራ መንግስት' እፈልጋለሁ ስል ይሄን የማድረግ ችሎታ ያለው ማለት ነው። …” አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ። ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ብርቱ ሃዘን በአንድ ወገን፤ የዛሬና የነገ ፈተናዎች እንዲሁም ዘላቂ መፍትሔ ፍለጋው በሌላው የሚፈተሹበት ውይይት ነው። በኢትዮጵያ በቅርቡ የደረሰውና በርካቶች በግፍ የተገደሉበት ጥቃት ካሳደረው ሃዘን እና የልብ ስብራት፤ ብሎም ከቀሰቀሰው የቁጣ ስሜት ባሻገር የዛሬውን ጉዳትና “እንዴት? ” የሚለውን በአስተዋይ ልቦና መመርመር ብቻ ሳይሆን የነገውን የሩቅ መንገድ በአርቆ አሳቢነት ለመመዘን እና ሁነኛ መፍትሔዎችን ለመሻት ጭምር የሚጥር ዝግጅት ነው። የሃገርን እና የህዝብን መጭ ዕጣም ይዳስሳል። አዎን! የችግሮቹን መንሴዎችም ሆነ ፈውሱን በቀጥታ ለማየት ጥረት መደረግ ያለበት ሰዓት አሁን ይመስላል:: ተወያዮቹ አቶ ይልማ አዳሙ፡ አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ እና አቶ ሙልጌታ አረጋዊ በየተሰማሩባቸው የሞያ መስኮች ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱና የተለያዩ የባሕል መሰረቶች ያሏቸው ናቸው። በውይይቱ ጠባይ ሳቢያ የማንነታቸውን ገጾች ከወትሮው ዘለግ ብለው ያስተዋውቁናል። የውይይቱን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።
a_amh-ak-intellectual-property-culture-development-part-1-114760144_1458700
https://amharic.voanews.com/a/amh-ak-intellectual-property-culture-development-part-1-114760144/1458700.html
የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት፥ ባህልና ልማት!
አንድ ቡና ዓይነተኝነት ወይም መለያ ሲሰጠው፤ አተካከሉን፥ አበቃቀሉን፤ ሲታጠብ ያለው ሁኔታ፤ ቡናው በበቀለበት ባህል የሚጠጣበት ጨምሮ፥ ያንን ሁሉ አንድ ላይ ይዞ ይመጣል። መለያውም ይሆናል።
የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና የንግድ ምልክት ለማስመዝገብና መብቱ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች ባለቤት ለመሆን የተደረገው ጥረት በሌሎች የአፍሪካ የምጣኔ ሃብትና የባህል ዘርፎችም መሰል ጠቀሜታን ማስገኘት ይችል እንደሆን የመረመረ ጥናት ነው። በቦስተን ዩኒቨርሲቲ የፍሬዴሪክ ፓርዲ የጥናት ማዕከል ለህትመት የበቃውና የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና ጅምር ጥረት በምሳሌነት የተመለከተው ይህ ጥናት፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጥበቃ፥ እስካሁን እምብዛም ተጠቃሚ ያላደረጋቸውን አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ደሃ አገሮችንም፤ እንደ ግዙፉ አትራፊ ኩባንያዎች ሁሉ፥ የትሩፋቱ ተቋዳሽ ሊያደርግ የሚያስችል አቅም እንደሚያጎናፅፍ ያመላክታል። አንድ የምርት ውጤት ቁሳዊ ይዞታው ከሚያስገኛቸው ቀጥተኛ ጠቀሜታዎች ባሻገር፤ ከምርቱን ልዩ መሆን፥ ምንነት፥ ሥምና ዝናው ወይም ዕውቅናው፤ እንዲሁም ምርቱ የፈለቀበትን ባህል የመሳሰሉ ባህሪያቱ የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች ዋነኞቹ ከአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ዕሴቶች ናቸው። «ቡና፥ ባህልና የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት፤» የምሽቱ የባህልና ማኅበረሰብ ፕሮግራም እንግዳ፥ የታሪክ አጥኚዋ ዶ/ር ሄራን ሰረቀብርሃን ያተኮሩበት የጥናት ርዕስ ነው። የጥናታቸውን ይዘትና ምንነት ጨምሮ፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነትን የዚህ መንገድ ትርጓሜ፤ እንዲሁም ዘርፉ ሊያስገኝ ይችላል ተብሎ የሚታሰበውን ጠቀሜታ የተመለከቱ ነጥቦች በተከታታይ ቅንብሮች እንመለከታለን። የመጀመሪያውን ክፍል አጭር ዝግጅት ቀጥሎ ያዳምጡ።
a_5903575
https://amharic.voanews.com/a/5903575.html
የባልደራስ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በእስር ላይ የሚገኙ አራት አመራሮቹ እና አባላቱ ለምርጫ እንዲወዳደሩ በእጩነት ለማስመዝገብ ያቀረበውን ጥያቄ ምርጫ ቦርድ ስላልተቀበለው ጉዳዩን በይግባኝ ለፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረው ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ የፓርቲውን አቤቱታ በልዩነት ውድቅ አድርጎታል።በዛሬው ዴሞክራሲ በተግባር የባልዳራስ ጥያቄ ምን ነበር? ፍርድቤቱ በልዩነት የሰጠው የፍርድ ውሳኔስ ምን ይመስላል? የሚለውን ይዳስሳል።
ዋሽንግተን ዲሲ — ባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የሕግ ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ፓርቲያቸው ለምርጫ እንዲወዳደሩ በአጩነት ያቀረቧቸውን ተወዳዳሪዎች አልመዘግብም በማለቱ ጉዳዩን ፍርድ ቤት መውሰዳቸውን አስረድተዋል። በእስር ቤት የሚገኙ ፓለቲከኞች ለመጪው ምርጫ እጩ ሆነው እንዲቀርቡ ከባልደራስ በተጨማሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ በሊቀመንበርነትየሚመሩት የኦሮሞ ነጻነትግንባር (ኦነግ)ም ሲጠይቅ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ፣ የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ እና መለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 መሰረት በማድረግ በእርስ ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች ለምርጫ ዕጩ ሆነው መቅረብ እንደማይችሉ ያስታወቀ ሲሆን ይህንን ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የወሰደው ባልዳራስ ብቻ ነው። አቶ ሄኖክ መቼ ወደ ፍርድ ቤትእንደወሰዱት እና ውሳኔውም በምን ቀን እንደሆነ አስረድተዋል። አቶ ያዕቆብ መኩሪያ፣ አቶ ሙሉሰው ድረስ እና አቶ ፈይሳ በዳዳ የተባሉ ሦስት ዳኞ የተሰየሙበት ችሎት ጉዳዩን በተመለከተ በትላንትናው ዕለትበልዩነት የፍርድ ውሳኔ የሰጠበት ሰነድ እንደሚያሳየው በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ያቀረበውን ባልዳራስን እና ምርጫ ቦርድን ሲያከራክር መቆየቱንጠቅሷል። ባልዳራስ ላቀረበው የይግባኝ ጥያቄ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እንዲሰጥበት መታዘዙን እና ቦርዱ መጋቢት 20/2013 ዓ.ም ምላሽ መስጠቱበፍርድ ውሳኔው ላይ ሰፍሯል። ቦርዱ ይግባኝ ባይ ይግባኙን ማቅረብ ካለበት ጊዜ ያሳለፈ በመሆኑ በይርጋ እንዲታገድለት ከጠየቀ በኋላ ይህ ምላሹ ቢታለፍ በሚል አዋጅናመመሪያን በመጥቀስ አማራጭ ምላሽ ሰጥቷል። ፓርቲው በአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች ያቀረባቸው ዕጩዎች በሕግ ጥላ ስር ያሉ በመሆናቸው በእጩነት መመዝገብ አይችሉም በመሆኑም የሕግትርጉሙ ወይም በተጠቀሱት አንቀፆች ውስጥ ያለው ሐሳብ በእስር ላይ ያሉ ሰዎች ዕጩ ሆነው መመዝገብ እንደማይችሉ እንደሚደነግግ በመግለፅ ምላሽ ሰጥቷል። በሁለተኛ አማራጭነትን በሰጠው ምላሽ ደግሞ በእጩነት ከመመዝገብ ተከለከልን የሚል ቅሬታ ያቀረበው ፓርቲ በእጩነት ያቀረባችቸው ዕጩዎች ቦርዱ የምርጫ ሰሌዳ ከማውጣቱ እና የዕጩዎች ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት ተከሰው በእስር ላይ ያሉ ሲሆን የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል ነው ተብሎ የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ ታስረው የሚገኙ ናቸው። ስለዚህ ግለሰቦቹ እንደልብ ተንቀሳቅሰውመቀስቀስ አይችሉም ይላል። ካለመከሰስ መብት ጋር በተያያዘም ተጨማሪ አንድ መከራከሪ አቅርቧል። የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በሁለት ዳንኞች ድምፅ ብልጫ በሰጠው ገዢ ውሳኔ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አፅንቶታል። በፍርድውሳኔውም በእስር ቤት የሚገኙ ሰዎች የመመረጥ መብታቸውን ጨምሮ በርካታ መብቶቻቸው የተገደቡ ናቸው ብለዋል። በውሳኔ ማጠቃለያቸው ላይም፤ “እስር ላይ የሚገኝ ሰው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ሕዝብን ለማስተዳደርም ሆነ የፓርቲዎ አጀንዳ ይዞ ሃገሪቱንወደታሰበው ግብ ሊመራ አይችልም። ይህ ደግሞ የምርጫ ዋነኛ ግብ የሆነውን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር የሚጎዳ እና ይመዝገቡ የተባሉትየይግባኝ ባይ እጪዎች (የባልዳራስ ማለታቸው ነው) በአሁኑ ሰዓት በሌላ ወንጀል ተከሰው የዋስትና መብታቸውን ተከልክለው በማረሚያ ቤትሆነው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ያሉ ስለሆነ የዕጩነት መብታቸው ተጠብቀው ቢመዘገቡና ቢመረጡ የመረጣቸውን ሕዝብ በእስር ላይ እያሉበነጻነት ተንቀሳቅሰው ሕዝቡን ሊያገለግሉ አይችሉም። ምክኒያቱም መመረጥ ብቻውን አንድን እስረኛ ያለፍርድ ወይም ያለሕጋዊ አሰራር ነፃአያደርገውምና። በዳኛ ያዕቆብ መኩሪያ እና በዳኛ ፈይሳ በዳዳ የአብላጫው ውሳኔ የሰጠው ችሎት የተገለፀውን ትንታኔ ካሰፈረ በኋላ ምርጫ ቦርድ የሰጠውንውሳኔ የሚነቅፍበት ምንም ምክኒያት የሌለ መሆኑን በመግለፅ የባልዳራስን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል። ፓርቲው ያቀረባቸው ዕጩዎች በእስር ላይመሆናቸው የመመረጥ መብታቸው የሚገድብ ስለሆነ ምርጫ ቦርድ እነርሱን በእጩነት አልመዘግብም ማለቱ ትክክል ነው በማለት መዝገቡንዘግቶታል። በሌላ በኩል ሐሳባቸውን በልዩነት ያሳፈሩት ዳኛ ሙሉሰው ድረስ፤ የምርጫ ሕጉ በእስር ላይ ያሉ እና የሌሉ ብሎ ክልፍልፋይ አያስቀምጥም ካሉበኋላ፤ ሕጉ በፍርድ ቤት መብቱ የተገፈፈ ነው የሚለው ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉዳይ ላይ እነ አቶ እስክንድር ነጋ መብታቸው በፍርድ የተገፈፈስለመሆኑ ወይም በፍርድ ቤት መብታቸውን ያጡ ስለመሆኑ ምርጫ ቦርድ ምንም ያቀረበው ማስረጃ የለም ብለዋል። ውሳኔያቸውንሲያጠቃልሉም። “በጥቅሉ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 20/3 በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 31 እንዲሁም ኢትዮጵያ ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍየሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች የሕግ ክልከላ በሌለበት ሁኔታ መልስ ሰጪ የይግባኝ ባይን ዕጩዎች በሕግ ጥላ ስር የሚገኙ ናቸው በማለትአልመዘግብም በሚል የሰጠው ውሳኔ የሕግ እና የማስረጃ መሰረት የሌለው ስለሆነ ተሽሮ ሊመዘገቡ ይገባል ተብሎ ሊወሰን ሲገባ አብላጫ ድምፅየይግባኝ ባይን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ አይደለም በሚል ከሥራ ባልደረቦቼ ሐሳብ ተለይቻለሁ” የሚፀናው ውሳኔው የአብላጫው በመሆኑ ይግባኙ ውድቅ የተደረገበት ባልደራስ ፓርቲ የሕግ ጠበቃ አቶ ሄኖክ ፓርቲያቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤትውሳኔውን እንዳልተቀበለው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን ስድስተኛውን ሃገርዊ ምርጫ በመጪው ግንቦት 28 ለማካናወን ቀነ ቀጠሮ መቁረጡ ይታወቅል።
a_alqaeda-france-africa-countries-07-28-10-99497539_1457860
https://amharic.voanews.com/a/alqaeda-france-africa-countries-07-28-10-99497539/1457860.html
ፈረንሳይ እና የአፍሪካ አገሮች አልቃይዳን እንፋለማለን አሉ
ምስራቁንና ምዕራቡን የአህጉሪቱ ክፍሎች እያወኩ ያሉትን ከአል-ቃይዳ ጋር የተቆራኙ ቡድኖች በተጨማሪ ወታደራዊ ኃይል እንደሚፋለሙዋቸው ቃል ገብተዋል።
ዩናይትድ ስቴትስም እየተስፋፋ ለመጣው ጸረ ሽብርተኛ ትግል ተጨማሪ ወታደራዊ እርዳታ እንደምታደርግ ቃል ገብታለች የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍሮንሷ ፊሎን ሀገራችው ከአል-ቃይዳ ጋር ጦርነት ላይ መሆንዋን በፈረንሳይ ራድዮ ተናግረዋል። የፈረንሳዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤርናር ኩችነር ይኽው ቡድን የውጭ ሰዎች ጠለፋና አልፎ አልፎም ግድያ የሚፈጽምበት ወደሆነው ወደምዕራብ አፍሪካ ጉብኝት ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ቡድኑ ፈረንሳዊውን የረደኤት ሰራተኛ ሚሼል ዤርማኖን ገድለነዋል ሲል ባለፈው ዕሁድ አስታውቋል። ያስታወቀውም የፈረንሳይና የሞሪታንያ ኃይሎች በማሊ በረሃ ካሉት ይዞታዎቹ አንዱን ወርረው ካጠቁ በኋላ ነው። ትናንት ማክሰኞ ቤርናር ኩችነር ከማሊ ፕሬዚደንት አማዱ ቱማኒ ጋር ተገናኝተው የጋራ ፈጥኖ ደራሽ ጸረ ሽብርተኛ ኃይል ማቋቋምን ጨምሮ በበርካታ ሴኩሪቲ ነክ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ። በሌላ በኩል የአልጄሪያ ባለስልጣናት በዚህ ሳምንት በኡጋንዳ ካምፓላ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ሲናገሩ በሰፊውና በአመዛኙ ህግ አልባ በሆነው በሰሜናዊ ምስራቁ የአፍሪካ ክልል በምናካሂደው ጸረ ሽብርተኛ ትግል ደካማዋ አስጠቂ ማሊ ነች ማለታችው ተዘግቧል። በበረሃው የሚኖሩ አልጄሪያውያን በየመንደራቸው የየራሳቸውን መከላከያ ሚሊሽያ እንዲያያቋቁሙ መመሪያ ሰጥተናል ሲሉም ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። የአፍሪካ ሴኩሪቲ ተንታኝ የሆኑት ፒተር ፋም ፈረንሳይ እየወሰደች ያለው ርምጃ አይገርመኝም ይሉና ክፋቱ የስላማዊው ማግረብ አልቃይዳ በቀጣዮቹ ወራትም መተናኮሉ አይቀርም በማለት ስጋታቸውን ይገልጣሉ። በዚህ ሳምንት በካምፓላ የተካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔም ባመዛኙ ያተኮረው በሽብርተኝነቱ ስጋት እና በሶማሊያ የሚገኝን የሰላም ጥበቃ ኃይል ማጠናከር ስለሚቻልበት ሁኔታ ነበር። መሪዎቹ ሁለት ሺህ ተጨማሪ ወታደሮችን ለመላክ ወስነዋል። ሰላም እስከባሪዎቹም ህይወታቸው ላይ ጥቃት ከተቃጣባቸው እንዲተኩሱ ፈቃድ ሰጥተዋል። በቅርቡ በኡጋንዳዋ መዲና በርካታ ሰዎች የተገደሉበትን የቦምብ ጥቃት ያደርስኩ እኔ ነኝ ያም የኡጋንዳ ወታደሮች ሶማሊያ መግባተትን ለመበቀል ነው ሲል አል-ሸባብ አስታውቋል። ሶማሊያ ውስጥ ሰላም አስከባሪዎቹ አዘውትረው ንጹሃን ሲቪሎች ላይ ይተኩሳሉ የሚል ስሞታ ይቀርብባቸዋል እል-ሸባብም በኡጋንዳ እና በሌላዋ ሰላም እከባሪ በላከቸው በቡሩንዲ ላይ ጥቃት ማድረሳችንን እንቀጥላለን ሲል ዝቷል። ተንታኝ ፒተር ፋም ታዲያ ለዚህ ሁኔታ ወታደራዊ መፍትሄ ይኖርል ብለው እንደማያምኑ ነው የሚናገሩት። ተጨማሪ ሰላም አእከባሪ መላኩ ሁኔታውን ያባብሰዋል ይላሉ። አልሸባብ የተጠናከረው እኮ ይላሉ የአፍሪካ ሴኩሪቲ ተንታኙ በባዕዳን ጣልቃ ገብነት ምክንያት ነው። ይልቁንስ የሚያዋጣው በጣም አክራሪ ያልሆኑትን አባላት ከውስጡ እየመረጡ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መስራቱ ነው በማለትም ያሳስባሉ። የኡጋንዳው የቦምብ ጥቃት ከደረሰ ወዲህ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ሀገራቸው ለአፍሪካ ሽብርተኝነትን መዋጊያ የምትሰጠውን ርዳታ ዕጥፍ እንደምታደርግ እስታውቀዋል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ለሶማሊያ የሽግግር መንግስት ካሁን ቀደም ለጦር መሳሪያ መግዣና ለወታደሮቹ ደመወዝ የሚከፍልበት በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ሰጥቷል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የቀጣዩ እኤአ የሁለት ሺህ አስራ አንድ ዓመተ ምህረት ለአፍሪካ የሴኩሪቲ ርዳታ መርሃ ግብሮች ባቀረበው የበጀት ዕቅድ ውስጥ ለአፍሪካ መንግስታት ለመሳሪያ ሽያጭ ፥ ለወታደራዊ ስልጠናና ጸረ ሽብርተኛ ፕሮግራሞች ከሰማኒያ ሚሊዮን ዶላር በላይ መመደቡ ይነገራል።
a_police-killed-oromya05-10-10-93326884_1458552
https://amharic.voanews.com/a/police-killed-oromya05-10-10-93326884/1458552.html
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አንድ ፖሊስ በተቃዋሚው መድረክ ደጋፊ መገደሉን ዘገበ
በምእራብ ሸዋ አንድ ፖሊስ የመድረከ በሆነው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ (ኦ.ህ.ኮ) አባል በሆኑ ሰዎች መገደሉን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ይፋ አደረገ። መድረክ ጉዳዮ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቛል።
ውንጀላው የቀረበበት የመድረክ ፓርቲ ጉዳዮ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቛል። በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን ሶስት የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላት ኮንስታብል ሀሰን ረጋሳ የተባሉ የፖሊስ ባልደረባን መግደላቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዘገበ። በኢሉገላን ወረዳ ኢያጂ 01 ቀባሌ የደረሰው ወንጀል በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ መፈጸሙን የመንግስቱ ልሳን የሆነው ኢ.ቲ.ቪ. አስታውቛል። ሶስቱ ተጠርጣሪዎች የስምንት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ አካል ኦ.ህ.ኮ. አባላት መሆናቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ብርሃኑ ሸንተማ፣ ታሪኩ ጌታቸውና ፍሮምሳ ቦጋለ መሆናቸውን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያትታል። “የአካባቢ ሰላም በሚጠብቁ የፖሊስ አባላት አሉ። እነዚህን መደብደብ ወይንም በመግደል አለበለዚያም መዝረፍ ያስፈልጋል” የሚል ተልእኮ እንዳላቸው የኢ.ቲ.ቪ ዘገባ አትቷል። ይህንንም ተጠርጣሪዎቹ ማመናቸውን ዘገባው ጠቁሟል። ውንጀላው የቀረበበት የመድረክ ፓርቲ ወንጀሉን የፈጸሙት የየትኛውም ፓርቲ አባላት ይሁኑ ድርጊቱን እንደሚያወግዝ ገልጧል። “እኛ ስለጉዳዩ የሰማንው ትናንትና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን …ጉዳዩ ሲዘገብ መዋሉን ነው የምናውቀው” በማለት የመድረኩ ቃል አቀባይ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተናግረዋል። ጉዳዮን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከሰማ ወዲህ መድረክ አባሉ ከሆነው ኦ.ህ.ኮ ጋር በመሆን በማጣራት ላይ መሆኑን ዶክተር ነጋሶ ገልጸዋል። መድረክ ድርጊቱን እስኪያጣራ ድረስ ስለተፈጠረው ነገር በእርግጠኝነት ለመናገር እንደሚቸገርም ተናግረዋል። “መድረክ ከአላማውና ከቆመለት የሰው ልጆች መብት ወይንም ህይወት ከማስጠበቅ አኳያ ፈጽሞ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ወንጀል እንዲፈጸም የማይፈልግና በጽኑ የሚያወግዝ መሆኑን እንገልጻለን። መድረክ ጉዳዩ በገለልተኛ አካላት እንዲጣራ ጠይቛል። ዝርዝሩን የአማርኛ ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ።
a_amh-gfi-africa-12-20-11-135950663_1460944
https://amharic.voanews.com/a/amh-gfi-africa-12-20-11-135950663/1460944.html
ከአፍሪካ ወደ ውጭ አገር የሚሸሸው ገንዘብ ከውጭ እርዳታ ከእጥፍ በላይ ይበልጣል
ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ የሚባል በዓለም ዙሪያ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን የሚመረምር ድርጅት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከ1993ዓም እስከ 2001 ዓም ወደ 12 ቢሊዮን ዶላር ከሃገር ሸሽቷል።
ችግሩ በአፍሪካ ከተደቀኑ የኢኮኖሚ ችግሮች ከቀዳሚዎቹ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቁሟል ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰት በጠቅላላው የአንድን አገር ድንበር አቋርጦ ህገ-ወጥ በሆኑ መንገዶች የተገኙ ገንዘቦች የሚዘዋወሩበት መንገድ ነው። በሙስና፡ በኮንትሮባንድ፣ በወንጀል ድርጊትና ቀረጥ ላለመክፈል የሚዛወር ሂሳብ ነው። ስሌቱና ቁጥጥሩ በጣም የተወሳሰበ በመሆኑ ለባለሙያዎቹም ቢሆን እራስ ምታት የሆነ ችግር ነው። ቁጥሩ ግን ለማንኛውም ሰው የሚገባና እራስን የሚያስይዝ ነው። ወደ አፍሪካ አህጉር እስከዛሬ ድረስ በእርዳታ መልኩ ከተለገሰው ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር ከአፍሪካ የሚወጣው ህገ-ወጥ ገንዘብ በእጥፍ፣ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ደግሞ እስከ ሶስት እጥፍ ይበልጣል። ሬይመንድ ቤከር Global Financial Integrity የተባለ ድርጅትን ይመራሉ። አንድ ሰው በህይወቱ ሊያየው ከሚገባ በላይ ከአፍሪካ ገንዘብ በህገ-ወጥ መልኩ ሲወጣ ተመልክቻለሁ፤ በጥናትም አስደግፌ አረጋግጫለሁ ይላሉ። ሁኔታው አስደንጋጭ ነው ይላሉ። “በጣም ብዙ ነው። ከአፍሪካ በህገ-ወጥ መልኩ የሚወጣው ገንዘብ የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ በስፋት የሚጎዳ ነው። ለትምህርት፣ ጤናና ሌሎች ለማህበራዊ አገልግሎቶች የሚውለውን ገንዘብ ያሟጥጣል። የአገሬው ባለሃብቶች በልማት ላይ የሚያደርጉትን የገንዘብ ፍሰጥ ይቀንሳል፤ ብድር እንደልም ማግኘትን ያግዳል፣ የኑሮ ውድነትን ያስከትላል፣ የውጭ ምንዛሬ እጦትን ያባብሳል…ብዙ ብዙ ችግሮች አሉት። በጥናታችን እንደጠቆምንው ድሃ አገሮችን በእጅጉ እየጎዱ ካሉ የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ትልቅ ድርሻ ያለው እክል ነው። በዚህ እክል እንደ አፍሪካ ክፉኛ የተጎዳ የአለም ክፍል የለም። በአለም ዙሪያ ከታዳጊ አገሮች የሚወጣው ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰት በአመት 1 ትሪሊየን ዶላር ይሆናል። ይህንን ሁኔታ በቁጥር ለማስቀመጥ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ሁለት ለረጅም ጊዜ በግልጋሎት ላይ የነበሩ ቀመሮችን ይጠቀማል። ሳይንሱን ለተመራማሪዎቹ እንተወውና፤ ለሁላችንም በሚገባ መልኩ ከቀመሮቹ የተገኙት ውጤቶች ላይ እናተኩል። በህገ-ወጥ መልኩ ገንዘብ የሚወጣባቸው መንገዶች በሙስና፡ በኮንትሮባንድ፣ በወንጀል ድርጊት (ማለት በአደንዛዥ እጽ ዝውውርና) ቀረጥ ላለመክፈል የሚዛወር ሂሳብ ናቸው። በተለምዶ የአፍሪካ ሀብት ከሀገር ይዛወራል የሚባለው፤ ለረጅም ጊዜ አገር በሚመሩ አምባ-ገነኖችና አጋሮቻቸው እንደሆነ ይነገራል። ይሄ መንገድ በእርግጥ ብዙ የአገር ሀብት የሚወጣበት ቢሆንም እንደ ሬይመንግ ቤከር አባባል ያለው ድርሻ በጣም ጥቂት ነው። “ድንበር ተሻግሮ በሚደረግ የህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከጉቦና ከስርቆት የሚገኘው ገንዘብ 3ከመቶ የሚሆነውን አለም አቀፍ ዝውውር ብቻ ነው የሚወስደው። ከወንጀል የሚገኘው፤ ማለት ከአደንዛዥ እጽ ንግድ ከወሮበላነትና ከመሳሰሉት የሚገኘው ወደ 33-35 ከመቶ የሚሆነውን ነው የሚሸፍነው” ይላሉ ቤከር። ከ60-65 ከመቶ የሚሆነውን የአለም አቀፍ አጠቃላይ ሂሳብ የሚይዘው ከቀረጥ የሚሸሽ ገዘብ ነው። ይሄም የትላልቅ ኩባንያዎች የቀረጥ አለመክፈል ነው። ከ1960ዎቹ ጀምሮ ላለፉት አርባ ዓመታት አፍሪካ በህገ-ወጥ መልኩ የወጣው ገንዘብ ወደ 1 ትሊሊየን ዶላር ይገመታል። በእርግጥ ይሄ ተመን የማያካትታቸው አጠራጣሪ አሀዞች በመኖራቸው-ገንዘቡ ከተባለው ሊበልጥ እንደሚችል ሬይመንድ ቤከር ይናገራሉ። በዚህ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ ከ16 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ የሸሸ ሲሆን ከአፍሪካ በ13ኛ ደረጃ ትገኛለች። ባለፉት ሶስት ዓመታት ደግሞ በኢትዮጵያ የታየው የገንዘብ የህገ-ወጥ የገንዘብ ሽሽት ከሌሎች አመታት በጣም የባሰ ነው። በ2001ዓም ከሃገር የሸሸው ገንዘብ የጠቅላላ የአገሪቱን አመታዊ የመንግስት በጀት ይስተካከላል። 3.25 ቢሊዮን ዶላር ከአገር ሸሽቷል። ለንጽጽር ያህል ጎረቤት ኬንያ ከ7-8 ቢሊየን ዶላር (22ኛ) ጅቡቲ 1 ቢሊየን ዶላር (45ኛ) ኤርትራ 117 ሚሊዮን ዶላር (51ኛ) ደረጃን ይዘዋል። በአፍሪካ ከፍተኛ ገንጸብ በህገ-ወጥ መልኩ የሚወጣባት አገር ናይጀሪያ ስትሆን 241 ቢሊየን ዶላር ግብጽ 131 ቢሊዮን ደቡብ አፍሪካ 74 ቢሊየን ዶላር በመሆን ከ1-3 የለውን ስምን በበጎ የማያስጠራ ሰንጠረዥ ተቆናጠዋል። ይሄ ገንዘብ ደግሞ የሚጓዘው--በጥናቱ መሰረት--ወደ አደጉ አገሮች ነው። እንዴት? ሬመንድ ቤከር ያብራራሉ። “በወጭና ገቢ ንግድ ዋጋዎች ላይ የሃሰት ደረሰኝ በመቁረጥ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ፣ የገቢና የጉምሩክ ቀረጦችን ማጭበርበር የታወቁ መንገዶች ናቸው” ከአንድ አገር ገንዘብ ለማሸሽ ዋነኛው መንገድ የወጭና ገቢ ንግድን ዋጋዎች በሃሰት ማጭበርበር ነው። ይሄ የሚደረገው ከውጭ የሚገባ ምርትን ዋጋ ከእውነተኛው ዋጋው በመጨመርና፤ የወጭ ምርትን ዋጋ ሆን ብሎ ማሳነስ ነው። ይሄ ማለት በሚገባ ቋንቋ። እንበል አንድ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ የቡና ነጋዴ ከሆነና ቻይና አገር ካለ ድርጅት ስሚንቶ የሚያስገባ ነው እንበል፤ በቀላሉ ለመረዳት። ከዚያ ኢትዮጵያዊው ነጋዴ ከቻይና ስሚንቶ ሲያስገባ፣ እንበል የስሚንቶው ዋጋ 1 ሚሊዮን ዶላር ቢሆን፤ ዋጋ ሲስማሙ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ብለው ድረሰኝ ይቆርጡለታል። ከዚያ ኢትዮጵያዊው ነጋዴ የ1.2 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለቻይናዊ የንግድ አጋሩ ይልካል። ቻይናዊ ነጋዴው ደግሞ የራሱን 1 ሚሊዮን ዶላር ከወሰደ በኋላ የቀረውን 200ሽህ ዶላር በደንበኛው የውጭ የባንክ ሂስብ ቁጥር ያስገባዋል። በዚህ መልኩ ኢትዮጵያዊው ነጋዴ 200ሽህ ዶላር የውጭ ምንዛሬ በአንድ የገበያ ልውውጥ አሸሸ ማለት ነው። ይሄ ሁኔታ ደግሞ በአገር ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ችግር ከማምጣቱ፣ የሃገር ሃብት ከመሸሹ፣ በተጨማሪ የስሚንቶ ዋጋን ያላግባብ ይጨምራል። ይሄው ነጋዴ ወደ ውጭ ቡና ሲልክ ደግሞ፤ ዋጋውን ይቀንስና እንዲሁ ዋጋው በተሰበረ ደረሰኝ ቡናውን ይልካል። በዚህም አገር ማግኘት ያለባትን የውጭ ምንዛሬና የገቢ ቀረጥ በውጭ አገር የባንክ ሂሳብ ቁጥሩ ያስቀራል ማለት ነው። በዚህ መልኩ ነው በርካታ የህገ-ወጥ ገንዘብ ከድሆች አገሮች ወደ ሀብታም አገሮች የሚተላለፈው። ሬመንድ ቤከር ይሄ ይቅር የማይባል እውነት ነው። አሁን ባለንበት የ21ኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ መታየት የሌለበት አስነዋሪ ሀቅ ነው ይላሉ። ቤከር የሚሰሩበት Global Financial Integrity ድርጅት ከአፍሪካ አገሮች ጋር ይህንን ወንጀል ለማስቆም አብሮ በመስራት ላይ ይገኛል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢሲኤ እንዲሁም የገንዘብና የልማት ሚኒስትሮች ጋር በአንድነት አፍሪካ የህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ልትቆጣጠር የምትችልበትን መንገድ ለማብጀት ይንቀሳቀሳል። የጥምረት ስራው- ገና በንግግር ደረጃ ላይ ይገኛል። አፍሪካ የገንዘብ ዝውውርን የሚከታተል ኮሚሽን እንድታቛቁምና የአፍሪካ መሪዎች አንድ የመወያያ አጀንዳ አድርገው መፍትሄ ለማብጀት ንግግር እንዲጀምሩ ጥረት ተጀምሯል። ከዚያም በላይ አገሮች የጉምሩክ ቀረጥ አሰባሰባቸውን ማቀላጠፍና በቴክኖሎጂ ማገዝ ይኖርባቸዋል። የገቢ ቀረጥ አሰባሰባቸውንም ከአለም አቀፍ የቀረጥ ሰብሳቢዎች ጋር ሊመሳከር የሚችልና፤ መረጃ መለዋወጥ የሚያስችል አሰራር መዘርጋትን ይጠይቃል። ፈጥኖ መረጃ መለዋወጥ መቻል፣ ነጋዴዎችና የንግድ ድርጅቶች በሃገር ውስጥና በውጭ ያላቸውን የገቢና ወጭ ሰንጠረዥ መመልከት የሚያስችል የመረጃ መስመር ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ባለሙያዎች ይመክራሉ። ሆኖም ችግሩ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የሚከናወነው፤ በጽሁፍ በሚደረግ ስምምነት ሳይሆን ብዙውን ጊዜ በቃል ስምምነት በመሆኑ፤ ወንጀለኞቹን ለመያዝ ከባድ ያደርገዋል። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይ ያደጉት አገሮች የገንዘብ ዝውውር መረጃን በማደግ ላይ ላሉ አገሮች ካካፈሉ፤ ተባብሮ ችግሩን ለመቀነስ መስራት እንደሚቻል ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ተስፋ ጥሏል።
a_obama-iraq-101997308_1457917
https://amharic.voanews.com/a/obama-iraq-101997308/1457917.html
ኦባማ በኢራቅ አዲስ ምዕራፍ የሚከፈትበት ጊዜ መሆኑን ገለጹ
ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢራቅ የነበረው የአሜሪካ የውጊያ ተልዕኮ እንዳበቃ አስታውቀዋል። ፕረዚዳንቱ አዲሱ የአሜሪካ ተልዕኮ የኢራቅ የጸጥታ ሀይሎችን ማማከርና መርዳት ነው ብለዋል።
የኢራቅ የነጻነት ተልዕኮ አብቅቷል። የመጠበቅ ሃላፊነቱን ተረክቧል ብለዋል ኦባማ የ አሜሪካ ወታደራዊ ሃይሎች ኢራቅን ከወረሩ ሰባት አመታት ተኩል ካለፉ በኋላ ፕረዚዳንት ኦባማ ወታደሮቹን ለአገልግሎታቸው አመስግነው የውጊያ ትልዕኮአቸው እንዳባቃ ገልጸውላቸዋል። “የኢራቅ የነጻነት ተልዕኮ አብቅቷል። አሁን የኢራቅ ህዝብ የሀገሪቱን ጸጥታ የመጠበቅ ሃላፊነቱን ተረክቧል። ፕረዚዳንት ኦባማ የፕረዚዳንትነቱን ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ከመስርያ ቤታቸው ለሀገሪቱ ህዝብ ንግግር ሲያደርጉ ሁለተኛቸው ሲሆን ስለ ድል አልተናገሩም። ነገር ግን ወደ አዲስ ተልዕኮ እያመራን ነው ብለዋል። “በ አሜሪካና እና በኢራቅ ታሪክ በነበረው ተጠቃሽ ምዕራፍ በኩል ሀላፊነታችንን ተወጥተናል። አሁን አዲስ ምዕራፍ የምንከፍትበት ጊዜ ነው። 50,000 የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች፣ በኢራቅ ይቆዩና፣ እስከ መጪው አመት ማብቂያ ባለው ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ተመድቧል። አዲሱ የ በአሜሪካ ተልዕኮ የኢራቅ የጸጥታ ሀይሎችን ማማከርና መርዳት ከጸረ አሸባሪነት ተልዕኮ ሀይሎች ጋር መተባበርና ሲቪሎችን መጠበቅ እንደሆነ ፐረዚዳንቱ አስገንዝበዋል። የ አሜሪካ የኢኮኖሚ ማገገም ባዘገመበት በአሁኑ ወቅት ፐረዚዳንት ኦባማ ትኩረታቸውን ወደ ኢኮኖሚ ጉድይ አዙረዋል። የአሜሪካ ዋናው አስቸዃይ ተግባር የታጡትን በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የስራ ዕድሎችን መመለስ ነው በማለት አስገንዝበዋል።
a_article---abdi-the-juggler-12-18-10-112130244_1460463
https://amharic.voanews.com/a/article---abdi-the-juggler-12-18-10-112130244/1460463.html
ሁለት ጥበበኛ እጆች
አብዱረዛቅ ረሽድ ወይንም በመድርክ ስሙ አብዲ ዘ-ጀግለር ታዋቂ የሰርከስ ትርዒት ባለሙያ ነው። ስለትግሉና ስኬቱ ከመስታዎት ዝግጅት ጋር ተወያይቷል።
ተወልዶ ያደገው ናዝሬት ከተማ ነው። አብዱረዛቅ ረሽድ አደም ገና በስምንት ዓመቱ የሰርከስ ልምምድ ለማድረግ ከትምህርት ቤት መልስ ከበጎ ፈቃድ አሰልጣኙ ሙያ ሊቀስም ሲሄድ ቤተሰቦቹ ደስተኞች አልነበሩም። “ይሄንን ቧልትና ዝላይ ትተህ በትምህርትህ በርታ” ነበር የወላጆቹ ምክር። በየቀኑ ወሳኝ ክህሎቶቹን እየተማረ የነበረው አብዲ ግን ተደብቆም ቢሆን ከልምምድ አይቀርም ነበር። “ቤተሰቦቼ ጊዜየን የከንቱ የማሳልፍ ይመስላቸው ነበር” ይላል አብዲ። የኋላ ኋላ ቤተሰቦቹን ከትርዒቶቹ አንዱን እንዲመለከቱለት ጋብዟቸው ስራውን ካዩ በኋላ ድጋፋቸውን ሰጡት። ዛሬ ይሄ ታዳጊ ወጣት የ27 ዓመት ሰው ነው። በስራውም ቢሆን በልጅነቱ ያደረበትን የሰርከስ ፍቅር ወደ ፕሮፌሽናል ሙያ ቀይሮት ታዋቂ ሆኗል። ሲጀምር ሰርከስ ናዝሬት ፥ ከዚያ ሰርከስ ኢትዮጲያ ፥ ዛሬ ደግሞ በዓለም ላይ የታወቀ ባውንሲንግ ጀግለር ወይም በርካታ ኩዋሶችን በማንጠር በቅንብር እየቀለበ በታላላቅ የዝናኛ ማዕከላት እና በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ከተሞች ስራውን ያቀርባል። ለሰርከስ ትርኢቱ ወዲህ ወደዩናይትድ ስቴትስ መጥቶ በዋሽግተን ዲሲ እና በተለያዩ በርካታ ከተሞች እየተዘዋወረ ነው። በታወቀው በኬኔዲ ሴንተር ዝግጅቱን ከአውሮፓ ከተሰባሰብ የሰርከስ ቡድን ጋር አቅርቧል በሌሎችም ከተሞች እንዲሁ እየተዘዋወረ ዝግጅቶቹን ያቀርባል። ከመስታዎት ዝግጅት ጋር ያደረገውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።
a_abortion-tablets-health-121968709_1461182
https://amharic.voanews.com/a/abortion-tablets-health-121968709/1461182.html
ያልተፈለገ ፅንስን በጥንቃቄ ለማቋረጥ የሚያስችል አዲስ ዘዴ ተግባር ላይ ዋለ
በኢትዮዽያ ጥንቃቄ የጎደለው ፅንስ የማስወረድ ሂደት በኣገሪቱ የሚታየውን የእናቶች ሞት 25 በመቶ በላይ ይሸፍናል።
የመቐለና የኣዲስ ኣባባ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ካሊፎርንያ ዩኒቨርሲቲ ስር ከሚገኘው VSI (Venture Strategies Innovations) መንግስታዊ ያልሆነ የጤና ድርጅት ጋራ በመተባበር ትግራይ ውስጥ ባካሄዱት ጥናት ያልተፈልገ እርግዝናን ለማስቀረት የሚረዳ ህክምናዊ ዘዴ ጀምረዋል። የጥናቱ ውጤትም ግንቦት 9 (በኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር) መቐለ ከተማ በተካሄደው ኣለም ኣቀፍ ሰሚናር ይፋ ተደርጓል። ጥናቱ ትግራይ ክልል ውስጥ በመቐለ፣ በዓዲ ግራትና ዓብዪ ዓዲ በሚገኙ 4,400 እናቶች ላይ ባለፉት 18 ወራት የተካሄደ ሲሆን ውጤቱም የናቶች ሞትን ለመቀነስ የበለጠ ዘዴ ሆኖ መገኘቱን ሊቃውንቱ ገልጿል። በጥናቱ ላይ የተሳተፉት የማህፀንና የፅንስ ከፍተኛ ሃኪም ዶ/ር ኣማኑኤል ገሰሰው “ኢትዮዽያ በኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር በ2005 ዓ/ም በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ያልተፈለገ ፅንስ ማስወረድ ህጋዊ መሆኑን ተደንግጓል። በዚህም ህጉ ከመሻሻሉ በፊት ከህክምና ውጭና በቂ እውቀት በሌላቸው ሰዎች ይካሄድ የነበረውን ጥንቃቄ የጎደለው ፅንስ የማስወረድ ሂደት ቀርቷል። ይህ ደግሞ የእናቶች ሞት ከመቀነስ ኣንፃር ራሱን የቻለ ትልቅ ሚና ተጫውቷል”ብሏል። ያልተፈለገ ፅንስን ለማስወረድ ወደ ሆስፒታል ይመጡ ከነበሩት እናቶች በኣመት ከ5-6 የሚሆኑት ሂወታቸው ያጡ እንደነበር ዶ/ር ኣማኑኤል በጥናቱ መሰረት ይናገራሉ። ኣሁን በተደረገው ክኒን በመስጠት የሚፈፀም ወርጃ ግን ኣደጋው በሚያስደንቅ ሁኔታ መቀነሱን ገልጿል። ጥናቱ ትኩረት የሰጠበት ይህንን የህክምና ዘዴ በከፍተኛ ሃኪሞች ብቻ ሳይሆን ከሆስፒታል ኣልፎ በጤና ጣብያዎችና በጤና ኬላዎች ደግሞም በጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች የሚሰጥበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደነበርም ባለሞያው ይናገራሉ። ይህ በትግራይ ክልል ተካሂዶ ኣመርቂ ውጤት ያስገኘው ጥናት ሌሎች ክልሎችም ያላቸውን የጤና ድርጅቶች ኣወቃቀርና ኣጠቃላይ ያከባብያቸውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ በወቅቱ ተገልጿል።
a_painting-tiztaexhibition-ethioipia-destahagos_3227636
https://amharic.voanews.com/a/painting-tiztaexhibition-ethioipia-destahagos/3227636.html
“ጥበብ...ሃቀኝነትንና ሰላምን ይወዳል” ሰዓሊ ደስታ ሃጎስ
በ1960ዎቹ ሴት ልጅ በአደባባይ መውጣት ባልተለመደበት ዘመን ፤ ደስታ ሃጎስ የራስዋን የስዕል ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ያዘጋጀች የመጀመሪያዋ የሴት ሰአሊ። ባሳለፈችው የጥበብ ስራ ዘመን ከሃምሳ ጊዜ በላይ የስዕል ኤግዚቢሽኖችን ለብቻዋና ከሌሎች ሰአሊዎች ጋር በጋራ በመሆን ለእይታ አቅርባለች።
ዋሽንግተን ዲሲ — የተወለደችው በትግራይ አድዋ ከተማ ነው። የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን አዲስ አበባ በሚገኘው በቴጌ መነን ት/ቤት ከጨረሰች በኃላ ከአዲስ አበባ የስነጥበብ ትምህርት ቤት በስዕል ስራ ትምህርቷን አጠናቃለች። በመቀጠልም በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ በሚገኘው ሉተራል ዩኒቨርስቲ የስዕል ትምህርቷን ለአራት አመት ቀጥላ ተምራለች። ከሃምሳ ጊዜ በላይ የስዕል ኤግዚቢሽኖችን ለብቻዋና ከሌሎች ሰአሊዎች ጋር በጋራ በመሆን አሳይታለች። ከልጅነቷ በስራዎቿ በመደነቅና በመሸለም ስኬቷን የተቀዳጀች ሴት አርቲስት ናት ደስታ ሃጎስ። በተለያዩ አውሮፓ ሃገራት እንዲሁም በአሜሪካ የስዕል ኤግዚቢሽኖችን ለረጅም አመታት አሳይታለች። ታዲያ በነዚህ የስኬት የስዕል ኤግዚቢሽኖች መሃል አንድ የማይረሳ አሳዛኝ ክስተት አጋጥሟታል፤ ወደ ሰላሳ የሚጠጉ የስዕል ስራዎቿን ለዕይታ ለማቅረብ ወደ ጀርመን ስትጓዝ ለኤግዚቢሽኑ የታሰቡት የስዕል ስራዎቿ በሙሉ በመንገድ ላይ ጠፉ። እስከዛሬም የደረሱበት አልታወቀም። በቅርቡ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ በዩናይትድ ስቴትስ በፍሎሪዳ ማያሚ ከተማ፤ ኢትዮጵያ ስትሳተፍ የመጀመሪያዋ የሆነው አለም አቀፉ አመታዊ የስዕል ኤግዚቢሽን ላይ “ትዝታ ኤግዚቢሽን” በሚል ስያሜ ከሌሎች አምስት ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ወክላ የስዕል ስራዎቿን ለዕይታ አቅርባ አድናቆትን አትርፋለች። ከመስታወት አራጋው ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጋለች። ከታች የሚታየውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።
a_onlf-ethiopia-wfp-abduction-5-30-11-122833809_1458290
https://amharic.voanews.com/a/onlf-ethiopia-wfp-abduction-5-30-11-122833809/1458290.html
ኦብነግ ገላልሼ ከተማን ለቅቄ ወጣሁ አለ፣ ነዋሪዎች ቀድሞውንም አልተቆጣጠረም ብለዋል
በሶማሊ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) የገላልሼ ከተማን ለቆ መውጣቱን አስታወቀ። አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ኦብነግ ከተማዋን በፊትም አልተቆጣጠረም ይላሉ።
ባለፈው ሳምንት ሀሙስ በሶማሊ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) በገላልሼ ከተማ አካባቢ ባደረገው ጥቃት በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጉዳት ማድረሱንና እስረኞችን ማስፈታቱን አስታውቆ ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ አማጺያኑ ለጥቃት ሲዘጋጁ በአካባቢው የፖሊስ ሃይልና ሚሊሻ የደፈጣ ጥቃት ደርሶባቸው 80 የሚሆኑ አማጺያንና፣ ሶስት የፖሊስ ባልደረቦች ሲገደሉ፤ አራት የመንግስት ሀይሎች ቆስለዋል ብሏል። በዛሬውለት ኦብነግ እንዳስታወቀው ገላልሼ ከተማን ለቆ ወጥቷል። የኢትዮጵያ መንግስት በሄሊኮፕተር የታገዘ ዘመቻ እያካሄደ እንደሆነ ነው ኦብነግ ያስታወቀው። በሀሙሱ ጥቃት በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጉዳት ከማድረሱ አልፎ በመቶዎች የተቆጠሩ እስረኞችን ማስፈታቱን ይናገራል። በዚህ ግጭት ከሳምንታት በፊት ደብዛቸው ጠፍቶ የነበረው የአለም ምግብ ድርጅት WFP ሰራተኞች በኢትዮጵያ መንግስት ታስረው ማግኘታቸውንና አሁን በኦብነግ እጅ እንዳሉ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት አማጺያኑ ይዘዋቸዋል የሚለውን የWFP ሰራተኞች ለማስለቀቅ ልዩ ሃሉን ማሰማራቱን የመንግስቱ ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል አርብለት መግለጻቸው ይታወሳል። ከአለም የምግብ ድርጅት ባገኘንው መረጃ መሰረት የታገቱት ሰራተኞቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። “ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ስማቸውን ልገልጽ አልችልም፤ ልናገር የምችለው በጂጂጋ የሚገኘው የመስክ ቢሮአችን የሚሰራ አንድ ሾፌርና አንድ የምግብ እርዳታ አሰጣጥ ተቆጣጣሪ ናቸው” ብለዋል የአለም የምግብ ድርጅት ቃል አቀባይ ጁዲዝ ሹለር። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሰራር የታገቱ ሰዎችን ማንነትና ዝርዝር መረጃን የመስጠት ልማድ ባለመኖሩ ተጨማሪ መረጃ መስጠት እንደማይችሉ ሹለር ይናገራሉ። የአማጺው ሃይል ኦብነግ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር ተነጋግሮ ታጋቾቹን በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል አማካኝነት ነጻ ለመልቀቅ እንደሚፈልግ አስታውቋል። በዚህ ላይ የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። WFP ከታጋቾቹ ቤተሰቦች ጋር በቅርበት እንደሚነጋገር ጁዲት ሹለር ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የኦጋዴን ህሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ሃሰን አብዱላሂን አነጋግረናል። ዝርዝሩን ከሬድዮ ዘገባው ያዳምጡ።
a_a-53-2008-05-03-voa1-93030979_1462855
https://amharic.voanews.com/a/a-53-2008-05-03-voa1-93030979/1462855.html
Tirunesh Dibaba Completes Ethiopia’s Medal Sweep in the Women's 10,000m
The World and Olympic 10,000 champion Tirunesh Dibaba completed an all-Ethiopian dominance at the 16th African Athletics Championships
DAY-4, May 03, 2008 RANK SILVER 1. 9 2 6 17 2. NIGERIA 4 5 3 12 3. ETHIOPIA 4 4 2 10 4. EGYPT 2 2 2 7 5. KENYA 2 2 3 7 6. MOROCCO 2 1 2 5 7. ALGERIA 1 2 1 4 RANK NAME NAT RESULT 1. TIRUNESH DIBABA ETH 32:49.08 2. EJEGAYEHU DIBABA ETH 32:50.36 3. WUDE AYALEW ETH 32:55.17 RANK NAME NAT RESULT 1. Chris HARMSE RSA 77.72 CR 2. Moustafa AL GAMAL EGY 69.70 3. Ahmed ABDUL RAOUF EGY 68.15 RANK NAME NAT RESULT 1. Mouhcine CHAOURI MAR 4.80 2. Larbi BOURADA ALG 4.50 3. Willem COERTZEN RSA 4.00 RANK NAME NAT RESULT 1. Ndiss Kaba BADJI SEN 17.07 2. Hugo Lucie MAMBA SCHLICK CMR 16.92 3. Tarik BOUGUETAIB MAR 16.82 RANK NAME NAT RESULT 1. Sunette VILJOEN RSA 55.17 2. SEY 52.92 3. Hanaa OMAR EGY 52.32 RANK NAME NAT 1. Hennie KOTZE RSA 13.95 2. Samuel OKON NGR 14.08 3. Nurudeen SALIM NGR 14.27
a_3197129
https://amharic.voanews.com/a/3197129.html
የአስመራ ከተማ በዩኔስኮ ለመመዝገብ እጩ ሆነች
አስመራ በዩኔስኮ UNESCO የአለም ታሪካዊ ስፍራዎች ወይም “World Heritage”፤ ህንጻዎቿን፣ ታሪኳን እና የግንባታ ውበቷን ልትመዘገብ እጩ ሆናለች።
ዋሽንግተን ዲሲ — ከዛሬ 700 አመት ገደማ በፊት ገዛ ግረቶም፣ ገዛ ሺለሌ፣ ገዛ ሰረንሰር እና ገዛ አስሜ የተባሉ በአራት የተከፈሉ ሰፊ የቤተሰብ አባላት በአስመራ ከተማ ይኖሩ ነበር። የዛሬዋ አስመራ በዛን ዘመን የንግድ መተላለፊያ ቦታ ነበረች። ታዲያ በዛን ጊዜ በአራቱ የቤተሰብ አባላት መካከል ስምምነት ይጠፋል በዚህም ምክንያት ከተማዋ ሰላም ይርቃታል። ለችግሩ መፍትሄ ይሆን ዘንድ የአራቱ ቤተሰብ አባላት ሴቶች ይሰባሰቡና ሰላምን እንዴት እንድሚያሰፍኑ መከሩ እናም የሰላም ህግጋትን አወጡ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አስመራ ሰላም ሆነች፣ የከተማዋ መጠሪያም የሴቶቹን በጎ ተግባር ለማወደስ አስመራ ተባለ። አስመራ ማለት በትግሪኛ ሴቶቹ አሰመሩ እንደማለት ነው። የአስመራ ከተማ የኤርትራ ዋና ከተማ ተብላ የተሰየመችው እ.አ.አ 1897 በጣልያን ቅኝ ግዛት በነበረችበት ወቅት ነው። አስመራ የምትታወቀው በከተማዋ ውበት በተለይም በማስተር ፕላኗ ሲሆን በከተማዋ የሚገኙት ታሪካዊ ሕንፃዎች ከአፍሪካ ከተሞች የተለየች ያደርጋታል። ይህ ልዩነቷ አስመራን በዩኔስኮ UNESCO የአለም ታሪካዊ ስፍራዎች ወይም “World Heritage”፤ በ19ኛው ክፍለዘመን ማብቂያና በሀያኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ የተገነቡ ህንጻዎቿን፤ ታሪኳን እና የግንባታ ውበቷን ሊመዘግብ እጩ አድርጓታል። ነዋሪነቱ በዩናይትድ ስቴትስ የሆነው ኢሳያስ ተስፋማሪያም አሁን ካሊፎርኒያ በሚገኘው በሁቨር የጥናት ማእከል የቤተ መዛግብት ባለሙያ ሆኖ ይሰራል፤ እንዲሁም በስታንፎርድ ዪኒቨርሲቲ በታሪክና በቋንቋ መምህርነት በመስራት ላይ ይገኛል።
a_amh-horn-drought-update9-9-12-142084193_1460222
https://amharic.voanews.com/a/amh-horn-drought-update9-9-12-142084193/1460222.html
ለአፍሪካ ቀንድ ድርቅ ተጠቂዎችና ስደተኞች ዩናይትድ ስቴይትስ ድጋፏን እንድትቀጥል ተጠየቀ
በዩናይትድ ስቴይትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የገንዘብ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ፤ በእርዳታ አቅርቦት ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች አሳስበዋል።
በዩናይትድ ስቴይትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገኝ ሸንጎ፤ በአፍሪካ ቀንድ በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች ምግብና ሌሎች አቅርቦቶች የማድረስ ጥረቱ እንዲቀጥል አሳሰበ። በአፍሪካ ቀንድ የቀጠለውን የስደተኞች ሁኔታ ለመመርመር የዩናይትድ ስቴይትስ የህግ መምሪያው ቡድኖች በትናንትናውለት ያደመጡትን የምስክሮችን ቃል ያስተባበሩት፤ የቶም ላንቶስ የሰብዓዊ መብት ኮሚሺን እና በቤቱ የረሃብ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ናቸው። የኮሚቴው አጋር ሊቀ-መንበር የማሳቹሴትሱ ዴሞክራት ጄምስ ምክገቨርን በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ባለፈው ወር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማሊያ ረሃብና ቸነፈሩ አብቅቷል ብሎ ቢያውጅም ድርቁና ተዛማጅ የስደተኞች ችግሮች አሁንም በስፋት ይታያሉ ብለዋል። “በጦርነትና በረሃብ የተንሳ ወደ 2.5 ሚሊዮን ሶማሊያዊያን በአገር ውስጥና ወደ ጎረቤት አገሮች ተሰደዋል። በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የተቸገሩ ሰዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በአካባቢው የስደተኞች ቀውስ ፈጥሯል። የዩናይትድ ስቴይትስ የአለም አቀፍ ተራድዖ USAID ከፍተኛ ባለስልጣን ናንሲ ሊንቦርግ፤ በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን ድርቅ ለመታደግ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ አሰራሮች ሚና ተጫውተዋል ብለዋል። ረሃቡና ቸነፈሩ በሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያና ኬንያ በተባባሰበት ወቅት 935 ሚሊዮን ዶላር አሰባስቦ ለአስቸኳይ የምግብ፣ የመጠለያ፣ የጤናና የመሳሰሉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟያ እንደዋለ ሊንቦርግ ገልጸዋል። “በእውነቱ ባለፉት 60 ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ አስቸኳይ የሰብዓዊ እልቂት ከፊታችን ተደቅኖ፤ በምን ያህል ፍጥነትና ብቃት ተደራጅተን ምላሽ እንደሰጠን ሳስበው ይደንቀኛል። ለውጥ አምጥተናል። ሊንቦርግና ሙያዊ አስተያየታቸውን የሰጡ የኦባማ አስተዳድር ባለስልጣናት፤ የአፍሪካ ቀንድ አሁንም የአለማችን ትልቁ የስደተኞች ቁጥር ያለበት አካባቢ መሆኑ አሳስበዋል። ድርቁ ጋብ ቢልም ቀጣይ የመልሶ ማቋቋም ስራዎችና ድርቅና ረሃብን እንዲሁም ጦርነት ሽሽት የተሰደዱ ሰዎች እለታዊ ፍላጎቶችን ማሟላትም ትኩረት እንደሚያሻው አስምረውበታል። ማርጋሬት መክሊቪ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ እርዳታ ቢሮ ሃላፊ ናቸው። ሶማሊያዊያን ስደተኞችን ጎረቤት አገሮች እንዲቀበሏቸው ማድረግ ከባድ ፈተና መሆኑን ይገልጻሉ። “የሶማሊያዊያን ስደተኞችን አስመልክቶ ያለብን ትልቁ ፈተና በጎረቤት አገር ጥገኝነት ማግኘት ነው። ለምሳሌ ጅቡቲ ወታደር ለመሆን እድሚያቸው የደረሱ ሶማሊያዊያንን ላለመቀበል ወስናለች። መክሊቪ አክለውም ሲያስረዱ፤ የኬንያ መንግስት ነጻ በወጡ የሶማሊያ ግዛቶች የሰብዓዊ እርዳታ ቀጠና ተዘጋጅቶ ስደተኞች በዚያ እንዲሰፍሩ እየጠየቀ ነው ብለዋል። ሆኖም በርካታ ሶማሊያዊያን ደህንነታቸው እንዲጠበቅና በሰላም እንዲኖሩ አገራቸውን ምልቀቅ እንዳለባቸው ባለስልጣኗ አስታውቀዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ዴብራ ማላክ፤ ድርቁ በአፍሪካ ቀንድ የምግብ እህል እጥረት እንዳስከተለ አብራርተዋል። ሆኖም በድርቁ ሳቢያ በርካታዎች እንዲሞቱና እንዲሰደዱ ምክንያት የሆነው የሶማሊያ የእስልምና አንጃ አልሸባብ መሆኑን ይገልጻሉ። “አልሸባብ በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች እርዳታ እንዳይደርስና የድህንነቱን ሁኔታ አስጊ በማድረጉ፤ የነበረው ድርቅ ወደለየለት ገዳይ ረሃብና ቸነፈር ተሸጋግሯል። በዚያ ላይ ለአመታት የዘለቀው ጦርነት ሶማሊያዊያን ድርቅን ለመቋቋም ለዘመናት ያዳበሯቸውን መንገዶች ሁሉ አክስሞባቸዋል። በሶማሊያ ድርቁ ክፉኛ በርካታ ሰዎችን ከጎዳባቸው አካባቢዎች 60 ከመቶ የሚሆኑት በአልሸባብ ቁጥጥር ስራ ያሉ አካባቢዎች ናቸው። የእስላማዊ አንጃው በጦርነት በታመሰችው የአፍሪካ ቀንዷ አገር ጥብቅ የእስላማዊ አስተዳድር ለመመስረት ይታገላል።
a_amh-swedish-journalists-12-22-11-136103023_1458510
https://amharic.voanews.com/a/amh-swedish-journalists-12-22-11-136103023/1458510.html
ወንጀለኛ የተባሉት ስዊድናዊ ጋዜጠኞች ያለቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ የመብት ተሟጋቾች ጠይቁ
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከሚንቀሳቀሱ አማጺያን ጋር ድንበር ተሻግረው ሲሰሩ የነበሩ ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በሃምሌ ወር ከተያዙ በኋላ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ፤ ረቡዕለት ጥፋተኛ ተብለዋል።
ኮንትነንት ፎቶ ጆርናሊስት ለሚባል የስዊድን የዜና አገልግሎት የሚሰሩት ጋዜጠኞቹ ማርቲን ሸበ እና ዮሃን ፐርሽን በኦጋዴን የተያዙት በአካባቢው ከሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ኦ.ብ.ነግ ታጣቂዎች ጋር በመሆን ከሰሜን ሶማሊያ ሰርገው ከገቡ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ሰራዊት ጋዜጠኞቹን አጅበው ይንቀሳቀሱ የነበሩ አማጺያን ላይ ገስግሶ ተኩስ በመክፈት፤ ብዙዎቹን ሲገድል ጋዜጠኞቹና ጥቂት ታጣቂዎች ቆስለው ተይዘዋል። በዚህ አይነት መልኩ ነበር ዓለም-አቀፍ አትኩሮትን የሳበው የጋዜጠኞቹ የፍርድ ሂደት የተጀመረው። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፎቶ ጋዜጠኛውን ዮሃን ፐርሽንና ጸሃፊውን ማርቲን ፐርሽን ሽብርተኝነትን በመደገፍና የሃገር ድንበርን በህገ-ወጥ መልኩ በመሻገር ውንጀል ከአቃቢ ህግ የቀረበውን ክስ ሲመረምር ቆይቷል። በትናንትናውለት በዚህ እስከ 18ዓመት ሊያሳስር በሚችል ወንጀል ዳኛው ሸምሱ ሰርጋጋ ጋዜጠኞቹን ጥፋተኛ ብለዋል። “ዮሃን ፐርሽን እና ማርቲን ሸበ እንደጋዜጠኞች ስራቸውን ሲሰሩ ነው የተያዙት። አንድም ቀን ቢሆን በእስር ቤት ማደር አልነበረባቸውም” ብለዋል የሲ.ፒ.ጄ የአፍሪካ መረጃ አጠናቃሪ ሞሀመድ ኪታ። በጣም የሚያሳዝነት የፍርድ ሂደቱ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነበረው ይላሉ ኪታ። “በፍርድ ቤት እስኪረጋገጥ ነጻ ናቸው የሚለው መሰረታዊ ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ሆን ተብሎ ተጥሷል። ጥፋተኛ መሆናቸው ሲነገራቸው ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መከላከያ አላቀረባችሁም ነው የተባሉት። የመጨረሻ ፍርዱን ያሳለፉት ዳኛ ሸምሱ ሰርጋጋም በመገናኛ ብዙሃን እንደተዘገበው፤ ጋዜጠኞቹ አሸባሪዎችን ላለመደገፋቸውና ለምን በህገ-ወጥ መልኩ ድንበር እንደተሻገሩ ማስረዳትና መከላከል አልቻሉም ብለዋል። በዓለም ዙሪያ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚሰራው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የኢትዮጵያ መንግስት እነዚህን ጋዜጠኞች በፍጥነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ ጠይቋል። “ሁለቱ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የጋዜጠኛ ስራ ሊሰሩ እንደሆነ እናምናለን። የታሰሩትም፣ በፍርድ ቤት ተከሰው ጥፋተኛ የተባሉትም የጋዜጠኝነት ስራቸውን በመስራታቸው ነው” ሲሉ የአምነስቲ የኢትዮጵያና ኤርትራ መረጃ አጠናቃሪ ክሌር ቤስተን አስታውቀዋል። “የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው አዲስ የጸረ-ሽብር ህግ የፈለጉትን ሰው በጅምላ እንዲወነጅሉ ያስችላቸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በኢህአዴግ የ99.6 ከመቶ አብላጫ ድምጽ የሚመራው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሳለፈው የጸረ-ሽብር ህግና ተከታትሎ አምስት ድርጅቶችን ሽብርተኛ ብሎ መሰየሙ ይታወሳል። በዚህም መሰረት አልቃይዳ፣ አልሸባብ፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጭ ግንባር፣ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባርና ግንቦት 7 አሸባሪ ድርጅቶች ተብለዋል። ከነዚህ ድርጅቶች ጋር የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት አዲስ በወጣው የኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ህግ መሰረት አሸባሪ ያስብላል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያና ኤርትራ መረጃ አጠናቃሪ ክሌር ቤስተን፤ ጋዜጠኞች የሚያነጋግሩትን ድርጅት ይደግፋሉ ማለት አሳዛኝ አስተሳሰብ ነው ይላሉ። “አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ ታጣቂ ሃይሎች ጋር መነጋገር፣ ሃሳባቸውን ትደግፋለህ ማለት አይደለም። በፍርድ ቤትም ወንጀለኛ አያስብልም። እኛ እራሳችንም ብንሆን አሸባሪ የተባሉ ሰዎችን እናናግራለን። ሁልጊዜም ቢሆን ለአንድ ሁኔታ ሁለት ድምጾች ይሰማሉ፤ የሁለቱንም ወገን አባባል ለማጣራት መነጋገር ያስፈልጋል” ብለዋል ቤስተን። በጸረ-ሽብር ህጉ የሚታዩ ክፍተቶችና ህገመንግስታዊ ተቀባይነት ማጣት ብቻ አይደልም በሂደቱ ለጋዜጠኞች በብት የሚከራከረው ሲፒጄ የሚያሳስበው። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋዜጠኞቹን በአደባባይና በሚቆጣጠሯቸው የዜና አውታሮች ወንጀለኛ አድርገው ማቅረባቸው የክሱን ሂደት ተቀባይነት የሌለው ያደርጉታል ይላል ሲ.ፒ.ጄ። በኢትዮጵያ ቴሌቪዢን የተላለፈ ዘገባ ጋዜጠኞቹ መሳሪያ ይዘው እንደሚያሳይና ምስሉ ሆን ተብሎ በኮምፒውተር የተቀናበረ፤ እንዲሁም ድምጽ የተቀየጠበት በመሆኑ የባለሙያዎችን አስተያየት ሰምቶ ፍርድ ቤቱ መረጃውን ውድቅ ማድረጉን የሲፒጄው የአፍሪካ መረጃ አጠናቃሪ ሞሃመድ ኪታ ያብራራሉ። የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ፣ የህዝቡ ንብረት የሆኑ ተቋማትን ከጥቃት ለመከላከልና በአጠቃላይ በአገሪቱ ሰላምን ለማስፈን አሸባሪ ድርጅቶችን ጠብቆ እንደሚዋጋ በተደጋጋሚ አረጋግጧል። ለዚህም ዘመቻ የሚረዳው የጸረ-ሽብር ህግ በፓርላማ ጸድቋል። ገና ከጅምሩ የጸረ-ሽብር ህጉን፣ የመገናኛ ብዙሃን ህጉንና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የሚያስተዳድሩት ህጎች አንዳንድ አንቀጾች አፋኝና ህገ-መንግስታዊ መስተጋብር የላቸውም በማለት ተቃዋሚዎች፣ የመብት ተሟጋቾችና ምእራባዊያን መንግስታት ተችተዋል።
a_solar-project-106686833_1457614
https://amharic.voanews.com/a/solar-project-106686833/1457614.html
አዲስ ዓይነት ምድጃዎች ለኢትዮጵያ ቤተሰቦች
በኢትዮጵያ ያለው የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ይዞታ ምን ይመስላል? በፀሐይ ኃይል በሚሠሩት መጠቀምስ ተለምዷል? -- ውይይት ከሶላር በረከት መሥራች ጋር፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ለታዳጊ ሀገሮች ቤተሰቦች ጤናና የአካባቢ ደህንነት ጠንቅ የሆኑ ምድጃዎችን ለማስወገድ እገዛ ልታደርግ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ በቤቶች ውስጥ በምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ጢስ ምክንያት የሚደርሱ ችግሮችን ለማስወገድ የንፁህ ምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ዓለምአቀፍ ጥምረት (Global Alliance for Clean Cook Stoves) የተባለና በቤተሰብ ጤና ላይ ጠንቅ የማይፈጥሩ የምግብ ማብሰያዎችን ለማስተዋወቅና ለማዳረስ የታቀደ ዓለም አቀፍ ህብረት ማደረጃ ሃምሳ ሚሊዮን ዶላር ልትሰጥ ቃል መግባቷን ባለፈው ሰሞን በዚሁ በሴቶችና ቤተሰብ ፕሮግራም ማቅረባችን ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ነበሩ ይህን ይፋ ያደረጉት። እንደአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር እስከ ሁለት ሺህ ሃያ ባለው ጊዜ ውስጥ መቶ ሚሊዮን የታዳጊ ሀገሮች ቤተሰቦችን የጤናም ሆነ የኣካባቢ ደህንነት ጠንቅ ከሆኑ ማብሰያዎች ለማላቀቅና የተሻሉ ምድጃዎችን ለማዳረስ የታለመ ዕቅድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የምግብ ማብሰያ ይዞታ ምን ይመስላል? ለመሆኑ በሀገሪቱ የፀሐይ ችግር እንዳለመኖሩ የፀሐይን ኃይል ለመጠቀምና ለማስለመድስ ምን ያህል ጥረት ይደረጋል? ወጣት በረከት ደሴ ሶላር በረከት የተባለ ድርጅት መሥራች ሲሆን በፀሐይ ኃይል ምግብን ማብሰልን እና ሌሎችንም የተሻሉ ምድጃዎችን ድርጅቱ ያመርታል። ስላሉት አማራጭ ምድጃዎች ያወሣል፡፡ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩትን በብዛት ማስለመድ አስፈላጊነቱን አጥብቆ ያምንበታል። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
a_ethiopia-price-hike-drought-4-18-11-120122194_1458519
https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-price-hike-drought-4-18-11-120122194/1458519.html
በደቡብ ኢትዮጵያ ድርቅ ተከሰተ፤ በአገሪቱ የኑሮ ውድነት በዚህ ወር በ25 ከመቶ አሻቀበ
በዚህ ወር ኢትዮጵያ ሁለት ተከታታይ እክሎች ገጥመዋታል። የኑሮ ውድነት በእጅጉ ጨምሯል፤ በደቡብና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በድርቅ ሳቢያ ምርት በመጨናገፉ በርካታ ቤተሰቦች ለረሃብ ተጋልጠዋል።
ባሳለፍንው የመጋቢት ወር የሸቀጦች ዋጋ በ25ከመቶ መጨመሩን የኢትዮጵያ ማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል። ይሄም በየካቲት ወር ከነበረው የ16.5 ከመቶ የዋጋ ግሽበት ጋር ተዳምሮ፤ የዋጋ ነረት አስከትሏል። በየወሩ ኤጀንሲው የሚያወጣው ሪፖርት ከወር ወር የሚተላለፈው የ12 ወር የዋጋ መወደድን የሚያሳየው አማካይ አሃዝ ወደ 11.3 ከመቶ አድጓል። በመጋቢት ወር በምግብ ዋጋ ላይ የታየው የዋጋ ውድነት 5.8 ከመቶ ነው። የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ያሲን ሙሳ በመጋቢት ወር ላይ የታየው የዋጋ ንረት ከጥቅምት2001 ዓ.ም ወዲህ ያልታየ ጭማሪ መሆኑን ይናገራሉ። የሸቀጦች ዋጋ ንረቱ የተከሰተው፤ መንግስት በጥር ወር የዋጋ ተመን አውጥቶ ገበያውን ለማረጋጋት መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ ነው። በሰሜን አፍሪካ የምግብ ዋጋ ጭማሪ ለዘመናት የቆዩ አስተዳደሮችን ከገረሰሰ ወዲህ ኢትዮጵያን ለ20 አመታት ያስተዳደረው ኢህአዴግ የሸቀጦችን ዋጋ በተመን አግዶ ነበር። ሆኖም አልተሳካም። የዋጋ ጭማሪው በገበያው ላይ እጥረት በመፍጠሩ በተጓዳኝ የጥቁር ገበያ ውስጥ ውስጡን ሸመታው ጦፎ ነበር የሰነበተው። በዚህ ምክንያት መንግስት በቀጥታ ስኳርና ዘይት የመሳሰሉ አላቂ እቃዎችን ማከፋፈል የጀመረበት ሁኔታ ይስተዋላል። የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚተነብዩት የሀገሪቱ የዋጋ ውድነት በሚያዝያ ወርም ይቀጥላል። በተለይ ከጥቂት ቀናት በፊት የነዳጅ ዋጋ በ14 ከመቶ እንዲጨምር ከመደረጉ ጋር ተያይዞ፤ ትንበያው እውን እንደሚሆን ባለሙያዎቹ አይጠራጠሩም። በሌላ በኩል ደግሞ የአደጋ መከላከልና የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ድርጅቱ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ጨምሯል ሲል በዚህ ሳምንት አስታውቋል። የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ በጥር ወር መጀመሪያ 2.8 ሚሊዮን ዜጎች የውጭ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቆ፤ ተገቢው እርዳታም እንዲደረግለት ለጋሾችን ጠይቆ ነበር። ለቪኦኤ በስልክ ቃላቸውን የሰጡት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ታደሰ በቀለ፤ የተረጂዎቹ ቁጥር 3.2 ሚሊዮን እንደሆነ ገልጸዋል። “ለደቡብና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ ማስተባበር ስራን በማዘጋጀት ላይ ነን። ባስቀመጥናቸው መስፈርቶች መሰረት አጋሮቻችን አብረውን እንዲሰሩም እንፈልጋለን። ይሄም የከብት ቀለብ ማቅረብ፤ የህጻናት ምግብና የመሳሰሉት ናቸው። በነዚህ ላይ አጋዦቻችን እንዲረባረቡ ጥሪ እናቀርባለን። የአለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) አርብለት ባወጣው መረጃ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ በዝናብ እጥረት ሳቢያ የአርብቶ አደር አካባቢዎች ድርቅ ተከስቷል። በአዲስ አበባ የWFፒ ቃል-አቀባይ ሱዛና ኒኮል ውሃና የከብት መኖ ለማጓጓዝ ጥረት ቢደረግም፤ ከችግሩ ስፋት አንጻር፤ ሁሉን ለማዳረስ አለመቻሉንና የከብቶች ሞት መቀጠሉን ይናገራሉ። “የከብት መኖና የውሃ እጥረት በአንዳንድ አካባቢዎች በእጅጉ የጠና ሆኗል። ከብቶቹ መሞታቸው ከቀጠለ፤ ችግሩ ይባባስና የሁሉንም ሰው ደጅ ያንኳጓል። ሰዎች እራሳቸውን መመገብ ሊቃቅታቸው ይችላል፤ ኑሯቸውም ይቃወሳል። የኢትዮጵያ የምግብ እጥረት የተከሰተው ባለፈው ሳምንት የአለም ባንክ በአለም ዙሪያ የ36 ከመቶ የምግብ ዋጋ ጭማሪ በዚህ አመት እንደተስተዋለ ይፋ ባደረገበት ማግስት ነው። የአለም ባንክ ፕሬዝደንት ሮበርት ዞለክ በጉዳዩ “በቋፍ ላይ እንገኛለን” ሲሉ አሳሳቢነቱን በአጽንዖት ገልጸዋል። ዩናይትድ ስቴይትስ ለኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ከሚሰጡ አገሮች ግምባር ቀደሟ ናት። የአለም የምግብ ድርጅት ባጠናቀረው መረጃ መሰረት ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ዩናይትድ ስቴይትስ 58 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የምግብ እርዳታ ለኢትዮጵያ ሰጥታለች። ይህ በእንዲህ እንዳለየኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን በመብራት ፍጆታ ዋጋ ላይ እስከ 200% ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ማጠናቀቁንና ይህንንም ጥናት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ተልኮ እንደነበረና፤ ለክለሳ ተመልሶ ወደ መብራት ሃይል መላኩን ሳምንታዊው የንግድና ኢኮኖሚ ጋዜጣ ካፒታል ዘግቧል።
a_amh-wfp-workers-released-6-30-11-124805359_1457921
https://amharic.voanews.com/a/amh-wfp-workers-released-6-30-11-124805359/1457921.html
ለስድስት ሳምንታት በሶማሊ ክልል ታግተው የነበሩት የWFP ሰራተኞች ተለቀቁ
ለአንድ ወር ተኩል ጊዜ በኢትዮጵያ የሶማሊ ክልል ታግተው የቆዩት ሁለት የአለም የምግብ ድርጅት ሰራተኞች መለቀቃቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።
በሶማሊ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጭ ግንባር (ኦብነግ) ሰኞለት ሁለቱን ሰራተኞች ለWFP ማስረከቡን ያስረከበው ሰኞለት ነበር። የአለም የምግብ ድርጅት በዛሬውለት ሁለቱ ታጋቾች በአዲስ አበባ ከቤተሰባቸው ጋር መቀላቀላቸውን ይፋ አድርጓል። ከስድስት ሳምንታት በፊት በሶማሊ ክልል አንድ የአለም የምግብ ድርጅት WFP ሰራተኛ ተገድሎ ሁለቱ የደረሱበት መጥፋቱ ይታወሳል። በክስተቱ ላይ የተለያዩ መረጃዎች ይፋ ሲሆኑ፤ የአለም የምግብ ድርጅት ሰራተኞቹ ላይ አደጋ መድረሱንና፤ የተሰወሩትን ፈልጎ ለማግኘት ተማጽኖውንና ጥረቱን ማጠናከሩን ሲገልጽ ቆይቷል። በዛሬውለት የአለም የምግብ ድርጅት በኦጋዴን ተሰውረው የቆዩት ሁለቱ ሰራተኞቹ መለቀቃቸውን አረጋግጧል። “በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ያገለግሉ የነበሩ ባልደረቦቻችን በሶማሊያ ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ተለቀዋል” ሲሉ የWFP ቃል አቀባይ ፋራሃን ሃክ ተናግረዋል። “አሁን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአዲስ አበባ ይገኛሉ። ጤንነታቸውን ለማረጋገጥ የህክምና ምርመራና፤ የመንፈስ መረበሽ የስነ-ልቦና ምክር እየተሰጣቸው ነው። ታጋቾቹ በመልካም ጤንነት ላይ ቢገኙም፤ የህክምና ማረጋገጫ ለማግኘት ምርመራ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል። እነዚህ የእርዳታ ሰራተኞችን ማን እንዳገታቸው የአለም የምግብ ድርጅት የሰጠው መግለጫ የለም። ከዚህ በቀደሙ ሳምንታት የኢትዮጵያ መንግስት በሶማሊ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጭ ግንባር (ኦብነግ) ሰራተኞቹ ላይ ጥቃት አድርሶ ሁለቱን ማገቱን ገልጾ ነበር። ኦብነግ በበኩሉ የWFP ሰራተኞች የታገቱት በኢትዮጵያ ሰራዊት ነው ሲል አስታውቋል። በሶስት ሳምንታት በፊት በገላልሼ ከተማ በተደረገ ውጊያ ኦብነግ እነዚህን ታጋቾች ከኢትዮጵያ ሰራዊት ማስለቀቁን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጿል። ቪኦኤ ያነጋገራቸው የአካባቢው ሰዎች በ WFP ሰራተኞች ላይ ጥቃቱን ያደረሱት የኦብነግ ታጣቂዎች እንደሆኑ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ለመሆኑ የ WFP ሰራተኞች ከተለቀቁ በኋላ ስለ-አጋቾቻቸው ምን መግለጫ ሰጡ? እንዲህ ያለ ክስተት ካለፈ በኋላ የታገቱትን ሰዎች ማነጋገር የተለመደ አሰራራችን ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ፋራሃን ካን፤ “ባለፉት ስድስት ሳምንታት የደረሰባቸውን ሁሉ በዝርዝር ይነግሩናል። ይሄንን ማጣራት ካደረግን በኋላ የደረሰባቸውን ሁሉ መረዳት እንችላለን። እስከዚያው ጊዜ ድረስ ግን በጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ መስጠት አንችልም” ብለዋል። በሌላ በኩል በአለማችን በ70 አገሮች ወደ 90 ሚሊዮን የሚሆኑ የተራቡ ሰዎችን የሚመግበው WFP በአፍሪካ ቀንድ ላለፉት ስልሳ አመታት ታይቶ የማያውቅ ድርቅ መከሰቱን ገልጿል። አስር ሚሊዮን ዜጎች የከፋ የምግብ እጥረት ለረሃብ እንዳጋለጣቸው ድርጅቱ በትናንትናውለት አስታውቋል። በኢትዮጵያ 3.2 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸው WFP በኬንያ 3.5 ሚሊዮን፣ በሶማሊያ 2.5 ሚሊዮን፣ በሰሜን ምስራቅ ዩጋንዳ 600ሽህ፣ እና በጂቡቲ 120 ሽህ ሰዎች መራባቸውን አሳስቧል። “ዋናው የችግሩ መንስዔ ድርቅ ነው። ባለፉት ሁለት አመታት በስልሳ አመታት ውስጥ ያልታየ ድርቅ ነው የተከሰተው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ እዲሉ፤ የምግብ ዋጋ መናርም ለችግሩ ተጠቃሽ ነው። ስለዚህ አስቸኳይ እርዳታ ለማከፋፈል የሚያስችለን የገንዘብ እርዳታ እንዲሰጠን በመጠየቅ ላይ ነን” ብለዋል ፋራሃን ካን። በችግር ላይ ከወደቁት 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች WFP ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉትን በእጅጉ የተጠቁ እርዳታ ለመስጠት አቅዷል። ሆኖም የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ እንደሚሉት ይህንን ለማድረግ የሚያስችል አቅም WFP የለውም። ይህንን ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ለመታደግ፤ የሚበሉት ለሌላቸው ህጻናት አልሚ ምግብ ለማቅረብ፤ ለእናቶች የህክምናና የምግብ አቅርቦት ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል ። በዚህ ላይ የአካባቢው መንግስታትም ሃላፊነት እንዳለባቸው የWFP ቃል አቀባይ ፋራሃን ሃክ ያስገነዝባሉ። “አንዱ የምንጠይቃቸው ነገር፣ በአካባቢው የሚታየውን ሁኔታ ለመታደግ የቀረበውን የሰብዓዊ እርዳታ ጥሪ ክብደት ሰጥተው፤ እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ ነው። መንግስታት ምግብ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎቻቸው እርዳታ ማቅረብ ይገባቸዋል። በዚህ ድርቅ የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች ህጻናት መሆናቸውን የገለጸው የአለም የምግብ ድርጅት፤ ቀዳሚ ተጠቂዎቹን ለመታደግ የእርዳታ ጥሪው አስቸኳይ መሆኑን አስምሮበታል።
a_voa-amharic-un-au-summit-_6369066
https://amharic.voanews.com/a/voa-amharic-un-au-summit-/6369066.html
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ እና የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ረቡዕ እለት በዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ በሚገኘው የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ቢሮ በአምስተኛው የአፍርካ ሕብረት እና የመንግስታቱ ድርጅት ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት እና የአፍሪካ ሕብረት በሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ሊኖራቸው ስለሚገባው የላቀ ትብብር እና አጀንዳ 2063 እና አጀንዳ 2030 ተብለው በሚታወቁት የዘላቂ ልማት ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ መሪዎች በኮቪድ 19፣ በነጻ ገበያ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በአሁን ሰዓት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ግጭት እንዲሁም በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያም ሃሳቦችን አንሸራሽረዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ "157 ከባድ መኪኖች ወደ መቀሌ ደርሰዋል፡፡ ስለዚህ ሰብዓዊ ድጋፎች ውጤታማ በሆነ መልኩ በድጋሚ እየጀመሩ ነው፡፡ ምናልባት የምንፈልገውን ያህል ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይሄ ጥሩ ምልክት ነው፡፡ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በረራዎች ከአዲስ አበባ መቀሌ በድጋሚ ተጀምረዋል፡፡ ስለዚህ ወደ ፊት ቀና የሆነ ውይይት ሊመጣ እንደሚችል የሚያመላክቱ ትናንሽ ተስፋዎች አሉ፡፡ ” ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው የቀድሞውን የናይጄርያ ፕሬዘዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆን በአፍሪካ ተፋሰስ ሃገራት በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ አተኩረው እንዲሰሩ ልዩ ልዑክ አድርገው መላካቸውን የገለጹ ሲሆን "እስካሁን ድረስ 3 ጊዜ ተመላልሷል፡፡ ሁለቱንም አካላት አዳምጧል፡፡ መንግስት ሕውሃት ወደ ድንበሩ እንዲመለስ ይሻል፡፡ በተጨማሪም የአብይ አሕመድ መንግስትን ሕጋዊነት እንዲቀበልና እውቅና እንዲሰጥ ይሻል፡፡ በሌላ በኩል ሕውሃቶች የስብዓዊ አቅርቦት እንዲሻሻል ይፈልጋሉ፡፡ የጉዞ ኮሪደሮች እንዲከፈቱ ይሻሉ፡፡ የኤርትራ ኃይሎች ለቀው እንዲወጡ እና በክልሉ የሕዝብ አገልግሎቶች እንዲመልስም ይፈለጋሉ፡፡ በሰፊው ካነሳነው በሁለቱም አካላት በኩል እነዚህ ነገሮች ናቸው የሚነሱት፡፡ ከሁለቱም ጋር መነጋገራችንን ብንቀጥልም አለመታደል ሆኖ መሬት ላይ ግን ጦርነቱ ቀጥሏል፡፡ በእርግጥ ከሰሞኑ ግንባር ላይ በጦርነቱ ቀጠና መረጋጋት እየወረደ መሆኑን አይተናል፡፡ ነገር ግን ይሄ ሁኔታ በጥልቅ ያሳስበናል፡፡ " ብለዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ
a_ivory-coast-conflict-4-1-11-119072249_1462502
https://amharic.voanews.com/a/ivory-coast-conflict-4-1-11-119072249/1462502.html
በአይቮሪ ኮስት የተቃዋሚው ታማኞች የፕሬዝዳንት ባግቦን ቤተ-መንግስት ከበቡ
በአይቮ ሪኮስት የፕሬዝደንታዊ ምርጫ አሸናፊነታቸው በአለማቀፉ ማህበረሰብ እውቅና ያገኘው አላሳን ዋታራ ሀይሎች የፕሬዝደንት ሮሎን ባግቦ ቤተመንግስት ከበዋል።
በአይቮሪ ኮስት የንግድ መዲና አቢጆ ተኩሱ ቀጥሏል። የታህሳስ ወሩን የፕሬዝደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን በአለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና የተሰጣቸው ፕሬዝደንት አላሳን ዋታራ ታማኝ ሀይሎች የሎሮን ባግቦን ቤተ-መንግስት ከበዋል። በአይቮሪኮስት ሁኔታዎች በፍጥነት እየተለወጡ ነው። የአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ትናንት ማምሻውን ስርጭቱን ማቋረጡን የዋታራ ቃል አቀባይ አሁዋ ዶን ሜሎ ገልጸዋል። የባግቦ ወታደሮች የአገሪቱን የአየር ማረፊያ ለተባበሩትም መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች አስረክበዋል። የሃገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ በደቡብ አፍሪካው አምባሳደር የመኖሪያ ቤት ተጠግተዋል። አላሳን ዋታራ የአገሪቱ ጦር አብሯቸው እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል። “በጥርጣሬ ላይ ያላቸሁ የጦሩ አባላት፤ ጄኔራሎችም ሆናችሁ መኮንኖችና ተራ ወታደሮች አገራቸሁን የማገልገያ ጊዚያችሁ አሁን መሆኑን አምናችሁ ወደ ህግ ተመለሱ። ጠመንጃ ያነገቡትን ወንድሞቻችሁን የመቀላቀያ ጊዜው አላለፈም” ብለዋል ዋታራ። አቢጆን ለመቆጣጠር ውጊያው የተፋጠነው ላይቤሪያን በሚያዋስነው የአገሪቱ ክፍል፤ የዋታራ ወታደሮች ያለምንም ቅዋሜ አካባቢውን ነጻ ካወጡ ወዲህ ነው። በዚህ ዘመቻ የፖለቲካ መዲናዋን ያሞሱክሮ እና የሳን ፔድሮ ወደብን ተቆጣጥረዋል። በስተምስራቅ በኩልም ጋናን በሚያዋስነው ድንበር ድል ቀንቷቸዋል። በአይቮ ሪኮስት ከታህሳሱ ወር የፕሬዝደንታዊ ምርጫ ወዲህ ከ500 የማያንሱ ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። ዋና ጸሀፊ ባንጊ ሙን ሁለቱም ተፎካካሪ ጎራዎች ዜጎችን እንዳይጎዱ አስጠንቅቀው፤ ሚስተር ባግቦ ከስልጣን እንዲወርዱና ዋታራ መንግስት እንዲመሰርቱ ጠይቀዋል።
a_article-------amh-ak-conversation-with-hilina-abebe-part-1-07april2011_1457724
https://amharic.voanews.com/a/article-------amh-ak-conversation-with-hilina-abebe-part-1-07april2011/1457724.html
በኢትዮጵያ ዛሬም በሴቶች ግርዛት የሚያምኑ አያሌ ናቸው
«ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቀረት ስንጥር ግዴታ የዛን ማኅበረሰብ እሴቶች መጠበቅ አለብን። ትምህርታዊው በብዙ ድርጅቶች አማካኝነት እየተካሄደ ያለው የማኅበረሰብ ውይይት መድረክ ለምሳሌ ብዙ ለውጥም እያመጣ ነው።»
ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚፈረጀው የሴቶች ግርዛት የሚያስከትላቸውን አስከፊ ጉዳቶች ለማስቀረት ታለመው የተከናወኑ ሥራዎች ሁነኛ ለውጥ ማስመዝገብ ቢያስችሉም፤ የተለያዩ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች በወለዷቸው እምነቶች ሳቢያ ግን ቁጥራቸው የበዙ ሴቶች ዛሬም ግርዛት ይፈፀምባቸዋል። ይህን መሰሉ በሥፋት የታመነበት፥ አደገኝነቱና በሴቶች ላይ በዘለቄታው የሚያስከትላቸው ጉዳቶች በጉልህ የታወቀ ምግባር ለጨቅላ ልጆቻቸው በሚሳሱና መልካም የሚመኙ ወላጆች እንዴት ይፈፀማል? በታላላቅ ከተሞች ሳይቀር ብዙዎች እንደምን ይህን ከመሰሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መራቅ ተሳናቸው? ውጤታቸው ጎጂ፥ መነሻ መሠረታቸው የተሳሳተ እሳቤም ቢሆን፤ ማኅበረሰቦች በልማድ ለረዥም ጊዜ ሲያከናውኑ የቆዩትን ድርጊት ለማስተውስ የትኞቹ መንገዶች ሰርተው ይሆን? ለእነኚህና ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች፥ በርዕሱ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ በሚንቀሳቀሱ ለትርፍ ያልቆሙ ድርጅቶች አማካኝነት አዲስ አበባ ውስጥ በእንግሊዝኛ የሚታተም መፅሄት ዋና አዘጋጅ ከሆነች ወጣት ጋር በሁለት ተከታታይ ክፍሎች የተካሄደ ቃለ ምልልስ ያዳምጡ። በኢትዮጵያ የሴቶች ግርዛት፥ በኢትዮጵያ የሴቶች ግርዛት፥
a_the-idea-series-ethiopian-history-arts-with-voa-surafel-wondimu-alula-kebede_3952740
https://amharic.voanews.com/a/the-idea-series-ethiopian-history-arts-with-voa-surafel-wondimu-alula-kebede/3952740.html
ታሪክ ስለ ምን? ... የትላንት ፋይዳና አንድምታ ላይ ያተኮሩ ወጎች!
“ማወቅ የምፈልገው፤ “ማ” ስለ ከትላንት ውስጥ “ምንን” ወይም የትኛውን ክፍል ጠቅሶ ዛሬ ላይ ምን ዓይነት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት መገንባት ይፈልጋል? ወይም እየገነባ ነው? ምን ዓይነት የአገዛዝ ሥርዓት እንዲቀጥል ይፈልጋል? .. ነገ ምን ዓይነት ሥርዓት እንዲመጣ በመናፈቅ ነው? የሚለው ነው።” ሱራፌል ወንድሙ።
“ሃሳብ እንደ መንገድ .. በማስረጃ የተደገፉ ጠቃሚ ወጎች” በሚል አብይ ርዕስ የተጀመረ አዲስ ተከታታይ ወግ አካል ነው። እንግዳችን ሱራፌል ወንድሙ:- ተዋናይ፥ ጸሃፊ-ተውኔት፤ የሬዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች አቀናባሪ፥ ጸሃፊ፥ ገጣሚ እና መምሕር ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ሥነ ጽሁፍና የድራማ ትምሕርቶች መምሕር እና እንዲሁም የ‘ሂዩማኒቲስ’ ትምሕርት ክፍል ረዳት ዲን ሆኖም አገልግሏል። ዛሬ በቴአትርና የትርዒት አጻጻፍ ታሪክ የድህረ ምረቃ ትምሕርቱን በመከታተል ላይ ነው። ሃሳብ፥ ታሪክ እና አንምታው፤ የትላንት ፋይዳ በዛሬና ነገ’አችን ውስጥ፤ በሚሉ ጭብጦች ላይ ያተኩራል። “ሴቶችና አብዮቱ” የተሰኘ ጥናቱን ገጾች መልከት እናደርጋለን። ተከታታይ ቃለ ምልልሱን ከዚህ ያድምጡ።